Page 2 of 29

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Posted: 03 Jan 2012 17:08
by bohera
ሰላም
ይድላቹ እንደ.......... ዋርካ ጻፉልን በደንብ እዚህም ቢሆን እየመጣን እናነባለን

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Posted: 03 Jan 2012 17:16
by bohera
ይድላቹ እንደ.......... ዋርካ ጻፉልን በደንብ እዚህም ቢሆን እየመጣን እናነባለን ለቤቱ ምርቃት አታስከፍሉም ብዬ ነው ደፍሬ የገባሁት ...ቅቅቅቅ በሉ ጨዋታ ለቀቅ ለቀቅ አድርጉልና

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Posted: 03 Jan 2012 17:48
by አንፈራራ
ቦኸራ እንኳን ደህን አመጣህ ...በጣም እናመሰግናለን ...ይልመድብህ


እዚያኛው ቤት እየደበረን መምጣት አቁመን ነበር:: አሁን ግን እዚህ የሚመቸን ይመስለኛል: በተጨማሪም ባልሳሳት ፎቶዎችም ማስቀመጥ እንችላለን:: አስተዳዳሪዎቹ በጣም የሚመቹ እኛንም ለመርዳት የተዘጋጁ ስለሆኑ በጣም ደስ ብሎኛል:: በአማርኛ በቀላሉ እንዴት እንደሚጻፍ የሚያስችል ቭዲዮ ልከውልኛል እንዴት ወደዚህ እንደማመጣው ግን ገና አላውቅሁም:: እስቲ እሞክራለሁ::


እስከዚያው ግን መልስ ለመጻፍ ስትፈልጉ በመጀመሪያ "በአማርኛ ለመጻፍ" የሚለውን ትጭናችሁ አዲስ ገጽ ትከፍታላችሁ:: መልክታችሁን በዚያ ገጽ ከጻፋችሁ በኋላ መልክታችሁን ኮፒ ታደርጋላችሁ: ከዚያም "ፖስት ኤ ረፕላይ" የሚለውን ተጭናችሁ የመመለሻውን ገጽ ትከፍታላችሁ:: ከርሱ ቀጥሎ ኮፒ ያደረጋችሁትን መልክት መመለሻው ግጽ ላይ ፔስት ታደርጋላችሁ:: ገጹ የፊደሎቹን ትልቅነት ምርጫ ስለሚሰጥ ያንንም ማድረግ ትችላላችሁ:: ደግሞ ከጻፋችሁ በኋላ ቀሪ ስላለ አንዳንዴ ዋርካ ላይ እንደሚሆነው ጽፋችሁ ጽፋችሁ ብን ብሎ አይጠፋም:: ስለዚህ በዚህ መንገድ ሞክሩና ጫወታው ይድራ::


አዶላን በተመለከተ አንድ የቀድሞ ታሪክ ስላለኝ ከተመቸኝ ነገ ብቅ እላለሁ:: ቻው!

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Posted: 03 Jan 2012 21:06
by ኦሽንoc
ሰላም የጀምጀም ልጆች:

እዚህ ሰፈር ጭቃ ሹም ቢጤ ስለሆንኩ ሁላችሁንም እንኳን ደህና መጣችሁ ብዬ እንዲያው ጥያቄ ቢኖራችሁ በተቻለ መጠን ለመመለስ እንደምሞክር ለመግለጽ ነው አመጣጤ::
ላሁኑ የአማርኛ መጻፊያውን ነገር የበለጠ ቀላል ለማድረግ እየሞከርን እንደሆነ መናገር እፈልጋለሁ:: እኔ የምጠቀምበት ቀላል የሆነ መንገድ አለ እንዴት እንደሆነ የምታሳይ ትንሽ ቬዲዮ ማስተማሪያ ስላለች እሱዋን ከታች ተመልከቱልኝ::
በዚህ ፎረም ምስልን ጨምሮ ቬዲዮ : ኤምፒ3 ድምጽ ፋይል : ፒዲፍ ፋይልን እና ሌሎች ነገሮችን ፖስት ከምታደርጉት ነገር ጋር ማስገባት ትችላላችሁ::
ይህችን ምስል ተመልከቱ::
Image




ይህች አጭር ቬዲዮ ደግሞ እንዴት በፋዬር ፎክስ ብራውዘር በቀላሉ አማርኛ መጻፍ እንደምንችል ታሳያለች:: የሚጫንበት ሊንክ ከታች ይገኛል::

[youtube]http://www.youtube.com/watch?v=FtFplPQfXj0[/youtube]

የፋዬርፎክስ መጻፊያ ማጣቀሻ
https://addons.mozilla.org/en-US/firefox/addon/any-key/

አድ ኦኑ ከተጫነ በሁዋላ
Go to Tools > Anykey Settings >
When the Setting box opens click Keymaps
then Select ethiopic sera as it showed below then Apply then Close
Image

በዚህ ፕሮግራም እና በማንኛውም ነገር ላይ ጥያቄ ካላችሁ በተቻለ መጠን ለመመለስ እሞክራለሁ

መልካም ጊዜ ለሁላችሁም::

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Posted: 04 Jan 2012 17:28
by አንፈራራ
ሰላም ወገኖች

ያሉንን ፎቶዎችና ቪዲዮዎች እዚህ ፔጅ ላይ ማስቀመጥም ስለምንችል፣ እስቲ ከዋርካ የተፋቁትን ፎቶዎቻችንን አምጥተን እዚህ እንጫን። እኔም አንዳንድ ፎቶዎች ስላሉኝ የማስቀመጥ ዘዴውን ካወቅሁበት በኋላ እዚህ አመጣቸዋለሁ። በነገራችን ላይ ዋርካ ያሉትን ፋይሎቻችንን እንዴት ወደዚህ ማምጣት የሚቻልበትን መንገድ እኔም እየፈለኩ ነኝና ባለሱቅና አደቆርሳ የሚያሳስባችሁ አንዱ ይኸ እንደሆነ ይገባኛል፣ ለነገሩ ሁላችንም ብንሆን ፋይሎቹ ቢመጡልን ደስ ይለናል። ከዋርካ መልቀቃችን ቅር የሚያሰኝ ነገር ካለ የፋይሎቻችን ጉዳይ ነው። ግን እነሱን እዚህ ማምጣት የሚቻል ይመስለኛል።

ቻዎ!

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Posted: 04 Jan 2012 17:40
by bohera
አንፈራራ ፎቶ መለጠፍም ሆነ ዮትዮብ ማስገባት በጣም ቀላል ነገር ነው....ፎቶ ለማስገብት ወደታች ወረድ ስትል ታገኘዋለህ....መቼም ያገራችሁ ሰው ባልሆንም አንባቢያችሁ ነበርኩ ..እዚህ ደግሞ ከተመዘገብኩ 2 አመት..እናንተን ተከትየ ነው የመጣሁት ..ስደት እኮ እንዲህ ያንከራታል...ቅቅቅቅቅ

እስኪ ይችን ዘፈን ጋብዠ ልውጣ

[youtube]http://www.youtube.com/watch?v=vS3LoHNQl_Y[/youtube]

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Posted: 05 Jan 2012 07:06
by አንፈራራ
ሰላም ቤቶች

ከዚህ በፊት ዋርካ ላይ ለጥፈን በኋላ ግን የተነሱትን አንዳንድ ፎቶዎች ለማስታወስ ያህል እዚህ ለጥፋቸዋለሁ:: እነሆ! መልካም ቀን::
407.JPG
407.JPG (2.15 MiB) Viewed 5209 times

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Posted: 05 Jan 2012 13:46
by ሞፊቲ
sorry