የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Forum rules
No cursing, bad language and offend other users !
No pornographic images or links!
This forum monitored regularly. We will BAN users without warning for not obeying rules.
እባክዎ የፎረሙን ህጎች ያክብሩ::
Dole
Starter
Starter
Posts: 19
Joined: 04 Jan 2012 20:47
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Dole » 28 Feb 2012 02:56

ከንቲባ ወንድሜ
አመሰግናለሁ የአደቆርሳን ምርጥ ፅሁፍ እዚህ አምጥተህ በመለጠፍህ
አንተ አደቆርሳ
ስለ-ደራሲ ስብሀት ገ/ግዚአብሄር የጥሣፍከውን አንብቤ... በቅናት ድብንንንን ብዬልሀለሁ
ለምን ብትለኝ
እኔ ለምንድነው የማደንቃቸውና የምወዳቸውን ሰዎች ሳልጨብጣቸው የሚያልፉኝ
ከምር በጣም ቀናሁ
ማንም ከመሞት አይድንም.. ነገር ግን ከመሞቱ በፊት ያንን ሰው ምን ያህል እንደምንወደው እና እንደምናደንቀው የምንገልፅበት አጋጣሚ ቢፈጠር እንዴት መልካም ነበር
እዚህ ያለሁበት አገር በአመት አንዴ ወይም ሁለቴ ገንዘብ እየከፈልክ የምታደንቀውን ሰው እጅ የምትጨብጥበት ፕሮግራም አለ
ገንዘብ ከፍለህ ተሰልፈህ ጨብጠኸው.... እንደምታደንቀውና እንደምትወደው ነግረኸው... እድለኛ ከሆንክ ፎቶ ተነስተህ ማለፍ
በገንዘብ የማይገኝ ደስታ እኮ ነው
አሁን ጥላሁንን በአሉ ግርማን ስብሀትን እንዲህ አድርገው ቢያቀርቡልን.... ምን ነበረበት አሰኘኝና ....
ድህነታችንን እናስታምም... ፖለቲካችንን... እናጠናክር... ጠላቶቻችንን እናብዛ... ወይስ እጅ ለመጨበጥ ስራት እንጨነቅ ሲሉኝ ሰማኃቸው... እና-እንትና
ደሀ ድሮስ ድሀ አገር የተወለደ... የኪነትሰው እንደደኸየ አይደል ሚያልፈው
ኤኒዌይ....
ግሩም ደራሲ ነው ያጣነው.... በተረፈ የበአሉ ግርማን ደራሲውን በተመለከተ... የገጠመኝን ገጠመኝ.. አንድ ቀን አጫውታቹዋ;ለሁ
እግዜር የዛ ሰው ይበለን
እስኪ ደራሲው ውስጥ ያለውን ውሻ ታሪክ ማነው ሚያስታውሰኝ?
ይሸለማል ከምር
............................................//.............................
ወንድሜ ተድላ
ስለጉተማ ለማውራት አንድ አዲስ ሙድ ያስፈልጋልና
ታገስ ካልተወራ ይነገራል
ምን ገዶን
አሁን ፊያሜታን እንሰናበታት
...................................//........................
> ሳትሰናበቺኝ እንዳትሄጂ... ብያት
+ እረ በፍፁም አላረገውም.. ብላኝ
በአንድ ቀኑን በማላስታውስበት ቀን ስልክ ደወለችልኝ
ከደቡብ ሱዳን.... ጁባ
> ሄድሽ እንዴ?
+ በድንገት ተነሺ አለኝና በሌሊት ይዞኝ ወጣ
> ላምን አስቸኮለሽ
+ ወደ-ሊቢያ ሊሄድ ስለተነሳ.... አስመራ ምትሄጂ ከሆነ አሁኑኑ ተነሽ ብሎኝ... ስልክ መደወያ ጊዜም አጣሁ
> ሊቢያ ለምን
+ አላውቅም.... ካርቱም ስደርስ ደውልልሀለሁ... አደራ ደውልልኝ
ብላኝ ተለያየን
በማግስቱ ስደውልላት ካርቱም ገብታለች... ከሁለት ቀን በኃላ ወደ ኤርትራ በባስ እንደምትሄድ ነገረችኝ
እንዳለችውም ከሁለት ቀን በኃላ ሳይሆን ከአራት ቀን በኃላ አስመራ ሆና ደወለችልኝ
+ በአንድ ወር ውስጥ ሁሉንም ነገር ጨርሼ እመጣለሁ
> ,ምን አስበሻል
+ ብሩንዲ ወይም ሳውዝ አፍሪካ እሄዳለሁ ልጄን ይዤ
> ምን አለሽ እዛ
+ እድሌን ሞክራለሁ
> ህምምምምም ምንም ልልሽ አልችልም... እስኪ በመጀመሪያ ተሳክቶልሽ ከአስመራ ውጪ እና..... ካምፓላ ከተገናኘን ከብዙ ኤርትራዊያን ጋር አገናኝሽና.. የሚሆነውን እንመካከራለን
+ ውይ ደስታውን አልችለውም እንደገና ብንገናኝ.... ግን የምንገናኝ ይመስለኛል
> ይመስለኛል... አንቺ ብቻ ይሳካልሽ
+ በአንድ ወር ውስጥ የሚያልቅልኝ ይመስለኛል... አንተ ግን የት ነው ያለሁት አልከኝ
> ኢትዮጵያ
+ በቃ ኢትዮጵያ ነው ምመጣው
> ኖ ኖ እንደሱማ በቶሎ ሀሳብሽን መቀየር የለብሽም
+ ላንተ ብዬ መሰለህ....
> ቢሆንም
+ ለማንኛም ከወር በኃላ ካምፓላ ካለህ እንገናኝ
> ሀራይ... ከወር በኃላ እመለሳለሁ ይመስለኛል
+ እስከዚያ ድረስ ግን ትደውልልኛለህ አይደል
> በሚገባ... እደውልልሻለሁ
+ በጣም አመሰግንሀለሁ
> አብሽር በርቺልኝ ናይ ሰመናይ ፅብቕቲ
+ እሺ ባለሱቅዬ
................................//.........................
ሁለት ወር ፈጀባት ጉዳዩዋን ለመጨረስ
በመጨረሻ ከሁለት ወር ተኩል በኃላ ተሳካላትና ካምፓላ መጣች
ይህ የሆነው ደሞ ዲሴምበር ለስራ በሄድኩ ወቅት ነው
ከባሏ ጋር መለያየት አልቻለችም እንዳሰበችው.... እንደነገረችኝ ከሆነ የቤተሰብ ግፊት እና ሀሳቧን ያለመቀበል ነገር ያለ ይመስለኛል
እሷ ግን ቆርጣለች
ባሏም ሊቢያ አልሄድም...
ደቡብ ሱዳል ለንግድ ይመላለሳል
እቤቱ ቁጭ ብላ ልጇን ማሳደግ ጀምራለች
እሱ ሲመጣ ሲመጣ ብቻ ነው ነፍሷ ሚሰቃየውና ህይወቷን ምታማርረው
እሱ ለስራ ሲሄድ ከልጇ ጋር ጥሩ ጊዜ እያሳለፈች ነው
አንድ ቀን ቁጭ ብለን ስናወራ.... እኔ... እሷ .. እና የ8አመት ቆንጅዬ ልጇ
በነገራችን ላይ ለክጇ ጋር በጣም ተግባብተናል... አማርኛ ባይችልም.. በምልክት
+ ባለሱቅዬ... አንድ ነገረ ብጠይቅህ ቅር ይልሀል
> የፈለግሽውን ጠይቂኝ... አትፍሪኝ
+ በእግዚአብሄር ይዘኸኝ ጥፋ
ኦ ማይ ጋድ
እንዴት አስደነገጠችኝ መሰላቹ
> ኖ ኖ እንደሱ ማድረግ ግብታዊነት ነው... አይሆንም
ዝም አለች ... በጣም ተከዘች
+ ሶሪ ስለጠየኩህ.. በቃ እርሳው.... ሶሪ ሶሪ
አቤት ፊቷ ሲቀላ እና እፍረቷ ሲያሳብቅባት ስታምር
እስካሁን ግን ለምን እንድንተኛ አልጠየከኝም.... ስትለኝ ግን ተጭበረበረብኝ
እምነቴን ነገርኳት.... የሰው ወርቅ የሰው ነው.... መነካካት ጥሩ አይደለም.... ወደ-ሌላ ነገር ይወስደናል
እንዲሁ በጥሩ ጓደኝነት .. እህትና ወንድምነት ብንቆይ የበለጠ........ ጥሩ ነው.... አልኳት
ከራሴ ጋር እየተፈታተንኩ
አቤት ስለራሴ ሳወራ ማሳመር ስችልበት
ብታምኑም ባታምኑም የሆነው ይኸው ነው
ኤኒዌይ
ታላቅ እህቷ ጋምቤላ እንዳለች .. እና ብዙ ጊዜ ነይ እያለች ትጨቀጭቃት እንደነበር ነገረችኝ.. እና
ኢትዮጵያ ለመሄድ እንደቆረጠች አበሰረችኝ
+ አዲሳባ አይሀለሁ አይደል
> ይመስለኛል... በአመት አንዴ... ግን እስካሁን ይህንን ያህል ጊዜ ስደውል ስልክ ቁጥሬን አይተሽ ግን እንዴት አልገመትሽም.. የት እንዳለሁ
+ እኔ እኮ ጠይቅሀለሁ እያልኩ... በ81 የሚጀምር ስልክ ቁጥር የኢትዮጵያ አይደለም.. ግን በናትህ የት ነው ያለኸው
> እሩ ቅ ምስራቅ
+ ነው ለካ......... እኔ እኮ ሁሌ እጠይቅሀለሁ እያልኩ... ግን የትስ ብትሆን እኔ ምንም ግድ አልነበረኝም... ስለዚህ ነው ያልጠየኩህ... ኢትዮጵያ ትመጣ የለ
> አዎን እመጣለሁ
+ ፕሊስ ጠይቀኝ... የእህቴን ስልክ ቁጥር ያዘው
> ኢሺ የኔ ቆንጆ
+ በጣም አመሰግናለሁ... በሀሳብ ስለረዳኸኝ... እንዳወራ ስለፈቀድክልኝ.. ጥሩ ጓደኛዬ ስለሂንክ
> እኔም ክብር ይሰማኛል... የታሪክሽ ተካፋይ በመሆኔ
በሄድሽበት ይቅናሽ... ፊያሜታ
ኢትዮጵያ ስመጣ እደውልልሻለሁ
ጲርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርር
ኦሮማይ

አንፈራራ
Runner
Runner
Posts: 50
Joined: 03 Jan 2012 12:51
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አንፈራራ » 28 Feb 2012 05:30

ባለሱቅ

ፊያሜታ ልጇን ይዛ ከባሏ ጋር ለአንዴና ለመጨረሻው ካልተለያየች በእርሱ እጅ ጠፊ ነች:: በእውነት የሚያስፈራ ሁኔታ ላይ ነው ያለችው:: ልትረዳት ከቻልክ በቶሎ መርዳት ነው በቶሎ ካለችበት ቦታ እንድትሸሽ ማድረግ ነው:: አሁን ገብተህበታልና ቶሎውኑ አንድ ነገር አድርግ በኋላ እንዳይጸጽትህ:: እንደሚመስለኝ ከሌላው ሁሉ ኢትዮጵያ ገብታ ብትገላገል ይሻላታል:: እኔ አንተን ብሆን የምመክራት ይህንኑ ነው::

እሺ ..... በሌላ በኩል ደግሞ .... አንተ ግን ምን ትባላለህ ባክህ? እርሷን በሃይል እንዳስቀየምካት ይገባሃል?

እየነካካህ ዳር ሳታደርስ "ወንድም ልሁንሽ እህት ሁኝኝ" የሚል ፈሊጥ ጀምረሃል ... ምን የሚሉት ቋንቋ ነው? "ወይ አይበላ ወይ አያስበላ" አሉ .....ኧረ ባለሱቅ ኧረ ተው ተው!!!! የአዶላ ልጅ እንዲህ ሲያደርግ አይቼም ሰምቼም አላውቅም::

የአዶላ ልጅ እንደ ፊያሜታ ያለችውን ሲያገኝ የገናሌን ወንዝ ሳያሻግር አይመለስም እኮ፣ አቦ ተወኝ:: ቅቅቅቅቅ

ቸር ይግጠመን::

Dole
Starter
Starter
Posts: 19
Joined: 04 Jan 2012 20:47
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Dole » 28 Feb 2012 11:09

አንፈራራ ያለውን አያቹልኝ
ህምምምምም
ባለሱቅ
ፊያሜታ ልጇን ይዛ ከባሏ ጋር ለአንዴና ለመጨረሻው ካልተለያየች በእርሱ እጅ ጠፊ ነች:: በእውነት የሚያስፈራ ሁኔታ ላይ ነው ያለችው:: ልትረዳት ከቻልክ በቶሎ መርዳት ነው በቶሎ ካለችበት ቦታ እንድትሸሽ ማድረግ ነው:: አሁን ገብተህበታልና ቶሎውኑ አንድ ነገር አድርግ በኋላ እንዳይጸጽትህ:: እንደሚመስለኝ ከሌላው ሁሉ ኢትዮጵያ ገብታ ብትገላገል ይሻላታል:: እኔ አንተን ብሆን የምመክራት ይህንኑ ነው::
እሺ ..... በሌላ በኩል ደግሞ .... አንተ ግን ምን ትባላለህ ባክህ? እርሷን በሃይል እንዳስቀየምካት ይገባሃል?
እየነካካህ ዳር ሳታደርስ "ወንድም ልሁንሽ እህት ሁኝኝ" የሚል ፈሊጥ ጀምረሃል ... ምን የሚሉት ቋንቋ ነው? "ወይ አይበላ ወይ አያስበላ" አሉ .....ኧረ ባለሱቅ ኧረ ተው ተው!!!! የአዶላ ልጅ እንዲህ ሲያደርግ አይቼም ሰምቼም አላውቅም::
የአዶላ ልጅ እንደ ፊያሜታ ያለችውን ሲያገኝ የገናሌን ወንዝ ሳያሻግር አይመለስም እኮ፣ አቦ ተወኝ:: ቅቅቅቅቅ
ቸር ይግጠመን::
እኔ የሰው ነገር አይስማማኝም ምንም ቢወጥረኝ
በዚህ ነገር ተማመንብኝ... ከምሬ ነው
በተረፈ እርግጠኛ ነኝ ኢትዮጵያ እንደምትሄድ...
ተስማምተናልና
በቅርብ ደውዬ አረጋግጣለሁ
አስፈላጊ ከሆነ ይነገራቹዋል
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ቸር እንሰንብት

አንፈራራ
Runner
Runner
Posts: 50
Joined: 03 Jan 2012 12:51
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አንፈራራ » 28 Feb 2012 11:41

ባለሱቅ!


ለመጀመሪያው መልክት ስለሰጠኸው መልስ አመሰግናለሁ። እርሷም ኢትዮጵያ በሰላም ከልጅዋ ጋር እንደምትሄድ ተስፋ አለኝ። ይቅናት እላለሁ።


ለሁለተኛው አስተያየት ግን መልሱን ለመስጠት አለመፈለግህ ገርሞኛል። ያውም አንተ! እንዲህ ዓይነት አስተያየት አይተህ የምታልፍ አይመስለኝም ነበር። ቅቅቅ


በል ቻው!

Dole
Starter
Starter
Posts: 19
Joined: 04 Jan 2012 20:47
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Dole » 28 Feb 2012 23:20

አንፈራራ ሊያናድደኝ ሲፈልግ
ባለሱቅ!
ለመጀመሪያው መልክት ስለሰጠኸው መልስ አመሰግናለሁ። እርሷም ኢትዮጵያ በሰላም ከልጅዋ ጋር እንደምትሄድ ተስፋ አለኝ። ይቅናት እላለሁ።
ለሁለተኛው አስተያየት ግን መልሱን ለመስጠት አለመፈለግህ ገርሞኛል። ያውም አንተ! እንዲህ ዓይነት አስተያየት አይተህ የምታልፍ አይመስለኝም ነበር። ቅቅቅ
በል ቻው!
አንተ ብሽቅ ጉጂ
ነገርኩህ እኮ..... አንደኛ የሰው ወርቅ የሰው ነው...
ሁለተኛ በእንዲህ አንየት ሁኔታ ያለን ሰው ለሌላ ችግር ለሌላ የስሜት መረበሽ.. ለሌላ እጦት መዳረግ አልፈልግም
ከተነካካህ ጣጣው ብዙ ነው.... ምን ማለት እንደፈለኩ ከገባህ
እኔ ደሞ ዝም ብዬ ሆ-ቢሻን-ኬ ብዬ አስተክዤ መሄድ አልችልበትም
እስኪ ጠይቁልኝ.... ምን አለችኝ ይላል
እንጨቱን ሰብሮልን በመሸከሚያችን
ውኃውን ቀድቶልን .. በመሸከሚያችን
አስቦ ተክዞ ሄደ ወዳጃችን
መባልን አልፈልግም... በተለይ በምወደው ሰው ነፍስ ውስጥ
ስለዚህ እንዲሁ መዋደድ ሲቻል... ለምን ሌላ ማስተከዝና ችግር ውስጥ ሰውን እንከታለን የሚል አመለካከት ስላለኝ
መነካካት አልፈለኩም
የአዶላ ልጅ በናንተ ዘመ ያሉት ይሆናል.... ገናሌን ሚያዘልሉት..... በኛ ጊዜ ያሉት እነ-ሽልንጌን ብትጠይቃቸው... ይነግሩሀል
ተንከባክበው አንፈራራን አሻግረው ነው ሚመለሱት እንጂ.... መንገድ የጠፋውን ሰው ወደ-ገናሌ ይዘው አይሄዱም
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
አደቆርሳና ራስብሩ ገደሉኝ..... እኛስ ብለው?
በናንተ ጊዜ ያሉት ደሞ... ወደ-ማርያም ዳገት.... እንደቡጡ እሼቴ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ድሮ ድሮ ያጫወትኳቹ ይመስለኛል... ቡጡ እሽቴ.. አንዲት የሻኪሶ ልጅ ይዞ ሲሄድ .. እኛ ከኃላ እየተከተልን ምቀኛ የሆንንበት
አይ ልጅነትትትትትት
ቡጡዬ... እክስሀለሁ.... በእህቴ በሉልኝ
ውይ ለካስ አሪፍ እህት የለኝም
አቦ ከሀረር አስመጣልሀለሁ... በሉልኝ
ሰላም ሁኑልኝ

Dole
Starter
Starter
Posts: 19
Joined: 04 Jan 2012 20:47
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Dole » 05 Mar 2012 20:05

Gosa Says


ባለሱቅ
እኔን
ደግሞ
"
ዱራ
" ያልከው
ነው
በጣም
ያሳቀኝ
:: ሞፊቲ
ገደለህ
:: ለነገሩ
እሱ
አያነበውም
::

ቅቅቅቅቅቅቅ
.....ቃሉ
አማሪኛ
ነው
ግን
? ገጠር
ዉስጥ
እንጂ
ከተማ
ሰምቼው
የማውቅ
አይመስለኝም
::Mofti brother
Are you mad at me?

Come and comment on the word DuraCheers

አንፈራራ
Runner
Runner
Posts: 50
Joined: 03 Jan 2012 12:51
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አንፈራራ » 05 Mar 2012 22:18

ባለሱቅየ፣


የክ/መ ልጆችን አሰባስቦ ለመቀጠል ያለህን ቆራጥነት አደንቃለሁ። ነገር ግን እንደምታውቀው የዋርካ ሰዎች ለግል ጥቅማቸው በማለት ዌብሳይቱ እንዲበላሽ በማድረጋቸው ብዙዎቻችን ለቀን ወጣን። ከዚያም እንደምታውቀው ሌላ ቤት ተከራይተን አለን፣ ግን ብዙ ሰው አልመጣ ብሏል።


ይህ በዚህ እንዳለ ፌስቡክ ላይ ደግሞ ሌላ የክ/መ ልጆች ቤት ተከፍቷል። ወደ 140 የሚሆኑ አባላት እስካሁን ተመዝግበዋል፣ እስቲ ጎራ ብለህ እየው።


ምናልባት ትወደው ይሆናል፣ ብዙ ሰዎችንም መገናኘት ትችላለህ፣ ትተዋወቃለህም።

ሞፊቲ
Jogger
Jogger
Posts: 33
Joined: 03 Jan 2012 14:19
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by ሞፊቲ » 10 Mar 2012 14:21

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን::


ውድ ወንድሜ ወቤ ጃሎ የመጀምርያዋን የ አብራክህን ክፋይ በአይንህ እንድታይ ስላበቃህ ለቸሩ ፈጣሪ ምስጋና ይድረሰው::
ደስታው የሁላችንም ነው::ቤተሰቡ በሙሉ በሃሴት ሰክሮአል::
የአብስራ አድጋ ጎልብታ እንዳባቷ ኮሜዲ እንደምትሆን ተስፋ አደርጋለሁ::
Attachments
IMG_0338.jpg
IMG_0338.jpg (2.31 MiB) Viewed 2930 times

Post Reply

Return to “የጀምጀም ልጆች መገናኛ”