የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Forum rules
No cursing, bad language and offend other users !
No pornographic images or links!
This forum monitored regularly. We will BAN users without warning for not obeying rules.
እባክዎ የፎረሙን ህጎች ያክብሩ::
አደቆርሳ
Jogger
Jogger
Posts: 45
Joined: 13 Jan 2012 04:13
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አደቆርሳ » 21 Jan 2012 15:12

ትናንት ቤታችን አላስገባ ብላኝ ነበር ዛሬ ግን ገና ሳላንኳኳ ቤት ለእንግዳ ስላለቺኝ ትናንት የጻፍኩትን እነሆ ! የዛሬውን ደሞ አስከትላለሁ ::
ዛሬ ጥምቀት ነው
የጥምቀት ክብረ በዓል በሃገራችን መከበር ከጀመረ የክርስትናን ወይንም የክርስቶስን
(በምቹ አባባል የዓመተ ምህረትን) ያህል እድሜ አለው ::
ዮሃንስ መጥምቁ በዮርዳኖስ ባህር እየሱስን ያጠመቀው በዛሬው እለት ነው ::
(በዕደዮሃንስ በማየ ዮርዳኖስ ይለዋል መጽሃፉ) መጥምቁ ዮሃንስ እየሱስን በመንፈቅ ያህል ይበልጠዋል እየሱስ በቅድስት ድንግል ማርያም ሆድ ጽንስ ሆኖ ሳለ ድንግል ማርያም ኤልሳቤጥን ለመጎብኘት ወደሷ ዘንድ ሄደች ከበሯም ደርሳ ሰላም ባለቻት ጊዜ በናቱ ማህጸን የነበረው ዮሃንስ በደስታ ዘለለ::
በሉቃስ ወንጌል ይመስለኛል ሙሉ ታሪኩ እዛ አለ ::
ባጭሩ እየሱስ በማየ ዮርዳኖስ በሰላሳ ዓመቱ ከተጠመቀ ጀምሮ :-
እነሆ ዛሬ ሁለት ሺህ አመታት ተቆጥረዋል ሃገራችንም ይህንን ያህል ዘመን የጥምቀትን በዓል ስታከብር ኖራለች ማለት ነው::
ልጆች ሆነን እንደጥምቀት በዓል የምወደው አልነበረም ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ወላጆች እጃቸው የሚፈታው በጥምቀት ሲሆን በአሉም ረዘም ያለና ብዙ ደስታ የምናሳልፍበት ስለሆነ ጥምቀትን እንወደዋለን::
አዋሳ በኖርኩበት ዘመኔ የጥምቀትን በአል ለማክበር ወደ ጥምቀተባህር ስንሄድ በወላይትኛ ጭፈራ ከምንም በላይ ተማርከን የምንውልበት ጊዜ ከመሆኑም በላይ ወደማታ አመሻሽ ላይ አንድ የለመድነው መዝናኛ ስለነበር ያስደስተኛል : ምንድነው እንዴት ነው ማለት አይፈቀድም::
ስለዚህም ቢቻለኝ አሁንም ቢሆን ጥምቀትን ከአዋሳ ውጪ የትም ማሳለፍ አልፈልግም::
ሴቶች ከየተቀጠሩበትም ከየሚሰሩበት ከየሚኖሩበትም ለጥምቀት አምረው ደምቀው ይመጣሉ ቅባትና ሽቶ አንጎል የሚያዞሩት ያኔ ነው:: ታዲያ ተቀባብተው አምረው ደምቀው ወደ ጥምቀት ሲመጡ ያየናቸው ቆነጃጅት ከጭፈራው በኋላ ፊታቸውና እግራቸው የአዋሳን አፈር ቅሞ አመድ መስለው ሲመለሱ ማየት ልዩ ግርምት ነበረው::
ክብረመንግሥት በመሰረቱ ጥምቀት የምናከብረው ጨፌ ስለሆነ አዋራ የምትባል ነገር አታገኘንም ሴቶቻችንም ቅባታቸው እንዳለች ውላ እንዳማሩ ስለሚመለሱ ኩራታቸው መከራ ነበር : ዳሩ ለጥምቀት ኩራት የለም ለምን እንደሆነ አላውቅም::
እንኳን አደረሳችሁ !
ፔሬድ ስላለቀ ነው ከቻልኩ ሞልቼ እመለሳለሁ አለዛም ሌላ ቀን እንገናኛለን ስለ ሰሞኑን ክስተቶች ትንሽ ለማለት ተመችቶኝ ነበር ለነገሩ ሁላችሁም እንደምትሰሙ አምናለሁ ፈረንጆች ቱሪስቶች በሃገራችን በደረሰባቸው የግድያና የአፈና ጉዳይ : ስለ ሎንዶኖ ኦሎፒክ ታዋቂ አትሌቶችን በተመለከተ በተለይም ቀነኒሳ በቀለን በተመለከተተተተተ..ሌሎችም ጉዳዮች (ልጅ ተድላ ናፈቀኝ እስቲ ጋብዙት ባካችሁ )
ሞፊቲኮ አሰብኩኝ እንጂ አልተሳካልኝም ስለዚህ አለሁ:ፔሬድ ሳታቆራርጠንቸር ያቆየን ወዳጃችሁ አደቆርሳ ዘሃገረ አዶላ

ራስብሩ
Starter
Starter
Posts: 23
Joined: 03 Jan 2012 09:45
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by ራስብሩ » 07 Feb 2012 10:03

ጤና ይስጥልኝ
ሞፊቲኮ ሰላም ነው? የአፍሪካ ካፕ ኦፍ ኔሽንስ እንዴት ነው ? የትናንት ወዲያው የቱኒዝያና
የጋና ጨዋታ አስገራሚ ነበር ውጤቱን ማወቅ ስለጓጓሁ 4 ሰአት ስራ የምገባው ሰውዬ እስከ 11 ቁጭ ብዬ አየሁት ቢሆንም ጋና ሞቶ ሞቶ ማሸነፉ ደስ ብሎኛል ::
የነገውንም ፍልሚያ ለማየት ዱብ ዱብ እያልኩ ነው ስለዋንጫው ምን ትላለህ ማን ያነሳዋል ?
ብለህ ትገምታለህ ?
እኔ ጋና ዋንጫውን ያነሳል የሚለውን ግምቴን ከቱኒዚያ ጋር ያደረገው ጨዋታ አደብዝዞታል ::
ራስብሩ

Dole
Starter
Starter
Posts: 19
Joined: 04 Jan 2012 20:47
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Dole » 09 Feb 2012 09:06

እናንተ ዛሬ አየኃቹ በአማርኛ
እንደምን አላቹ ያገሬ ልጆች
እንዴት መሰላቹ የጣፋቹት..... ከኮምፒተሬ ላይ ይህንን ቤት ማየት አልቻልኳአቹም እና ዛሬ በሰው ኮምፒተር ነው ያነበብኳቹ

ያቺን የዋርካ ቤታችንን እስካሁን አልተውኳአትም.... ግን ለመጻፍ ሞርፋሌን ግድልድልልልልልልልልልል አድርጋቹ ስላበቃቹ.....
ዝምምምምምምምምም ሆኖአል ነገሬ

በተረፈ
ከአደቆርሳ ጎረቤት ለመሆን ብዬ በዶሌ በኩል መጥቻለሁ

እንዲህ ሲመቸኝ ብቅ እላለሁ
እዛኛውም ቤት አለሁ
ብቅ ብላቹ አንቡኝ
አዲስ ኮምፒተር እስከምገዛ

በሰላም ባላቹበት ኑሩልኝ

ባለሱቅ
ከዶሌ

አንፈራራ
Runner
Runner
Posts: 50
Joined: 03 Jan 2012 12:51
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አንፈራራ » 09 Feb 2012 20:12

ባለሱቅየ
እንዴነህ ወዳጄ? እናንተ ባለመምጣታችሁ ብቻ ልንቀጥለ የነበርነውን የጽሁፍ መለዋወጥ መቀጠል አልቻልንም::

ብዙ የ ክ/መ ልጆች በ ፌስ ቡክ አጋጥመውኝ ጋብዣቸው እዚህ መጥተው ቤቱ ባዶ ሆነበን አሉ:: የሳመራ የመድሃኔ ድራር የዘውዴ አበሩ የፍቅሩ ተወልደ የገዳም ፎቶ እና የሌሎችም ልጆች::
አደቆርሳም ተበሳጭቶ ይመስለኛል የቀረው:: የምትመጡ ከሆነ እኔም መጣለሁ እንደ ዱሮው:: ዋርካ ግን ፎርጌት ኢት:: ኢየሱስን አላህን መሓመድን የሚሳደብ ቤት ሆንዋል:: የቀረ ይቀራል እንጂ እዚያ እንክዋን እርሳው መምጣት የለም::

ደግሞ የዚህ ፎረም አስተዳዳሪዎች ብዙ ነገር አሻሽለዋል:: አሁን ለምሳሌ "ዶሌ" ማለትህን ትተህ "ባለሱቅ" ብለህ በቀላሉ መግባት ትችላልለህ::

ስለዚህ በዚህ እንቀጥልና የወደፊቱ ፕሮግራማችንንም እንወያይ:: አይሆንም ካላችሁ ምን ይደረጋል? እዚያው ክ/መ እንገናኝ::
ለራስብሩ ሞፊቲ አደቆርሳ ቦሪቲ የግል አይፋ ሌሎቻችሁም ሰላምታየ ይድረሳችሁ:: ሽልንግየ አትጥፋ::

Dole
Starter
Starter
Posts: 19
Joined: 04 Jan 2012 20:47
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Dole » 09 Feb 2012 21:08

This is a copy and past from the other room

I dont know what you are writing unless I use another computer

Anyway here you go

ሰላም ሰላም ያገሬ ልጆች
እንደምን አላቹልኝ
ብትመጡም ባትመጡም እፅፋለሁ... ቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ያኛውን ቤታቹን ማየት በምችልበት አጋጣሚ ደሞ... ከዚህ እየገለበጥኩ ወደናንተ Copy and Paste
ምን ይደረግ እንግዲህ... ኮምፒተሬ ሲጠም!

እናላቹ አቤት ላወራላቹ አስቤ የነበረው በዚህን አዲስ አመት.... ስንትናስንት አርስት ላካፍላቹ ፈልጌ
ኤጭ... ተውት በቃ
ይልቅዬ... ዛሬ ምን ላወራቹ ፈለኩ መሰላቹ
ስለጦቢያ
ባለፈው አመት.... አንድ ወዳጄ ከዚህ ከምሰራበት መስሪያ ቤት ወደ-ኢትዮጵያ ለ4ወር ስራ ይሄዳል
ብዙ አፍሪካ አገር ለስራ ቢሄድም ኢትዮጱያ የመጀመሪያ ጊዜው ነበር
በወሬ በወረ ካልሆነ በስተቀር ምንም አያውቅም
ደሞ እንደማየት ለራስ እውቀት የሚረዳ የለምና
አይቶ ያየውን ሊነግረኝ ሄደ....
አዲስ-አበባ... ኢትዮጵያ
የስራ ባህሪው ሆኖ.... ባህር-ዳር አዋሳ... ናዝሬት.. አዳሚ-ቱሉ.... የሄደ ቢሆንም ብዙውን ጊዜያቱን ያሳለፈው አዲሳባ ውስጥ ነው
ግርድና ሚኒስቴር (ሶሪ ግብርና ሚኒስተር ማለቴ ነው)... አንዳንዴ እንደ-አቤ ቶኪቻው ያስቃዠኛል ይሄ እስኪፒርቶ
ጠንቀቅቅቅቅቅ ነው ጃል.... ቴረሪስት ለመሆን መፋለጥ ያስፈልጋል... ያለው ማነው?... ጉቦም ሙስናም ይጠይቃል አሉ... ታፔላ ለማግኘት .. የቴረሪዝም
ማን እንደሚያነብ ምን ይታወቃል... ህ ህ
እናላቹ
ይህንን የክረምት ወራት አዲሳባ ከርሞላቹ በኦክቶበር አካባቢ ይመስለኛል ተመልሶ መጣ
እሱ ተመልሶ ሲመጣ እኔ ለስራ ጉዳይ አፍሪካ ስለ ነበርኩ
አልተገናኘንም ማለት ነው
እኔም ከስራዬ ተመልሼ ቢሮ የገባሁ ቀን... ሰው ሁሉ እኔን ነበር ሚያየው
ግራ ግብት አለኝ
ሰላምታ ሰጥቼ.... ቦታዬ ልቀመጥ ስል
ያ የስራ ባለደረባዬ ጠራኝና
አንተ ግን አገር አለኝ ትላለህ? አለኝ
ክው ነው ያልኩት
በውነት... ጀርባዬን ሁሉ አላበኝ
ቻል አርጊው ቻል ፍቅሬ ቻል አርጊው
ቻል ቻል መውደድ ቻል ቻል ቻል ቻል
ወሬና ነገር.... ለፍቅ.........ር
እንዴት እንዴት እንዴት
እንዴት ይበጃል
ለምን ትዝ አለኝ ይሄ ዘፈን
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
እስኪ እመለሳለሁ

Dole
Starter
Starter
Posts: 19
Joined: 04 Jan 2012 20:47
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Dole » 10 Feb 2012 05:16

Copy and Past

ተመልሼ መጣሁ
በተሰረቀ ጊዜ
እና ቀጠለ ጉደኛው ጓዴ
.......
> ምን አይነት አገር ነው ግን... ያላቹ....
ድምፁ ምርርርር ያለ ነበር
* እንዴት ምን ሆነብህ.... ለማኝ በዛ.... ቀማኛ አስቸገረህ.... ባለስልጣን ጉቦ ጠየቀህ.... በረሀብ አለንጋ የተገረፈ አንጀት መንገድ ላይ ወድቆ አሰቀቀህ
> ኖ ኖ እንደሱ ማለቴ አይደለም
* ታዲያ ምን እንዲህ አስማረረህ
> ብርዱ
* ም.....ን
> ብርዱ አጥንት ውስጥ እኮ ነው ሚገባው
ሳቄ መጣ
እሱ ግን ከምር ብሽቅሽቅ ምርርር እንዳለው ያስጣውቃል
* ከዚህ አገር ይብሳል እንዴ ብርዱ... እንዲህ ያስመረረህ
> ኖ ኖ አልገባህም..... ያገራቹ ህንፃ አሰራር ብርድን ለመከላከል ምንም አይነት ነገር አልተሰራበትም
ማሞቂያ የለ
ብርድ መከላከያ የለ
ቢሮ ውስጥ ብርድ-ልብስ ተለብሶ መቀመጥ ቢቻል... ከምር እንደሱ ላደርግ ሁሉ አስቤ ነበር
የምትንቀሳቀስ እንኳን ቢሆን... ሰውነትህ ይሞቃል
ቢሮ ውስጥ ቁጭ ተብሎ
ብርዱን ታዳምጣለህ.. ወይስ ስራህን ትሰራለህ
* ይህንን ያህል ይበርዳል እንዴ ግን.... ክረምት ስለሆነ መሆን አለበት.... ለነገሩ እኔም ያዲሳባ ብርድ አይስማማኝም... ሆድ ይነፋል
> ልክ ነህ... አዋሳ... ባህር ዳር ምርጥ ቦታ ነው... ለመኖር.... እዛ ግን ብዙ አልቆየሁም... አዲሳባ ግን ... ሁለተኛ
ደሞ እኮ የሚገርመው የሰዉ ነው
* እንዴት የሰዉ ነገር
> ፈገግታ አንድም ሰው ላይ አታይም እኮ
ያ ሚወራለት ቁንጅና... ፈገግታ...
አፍሪካ ውስጥ ሁሌ የማየው.... ነፃ የሆነ በገንዘብ የማይገዛ ፈገግታ.. ርቆታል ሰዉ....
ጭፍግግ ያለ ፊት
አጎንብሶ ቅስስስ እያለ የሚኳትን ህዝበ
እንዴ በጣም ያስጠላል እኮ.... ምንድነው ችግሩ
* ብርዱ እንዳይሆን
> እረ ኤዲያ... ብርድ እንዲህ ያደርጋል እንዴ.... ልብስ ተለብሶ ሲወጣ.... ስትንቀሳቀስ... ብርዱ አይሰማህም.... ቢሮ ቁጭ ስትል እንጂ
ምንድነው ችግሩ ግን.... የህዝቡ
* እንግዲህ ብርዱ ካልሆነ.... ድካም ይሆናል... አልኩት
እና ስለ ቁምሳ... እና ምራት ልነግረው ፈልጌ
ተውኩት
ያኔ ያ ናይጄሪያዊ ጋዜጠኛ.... እንደዚያ ሙልጭ አድርጎ ሰድቦን (የደነዘ ህዝብ... መንግስት ላይ የማያምፅ .. ፅጥ ለጥ ብሎ የሚገዛ ፈሪ ህዝብ ) ብሎ .. ሲያበቃ....
ደሞ ምንም እንዳልተደረገ... ይስቃል.... በየመንገዱ ምታየው ህዝብ በፈገግታ ታጅቦ ነው....
እያለ የቀደደልኝን... ለንባብ የበቃ.... (የዛሬ 2አመት ገደማ መሰለኝ).... እሱን ነገር እዚህ አውርቼላቹዋለሁ
እሱ ነገር ትዝ አለኝና
በዚህ ሁለት አመት ውስጥ.... ይሄ የመስሪያ ቤት ባልደረባዬ... ፈገግታ አገራቹ የለም... ያለኝ ጊዜ
ህምምምምም ነገሩ ሲመር ለካስ ፊት ላይ ይውጣል... አሰኘኝ
እላቹዋለሁ

እውነት ግን አገሬ ፈጋግታ ጠፍቷል?
እስኪ ሄዳቹ የመጣቹ ካላቹ
ፈገግታ የጠወለገባትን ሀገሬን አሳዩኝ
እንዴት ያጠግበኝ ነበር መሰላቹ... ያገሬ ድሀ ህዝብ ፈገግታው
ወይስ ይህ ሰው ያየው አዲሳባን አይደለም?
አለበለዚያ ሰዉ እንደኔ... አገር ማለት ምን ማለት ነው... ብሎ ጠይቆ... መልስ ሲያጣ አኩርፎ ነው
ከምር ግን አገር ማለት... ምን ማለት ነው....
የኔ የምለው መሬት ለራሴ እና ለቤተሰቤ ከሌለኝ.... አገሬን አገሬ የምላት... ፓስፖርት እና ዜግነት (የተገደበውን) ስለምትሰጠኝ ብቻ ነው
ኡጋንዳ
ሞዛምቢክ
ኬንያ ሄጄ ከልቤ ያስቀናኝና ምርርር ያደረገኝ
እያንዳንዱ ህዝብ የራሴ የሚለው መሬት አለው..
ቤት ቢሰራበትም... ባይሰራበትም... ቢያርስም ባያርስም.... ቢጎበኘውም ባይጎበኘውም... የራሱ መሬት አለው,,,,
አንዳንደ የአለምን ካርታ ራቅ አድርጌ አይና..... የኔ የምለው በዚች ምድር ላይ ምን አለኝ ብዬ ስጠይቅ
ግርም ይለኛል
ምንም የለኝማ!
ምን ያደርግልሀል ነው ያላቹኝ?
ገነቴን ልሰራባት
ድንቄም እቴ... አለች የግልነሽ.... ገነትን ከሰማይ ቤት ይዛልኝ ልትመጣ አስባ
ምን እያወራሁ ነው ጃል
ደሞ ይህችም እንደ-ቴረሪዝም ተቆጥራ... ምላጭ ውስጥ እንዳታስገባኝ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ሰላም ሁኑ አቦ
ተመልሼ እመጣለሁ
ፈገግታን ላገሬ ህዝብ ይመልስልኝ
አሜን

አደቆርሳ
Jogger
Jogger
Posts: 45
Joined: 13 Jan 2012 04:13
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አደቆርሳ » 10 Feb 2012 15:46

የበር ላይ እንጨት አንች አሰናካይ
ወይ ነደሽ አትሞቂ ልመና ከልካይ
እያጉረመረመ እንደሰኔ ለማኝ
ሞገደኛው ነፋስ ድምጽሽን ያሰማኝ


እንደው ድምጽህን ሰሠማ የሆነ ነገር እንደጠጣ ሰው ቶሎ ሞቅ ይለኛል ለምን እንደሆነ አላውቅም :
ደስ አለኝ ስል ምን ትዝ አለኝ መሰለህ የዛሬን አያርገውና ድሮ በጠበሳ ዘበን ቀጠሮ ካለኝ ደስ ደስ ሲለኝ ይውልና ልክ ሰዓቱ
ሲደርስ ጭንቅ ጭንቅ የሚለኝ ነገር ነበረኝ ለምን እንደሆነ እስካሁንም አይገባኝም ::
ግን ባለሱቅ ለምን እንደሆነ የማይገባህ ነገር ለምን እንደሆነ ይገባሃል ? እኔ ግን በጭራሽ ::
ቆይ ቆይ ይሄ ሰውዬህ አዲስ አበባ ብርድ ገደለኝ ያለህ ከዛሬ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ስትመጣ ሚስትህን ይዘህ ና ብለውሃል በለው ::
ገና አፍሪካ በረዶ አውሮፓ ደሞ ግለት ይሆናል በለው : ዘመዶችህ የአቶም ዝቃጭ እያመጡ እዚህ የኛ ምድር ላይ ሲቀብሩ የናንተ
እድሜ እስኪያልፍ ድረስ ብቻ ነው ቀጣዩ ትውልድ ምን ዕጣ ይዞ እንደሚፈጠር ዛሬ ላይ ሆናችሁ ታውቁት የለም ወይ ? በለው ::
ለጊዜው ብቻ ያደሩ የአፍሪካ መሪያት የዳጎሰ ጉርሻ እያመነዠኩ የፋብሪካ መርዝ በምድራቸው ላይ ያስቀብራሉ : ይሁን እንጂ ችግሩ
ቀድሞ የሚጎዳው እናንተንው ነው በልልኝ ባክህ ::
ይልቁንስ ናይጄሪያዊው የተናገረው ትክክል ነው የሆነው ሆኖ እንደነሱ ከሳንጃና በጎራዴ ከመተራረድ በፈሪሃ እግዚአብሄር የታቀበ ህዝብ የተሻለ ነው :
የአፍሪካ ባህል ይመስል ጎሳ ለጎሳ ዘር ለዘር ሲተራረዱ ቆይተው አሁን ደግሞ በሃይማኖት መነካነክ ጀምረዋል አምላክ ኢትዮጵያን ከዚህ ይሰውራት::
ስለ ፈገግታ ያነሳልህ ነጥብ ግን በውነት ትክክል ታዝቧል ያሰኛል ::
ግን እንዴት ይህንን ነገር ሊታዘብ ቻለ ብዬ ገረመኝ ምክንያቱም እናንተ ሃገር ሰዉ እንኳንስ መንገድ ላይ ሊስቅ ይቅርና ቤታቸውስ ቢሆን
መቼ ፈገግ ይሉና ነው ? ጧት ማታ ሩጫ አይደል እንዴ ?
እንዴት እዚህ መቶ ሊገርመው ቻለ ? ዳሩ ህዝቡስ ከየት አምጥቶ ፈገግ ይበል ? በምኑ ፈገግ ይበል ? ፈገግታ እኮ ከውስጥ ደስታ ከወደፊት
ተስፋ አልያም ካለፈ መልካም ትዝታ ነው : እስቲ እግዚአብሄር ያሳያችሁ ከዛሬ አርባ ዓመታት ጀምሮ መከራ... ሞት... ስቃይ.. ረሃብ.. እስር.. ችግር ..ወደኋላ ብትል ወደፊት ምን አለና ህዝቡ ደስ ይለዋል ?
እንደውም ሳቅ ከመጥፋቱ የተነሳ በአጋጣሚ ስትስቅ ፌዴራል ካየህ በማን ላይ ነው የምትስቀው ተብለህ ሸቤ መግባትህ ነው
ስለዚህ አዲስ አበባ ውስጥ ሳቅ በልክ ነው ........
በዚህም ላይ አጅሬዎቹ ስራቸው እንደሚያስቅ ስለሚያውቁ ሰው ሲስቅ ደስ እንደማይላቸው ግልጽ አይደል ?
አስፋልቱን ግን ይሰሩታል ነው የሚባለው !
መቼም ሰው ማናዘዝ ትችልበታለህ ለመሆኑ የት ከርመህ ነው እንደዚህ የጠፋከው ?
ሚስት አገባህ ? ልጅ ወለድክ ? ይቅርታ ልጆች ወለድክ ወይ ማለቴ ነው ?
ስለ ልጅ ሲነሳ እኔኮ አንድ ሚስጥር ልነግርህ እፈልግና ሰነዱን ከጄ ለማውጣት እፈራለሁ የዘንድሮ ሰነድ መቼም መቆሚያ የለው ::
ሞፊቲን አታይም ከቦሬ ተነስቶ አንዴ ክብረመንግስት አንዴ ዲላ እንደገና ደሞ አዲስ አበባን እንደዚያ እያሰሰ ምንም ነገር ትንፍሽ አይልም :
አደቆርሳ ታዲያ ምን በወጣው አዋጅ ይናገራል እንደውም በቃ ትቼዋለሁ::


የምወድህ አንፈራራችን


ካገኘሃቸው የክ/መ ልጆች የአባባ መድሃኔ ድራር ቤተሰብ ውስጥ በጣም የማውቃቸው ሃና መድሃኔን እና አስፋው መድሃኔን ነው ::
ሃና መድሃኔ ፍጹም ለስላሳ እና ተጫዋች ልጅ እንደነበረች አስታውሳለሁ በጣም ተጫዋች መሳቅ የምትወድ እና ተግባቢ ልጅ ነች::
ብዙዎቹን ልጆች በደንብ አውቃቸዋለሁ እንጂ አውርቻቸው ወይንም ተነጋግረን የማናውቅ ልጆች ብዙ ነን ለምሳሌ ሃናን አብረን
ተማርን እንጂ አናግሬያት አላውቅም እርግጠኛ ነኝ ከነስሜ ብነግራት አታውቀኝም ምክንያቱም እኔ ያኔ ማናገር ቀርቶ መናገርም
የምችል አልነበርኩም::
አስፋውን በኳስ ነው የማውቀው እሱና አክሊለ በርሄ አሪፍ ኳስ ተጫዋቾች ነበሩ ትልቁ ወንድማቸው በርሄ መድሃኔም ታዋቂ ነበር ::
ጋሼ ዘውዴ አበሩ ቀደምት ከነበሩ በቅጡ ከተማሩና አውራጃውን ከሚያስተዳድሩ ሰዎች ውስጥ ቀዳሚው ናቸው : ብዙ ግዜ ደጋግመን
እንዳስታወስናቸው በክብረመንግሥት የመጀመሪያው አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀምሮ መምህር የነበሩ ሲሆን በጀምጀም አውራጃ
እንደራሴነትም ትልቅ ታሪክ ካላቸው የልማት ሰዎች ውስጥ ዘውዴ አበሩ አንዱ ናቸው ::
ፍቅሩ ተወልደ አብሮን የተማረ ልጅ ነው በእድሜ ግን እኔ እልቀዋለሁ እስከማውቀው ድረስ እንደውም እስከ በጣም ቅርብ ግዜ ሁሉ
እዚሁ እንደነበረ አውቃለሁ እንኳን ደስ ያለህ ! ብያለሁ ::
ታዲያ በል ቶሎ ብቅ በል ትፈለጋለህ በልልኝ.....
አቶ ገዳም ተስፋሚካኤል የኛ ትውልድ ሁሌም ሲዘክረው የሚኖር መልካም ታሪክ ያለው ሰው ነው !
ስለ ዋርካ የተናገርከው በጣም ትክክል ነው እኔም እንደዋርካ የሚመቸኝ የለም ነገር ግን ገና ስከፍተው ወዲያው የሚታዩት ጽሁፎች
ወይንም ርዕሶች ቀጣዩን ገጽ ለመክፈት ሞራልን ይሰብራሉ::
በውነት ከእናንተም ጋር መገናነት ይቀራል እንጂ እንደዚያ ያለ መልክት በሚስተናገድበት ቦታ ምንጨነቀኝ ብሎ መልሶ መልሶ መምጣት
ኅሊናን መሸጥ ኸረ የምን ህሊና እግዚአብሄርን መካድ ይሆናል ::
ዘግዚአብሄርን ወይንም ደግሞ አላህን በአስጸያፊ ቃላት መናገር ምን ማለት እንደሆነ አዕምሮአችን ለኛ ሊያስተምረን ይገባል ::
ያንን ቃላት ተመልክቼ ቀኑን ሙሉ ጥሩ ስሜት ሳይኖረኝ እውላለሁ ስለዚህ ይህ እንዲሆን ለራሴ መፍቀድ የለብኝም ::
ማየት ያለብን ብዙ መልካም ነገር አለና እንደዚህ ካለው ስፍራ መራቅ አለብን::ባለሱቅ ወንድሜ እንደተረዳሁህ አሁንም እዚያው አለህ ....
ወንድሜ ሆይ ይቅርብህ ያ ቦታ ያንተ ቦታ አይደለም::
አይ እዛ ለምን እንገባለን የራሳችንን ብቻ እንክፈት የሚባል ነገር የለም ዓይን ያያል ልብም ያስተውላል ውጤቱ ደግ አይድለም :: አንዴ ያየኽውን
ነገር ከኅሊናህ ማውጣት አይቻልም ስለዚህ ክፋቱ ማየት ነውና እንዳናይ እዚይ መሄድ ይቅርብን እላለሁ ::


ቸር ያቆየን ወዳጃችሁ አደቆርሳ ዘሃገረ አዶላ

አንፈራራ
Runner
Runner
Posts: 50
Joined: 03 Jan 2012 12:51
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አንፈራራ » 11 Feb 2012 14:25

ሰላም ለዚህ ቤት

ውድ አደቆርሳ ይህንን ሆነ ያኛውንም ቤት የምታንቀሳቅሰው አንተ ነህና የሚሰጥ ሽልማት ቢኖር በሰጠሁህ:: :)

ፍጹም መድሃኔ ድራር የፌስቡክ ግዋደኛ ነው, የሚኖረውም አውስትራሊያ ነው::በውነቱ ብዙ ብዙ የአዶላ/ክመ ልጆች በፌስቡክ አሉ:: ብዙዎቹ ጋር የተዋወኩትም አዶላ የተወለድኩና እዚያ ያደኩ መሆኔን ሲያዩ የፌስቡክ ፍሬንድ እንዳደርጋቸው ስለሚጠይቁኝና እኔም ስለምጠይቃቸው ነው:: ያው ብዙዎቹን አላውቃቸውም ባውቅም ወላጆቻቸውን አንዳንዶቹም አያቶቻቸውን ነው:: ብዙዎቹ ከአገር ወጥተው በየአገሩ ተበታትነው ነው ያሉት -- ኤርትራም ጭምር::

ደስ ይላል ከነርሱ ጋር ስለ አደግንበት አገር ማውራት::

በነገራችን ላይ በፌስቡክ የምትገናኙ ሰዎች የምትተዋወቋቸውን ሰዎች ማጣራት ያስፈልጋል:: አሁን በቀደም, አሜሪካ ቴኔሲ የሚባል ስቴት ውስጥ, አንድ አባትና ወንድ ልጁ, የሆኑ ባልና ሚስት ከሴት ልጃቸው ጋር የነበራቸውን የፌስቡክ ወዳጅነት ስላቋረጡ (በጣም ስታስቸግራቸው ስለነበር) "ልጃችንን አዋረድዋት" ብለው, ሄደው ባልና ሚስቱን ገደልዋቸው:: ስለዚህ የምንመርጣቸውን የፌስቡክ ፍሬንዶች በጥንቃቄ መምረጥ ያስፈልገናል::

በሉ መልካም ሰንበት::

Post Reply

Return to “የጀምጀም ልጆች መገናኛ”