የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Forum rules
No cursing, bad language and offend other users !
No pornographic images or links!
This forum monitored regularly. We will BAN users without warning for not obeying rules.
እባክዎ የፎረሙን ህጎች ያክብሩ::
አደቆርሳ
Jogger
Jogger
Posts: 45
Joined: 13 Jan 2012 04:13
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread postby አደቆርሳ » 18 Oct 2012 18:42

የልጅ ፍቅር የሚጀምረው ከእርግዝናው ነው እያለች እማማ ድሮ ስትናገር ግርም ይለኝ ነበር :
ከፍ እያልኩ ስመጣ ደግሞ አስናቀች ወርቁ ነፍሷን የገነት ያድርግላት እና
በሆዴ ተቀምጦ ናፍቆቱ ጎዳኝ
በጄ እንዳልዳስሰው ባይኔ አይታየኝ ....... እያለች ስታዜም
የእማማን አባባል አረጋግጥበት ነበር ::
ምናልባት አስናቀች ፍቅርን ይሆናል እንደዚያ የምትለው...... ቢሆንም ቢሆንም ከልጅ በላይ ምን ፍቅር ይገኛል ? እያልኩም አንድ ቀን ስወልድ ድድድ.... የሚል የቀን ተስፋ እንድሰንቅ አድርጎኝ ነበር ያደግኩት ::
እንደምን ከርማችኍል የማፈቅራችሁ የአዶላ ልጆች
ስለፍቅር እና ስለ ተስፋው ላወራላችሁ የተነሳሁት ዋርካ ገብቼ ሶስት ቀን ሙሉ ሳነብ ስገረም ስስቅ ስናደድ ደስ ሲለኝ ስቆም ስቀመጥ ካሳለፍኩ በኍላ ነው::
ግን ደሞ ምን መሰላችሁ ስለፍቅርና ፍቅር ብቻ ስናወራ ዘመን እንዳያልፍብን ስለፈራሁ እስቲ ስለቃልኪዳን እና ስለ ትዕግሥት እንነጋገር
ብዬ የዛሬውን ስንቄን ለመፍታት ተነሳሁ::
ለነገሩ ዛሬ እዚህ ብቅ ካልኩ ሁለተኛ ቀኔ ቢሆንም ዝር ስለማትሉ ቶሎ እንደማታዩኝ እገምታለሁ ምክንያቱም አንድ መንፈቅ ያህል የተዘጋውን ቤት ማን ሊያየው ይመጣል ብዬ ፍራቻ ቢጤ ይዞኝ ነበር ነገር ግን ቢያንስ ቢያንስ አንፈራራን አገኛለሁ አልኩና ስጋቴን በድፍረት ልውጥ !!
ቃልኪዳን እና ትዕግጽት ምንና ምን ወይንም ማን እና ማን እንደሆኑ ወደራሴ ህይወት ውስጥ ገብቼ ማፈላለግና ማየት ሞክርኩኝ :
ፖለቲካ ውስጥ- ህዝብ ውስጥ -ሙዚቃ ውስጥ -ሥዕል ውስጥ -ካሜራ ውስጥ - መጽሃፍ ውስጥ -ኅሊና ውስጥ ? የት ነው ቃልኪዳን እና ትዕግስት ያለው ? በዕውነት መጻህፍትን አንብቤያለሁ እላለሁ እንደፍቅር የሚገዛኝ እና የሚማርከኝ ምንም የለም::
የማነበው ጽሁፍ አልሆነ ቦታ ስለጣለኝ ንድድ አልኩና ታሪኩን ፍለጋ በቀጥታ ወደቦሬ እና ጎሳ አካባቢ አቀናሁ::
አካባቢውን ጂኦግራፊውን አየሩን የህብረተሰቡን ሁናቴ ወጣገባውን ዞርኩኝ ማንም ሊያሳየኝ አልቻለም
አሳምሬ የማውቃቸውን የሃሮ ቡቁዩን ስም ከታሪኩ መሃል ይዤ ነበርና በድካም አረፍ ካልኩበት መቶቆማ ስር ተጋድሜ ስለሳቸው ማሰላሰል ጀመርኩ ሆኖም ከድካም በስተቀር ምንም እንደማይተርፈኝ ሆኖም ያነበብኩት ልዩና (ፈረንጆቹ ክላሲካል እንደሚሉት )ዓይነት ጽሁፍ ውስጥ ብቻ እንደሚገኝ ተረዳሁና ተውኩት::
ምን ነገር ይዘበዝባል እንደማትሉኝ እርግጠኛ ነኝ ብትሉኝም ለኔ የገባኝ ለናንተ አልገባችሁም ማለት ነው ብዬ ከማለፍ በቀር ምንም የምለው የለም::
ከፍቅር በላይ ምን ልዘበዝብ ትፈልጋላችሁ ከጀዋኒ ጊቢ እስከ ወሎ ድረስ የተሰመረው መስመር አሁንም ቀለሙ ሳይደበዝዝ በውስጤ እንዳለ ነግሬያችሁ አልነበር ?
የጎሳ እና የጽጌ ፍቅር ብቻውን የሰው ፍቅር ነው ነገር ግን የታሪኩን ፍሰት በትክክል ብታዳምጡት በውስጡ ያለው እጅግ ኃይለኛ ቃልኪዳን እና ትዕግስት ነው !
በእያንዳንዷ ቃላትና እንቅስቃሴ ውስጥ ቃልኪዳን እና ትዕግስት አለ::
እንደታሪኩ መዘውር ጽጌ እና ጎሳ አሁን ተለያይተዋል አይገርማችሁም ? ከሁለት ቀናት በፊት ነው የታሪኩን ሲሶ ያህል እንዳነበብኩ ቀሪውን እና ሙሉውን ፕሪንት ያስደረኩና በወረቀት አንብቤ የጨረስኩት ያንን ለማድረግ 340 ብር ከፈልኩ::
አባታችን ዘመናቸውን ሙሉ ሃገራቸውን አገልግለው በወር 340 ብር ሳይከፈላቸው ነው ወደመቃብር የገቡት:ዛሬ ሃያ ሰላሳ ገጽ ወረቀት ፕሪንት ለማስደረግ 340 ብርርርር የኢኮኖሚው እድገታችን አሪፍ ነው አይደል ? ወያኔና ኢትዮጵያ እንዲህ እንደተፎጋገሩ ሁለት አስርት አለፋቸው ? .... እስቲ ፖለቲካውን እንመለስበታለን ወደቁምነገሬ ልመለስ ::
እና ያንን የፍቅር ታሪክ ሳነብ ፍቅር ማለት ምን ማለት እንደሆነ እና በህይወታችን ውስጥ ምን ያህል ጉልበት እንደነበረው አሰላሰልኩ :ታዲያ ስለምንድን የሰውልጅ ክፉ ይሆናል ? ስለምንስ ክፋት ይኖራል ? እየሱስ ክርስቶስ ከፍቅር ሌላ አስተምሮናልን ? አለሂ ሰላት ወሰላም ነብዩ መሃመድ ፍቅር የሰዎች ሁሉ የህይወት መመርያ ይሁን ብለው አላስተማሩምን ? ስለምን ፍቅር ከሰዎች ትርቃለች ? ስለምን ሰው በቃልኪዳኑ አይጸናም ? ስለምንስ ሰው ትዕግስተኛ አይሆንም ? እያልኩ ሃሳቤን ማቆም እስኪያቅተኝ ድረስ የፍቅራቸውን ግለት ሞቅኩት::
ይሄ ልጅ ይህንን ፍቅር እኛ ውንድሞቹ ዘንድ መጥቶ ሊዘክር የወደደበትን ሚስጥር ተረዳሁ
ጎሳን ወደድኩት ጽጌንም አደነቅኳት
በዚያ ፍቅር ውስጥ እርካታን አገኘሁ በዚያ ፍቅር ውስጥ ሰላምን አገኘሁ ደስታን አገኘሁ ጎሳ ምንኛ ታድለህ ነበር! አልኩ በውስጤ ::
እርግጥ ነው ስለ ፍትህ ብዙ ወጣቶች ህይወታቸውን ከፍለዋል
ስለ ሰላም ሚሊዮኖች ራሳቸውን አሳልፈዋል ::በጸረ ፍትህና ሰላም አንጻር ሰዎችን የሚዋጋው ግን ሰው ነው ይሄ ነው እኔን የሚያስጨንቀኝ::
አልፎ አልፎም የማነባቸውን መትሳህፍት አስታወስኩና
ስለ እርግማን ስለ ትግል ስለ ውቨት ኢኮኖሚ ስለ ወንጀል ስለ አታላይ ፖለቲከኛ ወዘተ እያነበብኩ ቆይቼ እዚህ ቤት መጥቼ ስላነበብኩት ጥሩ የፍቅር ታሪክ ህዋሳቶቼ መዝናናትን እንዲያገኙ ስለረዳሃቸው አመሰገንኩህ::
የአለማየሁ ኒኮላስን እና የተዋበች ደንቦባንም ጣፋጭ ታሪክ ለመጨረስ አሁንም እንደጓጓአሁ ነው
ዛሬ ማንም ሰው ማለት እችላለሁ ገንዘብ ለማግኘት የሚከፍለውን መስዋዕትነት ለፍቅር አይከፍለውም አይገርማችሁም ? እኔን ይገርመኛል::
ጎሳ ጥሩ አፍቃሪ ልቦና ያለህ ያገራችን ልጅ በመሆንህ ደስ አለኝ ብዙ አስተያየቶችህን በጽሞና አየኋቸው ቀጥተኛና ግልጽ ናቸው የዋህና አዛኝ ነህ ስለዚህም ወደድኩህ !
ይሄንን አንብቤ እንደጨረስኩ ቀልቤን የሳበኝ የዚያ የከውካዋ ነገር ነው መቸም አጭርና ምን አንቱ ሳይባል ያረጃል እንዲሉ ባለሱቅ የደረስክበት ማዕረግ አንቱ እንድልህ ቢያስገድደኝም ፍቅርህ ብቻውን እንደፈለኩ እንድናገር ድፍረት ይሰጠኛል::በምንም ይሁን በምን ስምህን በጠራሁ ቁጥር ሁሉ አክብሮቴ አብሮህ እንዳለ :ግን አትርሳ : :
የሆነው ሆኖ ይሄ በየሄድክበት እቃ መጣልና እቃ ማንሳት በቃ አመልህ ሆኖ መቅረቱ አሳስቦኛል ? አንድ ቃል እንዳትተነፍስ ዋ አለዛ ያነሳሃትን ሁሉ ከች ነው ማረጋት :: በነገራችን ላይ ስለ እኔና አንተም ጥልና ፍቅር አንብቤያለሁ ግን ትዝ አይለኝም ::
ይገርማል እግረመንገድህን ስለ ወይዘሮ አዜብ መስፍን ከፈረንጆቹ ባልደረቦችህ የሰማሃት ዜና በጣም ዘገየችብህ እንጂ መስማትህ አንተን ሳይሆን እኔንም አሞኛል ዳሩ የሷ ነገር ሁሌም እንዳመመኝ ነው::
በባለ ራዕዩ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ላይ በደረሰው ሞት ወይንም በቀዳማዊት እመቤታችን አዜብ መስፍን ላይ በደረሰው መሪር ሃዘን የተሰማኝን ሃዘን የዛንው ሰሞን አግኝቻችሁ ባካፈልኳችሁ ደስ ይለኝ ነበር አሁን ስለ አርባው ካልሆነ በቀር ስለ ለቅሶው ብናገር የከርሞ ሰው ብላችሁ እንዳትስቁብኝ ፈራሁ ::
ያም ሆነ ይህ በመሃከላችን አለመግባባቶች እንዴት እንደተፈጠሩ እኔ ያየሁትን አንድ ሳልል ማለፍ ስሜቴ አልፈቀደልኝምና እመለሳለሁ
ቸር ያቆየን ወዳጃችሁ አደቆርሳ ዘሃገረ አዶላ

አንፈራራ
Runner
Runner
Posts: 50
Joined: 03 Jan 2012 12:51
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread postby አንፈራራ » 19 Oct 2012 07:38

ወየው አደቆርሳ....እልልልልል እንኳን በደህና መጣህ...ሁሉም ቤት ጭር ብሎ ነበር:: ግን እዚህ መምጣት እየፈለኩ አንተ በመጨረሻው መልክትህ እንደማትመለስ ስለጠቆምክ እኔም ወደዚሁ መምጣት አቆምኩ:: ግን ዛሬ እድሜ ለ ከንቲባ እርሱ ነው እዚህ መሆንህን የነገረን::

ስለ ፍቅር እንዲሁም ስለ ጎሳ የጻፍከው እኔም የምስማማበት ነው...ጎሳም ከጽጌ ጋር ያለውን መጨረሻ ሳይነግረን አሁንም እየጠበቅን ነው...ወደዚህ ቤት እንዲመጣም ፈልገን ነበር ምክንያቱም "ኢትዮፎረም" ታሪካችንን በ ፎቶና በ ቭዲዮ እንድናስደግፍ ስለሚያስችለን ነው::

የዓለማየሁ ኒኮላስና የተዋበችም ጉዳይ በሕይወት አለ: እስቲ ፍጣሜውን በቅርቡ እናያለን ብየ ተስፋ አለኝ::

እኔ ሳር ሳጭድ ያላየሁት የዛፍ ጉቶ አደናፍቆኝ ግራ እግሬን ስለተጎዳሁ ለ አንድ 4 ወር ያህል ብዙም እንቅስቃሴ አላደረኩም:: የሚገርመው እግርህን በሃይል ከተጎዳህ ለካ ሌላ ነገር ለመስራትም አያምርህም:: ግን እግዚአብሔር ይመስገን አሁን ስለተሻለኝ እኔም ወዳልተጨረሰው ሥራ ተመልሻለሁ::

በፌስቡክ በባልነት ወደ 400 የሚጠጉ የአዶላ ልጆች የሚተራመሱበት ክፍል አለ:: እዚያም ባለሱቅ ብቅ ሲል አቤት የሚያጅቡት ቲፎዞዎች በተለይ ሴቶቹ :D የሚያስደንቅ ነው:: ራስብሩም እኔም እዚያ ቤት ብቅ እያልን አንዳንድ ነገር ጣል አርገን እንወጣለን:: እስቲ አንተም ብቅ በል::
እንኳን ደህና መጣህ: ከንግዲህ እኔም ብቅ እላለሁ::

አደቆርሳ
Jogger
Jogger
Posts: 45
Joined: 13 Jan 2012 04:13
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread postby አደቆርሳ » 26 Oct 2012 16:10

አንፈራራችን እግዚአብሄር ጨርሶ ይማርህ ዋናውኮ እግር ነው በተለይ ያለህበት ዓለም ካልተንቀሳቀሱ ህይወት የለም ስለዚህ በደንብ ታከም ትልቁ ነገር ግን እዛ ታክሞ መዳን አለ ::
የምወድህ ባለሱቅ እንደምን አለህልኝ በቀደም እዚህ መጥቼ እንደለመድኩት መጫር ከመጀመሬ በፊት ከዚህ ቀደም (የዛሬን አያርገውና ) ደሃ ፌስ ቡክ ሬጂስተር አድርጋ መጠቀም እንድምችል ነግራኝ ነበር የሄደችውና ብዙም ስላልታየኝ ዝም አልኩና ተውኩት : ታዲያልህ ትናንት ጊዜ ስለነበረኝ ልሞክረው ጎራ እልልሃለሁ አንፈራራን እንደዓሳ አጥማጅ ቁጭ ብሎ አላገኘው መሰለህ ?
በዚህ ላይ በአይኔም አየሁት በቃ ሌላ ከተማ ውስጥ የገባሁ ሁሉ ነው የመሰለኝ ደስ አለኝ ሞቀኝ እያዟዟረ እያንዳንዱን ክፍል ካስጎበኘኝ በኋላ ጥሎኝ ሄደ የቻልኩትን ያህል አነበብኩ ጻፍኩ የፌስ ቡክ አጻጻፉ የልብ አያደርስም እንጂ ብዙ የአዶላ ልጆች አሉ ከነሙሉ ስማቸው የአራዳ አካባቢ ልጆችማ አንተ ነህ መሰለኝ የሰበሰብካቸው ሞልተዋል::
ሆኖም በጣም ከጥቂቶች በስተቀር አንዳቸውንም አላውቅም ያወቅኳቸውንም በስም ብቻ ነው
ቆይቼ ግን አንድ ጥያቄ ለራሴ አቀረብኩ ምን አትሉኝም ራስብሩ ሩም ውስጥ ይሄ ሁሉ ሰው መምጣት ለምን አቃተው ? የሚል ..... ነገር መደጋገም እንዳይሆንብኝ ልተወውና ወደጉዳዬ ልግባ : ብቻ ባለሱቅን ሞፊቲኮዬን ራስን አንፈራራችንን እንዲሁም ጎሳን አልጣችሁ እንጂ ......በሉ ቸር ያቆየን ወዳጃችሁ አደቆርሳ ዘሃገረ አዶላ

አንፈራራ
Runner
Runner
Posts: 50
Joined: 03 Jan 2012 12:51
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread postby አንፈራራ » 05 Feb 2013 18:56

ሰላም ለክብረ መንግስትና ለአካባቢው ልጆች

እንኳን ለፈረንጆቹ 2013 ዓ.ም. በሰላም አደረሳችሁ:: ስለ አካባቢያችን ሆነ ስለራሳችን ወይም ስለምንፈልገው አርእስት ለመወያየት ብንፈልግ ከዚህ የተሻለ ቤት አናገኝምና እስቲ እባካችሁ እዚህ እየመጣን ቤቱን ሞቅ ሞቅ እናድርገው::

የዚህ ዌብሳይት አስተዳዳሪዎች በውነቱ በጣም የሚመሰገኑ ናቸው: ምንም ዓይነት ጥያቄ ሲኖረን በተቀላጠፈና በጨዋ መንገድ ሁሌ ስለሚረዱን ቤቱን እንደ ቤታችን አድርገን እንድናየው ያስፈልጋል:: በፌስቡክ የክ/መ አዶላ ሻይ ቤት የሚባል ተከፍቷል ግን እዚያ መጻፍ የሚቻለው ከአንድና ሁለት መስመር በላይ ስለማይሆን እዚያ ያሉትንም እየጋበዝናቸው ወደዚህ እናምጣቸው::

አደቆርሳ ራስብሩ ሞፊቲ ባለሱቅ ጎሳ ኦዶ ሻኪሶ የግል አይፋ የቦሬ ሌሎችም ለጊዜው ያልጠቀስኳችሁ ወደዚህ ብቅ በሉ::

አክባሪያችሁ

አንፈራራ
Last edited by አንፈራራ on 06 Feb 2013 16:03, edited 1 time in total.

ራስብሩ
Starter
Starter
Posts: 23
Joined: 03 Jan 2012 09:45
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread postby ራስብሩ » 06 Feb 2013 11:46

ጤና ይስጥልኝ
ውድ አንፈራራችን እንደምን አለህ ?
ፋየርፎክስ አላስገባ ብሎኝ ትቼው እንደገና በኤክስፕሎረር ስሞክር በቀላሉ ሎግ ኢን ማድረግ ቻልኩ::
ያስቀመጥክልን መልክት ትክክል ነች በሚገባ ተቀብለን እዚሁ ብንሰባሰብ ጥሩ ነው::
ዋርካ በአደገኛ ዌብሳይቶች ተራ ውስጥ ገብታለች::
ከእንግዲህ በኋላ የጀምጀም ልጆች መሰባሰቢያ ይህ መድረክ ቢሆንና በደንብ ብንገናኝበት መልካም ስለሆነ የአንፈራራን ሃሳብ ሙሉ በሙሉ እቀበላለሁ::
የዚህ ፎረም ባለቤቶችም አጠቃላይ ዶክሜንቶቻችንን እዚሁ ስላመጡልን እንደዚህ በአንድ ጀምበር ሃብታችንን ከማጣት አድነውናልና ምስጋና ይድረሳቸው::
በፌስ ቡክ የአዶላ ካፌ ሩም ውስጥ ያላችሁ መላው የጀምጀም ልጆችም ወደዚህ መጥታችሁ የማዕዱ ተካፋይ እንድትሆኑ ግብዣ እናቀርባለን !
ራስብሩ

ሞፊቲ
Jogger
Jogger
Posts: 33
Joined: 03 Jan 2012 14:19
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread postby ሞፊቲ » 07 Feb 2013 15:24

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን::


አንፈራራ= ፌስቡክ ላይ ስላስታወስከን ምስጋና ይድረስህ:: ዋርካ ሃይለኛ ጉዳት ደርሶባት መገናኛችን ስለተቋረጠ እዚህ እንድንመጣ እንደተለመደው ምቾት ስለሰጠሀን መሰባስበችን አይቀር ሆኑአል::


ለግዜው አለሁ ለማለት ስለመጣው የምለው የለኝም::እንደማንጠፋፋ ተስፋ በማድረግ ለነገ ብቅ ለማለት በቃል እየተስማማሁ ሰላም ሁኑልኝ እላለሁ::


ቸር እንሰንብት!!!

አደቆርሳ
Jogger
Jogger
Posts: 45
Joined: 13 Jan 2012 04:13
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread postby አደቆርሳ » 12 Feb 2013 14:51

ለዘመናት ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን ሬዲዮ ጣቢያ ጀግናው የኢህአዴግ ሠራዊት ለሰፊው ህዝብ ጥቅም ተቆጣጥሮታል የሚለውን ለዛ ያለውን አማርኛ ከሰማሁ 22 ኣመት መሆኑ ነው መሰለኝ አሁን ደሞ ሌላ አማረኝ :: ምን የሚል ? አትሉኝም............ ለዘመናት ዋርካ ሲጠቀምበት የነበረውን የራስብሩን ሩም ጀግናው የኢትዮ ፎረም ሠራዊት ለመላው የአዶላ ልጆች ጥቅም ተቆጣጥሮታል..... የሚል ::
አይገርማችሁም በቅርቡ ፍቅር አስገድዶኝ ዋርካ ከመጣሁ በኋላ እነዛን የምወዳቸውን የዋርካ ልጆች እንኳን መለስ ብዬ አይቻቸው አላውቅም ነበር ::
ያም አለ ያም አለ ያተር ገለባ ነው
ሳቅና ጨዋታ ከሚወዱት ጋር ነው .......... አለች ብዙዬ ነፍሷን ይማረውና
ሳቅና ጨዋታችንን በማይጎረብጥ ቦታ... ድሮ ትዝ ይላችኋል መሸት ሲል ሰፈር አካባቢ ወይንም ትምህርት ቤት ጊቢ ውስጥ ሳር ላይ ሰብሰብ ብለን ስንቀመጥ የምንጫወተው ጨዋታ ሳቅና ቀልድ በተለይ ሴቶች መሃላችን ቀየጥ ካሉማ አቤት እንዴት ደሰሰስስስስ እንደሚል እንደዛ ነው የዚህ ቤት ጨዋታ ::
ግን ደሞ አንድ ጥያቄ አለኝ
ምናልባትም ከአንድና ሁለት ልጆች በስተቀር ይሄንን ኢትዮ ፎረም አትወዱትም ለምንድነው ?
እርስበርስ የምትተዋወቁበት ጉዳይ አለ ? ወይንስ ፖለቲካ ነገር አለው ? ምንድነው ችግሩ ?
ግልጽነት ካልጎደለብን በሰተቀር ለምን በነጻነት አትናገሩም ?
አንተ ሸፋፋ የአራዳ ፈሪ አሁን ምን ይዋጥህ ? እያነከስክም ቢሆን ትመጣታለህ ::
ፈሪ ስል ምን ትዝ አለኝ መሰላችሁ በጣም ልጆች ነበርን አንዴ የራስብሩ ትምህርት ቤት ተረበሸና ጊቢውን ቀወጥነው ትልልቆቹ የትምህርት ቤቱን መስታወት የቻሉትን ያህል ካደቀቁ በኋላ ጊቢውን ሲያምሱት እኛ የሚሆነውን ከማየት በስተቀር ምንም አናደርግም ነበር::
ሴቶች አጥሩን እየሾለኩ ለማምለጥ ሲታገሉ የጊቢው ሸቦ አጥር ቀሚሳቸውን ሲቀማ እኛ ድራማ እናያለን::
ተማሪው በሰልፍና በዝማሬ ወደ አራዳ አውራጃው አስተዳደር አካባቢ ሊሄድ ሲዘጋጅ
በኋላ ሳይታሰብ ፖሊስ ጊቢውን ከበበና በተኩስ አካባቢውን አቀለጠው ይሄኔ ወዴት እንደሮጥን እንኳን አናውቅም በአጥር ሾልኬ ቁልቁል ስንደረደር አንዱ ፊት ለፊት ያየሁትና ክፍት ያገኘሁት ቤት እየተንደረደርኩ ዘው !
ዘው አልኩና የገባሁበትን በር ዞሬ ጥርቅም አድርጌ ልዘጋ ስል አንድ የኔ ቢጤ ፍርሃት ያበረረው ኖሮ ገባለሁ አትገባም ዓይነት ስንታገል አሸንፎኝ እሱም ዘው ! እንደምንም በደመነፍስ ዘጋሁትና ጭለማ ውስጥ ሰው ቤት በፍርሃት ሳለን ድንገት ከኋላ በኩል የቤቱ ባለቤት ወደውስጥ ሲገቡ እኔና አስቴር ገላን የምትባል ልጅ ተናንቀን ቆመናል::
አቤት እንዴት ፈሪ ነበረች ቅቅቅቅቅ አለች የግልዬ
ፍርሃት ግን አይገርማችሁም እየሮጠች ስትመጣኮ ሴት ትሁን ወንድ ወታደር ትሁን ተማሪ ምንም አልለየሁም ነበር ከዛ በኋላም እንደኔ የፈራች መሆኗን እንጂ ሴት ትሁን ወንድ እንኳ አለማወቄ ቱ ምንያለሁት በጭባጫ ነበርኩ ሳስበው ግን እስካሁን ያስቀኛል::
ወዳጃችሁ አደቆርሳ ዘሃገረ አዶላ

ራስብሩ
Starter
Starter
Posts: 23
Joined: 03 Jan 2012 09:45
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread postby ራስብሩ » 13 Feb 2013 11:46

Jigsa እንደጻፈው

Jigsa wrote:የተከበራችሁ የጀምጀም ተወላጆችና ወዳጆች!
በ አዶላ ኮፊ ኤንድ ቲ ሩም የተዋወቅናቸው ወዳጃችን ምስጋና ይድረሳቸውና ይሄው በዚህ መድረክም ብቅ ለማለት ችያለሁኝ፡፡ እኔ አቶ ጅግሳ ገበያ ክፍል ተወልጄ ፈረንጅ ውሃና ካምቦ አድጌ የአዶላ አባዜ ልለቅህ ብሎኝ ነጌሌ ቦረናና አዶላ መካከል ስወዛወዝ ጠጉሬ ላይ የማላውቀው ነጣ ነጣ ያለ ጸጉር ነገር ወጣብኝ፡፡ ወጉለበቴም ደከም እያለ አይኔም እንደወትሮው አልሆን ማለት ጀምሯል፡፡
አንዱ ወዳጃችን ማን ነበር ስለ አቶ ቢሉ ባነታ አንስቶ ኢህአዴግ ወደ አዶላ ሲገባ ጦር ወደ ሃገረ ሰላም ይዞ መዝመቱን ያስታወሰኝ፡፡አረ እኔ ራሴ ነበርኩኝ አዶላ ስታዲየም ላይ ግንባሩ ሲቋቋም… ወደፊት ጫር ጫር አድርጌ አወጋችኋለው ይህ ፎረም እንዲህ ያለ ነገር ፖስት ማድረግ ከፈቀደ!
ነገር ግን ይህ ፎረም ትዝታን ከማውጋት በሻገር ስለ ሀገራችን ፣ ት/ቤታችን… ወዘተ መልሶ መቋቋም የምናወጋበት (በዘመኑ ቋንቋ) ልማታዊ መድረክ ብናደርገው! ቅቅቅቅቅቅ! ቸር ሰንብቱልኝማ!
ወንድማችን ጅግሳ እንኳን በደህና መጣህ
ወደ ጀምጀም ሩም ስመጣ መንገድ ላይ ያንተን ፖስት ተመልክቼ ወደቤቱ አስገብቼዋለሁ::
ስለዚህ በሚቀጥለው ፖስት ስታደርግ መጀመሪያ የጀምጀም ልጆች መገናኛ የሚለውን ሩም መክፈት ከዛም መልስ የሚለውን በመጫን ዋናው የወዩ ዋርካ ሥር ተሰብስበን እንጠብቅሃለን::
ሌሎቹም እንደዚሁ ቢመጡና ወራ አዶላ አንድ ላይ ብንገናኝ በጣም ደስ ይለናል ::
በድጋሚ እንኳን በደህና መጣህ !
ራስብሩ


Return to “የጀምጀም ልጆች መገናኛ”