Page 1 of 29

የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Posted: 02 Jan 2012 08:12
by Wadera
ሰላም ለክብረ መንግስት፣ ለቦሬ፣ ለአገረ ሰላም፣ ለሻኪሶ፣ ለዘንባባ ውሃ፣ ለዋደራ፣ ለገናሌ፣ ለጨንቤ፣ ለኢርባ ሙዳና ለመላው የአካባቢው ልጆች እንደምን ሰነበታችሁ? በየጊዜው የምንገናኝበት ዋርካ ጄነራል አጸያፊ ጽሁፎችን ከማስነበቡም በላይ አንዳንድ ግለሰቦችም አልፈው ተርፈው የሌሎችን ሃይማኖት በማጥላላት አምላካችንን ሁሉ ሳይቀር በማዋረድ የሚያካሄዱት ተግባር በጣም የሚዘገንን ሆኖ ስላገኘሁት ወደዚያ ቤት መሄዱ በጣም ስላስጠላኝ ይህን ቤት ለማግኘት በመቻሌ ደስ ብሎኛል።

የዋርካ ዌብሳይት ሃላፊዎች ብልግና የተሞላባቸውን ጽሁፎች እንዲያስወግዱ ጸሐፊዎቹንም ከዚህ ዓይነት ተግባር እንዲቆጠቡ እንዲነግሩዋቸው በተደጋጋሚ ቢጠየቁም ጥያቄዎቹን ሁሉ ስላልተቀበሉ ሌሎቻችን ያለን ምርጫ ከዚያ ቤት መውጣት ብቻ ነው። ስለዚህ ይህን ገጽ እዚህ ጀምረን ስለ አደግንበት አካባቢና ስለ ሌሎችም ተዛማች ጉዳዮች እዚህ እየተገናኘን እንድንወያይ በአክብሮት እጠይቃለሁ።

አመሰግናለሁ

ዋደራ (የዋርካው አንፈራራ)

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Posted: 03 Jan 2012 07:03
by Wadera
ስላም ለሁላችሁ

ሞፊቲ በዋርካ ላይ የጻፍከውን አነበብኩት፣ በጣም ደስ ብሎኛል፣ እዚያ ያለህን ስም እንደያዝክ እዚህም መመዝገብ የምትችል ይመስለኛል። አስተዳዳሪዎቹም የ "እንክዋን ደህና መጣህ" መልክት ልከውልኛል፣ እዚህ ሁሉ ነገር በሥርዓት እንደሚካሄድም አረጋግጠውልኛል። ስለዚህ እባካችሁ እዚህ እየተመዘገባችሁ ያቋረጥነውን ውይይት እንቀጥል።

ቻው ላሁኑ።

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Posted: 03 Jan 2012 10:15
by ራስብሩ
ሰላም ጤና ይስጥልኝ
ወደአዲሱ ቤታችን ለመምጣት መንገዱ ቀላል ቢሆንም በአማርኛ ቶሎ ለመጻፍ ቀላል አልነበረም
ወደኋላ ተመልሼ በፍለጋ ነው ያገኘሁት : ያም ሆነ ይህ ወንድማችን ዋደራ ከልብ የመነጨው ምስጋናችን ይድረስህ
የፈጠረንን አምላክ እንዲህ ባለ ፍጹም ባልጌና ጸያፍ ቃላት ሲሰደብ ማየት ራሱ በውነት አለመታደል ነው
ዋርካዎች (ባለቤቶቹ) ምን አይነት ልቦና እንዳላቸው በውነት ግራ ነው የሚገባኝ :
አንደኛ በዌብ ሳይቱ ላይ በትክክል የተቀመጠውን መመሪያ አላስከበሩም እነሱም አላከበሩም
ሁለተኛ ይሄ ጉዳይ የህብረተሰቡን መብት የሚነካና እና ሃይማኖትን የሚነቅፍ መሆኑን በሚገባ ያውቃሉ
ሶሰተኛ ተደጋገሞ ተነግሮአቸው ሊያርሙ አለቻሉም ................
ሰለዚሀ በዚህ ሁኔታ ላይ አብረን መገኘት የለብንም ::

ወራ ጀምጀምቱ እንግዲሀ አዲስ ቤት ሰርተናል
ጎራ በሉ

የናንተው ራስብሩ

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Posted: 03 Jan 2012 10:21
by Wadera
ሰላም ራስብሩ እንኳን ደህና መጣህ
አማርኛው እውነትም በጣም ቆንጆ ፊደሎች አሉት::ግን ወደዚያ የሚሸጋገርበትን መንገድ ለማግኘት ያስችግር ይሆናል ለማንኛውም ልሞክር::

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Posted: 03 Jan 2012 12:34
by Wadera
"በአማርኛ ይጻፉ" የሚለውን ስትጫኑ አንድ መጻፊያ ክፍት ቦታ ይሰጣል: ከዚያም በክፍቱ ቦታ ላይ ጽፎ ያንን ኮፒ አድርጎ ዋናው መልክት መላኪያው ላይ መለጠፍ ማለት ፔስት ማድረግ ነው::

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Posted: 03 Jan 2012 14:32
by ሞፊቲ
ሰላም ሰላም ::

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Posted: 03 Jan 2012 14:39
by ሞፊቲ
ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን::

ዋደራ ቤታችንን አደራጅተህ ስለጠበከን ከልብ አመሰግናለሁ::
የ አማርኛውን ፊደል በቀላሉ እንደዋርካ የምንጽፍበት መንገድ ቢኖር መልካም ነው::ትንሽ ግራ ያጋባል::ለምንኛውም ስንለምደው ይቀል ይሆናል::
ሆዴን ባር ባር ብሎታል:: ያም ቢሆን ያንን ሁሉ የተካበት የጽሁፍ ሃብት ወደዚህ የምንስብበት መንገድ ቢኖር መልካም ነው እላለሁ::

በሉ እንበርታ!
ሰላም ሁኑልኝ::

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Posted: 03 Jan 2012 16:04
by አንፈራራ
ወደ ተለመደው ስሜ ተመልሻለሁ:: አሁንም "አንፈራራ" ነኝ:: ዋደራ! አመሰግናለሁ ቤቱን ስለከፈትክልን: አሁን ግን ወደ ቤትህ ተመለስ:: :)