የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Forum rules
No cursing, bad language and offend other users !
No pornographic images or links!
This forum monitored regularly. We will BAN users without warning for not obeying rules.
እባክዎ የፎረሙን ህጎች ያክብሩ::
Dole
Starter
Starter
Posts: 19
Joined: 04 Jan 2012 20:47
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Dole » 22 Feb 2012 13:56

ጋሽ ኃይሉ
በሣይንስ የተሠጠው ስም 'Ficus sycomorus' ነው
በጣም አመሰግናለሁ.... እስኪ በሳይንሳዊ ስሙ የሚሸጥ ካለ ብዬ ለማግኘት እፈልጋለሁ...
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
በነገርህ ላይ ያኔ ስለ ዶቅማ ሾላ እንጆሪ ዝግባ ስናወራ... የሁሉም ስም ተገኝቶ ስሙ የጠፋው የዶቅማ ነበር ይመስለኛል
የፎረስትሪ ባለሙያ ስላልሆንኩ ሁሉንም ስም አልያዝኩም.... ሾላ ግን ከስሙ የበለጠ ትዝ የሚለኝ... በልጅነቴ ለመጀመሪያ ጊዜ በአስተማሪ ክፉኛ ስመታ መምህሩ ተቀምጠው የነበረው የሾላ ዛፍ ስር ነበር
ከዚያ በተረፈ ስራዬ ብዬ ስሙን አልያዝኩትም
አሁንም ለነገሩ 'Ficus sycomorus' ብዬ ገበያ ብወጣ እንደማላገኘው እርግጠኛ ነኝ
ለማንኛውም ፈልጌ ገዝቼ ቀምሼ ጣዕሙን በዋርካ መስኮት አቀብልሀለሁ
ተስማማን?
...........................................
ብሩኬ
"ሚስትህ ባንተ ላይ ከኔ በላይ ምን መብት አላት - የተለዋወጣችሁት ቀለበት ነው ቁምነገሩ ?
ባታውቀው ነው እንጂ እኔ ህይወቴን ልለውጥልህ ነበር ..."
ስትል ልቤን ነው ያጠፋኸው ከምር
እንዴት ያለ ወርቅ የሆነ አባባል ነው በግዚአብሄር
የኔዋን ፊአሜታ ከዋናዋ ፊያሜታ ጋር ፕሊስስስስስስስስ እንዳታወዳድራት
ከበአሉ ግርማ መንፈስ ጋር ታጣላኛለህና
አደራ
........................ ልቀጥል እስኪ .........................
ካምፓላ መጥቻለሁ
መቼ እንደሆነ ቀኑ ትዝ አይለኝም
ለፊአሜታ እንደመጣሁ ነግሬአታለሁ
ከዚያን ቀን በኃላ አሁንም በየጊዜው እየተደዋወልን እንገናኝ ስለነበር... ቶሎ ለማግኘት አልጓጓሁም
ግን መምጣቴን ማወቅ ስላለባት ነገርኳት
ምክንያቱም ከሳምንት በኃላ ወዳገሬ ልመለስ ነው
ስለዚህ አግኝቻት ብለያት ምን ይላቹዋል
....................................//............................
ብንዝናና ምን ይልሻል ወይ ወይ
የእድሜ አውቶቡስ ያልፍብሻል ወይ ወይ
ደረጄና ኃብቴ እያሾፉብን ነው
...................................//...............................
ካምፓላ በመጣሁ በሶስተኛው ቀን ይመስለኛል... ፊያሜታ ደወለችልኝ
> ባለሱቅዬ... በናትህ ነገር የሚኡመጭ ከሆነ እንገናኝ
+ በምን እድሌ... እሺ ... ስንት ሰአት
> ጠዋ,,,,,,,,,,,,ት.... ይመችሀል?
+ ምንም ችግር የለም... እንደውም ቁርስ አብረን እንበላለን
> እሺ.. ግን የት?
+ የኢትዮጵያ ቪሌጅ... ብንገናኝ ምን ይመስልሻል
> እሺ ... ጠዋት 9ሰአት እዛ እጠብቅሀለሁ
+ አምላክ ያሳድረን... እመጣለሁ... በ10ሰአት ግን ስብሰባ ነገር አለችኝ... ብዙ አላጫውትሽም
> እሺ... እኔም ብዙ ጊዜ አይኖረኝም... አግኝቼህ አይንህን እያየሁ ይቅርታህን መቀበል ስለፈለኩ ነው ላገኝህ የፈለኩት
+ እኔም መሄዴ ስለሆነ... ከመሄዴ በፊት ባገኝሽ ብዬ ነው
> ውይ ልትሄድ ነው
+ አዎን ስራዬን ጨርሻከሁ
> የት ነበር ያለሁት ያልከኝ
+ ኢትዮጵያ ነው... ከዚያ እየተመላለስኩ ነው ምሰራው
> በጣም ያሳዝናል... ግን ፕሊስ ከመሄድህ በፊት እንገናኝ,... ነገ ጠዋት እጠብቅሀለሁ
+ እሺ የኔ ቆንጆ.... አሁን ደህና ደሪ... ነገ 9ሰአት ኢትዮጵያ ቪሌጅ.. ኦክ!
> ፅቡቕ
+ ናይ ሰመናይ ፅብቅቲ... ትንሿ ነበልባል ደህና ደሪ
> ቆይ ቆይ ... ከመዝጋትህ በፊት... ለምንድነው ሁሌ ትንሻ ነበልባል ምትለኝ
+ ውይ አልነገርኩሽም እንዴ,.,.... የጥንቷን ፊያሜታ ስለሚያስታውሰኝ ነው
> እና ትንሿ ነበልባል ምን ማለት ነው
+ የፊያሜታ ትርጉም ነው
> የፊያሜታ ትርጉም?
+ አዎና... ምነው አልነገርኩሽም እንዴ
> እንደነገርከኝ ትዝ አይለኝም... ማነው ግን እንደሱ ብሎ የተረጎመው
+ መፃፍ ላይ ነው ያነበብኩት... ምነው ትክክል አይደለም እንዴ
> ህ ምምምምምም እንጃ እኔ አላውቅም... ግን እናቴ አንዴ በጨረፍታ ስታወራ ትዝ የሚለኝ
ፊአ-ምታ ማለት ... ሀሜት ወዲያ በል... እንደማለት ነው የተረዳሁት
+ ምን አልሽ?... ሀሜት ወዲያ?... ለምን
> እናቴና አባቴ መሀን ናቸው እየተባለ ይወራ ነበር.... ልጅ አይወልዱም ተብሎ ተወርቶ... ከተጋቡ ከስንት ጊዜ በኃላ እንደሆነ አላውቅም... እኔ ስወለድ,.... ሀሜት ወዲያ ... የሚል ስም አወጡልኝ... ፊያ-ሀሜታ.... በምንኛ እንደሆነ አላውቅም
መናገር አልቻልኩም... ዝምምምምምምምም አልኩኝ በቃ
> እንዴ ባለሱቅ አለህ?
+ አለሁ አለሁ እየሰማሁሽ ነው
> ምነው ዝም አልክ ታዲያ
+ በቃ ነገ ጠዋት እንገናን
> ችግር አለ?
+ ችግር የለም.. ነገ እንገናኝ... ደህና ደሪ... የስልክ ገንዘቤን ልትጨርሺብኝ ነው .... ደህና ደሪ ሀሜት ወዲያ
> ደህና ደር ሸጋ ልጅ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ፊአ-ሜታ.... ሀሜታ ወዲያ.... እንዴት ሊሆን ይችላል
አዲአ ቋንቋ ፈጥረው መሆነ አለበት... እንጂ
እናቷን ነገ ላግኛት
ደከመኝ
ደህና ደሩልኝ
ቸር ሰንብቱ

Dole
Starter
Starter
Posts: 19
Joined: 04 Jan 2012 20:47
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Dole » 23 Feb 2012 14:05

I am realy tired of this COPY and PASTE thing


Anyways this is COPY PASTE No. ####

ተንዛዛሁ አይደል
በደንብ ገብቶኛል
ነገር ግን ሀዘን ላይ ስለነበርኩ ነው
ስብሀት ለአብ ገ/እግዚአብሄር መሞቱን ሰምቼ ክፉኛ አዘንኩኝ
እድሜ የጠገበ ቢሆንም.... የሚሞት ስለማይመስለኝ ይሆን.... ወይስ እንደ-አጋፋሪ እንደሻው ሞትን እየሸሸ የሚኖር ስለሚመስለኝ
መሞቱ አስደንግጦኛል
አምላክ ነፍሱን ተቀብላ.. ከነ-በአሉ ግርማ ጋር ታኑረው
.................................ልቀጥል እስኪ....................
በጠዋት 9ሰአት ላይ ኢትዮጵያን ቪሌጅ ሬስቶራንት ስሄድ.... ጭርርርርርርርር ብሏል
ወደውስጥ ብገባ ማንም የለም
ከወደ-ጓሮው በኩል
አንዲት ቆንጅዬ ልጅ ተቀምጣለች
ፀጉሯን ወደኃላ ለቃው......አቀርቅራ ተቀምጣ. ስትታይ...
የሆነ ደስስስ የሚልና... የሚያምር ትዕይንት ይሰጣል
ፊአሜታ እንዳልሆነች እርግጠኛ ነኝ
ምክንያቱም ያኔ ሳያት...
እንዴ ፀጉሯን አይቼዋለሁ እንዴ?
እሷን እንዳትሆን ብቻ
> ፊአ-ሜታ... ብዬ ስጣራ
ብድግ አለችና... ወደኃላዋ ዞር አለች
አይኔን ማመን አልቻልኩም
ለካስ ውብ ልጅ ናት... ቆንጅዬ
ፊቷ ላይ... በተለይ ቅንድቦቿ ላይ ያለው ስንጥር ምልክት አጭበርብሮብኝ እንጂ...
ወየው እንዴት ታምራለች በናታቹ
ያኔ ያየሁት አይኗ ደሞ...
+ መጣህ... ውይ ባለሱቅዬ
> አንቺ አልመሰልሽኝም እኮ....
አልኳት በመገረም እያየኃት
+ ምነው ተለወጥኩብህ እንዴ
> ኖ ኖ ... የዛን ቀን በደንብ አላየሁሽም ማለት ነው... ስታምሪ
+ ሂይ... በናትህ አታሹፍ... አሁን ና ሳመኝ
እቅፍፍፍፍፍፍ አድርጌ ጉንጫልን ሳም ሳም... አድርጌ ፊትለፊቷ ተቀመጥኩ
> ቁርስ ምን ትበያለሽ
+ ኖ ቁርስ ይቅር... ለስላሳ ይበቃል.. ሰአት የለኝም
> ምን ሆነሻል ግን.. ምንድነው ችግርሽ... ለምንድነው የጠፋሽው
+ በናትህ እንዳትቀየመኝ
> እረ በፍፁም... እንዴ ምን ልሁን ብዬ ነው ምቀየምሽ... ሰው.... ብዬ ልቀጥል ስል.. አቍረጠችና
+ ባለትዳር ነኝ....
አለችኝ,, እና ዝም ብላ አየችኝ
> ውይ ደስ ሲልልል... ታዲያ በዚህ የተነሳ ይቀየመኛል ብለሽ አስበሽ ነው... ምንም ችግር የለውም እኮ... ወንድምሽ ነኝ አብሽር
+ ቴንኪውውው... እንዴት ፈርቼ ነበር ለመንገር
> እንዴ ምን ያስጨንቅሻል... እኔ ውዴ ሁኚ ብዬ አልጠየኩሽ... አስቸግሬሻለሁ እንዴ
+ ሳይሆን... በጣም ለመድኩህ.... በጣም ብዙ ብዙ ነገር ብናወራም .. ባለመናገሬ በጣም ይሰማኝ ነበር
> ይሄ ነው ችግርሽ ?.... በይ በደንብ እንተዋወቅ... ባለሱቅ እባላለሁ... ባለሶስት ትንንሽዬ ባለሱቆች አባት
+ ቅቅቅ ታድለህ
> አንቺስ ልጅ የለሽም
+ አለኝ... ወንድ ልጅ... አስመራ ነው ያለው
> ፅቡቕ ፅቡቅ... ጥሩ ነገር ነው... ደስ ይላል ልጅ በልጅነት አይደል
+ እኔ ግን ደስተኛ አይደለሁም
> ምነው ምን ገጠመሽ
+ ባለቤቴ ይደበድበኛል
> ምን...አልሽ?
+ ዝም ብሎ ይመታኛል
> ለምን... ምን አድርገሽው.... ወጣ ወጣ ማለት ታበዣለሽ እንዴ?.. ይቀናል?
+ በሆነና ባላዘንኩ
> እኮ ለምንድነው ሚመታሽ
+ እንዴት ብዬ ልንገርህ.... አንተ አታውቅም እንደሆን እንጂ... የአስመራ ወንዶች.. ሴቶችን በጣም ዝ...ቅ አድርገው,,,, እንደቤታቸው እቃ ነው ሚቆጥሩት.... እና እንደቤቱ እቃ እንዳንዱ እንድሆንለት ነው ሁሌ ሚያዘኝ
> አልገባኝም.. አልገባኝም... አሁን እኮ ያለነው አስመራ አይደለም
+ እሱ ግን ከአስመራ ልጅ ጋር ነው
> ቆይ እስኪ እንዴት ነው... ነገሩ... በደንብ አስረጂኝ... እንደቤት ውስጥ እቃ ስትይ
+ አያወራኝም... አያናግረኝም.... እቤት ውስጥ እንዳለሁ አይቆጥረኝም.... ብኖርም ምግብ አብስሎ ለማቅረብና... አልጋው ላይ በፈለገኝ ሰአት ዳብሶ ሊያገኘኝ የሚፈልገኝ እቃው ነኝ
> ኖ ይሄ ድሮ የቀረ ይመስለኛል.. የተሳሳትሽው ነገር ቢኖር እንጂ
+ ሙት እውነቴን ነው.... እየው... እዚህ አገር ከመጣሁ ገና 3 ወሬ ነው... አንድም ሰው አላውቅም... አንተ የመጀመሪያዬ ነህ... እንደልቤ የማወራው ማንም ሰው የለም... አጠገቤ ያለው እሱ ስለሆነ... ገና ሳወራው... እንዲ...ህ አድርጎ ይመታኛል
> እንዴ አልገባኝም... እስኪ በምሳሌ ንገሪኝ
+ ለምሳሌ ትላንትና.. ሶፋ ላይ ተቀምጠን ቲቪ እያየን ነበር
እና በርዕሰ ጉዳዩ ላይ.. አስተያየት ስሰጥ... በግራ እጁ.... እዚህ አይኔ ላይ
ብላ እስካሁን ያላየሁትነ ከአይኗ በላይ ያለውን ብልዝ ስታሳየኝ
> እንዴ እንዴ.. ምንድነው ይሄ
+ እሱ ብቻ አይደለም... ይህወልህ
ብላ ክንዷን... ባቷን... ሆዷን....
እንዴት በልዟል ሰውነቷ
አይኗ እንባ አቀረረ
ልቤ ጭንቀቱን ጀመረ
ምንም ማድረግ ለማልችለው... ነገር... ለምን....
> ለምን ግን ፖሊስ ጋ አትሄጅም
+ ቤተሰቤስ... ጣጣው ብዙ ነው.. አንተ ስለኤርትራ ባህል ምንም አታውቅም
> እና እየደበደበሽ ልትሞቺ ነው ምትፈልጊው
+ አይ ምን መሰለህ
> ቆይ አሁን እኔ ምን ባደርግልሽ ደስ ይልሻል
+ ካንተ ምንም አልፈልግም... አዳምጠኝ.... Let me talk and release my stress PLEASEEEEEEEEEE
የማወራበት ቦታ የለኝም... የምናገረው ሰው የለኝም.... የማለቅስበት ቦታ የለም... .. ካንተ ምንም አልፈልግም... አውራኝ ላውራህ
> እሺ የኔ ቆንጆ...... በቃ አንቺ አውሪ እኔ ልስማሽ
ልቤን እንዴት ሙቀት ተሰማው መሰላቹ
እኔ አንድ ተራ ባለሱቅ... ተመርጬ... ላውራልህ,, ሚስጢሬን... ስማኝ... ተብዬ ስለመን....
+ በጣም ደግ ሰው ነህ አንተ ግን
> በይ አሁን እሱን ተይና.. እስኪ ንገሪኝ... እንዴት ተገናኛቹ.. እንዴት ተጋባቹ... እንዴትስ ለዚህ ልትበቁ ቻላቹ
.......................................//...............................]
ፊያሜታ የመጨረሻ ክፍል
ውይ መጨረሻ አለው እንዴ... ገና በእውኑም ያላለቀ ታሪክ ነው
እስካለበት ድረስ እንቀጥላለን

ደከመኝ ከምር
ኡ ኡ ኡ ኡ ኡ ኡ
አንድም ሚያዝንልኝ የለም
ቲች... ቀሽም ሁላ

ሰላም ሁኑ
በፍቅር

አንፈራራ
Runner
Runner
Posts: 50
Joined: 03 Jan 2012 12:51
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አንፈራራ » 23 Feb 2012 21:13

ኧረ ባለሱቅ ወንድሜ...

ኡ በጣም የሚያሳዝን ወሬ ነው የነገርከን:: በእውነት ልጂቷ በጣም የሚያሳዝን ሁኔታ ላይ ነች ያለችው:: አይ እህቴን ምን ዓይነት ችግር ውስጥ ናት ያለችው....

የሚገርም ነው ከኤርትራውያን ጋር ለረጂም ጊዜ ከክብረ መንግስት ጀምሮ አብሬ ኖሬአለሁ ግን ወንዶቹ ለሴቶቻቸው እንዲህ መሆናቸውን አላውቅም ነበር:: ለዚህ ነው ለካ የትግሬ ማለት የኤርትራ ሴቶች የአማራ ወይም ትግሬ ያልሆነ ወንድ ይመርጣሉ የሚባለው? በዚያው አኳያ ደግሞ ብዙ ጊዜ የሚታየው ሁኔታ ግን እርስ በርሳቸው ተፈላልገው ሲጋቡ ነው:: ሊገባኝ አይችልም::

ለማንኛውም አሁን ያንተን ፊያሜታን ከተነከረችበት ማጥ ውስጥ ለማውጣት እንዴት ማድረግ እንደሚገባ ማሰብም መመካከርም ያስፈልጋል:: ምንም ሁለቱም ከአገራቸው ውጭ ቢገኙም ሰውየው እርሷን ሁሌ እንደ ኳስ ሊጫወትባት መብት የለውም:: እዚህ አሜሪካ ቢሆን ፖሊስ አንጠልጥሎ ነበር እስር ቤት የሚወስደው::........

ቆይ ቆይ ቆይ እንዲያውም የሚገርም ነው አንድ የሆነ የተመሳሰለ ኬዝ ትዝ አለኝ እኔ ራሴ ለጉዳዩ የሩቅ ምስክር የሆንኩበት:: የሚገርም ነው እዚህ ያሉትም እዚያ አንተጋ እንዳሉት ከኤርትራ የመጡ ናቸው:: ባልየው ቀደም ብሎ እዚህ ተደራጅቶ ይኖር ነበር:: ከዚያም ልጅቷን ከአስመራ ካስመጣና ካገባት በኋላ ከቤት እንዳትወጣ አድርጎ: እንዳትማር እንዳትሰራ ከልክሎ: እየደበደበ የወሲብ ባሪያ አድርጓት ከቆየ ከ2 ዓመት በኋላ; ልጂቷ እንደ ምንም ብላ በሰው እርዳታ ከጠበቃ ጋር ተገና ኘት:: ከዚያም ሁኔታው ፍርድ ቤት ደርሶ በመጨረሻም ሚስቲቱ የሰውየውን ሀብት እንድትወርስ ተፈረደላት:: ባልየው ለ8 ወር እንዲታሰርና የመኖሪያው ፈቃድ እንዲነጠቅ ከዚያም ከአገር እንዲወጣ ተፈረደበት:: የሁላችንንም አንጀት ነው ያራሰው ዳኛው::

የአንተን ጓደኛ ጉዳይ የዩጋንዳ መንግስት እንዴት እንደሚያየው ማወቅ አይቻልም:: ግን እግዚአብሐር ይርዳት:: አንተንም ይርዳህ በጉዳዩ እንደተጨነክ ይገባኛል:: በርግጥም ሁኔታው አስጨናቂ ነው::

ራስብሩ
Starter
Starter
Posts: 23
Joined: 03 Jan 2012 09:45
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by ራስብሩ » 24 Feb 2012 16:47

የፊያሜታ ኑሮ በጣም በጣም የሚያሳዝን ነው ካነበብኩ በኋላ እስከመቼ እንደዚህ ሆና ትኖራለች
ብዬ ሳስብ ግራ የሚገባ ነገር ነው በውነት::
በሃገራችን በመላው አፍሪካም ይሄ ችግር በጣም ትልቅና ዋና ችግር ነው ምክንያቱም

ባለስልጣኑም ዳኛውም ህግ አውጪውም ፖሊሱም ሁሉም የችግሩ ባለቤት ናቸው::
ህግ ያወጣሉ አይፈጽሙም አንዳንዴ አቤት የሚባልበት ቦታ ስለሚያጡ ብቻ ሴቶች ባርያ ሆነው

ለመኖር ይገደዳሉ :ዱላ አልበቃ ሲላቸው ደሞ ባለፈው ሞፊቲኮ እንዳስነበበን ዓይን ያወጣሉ አካል ያጎድላሉ ::
በውነት እንደዚ ያለ በወንዶች የሚፈጸምባቸውን የሴቶችን ችግር መስማት ያሳምመኛል
አንዴ እዚህ እኔ ያለሁበት ጀርመን ውስጥም ተመሳሳይ ችግር ተፈጥሮ ፖሊስ ነገሩን ሲመረምር ሶስት አመት ሙሉ

ከቤት ሳትወጣ እየደበደበ ሲጫወትባት እንደኖረ ተረጋግጦበት አንፈራራችን እንዳልከው የፍርድ ውሳኔው እኛንም አንጀታችንን አርሶናል::
የሃገራችን ሴቶች እንደፊያሜታ ያሉ አሳዛኝ ፍጥረቶች መቼ የህግ ጥላ እንደሚያገኙ አይታወቅም::

ፊያሜታዬ እግዚአብሄር ከዛ መከራ ያውጣሽ ብያለሁ::
ባለሱቅ መቼም ያቅምህን ያህል የሃሳብና የሞራል እገዛ እንዳደረክላት በደንብ አምናለሁ
በመፍትሄም እርዳታ የምትሻ ከሆነ ጻፍ ጻፍ አድርግ::
ራስብሩ

አንፈራራ
Runner
Runner
Posts: 50
Joined: 03 Jan 2012 12:51
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አንፈራራ » 25 Feb 2012 06:36

ሰላም ለሁላችሁም

በ Facebook Adolla Coffee and Tea Room (የክብረ መንግስትና አካባቢ ልጆች) የሚባል ግሩፕ ተቋቁሟል:: ሄዳችሁ ጎብኙት:: ፎቶዎችም ለጥፈዋል:: እንደሚመስለኝ ግሩፑን የጀመረው "ሽልንግየ" ነው:: እኔንም አስገብቶኛል:: እስከዚያው በነዚህ ፎቶዎች አዝግሙ::
Attachments
Adolla Coffee and Tea Room (የክብረ መንግስት ልጆች).jpg
Adolla Coffee and Tea Room (የክብረ መንግስት ልጆች).jpg (10.86 KiB) Viewed 3341 times
Adolla High School.jpg
Adolla High School.jpg (17.46 KiB) Viewed 3341 times

Dole
Starter
Starter
Posts: 19
Joined: 04 Jan 2012 20:47
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Dole » 26 Feb 2012 15:09

This is a copy made from Warkaበጣምምምምምምምምምምምምም
ቢዚ
ሆኛለሁ
... ነገር
ግን
እነዚህን
ነገሮች
ማለፍ
ስላልቻልኩ
ነው
በተሰረቀች
ሰአት
ብቅ
ያልኩት
ጋሽ
ተድላ
ምን
አለ
መሰላቹ
[table] [tr] [td]
Quote:[/td][/tr] [tr] [td]አንዳንድ
የአገር
ቤት
ትዝታ
ላጫውትህ
:- ሾፌርና
ፀጉር
አስተካካይ
የመንግሥት
ሠላይ
: ሊስትሮ
የሠፈር
ታሪክ
አጫዋች
: የአንተ
ቢጤ
ባለ
ኪዮስክ
የሠፈሩ
ገንዘብ
ሚኒስቴር
: ልብስ
ሠፊና
ሸማኔ
(በሴት
ወዳጅነታቸው
ስማቸው
በጥሩ
አይነሣም
) : እያለ
ይቀጥላል
:: አንተ
የኪዮስክ
ባለቤትነትህን
ትተህ
ወደ
ሣይካትሪስትነቱ
ተጠግተሃል
:: [/td][/tr][/table]

አቤት
ነገር
ማሳመር
ስትችልበት
እንደው
ግን
ይሄ
ጠጋ
ጠጋ
... ማለት
ሱቄን
ለመውረስ
ነው
ወይስ
የኔን
ሱቅ
አፍርሰህ
ጠጅ
ቤት
ልትከፍትበት
... ሳይካትሪስት
ሁን
ምትለኝ
ደም
ምን
ደስ
እንዳለኝ
ታዋለህ
ከአባባልህ
....
[table] [tr] [td]
Quote:[/td][/tr] [tr] [td]ልብስ
ሠፊና
ሸማኔ
(በሴት
ወዳጅነታቸው
ስማቸው
በጥሩ
አይነሣም
) [/td][/tr][/table]

የምትለዋ
ፓርት
ብዙ
ነገር
እንዳስታውስ
አደረከኝና
አውርቼላቹ
ይሆንንንን
ብዬ
የማስታወሻ
ጭንቅላቴን
ማሰራት
አቅቶኝ
ተውኩት
ልብስ
ሰፊ
እንደነበርኩ
.. (ማለቴ
ዘምዛሚ
እና
ልብስ
ተኳሽ
) እንደነበርኩ
ነግሬአቹ
ከሆነ
የልብስ
ሰፊ
ጉተማን
ታሪክ
ያጫወትኳቹ
ይመስለኛል
አይ
ጊዜ
እንዴት
ደስ
ይላል
ግን
ልብስ
ሰፊ
መሆን
ባሏ
ፊት
እኮ
ነው
... ልለካት
ብለህ
ጡቷን
ዳሌዋን
ወገቧን
እየተሽከረከር
እያቀፍክ
እያሸተትክ
ምትዝናናው
አይ
ጊዜ
ስንት
ነገር
አስታወስከኝ
አቦ
... የልጅነት
ጊዜዬን
ህምምምምምምምም
...............................................................//.....................
ጎሲና
ጎስነት
ጎሳ
አንተ
ደሞ
ምንድነው
ያልከው

[table] [tr] [td]
Quote:[/td][/tr] [tr] [td]መጻፍ
አንችል
: መሳል
አንችል
...ግን
ምናባቱ
...እነ
ባለሱቅንም
ማድነቅ
ከቻልን
እራሱ
ይበቃናል
::[/td][/tr][/table]

ድንቄም
እራስህን
ዝቅ
አድርገህ
ሞተሀል
ጣፋጭ
ጉጂ
ይልቅ
ያንን
ሞፍቲ
ያገርህን
ልጅ
በጉጂኛ
አማላጅ
ልከህም
ቢሆን
ተመለስ
በለው
ጠፍቷል
ጨዋታውን
ይዞ
እነ
-አንፈራራና
አደቆርሳማ
...
ተዋቸው
ቆይ
እኔ
ካልሰራሁላቸው
በተረፈ
አሁን
ጊዜ
ውጥርርርር
አድርጋኛለች
ሶሪ
እመለሳለሁ
ቸር
ቆዩን
በወዳጅነታችን
እንሰንብት
አንተም
ብቅ
ብቅ
እያልክ
ማንበብ
ብቻ
ሳይሆን
በቤቱ
ውስጥ
ድድድድድድ
በልበት
በጣቶችህ
ብዕር
ሰላም
ሁኑ
እየጠበቀኝ
ነው
አለቃዬ
ለእራት
ባይይይይይይይይይ

Dole
Starter
Starter
Posts: 19
Joined: 04 Jan 2012 20:47
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Dole » 26 Feb 2012 15:11

Copy and Paste
እራት
በልቼ
መጣሁላቹ
ኢንተርኔት
ሞዴም
ስላለቀብኝ
ኔት
-ካፌ
ውስጥ
ሆኜ
ነው
በገንዘቤ
ላወራቹ
የመጣሁት
ስለዚህ
ጊዜ
አላጠፋም
ወዳላለቀው
ታሪክ
ልውሰዳቹ
..............................................
ኡጋንዳ
.... የኢትዮጵያ
ቪሌጅ
ሬስቶራንት
.................................
..................... እኔና
ፊያሜታ
ለስላሳችንን
እየጠጣን
እናወጋለን
............
ያለችን
ሰአት
በጣም
አጭር
ናት
አቤት
የሚጣፍጥ
ሰአት
ማጠሩ
ቀጥለናል
ወጋችንን
>
ትወጂዋለሽ
?
+ ምን
አይነት
ጥያቄ
ነው
...
> ዌል
ሶሪ
... ወደሽው
ነው
ያገባሽው
አይደል
+
አዎና
!... ግን
የተጋባነው
በቤተሰብ
ነው
... ጥሎኝ
እስከጠፋ
ድረስ
ወደው
ነበር
> ጥሎኝ
እሰከጠፋ
ስትይ
+ አየህ
ባለሱቅ
... አሁን
እኔ
እይዚህ
ምታየኝ
.. 6አመት
ሙሉ
ጠብቄው
ሳጣው
ፍለጋ
መጥቼ
ያገኘሁትን
የባሌን
ታሪክ
ነው
ማወራህ
.... እና
አዎን
እወደው
ነበር
... ነገር
ግን
... ..
በናትህ
አታስጨንቀኝ
> ኦኬ
ንገሪኝ
እኔ
መጠየቄን
ላቁምና
አልንቺ
አውሪልኝ
... እንዴት
ተጋባቹ
,.... እንዴትስ
ጥሎሽ
ጠፋ
................... ከዚህ
በኃላ
ለሷ
ተውላቹዋለሁ
... ታውራላቹ
በራሷ
አንደበት
ስንጋባ
እናቱ
አደራ
አሉኝ
ፀባዩ
በጣም
ኃይለኛና
የሰውን
ስሜት
የማያዳምጥ
ስለሆነ
...
ያስቸግርሻል
.. እና
አደራ
ልጀ
...
ቻይው
......... ችግር
ካለ
ለብቻሽን
ከመወሰንሽ
በፊት
አማክሪኝ
ብለውኝ
እንደነበር
ትዝ
ይለኛል
ተጋባን
ኦህ
ሶሪ
... እንዴት
እንደተዋቅወቅን
ሳልነግርህ
ነርስ
ነኝ
ብዬ
አልነበር
ሳዋ
እያለን
እኔ
ነርስ
ሆኜ
እሱ
ከዩኒቨርሲቲ
ወጥቶ
ሳዋ
ለውትድርና
ሲገባ
ነው
የተዋወቅነው
ዘምተሻል
ወይ
ኢትዮጵያን
ለመውጋት
ላልከኝ
.... ያው
ነርስ
ሆኜ
ዝምቻለሁ
.... ግን
በጦርነቱ
አላምንበትም
...
እነ
ብቻ
እሱም
እና
ብዙ
ጓደኞቼ
አያምኑበትም
... እሱ
አሁን
አልፏል
...
እና
እዛ
ነርስ
ሆኘ
ነው
የተዋወቅነው
ተጋባን
ልጅ
መጣ
ልጄ
በተወለደ
ሁለት
ወር
ሳይሆነው
ይመስለኛል
... ጠፋ
በቃ
ጠፋ
እኔ
ገደሉት
ወይ
ብዬ
ስጨነቅ
... ከሳምንት
በኃላ
ስልክ
ደወለልኝ
................................
ከሱዳን
.... ካርቱም
ነደድኩ
...
ተበሳጨሁ
... ለምን
አላማከረኝም
ብዬ
አየህ
ምን
እንዳናደደኝ
አንተ
አይገባህም
... ምክንያቱም
ስለኤርትራ
ምንም
አታውቅም
ቢያማክረኝ
እንቅፋት
የምሆንበት
መስሎሀል
አይደልም
... አይደለም
አይደለም
ዋናው
ነጥብ
እሱ
አይደለም
... እኔ
የሱን
መውጣት
አልቃወምም
ግን
ሊነግረኝ
ይገባ
ነበር
....
ሊያማክረኝ
ይገባ
ነበር
አየህ
አንተ
አይገባህም
እንጂ
ቢያማክረኝ
... እኔም
ለመውጣት
አልቸገርም
ነበር
ይህንን
ያህል
ጊዜ
አንለያይም
ነበር
አንዲት
ሴት
ኤርትራ
ውስጥ
በህግ
ጋብቻ
ካላት
... ውጭ
አገር
መውጣት
ብትፈልግ
,,, ባለቤቷ
ፍቃድ
መስጠትና
መፈረም
አለበት
ምን
ማለት
እንደሆነ
ይገባሀል
አሰረኝ
በቃ
አሰረኝ
እሱ
ወደውጭ
ወጥቶ
እኔን
አሰረኝ
...

ተበሳጨሁ
.... ልፈታው
ፈለኩ
....
ምንም
አቃተኝ
//// ለመፍታትም
እሱ
መኖር
አለበት
... ከአገር
ለመውጣትም
እሱ
መፈረም
አለበት
ይገባሀል
.. ምን
ማለት
እንደሆነ
ሰት
ልጅ
የወንድ
ልጅ
እቃው
ናት
....
በባህልም
.. በመንግስትም
ደረጃ
አያበሳጭም
በናትህ
ውይይይይይይይ
ሶሪ
አስጨነኩህ
አይደል
አውርቼው
አላውቅም
እኮ
... ግን
በቃ
በዛብኝ
... የማወራው
ሰው
አልነበረብኝ
አንተ
ግን
ምን
አይነት
ሰው
ነህ
.. በማርያም
ኦኬ
ኦኬ
... እንዴት
ወጣሁ
መሰለህ
ባሌ
አጠገቤ
ሳይኖር
አምስት
አመት
ያህል
ከቆየ
.... ለመውጣት
የቤተሰቤ
ፍቃድ
በቂ
ነበር
... እና
ብዙ
ብዙ
ለፍቼ
ነው
ልወጣ
የቻልኩት
ከኤርትራ
በፍለጋ
አግኝቼው
...

6አመት
በኃላ
ተገናኝተንም
አሁንም
እንደእቃው
ሊያየኝ
ይፈልጋል
ይደበድበኛል
...
ይንቀኛል
...
አይሰማኝም
... እያለሁ
እንደሌለሁ
ነው
ሚቆጥረው
እና
ቆርጫለሁ
ግን
አንተ
ምን
ትመክረኛለህ
.........................................//...................................
> እስኪ
ምን
እንዳሰብሽና
ምን
እንደቆረጥሽ
ንገሪኝ
+ ኤርትራ
እመለስና
.. የናቱን
ፍቃድ
,.. የቤተስቤ
እርግማን
እንዳይኖር
አድርጌ
ፈታዋለሁ
.... የሚያስጨንቀኝ
ግን
የልጄ
ነገር
ነው
ልጄ
ያለአባት
ሊያድግ
ነው
....
ግን
ለነገሩ
እስከዛሬ
ያላባት
ነው
ያደገው
በቃ
አላውቅም
እኔ
ወስኛለሁ
> እና
ለዚህ
ጉዳይ
ብለሽ
ወደ
-ኤርትራ
ልትሄጂ
ነው
?
+
አዎን
...
ነግሬዋለሁ
.... ልጄም
ናፍቆኛል
... መሄድ
አለብኝ
> ምን
እንደምልሽ
አላውቅም
.... እዚሁ
ወስነሽ
ብትጨርሺው
እወድ
ነበር
... ምንም
ላደርግልሽ
ባለመቻሌ
በጣም
ነው
ማዝነው
.... ግን
እንድረዳሽ
የምትፈልጊው
ነገር
ካለ
................. በቃ
ልትመለሺ
ነው
ማለት
ነው
ኤርትራ
....
+
ልጄን
ይዤ
እመጣለሁ
... እሰደዳለሁ>
ኦህ
.... ማይ
ጋድ
+
አታስብ
... አንተ
በጣም
ከምገምተው
በላይ
ነው
ያደረክልኝ
... በትግስት
ስላዳመጥከኝ
በገንዘብ
የማይለወጥ
ነገር
ነው
ያረክልኝ
.... አሁን
ቅልልል
ብሎኛል
..
አመሰግናለሁ
.... አሁን
መሄድ
አለብኝ
.... እደውልልሀለሁ
የተለወጠ
ነገር
ካለ
+ ደህና
ሁንልኝ
... በጣም
ነው
የምወድህ
.... ባቅፍህ
ቅር
ይልሀል
እውነቴን
ነው
ምላቹ
እግሬ
እራሱን
ችሎ
መሸከም
ነው
ያቃተው
ዝምምምምም
ብዬ
አየኃት
እንደፈለገችው
ሆንኩላት
ሳመችኝ
እና
በቆምኩበት
ጥላኝ
ሄደች
ፊጧን
አንዴ
እንኳን
አላዞረችም
በቃ
ሄደች
...............................//...............................
ስትደውል
እነግራቹዋለሁ

አደቆርሳ
Jogger
Jogger
Posts: 45
Joined: 13 Jan 2012 04:13
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አደቆርሳ » 26 Feb 2012 17:15

ትልቁ የኪነጥበብ ሰው መምህር ጋዜጠኛ አርታኢና ደራሲ ስብሃት ለአብ ገብረእግዚአብሄር አረፈ !
ዜናው ያስደነግጣል አይደል ? በጣም እንጂ ! በጣም ያስደነግጣል ::
ኖሮ ኖሮ ከመሬት ዞሮ ዞሮ ከቤት ...
እንዲሉ የተፈጥሮ ግዴታ ሆነና ጋሸ ስብሃት ወደማይወዳት ዓለም ቀድሞ ተጓዘ
ማንም ሠው በምድር ላይ ሳለ በሰራው ስራ እርሱ ሲያልፍ ስሙ ከመሬት ይቀራል ክፉም ሠው ክፋቱ ይቀርለታል
መልካምም ሠው መልካምነቱ ይቀርለታል :
ምናልባት የእግዚአብሄርንም ቃል ያየን እንደሆነ ለምድራችን የመኖሪያ
ጉልበት ሆኖ እናገኘዋለን:: ሠው የስራውን ዋጋ ያገኛል ይላ ልክ እንደዚሁ ነው
ጥሩ ሰዎች ጥሩ ስራቸው መጥፎ ሰዎችም መጥፎ ስራቸው በህይወት ሳሉም ጀምሮ ከጀርባቸው ምንም ያህል ሳይርቅ የሚከተላቸው::
እነርሱ ካለፉ በኋላ ደግሞ እስከ ዘለዓለም ይኖርባቸዋል ወይንም ይኖርላቸዋል::
ስብሃት ገብረ እግዚአብሄርን እንደ መታደል ሆኖ ጥቂት ቀናትን አብሬው ውዬ አውቃለሁ ዝምምምምምም
ብዬ ከአፉ የሚወጣውን ሳዳምጥ ውዬ አመሽ ነበር ብዙ ነገር ለመጠየቅ ስሜቴ ውጥርርር ቢያደርገኝም
የሚናገረው የሚያመልጠኝ ስለሚመስለኝ ከጥቂት ጉዳዮች በስተቀር ልጠይቀው አልቻልኩም ነበር::
ከዚህ ቀደም አንድ ያላሰብኩት ቦታ ለስራ (በቀን ሰራተኝነት) ሄጄ አንድ ላገኘው የማልችል በጣም በጣም ሃብታም ሰው
አጠገቤ ሆኖ አየሁትና ተገረምኩ: እንዴ እንትና ይሄውና አልኩ ለራሴ ዝም ብዬ የሚናገረውን እና የሚያደርገውን በጥሞና
ስከታተል ለሰዓት ቆየሁ ታዲያ በውስጤ አንድ ነገር አስብ ነበር በጣም ብዙ ገንዘብ ያለው ሃብታም ሰው እንዴት እንደሚኖር ምን
እንደሚበላ እንዴት እንደሚናገር ምን እንደሚያደርግ ወዘተ ከልጅነቴ ጀምሮ የራሴ የሆነ አመለካከት የነበረኝ ይመስለኛል .... ::
ያንን ሃብታም እንደዚያ አድርጌ የሚናገረውን የሚያደርገውን በጣም ያየሁትና የሰማሁት የተለየ ነገር የማይባቸው ስለሚመስለኝ
መሰሎኝ እንደሆነ አውቃለሁ:: ጋሼ ስብሃትን የተከታተልኩት ልክ እንደዚያ በነበረ ጥልቅ ስሜት ቢሆንም ወደውስጤ ለማስገባትና
መንፈሴን ለማርካት ሲሆን ሃብታሙን ሰው የተከታተልኩት ግን ለመገረም ይመስለኛል::
እንጂ በእርሱ ሁኔታ ረክቼ ራሴን ለማዝናናት ሊሆን መቼም ከቶም አይችልም::
የሚገርመው ነገር ግን ምንም የገረመኝም የተለየም ነገር አለማየቴ ሃብታም ማለት ?
ብሎ አዕምሮዬ ድሮ የሚስለው ሸራ የሌለው ሥዕል ስህተት መሆኑን ተረዳሁኝ::
ስለዚህ ለውጡ ያለው ኪስ ላይ ብቻ ነው ማለት ነው አልኩና ከዚያ በኋላ ለሃብታም ኬሪዳሽ ሆንኩኝ:
ለችሎታ ሃብታሞች ግን ለጥበብ ባለጸጎች ግን ለድንቅ ደራሲያን ግን ያለኝ መገረም ውስጤን የሚነካ ፍላጎቴን
የሚያረካ ህይወቴን የሚያፈካ ቁምነገር ማግኘት ነው ::
ስለ ጸሃፊያን ግን በደንብ አስባችሁ ታውቃላችሁ ሴት ልጅ ለመውለድ እንደምታምጥ እነሱ ቃላትን ሲያምጡ ማሰብ ኦህ በጣም ነው የሚገርመኝ::
በአሉ ግርማን የሚያህል ደራሲ መቼም ይፈጠራል የሚል እምነት አልነበረኝም ደራሲውን ሲጽፍ
ጋሽ ስብሃትን እንደቀረጸው ካወቅኩ በኋላ እንደገና ደራሲውን አነበብኩ::
አንዲቱን ቀን በጠዋት እንደተገናኘን እንዴት አደርክ ጋሽ ሥብሃት ? አልኩት
እንዴት ላድር ትፈልጋለህ ? አልጋ ላይ ተኝቼ ነዋ !
ሳቅ አልኩና እንደምን አደርክ ማለቴ ነው አልኩት ስህተቱ የገባኝ መስሎኝ
ቀንቶኝ ነው ያደርኩት አለኝ
ምን ቀናህ ?
ከዚህ በላይ እኔም አላውቅ አለኝ ...........
በጣም ያሳቀኝ አባባል ነበር::
ጸሃፊ ዘነበ ወላ ለጋሽ ስብሃት ግባ መሬት ስንብት ሲያደርግ እንዲህ አለ … በሌለህበት ቦታ ሁሉ ያንተን ስም ሳነሳ በታላቅ ኩራት ነው !
ደስ ያለኝ አባባል ነው ::
ጋሽ ስብሃትን ከሚያስታውስበት ነገሮች ሁሉ ትልቁን ስጦታው እንዲህም ብሎኛል አለ ....
እድሜ ለአጤ ምኒሊክ ባንዲራን እና አማርኛን አምጥቶ እኔንና አንተን አገናኝቶ አንድ አደረገን
አለበለዚያማ እኔም ከመይ እያልኩ አንተም ሃይመሌ እያልክ ሳንግባባ እንቀር ነበር .....
አስተማሪና ድንቅ አባባል ነው ::
ኢትዮጵያ በውነት በዚህ ዘመን ያጣቻቸው ትልልቅ ሰዎች
በዓሉ ግርማ ጸጋዬ ገብረመድህን ስብሃት ገብረእግዚአብሄር ጥላሁን ገስስ ሌሎችም ሌሎችም ታላላቆቹና ስመጥሮቹ
ኢትዮጵያውያን ትተውልን ያለፉት ውርስ ፍቅር ብቻ ነው::
ልዩ በሆነውና በራሱ የአጻጻፍ ችሎታ አገር ያደነቀው ጸሃፊ ስብሃት ገብረእግዚአብሄር ብዕሩ ሃሰትን በፍጹም አታውቅበትም ስታስረዳም ስትናገርም
እንደወረደች ናት ለዚህም ነው ሁለተኛው ስሙ <<እንደወረደ>> የተባለበት::
ጋሽ ስብሃትን እንደወረደ ተብሎ የሚጠራበት ምክንያት :- ጽሁፎቹ ቅኔያዊነትን አያውቁም ገላጭ አረፍተነገሮችን አይከጅሉም አስረጅ አያሻቸውም
እንደው በቀጥታ የፈለገውን ቃልና ዓረፍተ ነገር ቁጭ በማድረግ ለእርሱ በተቸረው ልዩ የጽሁፍ ችሎታ በአንባቢው ስሜት ውስጥ ገብተው ሲዋኙ :
ከልቦና አለመጥፋታቸውና ዳግም መጽሃፉን ማንበብ አለማስፈለጉ ብቸኛ መግለጫው ነው:
የኢትዮጵያ የስነጽሁፍ ጥበብ እንዲያድግ እድሜውን የሰጠ ታላቅ ደራሲ : እንደለማኝ ለምኖ እንደመምህር አስተምሮ እንደድሃ አጥቶ እንደጸሃፊ ጽፎ
እንደጋዜጠኛ ዘግቦ ህይወቱን ለማስተስተማሪያነት ለወገኑ ገጸበረከት ያቀረበ ትልቅ ሠው ስብሃት ለአብ ገብረእግዚአብሄር እስከወዲያኛው አሸለበ ::
አፈሩን ያቅልልለት
እንዲሁም ተወዳጁና ባለ ብዙ ታሪኩ የጥበብ ሰው ሱዳናዊው መሃመድ ዋርዲ በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ
እጅግ በጣም አሳዝኖኛል የእርሱንም ነፍስ ይማር ::

ቸር ይግጠመን አደቆርሳ ዘሃገረ አዶላ

Post Reply

Return to “የጀምጀም ልጆች መገናኛ”