የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Forum rules
No cursing, bad language and offend other users !
No pornographic images or links!
This forum monitored regularly. We will BAN users without warning for not obeying rules.
እባክዎ የፎረሙን ህጎች ያክብሩ::
አንፈራራ
Runner
Runner
Posts: 50
Joined: 03 Jan 2012 12:51
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አንፈራራ » 28 Mar 2013 23:32

ባለሱቅ የ

በመጀመሪያ ስምህን ለማስገባት ሆነ መልክት ለማስተላለፍ "በአማርኛ ለመጻፍ" ስትፈልግ ይህን ተጫን የሚል ምልክት ይሰጥሃል:: ከዚያም አንድ አዲስ ገጽ ይከፈትልሃል::

እዚያ በአማርኛ ከጻፍክ በኋላ የጻፍከውን ሃይላይት አርገህ ኮፒ ታደርገዋለህ ከዚያም ያንን ገጽ ዘግተህ "Post Reply" ወደሚለው ገጽ ትሄድና ኮፒ ያደረከውን ጽሁፍ ፔስት ታደርገዋለህ:: ከዚያም ፊደሎቹን ለማሳደግ አማረጭ ይሰጥሃል ይኸውም የለጠፍከውን ጽሁፍ ሃይላይት አርገህ የፎንት ሳይዝ ሲያማርጥህ ሳይዙን መጫን ነው:: እንደ ወደሬ ጠጅ ቀለል ይላል::
:-D

ጎሳ
ጀማሪ Starter
ጀማሪ Starter
Posts: 8
Joined: 13 Mar 2013 02:51
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by ጎሳ » 29 Mar 2013 18:58

ሰላም ለሁላችንም ይሁን
ጉቦ መስጠትም ሆነ መቀበል እንኳን በምድራዊ ህግ ወንጌሉም የሚፈቅድ አይመስለኝም:: ቁርአንም ላይፈቅድ ይችላል :: እዚህ ላይ ባለሱቅ የሚለን ካለ ቅቅቅቅ ያም ሆኖ መጠኑና አወሳሰዱ ይለያይ እንጂ በየትኛውም ሀገር እና ደረጃ ሙስና ያለ ነው:: ዛሬ የአዶላ ወረዳ ባለስልጣናት የጀመሩት ነገር አይመስለኝም:: ከኢህአዴግ በፊት ጉቦ አልነበረም ይሆን? ስለ ክብረመንግስት ብዙ ስለማላውቅ በደንብ የማውቀውን የቦሬን ከተማ ብንወስድ ሞፊቲ የሚያውቃቸው እነ አየለ ተሰማ፣ አበራ ደርሶልኝ፣ ቦጋለ አለሙ እና ሌሎችም ቁጥር ስፍር የሌላቸው ባለስልጣናት ህዝብን ያራቆቱ እና ያስለቀሱ ጉበኞች እንደነበሩ ስንሰማ ነው ያደግነው:: ዛሬ የአከባቢው ተወላጆች የጉጂ ልጆች ስልጣን ላይ ስለተቀመጡ ያመጡት አዲስ በሽታ አይደለም:: ለነገሩ ጨወታው መች ስለ ጉቦ ብቻ ሆነና:: የልማቱን ጉዳይ ስናይ ኢህአዴግ ከያዘ እኮ ገና ሁለት አስርት አመታት ብቻ ናቸው የተቆጠሩት:: በዚህ ጊዜ ውስጥ የታየው ለውጥ ካገሪቷ የገቢ ምንጭ እና የነበረችበት ሁኔታ ጋር ሲስተያይ የሚያስኮንን አይመስለኝም:: ባጭሩ ጂግሳ የጠቃቀሳቸው በራሳቸው ቀላል አይደለም:: ዛሬ ግማሹ ብሶበት የፊውዳሉን ስርአት እየናፈቀ አሁን ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ለመካድ ብዙ ነገር ያወጣል ያወርዳል... ንጉሡ ይሄንን ፋብሪካ ሊከፍት ነበረ...ይባልልኛል:: አሁን ብዙ ነገሮችን አላንሳ:: ያን የጨለማ ዘመን እንተወው:: ንጉሱ ለሚያመልኩት ይጠቅማቸው እንደሆን አላውቅም እንጂ ለጉጂ ህዝብ ያደረጉት ነገር የለም:: ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ የይለፍ ወረቀት እየተጠየቁ... ማዕድን ይውጣል በሚል ጥርጣሬ ምስኪኑን ህዝብ ባገሩ በግድ ኮሶ እያጠጧቸው ሲያሰቃዩአቸው እንደነበር ሳትሰሙ አትቀሩም:: ገንቦ አሸክሟቸው በጀርባቸው ጠላ እየተጠመቀ ከቦሬ አዲስ አበባ የተነዳው ባሪሶ ቶኖሪ (ዲማ ቶኖሪ) ዛሬን በህይወት ቢኖር ስንት ነገር ይነግራችሁ ነበር...መቼም አታምኑም:: እነሱ ከዚሁ ምስኪን ህዝብ ላይ በወሰዱት በቅሎዎች ጠላውን እየጠጡ ከብቶቹን(ሰዎቹን) ይነዳሉ:: እዚህ ላይ ዛሬም ሆነ ነገ በስራቱ እንጂ ባማራው ህዝብ ላይ ጥላቻ እንደሌለኝና እንደማይኖረኝ ተረዱልኝ:: ያንን ስርአት እያሞጋገሱ አሁን ያለውን የሚኮንኑትን ስሰማ ስለሚያናድደኝ ብቻ ነው ያልኩትን ያልኩኝ::
“እስቲ እግዚአብሄር ያድርገውና ኢህአዴግ ይወገድና አንድ ዴሞክራት መሪ ወይንም ፓርቲ ይምጣ
በመላው ሃገሪቱ ያለውን ወጣት ኃይል ወደ አንድ ብሄራዊ የቋንቋ ትምህርት ፕሮግራም ለመመለስ እጅግ ከፍተኛ የቤት ስራ እንደሚሆን ልንጠራጠር አይገባንም::
በየብሄር ብሄረሰቡ ያለው በዕድሜ ትንሹ ትውልድ ወደኮሌጆች ወደዩኒቨርሲቲዎች ገብቶ ተምሮ ደረጃውን ጠብቆ ሊወጣ ሌላ የአንድ ትውልድ ጊዜ ይጠይቃል:;”
በናንተ አስተሳሰብ ዴሞክራት ማለት በፈጣሪ የተሰጠንን ቋንቋ እንዳንናገር እና እንዳንማርበት ባህላችንን እንዳናሳድግበት በሀይል ረግጦን አፍኖ አንድን ቋንቋ ብቻ በግድ እላያችን ጭኖ የሚገዛን መሪ ማለት ነው:: እንደ ሂሳብ ብታጣፋው ምኒልክ እና ሀይለስላሴ ማለት ነዋ ደርግ እንኳን ቢያንስ መሰረተ ትምህርትን በአፋን ኦሮሞ ፈቅዷል:: ይህ ሀሳብ ከማከብረው አደቆርሳ መምጣቱ ደግሞ በጣም ገርሞኛል:: እስካሁን የተማሩትን ሁሉ ወጣት ሀይል በትኖባቸው ድራሹን ለማጥፋት ያቅድልኛል:: ይህንን ሀሳብ ባብዛኛዎቻችሁ ልብ ውስጥ ስላየሁ ነው ቤቱ የቀፈፈኝ:: አንድ ነገር ያልተረዳችሁ ከእንግዲህ በግድ አፋን ኦሮሞን ማጥፋት እንደማይቻል ነው:: በግድ አንድ ቋንቋ የምትናገር አንዲት ኢትዮጵያን መመስረት ከእንግዲህ ምኞት ብቻ ይመስለኛል:: እግዚአብሔርም ለእንደዚያ አይነት የሰባዊ መብት ረጋጭ መርዘኛ እና የከፋ ዘረኛ መንግስት እጅ አሳልፎ አይሰጠንም:: አፋን ጉጂ ያድጋል እንጂ አይሞትም:: ከስራ ገብቼ አንብቤ መተኛት ስላቃተኝ ብቻ ነው የጫርኩኝ:: ይህንን ጉዳይ ተረጋግቼ የምመለስበት ይመስለኛል:: ገና ምንም ተናግሬ አልወጣልኝም::

Jigsa
Starter
Starter
Posts: 21
Joined: 13 Feb 2013 01:27
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Jigsa » 30 Mar 2013 15:34

ወንድሜ ጎሳ
በቅድሚያ በችኮላም ቢሆን ለሰጠኸን አስተያየት በጣም አመሰግናለሁ፡፡ ብዙ መፃፍ የሚያስችል ሃሳብ ቢሆንም ማደር የሌለበትን ብቻ በጥያቄ መልክ ላቅርብ፡፡
• አንደኛ የአደቆርሳ ሃሳብና ያንተ የተቃውሞ አስተያየት የትጋ እንደተገናኘ አልገባኝመና…..
• ሁለተኛ የአፋን ኦሮሞን ቋንቋ እየተጠቀሙስ ዴሞክራሲን ማከበርና ማስከበር አይቻልም እንዴ፤ ደግሞስ ዛሬ በአፋን ኦሮሞ ስልተናገርንና ስለተማርን ዴሞክራሲያዊ መብታችን በቃ ተከበረ ማለት ነው? የአንድ ብሔረሰብ የመብቱ መጨረሻስ በቋንቋው መጠቀም መቻሉ ብቻ ነው ?ለኔ ሃሳብህ ሁሉ ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ሆነብኝ እኮ!!!
• ምናልባት በሀገር ውስጥ ካለህ ላውቅም እንጂ የኦሮሞ መብት ዛሬም ከድሮው ባላነሰ መልኩ አፈር ድሜ እየበላ ነው!! ለኔ በቋንቋ እየተጠቀማችሁ ነው መባላችን ከሽፋን የዘለለ አይደለም… በቋንቋ መጠቀማችን ፋይዳ የለውም ማለቴ ግን አይደለም፡፡ በፍጹም ! ዴሞክራሲ ከዚህ በጣም ያለፈ ነው ማለቴ እንጂ!!!
ቸር ይግጠመን፡፡

ጎሳ
ጀማሪ Starter
ጀማሪ Starter
Posts: 8
Joined: 13 Mar 2013 02:51
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by ጎሳ » 31 Mar 2013 01:59

ሰላም ጂግሳ!
“አንደኛ የአደቆርሳ ሃሳብና ያንተ የተቃውሞ አስተያየት የትጋ እንደተገናኘ አልገባኝመና…..” ላልከው ምናልባት እኔ “ኮት” ያረኩት የአደቆርሳ ሀሳብ የኔ መስሎህ እንደሆነ አላውቅም እንጂ የትኛውን የአደቆርሳ ሀሳብ እንደተቃወምኩ ግልጽ ያደረኩ መሰለኝ:: ምናልባት አማርኛዬ አልገባህም ይሆናል:: ለዚያ ደግሞ አልወቀስም ተማርኩት እንጂ አፌን አልፈታሁበትም: በደሜም ውስጥ የለም:: እስቲ ድጋሚ ልሞክረው ከተረዳኽኝ::
“በመላው ሃገሪቱ ያለውን ወጣት ኃይል ወደ አንድ ብሄራዊ የቋንቋ ትምህርት ፕሮግራም ለመመለስ እጅግ ከፍተኛ የቤት ስራ እንደሚሆን ልንጠራጠር አይገባንም::”
እንግዲህ በጣም የምቃወመው ይህንን ሀሳቡን ነው:: ትልቁ እና ከፍተኛ የቤት ስራው አሁን ያለውን በራስ ቋንቋ የሚሰጠውን ትምህርት ወደ ‘አንድ ብሄራዊ የቋንቋ ፕሮግራም’ መመለስን ነው የምቃወመው:: የቤት ስራው አፋን ኦሮሞን የመሰለ በብዙ ሚልየን ህዝብ የሚነገር ቋንቋ ለዘመናት ተቀብሮ ከነበረበት እያንሰራራበት ባለበት ባሁኑ ወቅት መልሶ ወደነበረበት መቃብር ማውረዱ መሆኑ ነው የሚያንገበግበኝ:: እንዴ...የኦሮሞ ከመቶ ሀምሳ አመት በፊት አማርኛን ሰምቶ የማያውቅ ህዝብ ነው:: በራሱ ባህል እና ፖለቲካዊ አስተዳደር (ገዳ) የሚተዳደር ህዝብ ነበር:: በማንነቱ በባህሉ እና በቋንቋው ላይ ዘመቻ ተከፍቶበት እንዳልነበረ የተደረገው የዛሬ ሶስት ሺህ አመት አይደለም:: እጅግ የቅርብ ታሪክ ነው:: ምናልባትም ከ 150 አመታት ወዲህ እንጂ:: ቋንቋውን እና ባህሉን ለመተው ወዶ የገባበት ስምምነት የለም አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ተጨፍጭፎ እና ተገዶ እንጂ:: ረዥም መጽሀፍ አንብብ አልልህም:: እስቲ የተባበሩት መንግስታት አውጥቶ የነበረውን ሰነድ ከሁለት ገጽ የማታልፈውን ስለ ኦሮሞ ታሪክ ክሮኖሎጂ ከፈለክ አንብበው:: http://www.unhcr.org/refworld/country,, ... 71c,0.html
በዚያ ሰነድ ውስጥ
"1855 – 1908 Successive Ethiopian emperors from the Amhara and Tigre groups expanded the influence of their own peoples by securing territories occupied by other ethnic groups. Since the mid-1800s, the emperor's army had erected ketemas, garrison towns, to rule Oromo and Somali areas. Political authorities imposed the Amhara-Christian culture upon those residing in ketemas in the southern periphery and extracted resources from them. " እና ያኔ በግድ የተጫነብን ቋንቋ እና ባህል ለዘላለሙ ይቀጥል የሚል አስተሳሰብ ዛሬም መኖሩ ነው የሚገርመኝ:: እዚህ ላይ ድሮ እንደዚህ ተበድለናል ሳንፈልግ ተገዝተናል እና አሁን ተገንጥለን ነጻ እንውጣ የሚል ሀሳብ የለኝም:: እነኚያ ነገስታት ለኔ አስበው ባያደርጉትም በግድ የተጫነብን ቋንቋ አስፈላጊነቱ ከአፋን ኦሮሞ በላይ ነውና በዚሁ እንዘልቃለንም አልልም:: ነገር ግን ያለፈው ታሪክ አልፏል እና ማንንም ተጠያቂ ሳናደርግ የሆነውን ሁሉ ወደ ጎን ትተን ባህላችንን እና ቋንቋችንን ከተቀበረበት አንሰራርተን ከሌላውም ህዝብ ጋር ልዩነታችንን ይዘን በግዴታ ሳይሆን በፍቅር አንድነት መስርተን እንዝለቅ የሚል ሀሳቤ በቅርቡ የሚለወጥ አይመስለኝም:: ስለዚህ ልጆቻችን በቋንቋቸው እንዳይማሩ ለማድረግ ትልቅ የቤት ስራ ይዞ የሚንቀሳቀስ እና በዴሞክራሲ ስም የቅኝ ግዛቱን ለማስፋፋት የሚጥር ሰው መቼም ቢሆን ለመብቴ ይከራከርልኛል ብዬ አላምንም::
“ሁለተኛ የአፋን ኦሮሞን ቋንቋ እየተጠቀሙስ ዴሞክራሲን ማከበርና ማስከበር አይቻልም እንዴ፤ ደግሞስ ዛሬ በአፋን ኦሮሞ ስልተናገርንና ስለተማርን ዴሞክራሲያዊ መብታችን በቃ ተከበረ ማለት ነው? የአንድ ብሔረሰብ የመብቱ መጨረሻስ በቋንቋው መጠቀም መቻሉ ብቻ ነው ?ለኔ ሃሳብህ ሁሉ ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ሆነብኝ እኮ!!!"
ላልከው ሊሆንብህ ይችላል:: ነገር ግን በገዛ አፌ እንዳልማር ያገደኝ ሰው አፌን ለጉሞ የቱን የዴሞክራሲ መብቴን ሊያስከብርልኝ እንደሆነ ግልጽ ይደረግልኝ:: አሁን እኮ አይደለም ዴምክራሲያዊ... መሰረታዊ የሆነውን የሰውን ልጅ ሰብአዊ መብቴን እየነፈከኝ ስለሆነ ባፌ መማር እና አስተያየቴን በጽሁፍም ሆነ በንግግር እንዳላቀርብ የምታግደኝ ከሆነ ስለ ዴሞክራሲያዊ መብት እንኳ ማውራት አንችልም:: የሚቀድመው ሰብአዊ መብት አይመስልህም? የሚገርምህ አይደል በብዙ ሚልየን የሚቆጠር የኦሮሞ ህዝብ ይቅርና ማይኖሪቲ የሆነ ብሄር እራሱ ይህንን ሰብአዊ መብት ሊነፈግ አይገባም..የሰው ልጅ በሙሉ ማለቴ ነው:: የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጉባኤ
Declaration on the Rights of Persons Belonging to National or Ethnic Religious and Linguistic Minorities በሚል አርትክል 2 ስር
“ Persons belonging to national or ethnic, religious and linguistic minorities (hereinafter referred to as persons belonging to minorities) have the right to enjoy their own culture, to profess and practise their own religion, and to use their own language, in private and in public, freely and without interference or any form of discrimination. Minorities should not have to hide away their cultures, languages and religions.” http://www.ohchr.org/Documents/Issues/M ... nglish.pdf
እንግዲህ መሰረታዊ መብቴን እየነፈግከኝ የዴሞክራሲ መብቴን እጠብቅልሀለሁ ብትለኝ ቱ! ትዝብት ነው :lol:
ሌላው ደግሞ አሁን አሁን ብዙ ቦታ የሚታየው አንድ ፈሊጥ አለ “የኦሮሞ መብት ዛሬም ከድሮው ባላነሰ መልኩ አፈር ድሜ እየበላ ነው!! " አይነት ነገር:: እስቲ ባደግክበት በአዶላ ከተማ ኦሮሞ በመሆኑ ብቻ ያለምንም ፍርድ በእስር ቤት የሚሟቅቅ የፖለቲካ እስረኛ አንድ ሶስቱን ጥራልኝ:: አገር ውስጥም ባልሆን ወዳገር ቤት የተወሰነ ጊዜ ተመላልሻለሁ:: በእርግጥ ክ/መ ከተማ አልቆየሁም:: ቦሬ ላይ ግን በበፊቱ ምርጫ የኢህአዴግ ተቃዋሚ ሆነው አሸንፈው ኦሮሚያ ፓርላማ ገብተው በኋላም ተሸንፈው ወደ ወረዳው የተመለሱት እነ ቦረማ ጀኖ እና ሀይሌ ሀሮ ቡቁዩ እንደልባቸው ያሻቸውን ተናግረው ቦሬ ውስጥ ደረታቸውን ነፍተው ሲሄዱ አይተን በመደሰታችን ሻይ ተገባብዘናል:: በግልጽ መንገድ ላይ ከባለስልጣናት ጋር ሲከራከሩ ታያቸዋለህ:: አንድም የታሰረ የፖለቲካ እስረኛ አላየሁም አልሰማሁም:: በእርግጥ ያኔ ኢህአዴግ እንደገባና ኦነግ ቻርተሩን ልቅቆ ለመውጣት በተገደደበት ወቅት ማን ኦነግ ይሁን ማን ደግሞ ኦህዴድ በግልጽ ስለማይታወቅ ከፍርሀት አንጻር በብዙ የኦሮሞ (ጉጂ) ልጆች ላይ ድብደባ ሁሉ ሳይቀር ደርሷል:: በወቅቱ እንደዚያ ሲያስደርጉ የነበሩት እየፖለቲካ ቢሮ ተወካይ የነበረው አብድርቃድር በሚባል የሌላ ዞን ሰው እና አጨብጫቢዎቹ ነበር:: በተለይ አንድ ወልዴ የሚባል ቀይ ጃኬት እና ኮፊያ ይለብስ የነበረው የክብረመንግስት ነዋሪ በጉጂ ልጆች ላይ በሀሰት በመመስከር እና በመጠቆም ያሳስራቸው እንደነበር በደንብ አስታውሳለሁ:: እነ መሀመድ ጅሎ ታጥቀው የነበሩትን መሳሪያ ዘራፊዎች አውቶቡስ አስቁመው ስለዘረፏቸው ታስረዋል: ከስራም ተባርረዋል:: ያ የግርግሩ ጊዜ አልፎ ባለፈው ኢትዮጵያ ሲሄድ መሀመድንም አግኝቼው እንደውም በኦሮሚያ ደረጃ የመንገዶች ጉዳይ ባለስልጣን ሆኖ እየሰራ መሆኑን ነው የነገረኝ:: እና ከምንጊዜውም በላይ የኦሮሞ ህዝብ እየተደበደበ እየታሰረ ነው የምትሉት ነገር የአዞ ዕንባ እንዳይሆን ነው የምጠራጠረው:: የኦሮሞ ተወላጅ ሁሌም ፍትሀዊ ፍርድ ያገኛል ማለቴ አይደለም:: ነገር ግን በጀርባቸው ሌላ ነገር ተሸክመው ስለ ኦሮሞ ህዝብ መብት ከሚያለቃቅሱት የሀይል አንድነት ናፋቂዎች አሁን ያለው ስርአት በጣም የተሻለ እንደሆነ አምናለሁ:: ባንድ ጀምበር ሙሉ ዴሞክራሲ አይመጣም:: ያለው ጅምር ግን የሚበረታታ ነው የሚመስለኝ::ሁሌም ኢህአዴግን ባሰብኩ ቁጥር ደስ የምለኝ ነገር ምን እንደሆን ታውቃለህ? አፋን ኦሮሞን እና በራስ ህዝብ መተዳደርን በተመለከተ እንደቀልድ ሊዳፈን የማይችል እሳት ቆስቁሷል:: ከእድሜያችንም አንጻር እኛ ነገ እናልፋለን:: ልጆቻችን ግን እሳቱን ያባብሱታል እንጂ እንዲጠፋአይፈቅዱም የሚል ትልቅ ተስፋ! እሱ ነው የሚያስደስተኝ:: ዛሬ በልዩነታችን ተከባብረን እና የማንነታችንን መለያ ይዘን ተዋደን ባንድነት ከመኖር ውጭ በሀይል ቅኝ ግዛት የማያምነው ጎሳ ነገም ከዚህ ውጪ አያምንም::

አደቆርሳ
Jogger
Jogger
Posts: 45
Joined: 13 Jan 2012 04:13
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አደቆርሳ » 31 Mar 2013 07:19

ወንድሜ ጎስሽክም እንደምን አለህ ?
ምናልባት ዘንድሮ ሰባትና ስምንት ዓመታትን ገደማ አብረን ስንኖር እንዲህ ያለ አለመረዳት ሲገጥመኝ ዛሬ የመጀመሪያዬ ነው::
(በናንተ አስተሳሰብ ዴሞክራት ማለት በፈጣሪ የተሰጠንን ቋንቋ እንዳንናገር እና እንዳንማርበት ባህላችንን እንዳናሳድግበት በሀይል ረግጦን አፍኖ አንድን ቋንቋ ብቻ በግድ እላያችን ጭኖ የሚገዛን መሪ ማለት ነው)
ይቺን ስትናገር የወያኔ ፖለቲካ ምን ያህል ዓላማውን አሳክቷል አልኩኝ !
ወንድሜ ጎስሽክም ኢህአዴግ አሁን በሃገራችን ያለው የዘር ፖለቲካ ሂደት በህዝቡ ውስጥ እንዲሰርጽ የሚፈልገው የፖለቲካዊ ቅርጽ ይሄው አንተ ያንጸባረቅከው ሁኔታ ነው::
ኢትዮጵያም እንዲህ እንድትሆን ነው የሚፈልጉት አንተም አረጋገጥክላቸው::
አየህ ! አንተ ያለኸው ወይንም የምትኖረው በሰለጠነና የኑሮ ደረጃው ከፍተኛ በሆነ ሃገር ውስጥ ነው
ለመሆኑ አሁን አንተ ያለህበት ሃገር የብዙ ብሄሮች መኖሪያ መሆኑን አታውቅ ይሆን ? ነገር ግን የስራና ብሄራዊ ቋንቋቸው ሥንት ነው ? የዚህን ጥያቄ ሳትመልስልኝ እንዳትቀር አደራ እልሃለሁ ::
በቋንቋ መናገርን የሚከለክል ወይንም የሚቃረን ጽሁፍ እኔም ሆንኩ ጅግሳ በየትኛውም ቦታ አልጻፍንም ልጽፍም አልችልም እንደው የተናደድክ ስለምትመስል የንዴት አነጋገር እንደሆነ እረዳለሁ ነገር ግን አትናደድ በነጻነት መናገር የሚቻለውና መተማመን የሚቻለው በፍቅር መነጋገር ስንችል ብቻ ነውና ::በመጨረሻ ስለተናከርከው
(((((በግድ አንድ ቋንቋ የምትናገር አንዲት ኢትዮጵያን መመስረት ከእንግዲህ ምኞት ብቻ ይመስለኛል:: እግዚአብሔርም ለእንደዚያ አይነት የሰባዊ መብት ረጋጭ መርዘኛ እና የከፋ ዘረኛ መንግስት እጅ አሳልፎ አይሰጠንም:: አፋን ጉጂ ያድጋል እንጂ አይሞትም:: ከስራ ገብቼ አንብቤ መተኛት ስላቃተኝ ብቻ ነው የጫርኩኝ:: ይህንን ጉዳይ ተረጋግቼ የምመለስበት ይመስለኛል:: ገና ምንም ተናግሬ አልወጣልኝም))))))
በጣም አሳቅከኝ
ይልቁንም ረጋ ብለህ እንደገና አንብበህ ለመረዳት ሞክር ከዚህ የበለጠውን ጅግሳ በሚገባ ስለመለሰው እኔ ከዛ በላይ የምለውም አይኖረኝም::
ውድ ጎስሽክም መጽሃፍ ቅዱስንም ቢሆን ለመረዳት እንደምትፈልግ ካልተረዳኸው ወይንም እንደአጻጻፉ መንፈስ ካልተረዳኸው በቀር እንዳሻህ መተርጎምም ሆነ መረዳት ይቻላል ::
በነገራችን ላይ እኔም ጥሩ የኦሮሞ ልጅ መሆኔን አትዘንጋ !
አንተ የምትኖርበትን ጨምሮ በአለም ያሉ ትልልቅና እጅግ የበለጸጉ ሃገሮች አሁን ያሉበት ደረጃ ሲደርሱ በታላቅ የብሄሮች መቻቻል ውስጥ አልፈው አሁን ምንም አይነት የዘር የብሄር የቋንቋ ወዘተ ችግር እንደሌለባቸው ሁሉ አደቆርሳ እንዲህ ያለች ኢትዮጵያን ይናፍቃል ! ከዚህ ውጭ የሆነ አስተያየትም ሆነ ምኞት የለኝም ::
ሌላው ጉበኞችን ስንሰማና ስናይ ነው ያደግነው ጉቦ ለኛ አዲስ አይደለም ስለዚህ ጉበኝነት ምን ያስደንቃል የሚል ሃሳብ ሰንዝረሃል::
ታዲያ ስለምን የቀደመውን ስርዓት መቃወም ይገባሃል ? ስለምን የመልካም አስተዳደርን ጉድለት ስንቃወም ኖርን ? ስለምን የሰው በሰው መበዝበዝን እና መበደልን ለማስወገድ ትግል አስፈለገ ?
ስለምንስ ዴሞክራሲ እና የፍትህ ስርዓት ናፋቂዎች ሆንን ? ወዘተ የመላው ኢትዮጵያ ልባዊ ትግል ይሄንን የሰው በሰውና የዘር ልዩነት ያለበት ጅላጅል ስርዓት ለማስቀረትና ማንም ሰው በዘሩም ሆነ በመልኩ በጎሳውም ሆነ በትውልዱ ሳይለይ በሃገሩ ውስጥ በፍጹም እኩልነት ሰርቶና በልጽጎ ለማየት እንዲቻል ነው::
የራሱን ቤት የሚሰርቅ ሌባ ቢኖር አያስደንቅም ማለትህ ጎሳን ምንነካው ከማለት በስተቀር ብዙ ማለት አላስፈለገኝም::
ስለንጉሱ የተናገርከው ከምን ተነስተህ እንደሆን ባይገባኝም ፋብሪካ ሊገነቡ አስበው እንደበረ ሊካድ የማይቻል ታሪክ ነውና ደግሜ ልናገረው እችላለሁ::
ሌላው ከአዶላ ኬላ ኮሶ እያጠጡ ያሳልፉ ነበር ላልከው ኮሶ ለማጠጣት ዘር ይመረጥበት ግን ከቶም አልነበረም :ይልቁንም ከሞቀ ኑሯቸው ላይ እየታደኑና እየታነቁ አዶላ ተግዘው ተጥለው ዘመናቸውን በሙሉ ቦሴቶ ለቦሴቶ እንዲንከራተቱና ስንቶቹም በናዳ ተቀብረው እንዲቀሩ የተደረጉት የመላው ኢትዮጵያ ዜጎች እንጂ የአንድ ጎሳና ብሄር ተወላጆች አይደሉም::
እስካሁን ድረስ በክብረመንግስትና አካባቢው የመጨረሻውን የድህነት ኑሮ የሚኖሩትና በልመና ኑሯቸውን ሊገፉ ግድ የሆነባቸውን አብዛኞቹን መጥቀስም ይቻላል::
ባጭሩ የአዶላን ከርሰ ምድር ያሰሰው ከአዶላ ሳይሆን ከመላው ሃገሪቱ የመጣ ኢትዮጵያዊ ነው ::
ስለ አዶላና ማህበረሰቡ ከኔ በላይ ማንም ሊናገርልኝ አይችልም እኔ ከዚሁ ማህበረሰብ የተፈጠርኩ ነኝና ችግሩም እድገቱም ይመለከተኛል::
ደግመህ የጻፍከው ከምንነጋገርበት ርዕሰጉዳይ ወጣ ያለና ፖለቲካዊ ይዘት ስላለው ወደዛ መግባት አስፈላጊ አይደለም::
ስለ ኦሮሞ ህዝብና ነጻነት ጉዳይ በተለይም ስለራሳችን ስለጉጂ ከአምስትና ስድስት አመታት በፊት
የጻፍነውን ፈለግ ፈለግ አድርገህ ተመልከት::
አንተ እንደምትለው ወይንም እኛን አድርገህ ለመግለጽ እንደ ሞከርከው ዓይነት ሰዎች አይደለንም ማንነቴን ጠንቅቄ የማውቅና ነገር ግን የዘር ፖለቲካን በጥብቅ የምቃወም ዘሬ የማያመጻድቀኝ የማያሳንሰኝም ኢትዮጵያዊ ነኝ ::
ስለዚህ ወንድሜ ሆይ ስለአካባቢያችን ያነሳነው እንደሂስና ግለሂስ የምታይና የሚታለፍ እንጂ እንደዚህ አንተን እንቅልፍ ሊነሳህ ወደሚችል ፖለቲካ ያዘነበለ ሃሳብ የሌለን መሆኑን ተረድተህ እንድትተው በወንድማዊ ፍቅር አሳስብሃለሁ::
ይህንን መሰሉን ስሜት መፍጠር ትልቁ የኢህአዴግ አላማና ግብ ስለሆነ እጃችንን አንስጥ::
አክባሪህ አደቆርሳ ዘሃገረ አዶላ

ኦዶ ሻኪሶ
Posts: 1
Joined: 31 Mar 2013 11:17
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by ኦዶ ሻኪሶ » 31 Mar 2013 13:05

መጣና ባመቱ እንደምን ሰነበቱ
ክቡር ራስብሩ
ሞፊቲኮ
አንፈራራችን
አደቆርሳ
ባለሱቅ
ጎሳ
እንግዳው ጂግሳ
ስማቹን ያልጠቀስኩት ካላችህ እንደምናላችሁ ?
ምዝገባችንን አጠናቀን መጥተናል
እንኳን ደህና ቆያችሁን
ባለሱቅም ብዙ አልቀደምከኝም ግንናማርኛ ጠፋብኝ ብለህ ፎገርከን እንጂ
ለመመዝገብ ብዙ ሞክሬ አቅቶኝ ነበር ዛሬ ለመምጣት ተጋድሎ ያረኩት በነጎሳ ዲያሎግ ላይ ቶሎ መትሳፍ ፈልጌ ነው ::
አደቆርሳና ጂግሳ የምትወያዩት ብውነት ላይ ነው
ጎሳ በደንብ አልተረዳህላቸውም ለምን እንደዛ አልክ ባልልም በተለይ አደኦቆርሳ ያነሳው አሳብ በቋንቋ መናገር አይገባም የሚል አደለም ዝም ብለን ብናስበውም ሊል አይችልም:
ስለጉጂ ባህልና ቋአንቋአ በጣም ብዙ ብዙ ነገር ያስተማረን አደቆርሳ ብቻ ነው የትም ቦታ የማይገኝ ነገር ነው የሚጽፈውና የምናነበው
አንተንም እሱንም በደንብ እናቃችሁለን እንደዚህ አይነት ነገር እዚቤት ሊነገር በፍትሱም አይቻልም
እንደተረዳሁት ዋናው ጉዳይ አደቆርሳ የኢትዮ<ጵያ ቋአንቋአ አንድ ቢሆን እንደሚመኝ ተናገረ እንጂ ኦሮምኛ ይሁን አማርኛ ይሁም ምንም ያለው ነገር የለም
ከዚ በፊት የተናገረው ትዝ ስላለኝ ነው ዛሬ ለመትሳፍ የፈለኩት
ጎሳ ይሄን ጠይቀከው ቢሆን እንደዛ ባልተናገርክ ነበር
ስለዚ ለሌላ ወሬ መንገድ እንዳይፈጠር ይሄንን ነገር መተው አለባችህ
ማንም ሃገሩንና ወገኑን የሚጠላ የለም ስለዚ ካልገባን እንኩዋን ለምን እንደዚ አልክ ብሎ መጠየቅ መረዳት ነውንጂ ሌላ ነገር መነጋገር ለንትርክ መንገድ መክፈት ይሆናል:
ጂግሳም ረጋ ያለና ቀለም የገባው ሰው እንደሆነ ከጽሁፎቹ መረዳት ይቻላል ስለዚህ ሁላችንም መግባባት የምንችል እስከሆንን ድረስ በፍቅር ከመነጋገር ያለፈ ማረግ የለብንም:
ልምዳችንም አይደለም::
ጎሳ ተወዳጆችትስሁፎቸሀን እንድናነብ እንፈልጋለን ስለዚ ይሄንን የማያልቅ ፖለቲካ መትሳፍ ማቆም አለብን
አደቆርሳም ጂግሳም ኬንጊህ ይሄንን ጉዳይ እንዳታነሱት አደራ አላችሁዋለሁ::
ሶስታችሁንም በቅድሚያ አመሰግናለሁ
የአዶላ ቤት የፍቅር ቤት ነው ሁላችንም ወንድማማቾች ነን
ኦዶ ከአረንፈማ

ጎሳ
ጀማሪ Starter
ጀማሪ Starter
Posts: 8
Joined: 13 Mar 2013 02:51
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by ጎሳ » 31 Mar 2013 20:36

ሰላም ኦዶ ኪያ::
"የያዘውን (ያለውን) የወረወረ ፈሪ አይባልም " ይባል የለ? እንደምንም ብለህ ገብተህ የወረወርካትን በመወርወርህ ልትመሰገን ይገባል እንጂ አንወቅስህም::
“ጎሳ በደንብ አልተረዳህላቸውም ለምን እንደዛ አልክ ባልልም በተለይ አደኦቆርሳ ያነሳው አሳብ በቋንቋ መናገር አይገባም የሚል አደለም ዝም ብለን ብናስበውም ሊል አይችልም: ስለጉጂ ባህልና ቋአንቋአ በጣም ብዙ ብዙ ነገር ያስተማረን አደቆርሳ ብቻ ነው የትም ቦታ የማይገኝ ነገር ነው የሚጽፈውና የምናነበው አንተንም እሱንም በደንብ እናቃችሁለን እንደዚህ አይነት ነገር እዚቤት ሊነገር በፍትሱም አይቻልም እንደተረዳሁት ዋናው ጉዳይ አደቆርሳ የኢትዮ<ጵያ ቋአንቋአ አንድ ቢሆን እንደሚመኝ ተናገረ እንጂ ኦሮምኛ ይሁን አማርኛ ይሁም ምንም ያለው ነገር የለም ከዚ በፊት የተናገረው ትዝ ስላለኝ ነው ዛሬ ለመትሳፍ የፈለኩት ጎሳ ይሄን ጠይቀከው ቢሆን እንደዛ ባልተናገርክ ነበር”
ስለ ችኮላዬ ይቅርታ መጠየቅ ካስፈለገ እጠይቃለሁ:: ግን ግን "የትኛው ቋንቋ ብሔራዊ ቋንቋ እንዲሆን ትፈልጋለህ? " ብለህ አደቆርሳን ብትጠይቀው "አፋን ኦሮሞ " ይልህ ነበር ነው የምትለኝ? ይህ እንግዲህ ትንሽ አስፈግጎኛል:: እሱም እራሱ ያንን ሀሳብ አላንጸባረቀም በዘር እና በቋንቋ አላምንም አለ እንጂ:: እኔ ደግሞ አንዱን ቋንቋ እያሳደግን ሌላውን እናጥፋ የምል አይነት ሰው አይደለሁም:: እንደዚያም ቢሆን አፋን ኦሮሞ ባህርዳር ወይም ጎንደር ተወስዶ በማይናገሩት ሰዎች ላይ በግድ መጫን አለበት ብዬ አላምንም:: እስቲ አስበው....አፋን ኦሮሞን ብሄራዊ ቋንቋ ለማድረግ ደብረማርቆሶች ስብሰባ ሲቀመጡ....ሰማይ ምድሩ አይገለባበጥም ብለህ ነው? ያኔ እኮ ነው...ሰማሁ እንጂ በእርግጥ በቦታው አልነበርኩም....1986 እ.ኢ.አ... ቦታው ጉደር ነው...ከአምቦ 12 ኪሜ ወደ ምዕራብ ...ታቦት ወጥቶ ህዝበ ክርስቲያኑ አጅቦት ሊያስገባው በመዝሙርም በምንም አካባቢውን ሞቅ ደመቅ አድርጎታል:: በድንገት ታቦቱ ይቆማል:: ታቦቱ ቢጠበቅ ቢጠበቅ አይንቀሳቀስም:: ምንድነው ነገሩ የምን ቁጣ ነው ታቦቱ የማይንቀሳቀሰው ሲባል "ቁቤ ካልተረገመ አልገባም ብሏል " ተባለልህ ይባላል:: በመጨረሻም እንዴት እንደገባ አልነግራችሁም:: በወቅቱ ትልቅ ኢሹ ነበር:: ሃይማኖትን መንካት ፈልጌ ሳይሆን ሌላውን ቋንቋ ለማጥፋት ሰዎች የማይሞክሩት መንገድ የለም ለማለት ብቻ እንጂ::ግራ ቀኙን በኦሮሞ ህዝብ ተከቦ እንደዚያ ሊል የደፈረ የዲማው ገብርኤል ቄስ እሽ ብሎ አፋን ኦሮሞን እንደ ብሔራዊ ቋንቋ ይቀበላል ብለህ ካሰብክ የዋህ ነህ:: እና ወንድሜ ኦዶ እኔን ልታሳምነኝ እና ጥፋተኛ ልታደርገኝ ማንንም ሰው የማያሳምነውን ሀሳብ ባታነሳው ጥሩ ነበር:: ግን ሰው ሀሳቡን በነጻነት የመግለጽ መብቱን ቅንጣት ያህል መነፈግ ስለሌለበት ያልከውን ሁሉ መብትህ እንደሆነ ወስጄልሃለሁ::
ሰላም አደቆርሳ!
ከዚህ በፊት የጻፍኩት አንድ ብሔራዊ ቋንቋ ብቻ ያልከውን በዝርዝር ሀሳብ የሰጠሁበት እንጂ አዲስ ያመጣሁት አርዕስት አለመሆኑ ግልጽ ነው:: “በመላው ሃገሪቱ ያለውን ወጣት ኃይል ወደ አንድ ብሄራዊ የቋንቋ ትምህርት ፕሮግራም ለመመለስ እጅግ ከፍተኛ የቤት ስራ እንደሚሆን ልንጠራጠር አይገባንም::” ያልከውን:: ያለመወያየት መብትህን ግን አከብርልሀለሁ::
“ሌላው ጉበኞችን ስንሰማና ስናይ ነው ያደግነው ጉቦ ለኛ አዲስ አይደለም ስለዚህ ጉበኝነት ምን ያስደንቃል የሚል ሃሳብ ሰንዝረሃል:: ታዲያ ስለምን የቀደመውን ስርዓት መቃወም ይገባሃል ? ስለምን የመልካም አስተዳደርን ጉድለት ስንቃወም ኖርን ? ስለምን የሰው በሰው መበዝበዝን እና መበደልን ለማስወገድ ትግል አስፈለገ ? ስለምንስ ዴሞክራሲ እና የፍትህ ስርዓት ናፋቂዎች ሆንን ? ወዘተ የመላው ኢትዮጵያ ልባዊ ትግል ይሄንን የሰው በሰውና የዘር ልዩነት ያለበት ጅላጅል ስርዓት ለማስቀረትና ማንም ሰው በዘሩም ሆነ በመልኩ በጎሳውም ሆነ በትውልዱ ሳይለይ በሃገሩ ውስጥ በፍጹም እኩልነት ሰርቶና በልጽጎ ለማየት እንዲቻል ነው:: የራሱን ቤት የሚሰርቅ ሌባ ቢኖር አያስደንቅም ማለትህ ጎሳን ምንነካው ከማለት በስተቀር ብዙ ማለት አላስፈለገኝም::”
እኔ ያልኩት የሙስና ነገር ድሮም የነበረ እንጂ አንተ ከዚህ በታች በምጠቅስልህ በራስህ ጽሁፍ ለማስቀመጥ እንደሞከርከው ህዝቡ በራሱ ህዝብ መተዳደር ስለጀመረ (የአዶላውን ከወሰድን ባብዛኛው ባካባቢው ልጆች ማለቴ ነው) እየተባባሰ የመጣ ጉዳይ አይደለም:: እስቲ መለስ ብለህ አንብበው:: መጀመሪያ ያንተን እጠቅስልሀለሁ:: ከዚያም እኔ ያልኩትን እጠቅሳለሁ::
“ኅዝባችን ያልተማረ እንደመሆኑ መጠን የራሱን ችግር በራሱ ሰዎች ስንነግረው ይገባዋል .... ብለው አምነውበት ነው ያደረጉት :ችግራችንን ችግራችሁ ነው ብለው ሊያስተምሩን ማለትኮ ነው አይገርምህም ?
ባለፈው በቦታ ጉዳይ የተፈጠረ ነገር ላጫውትህ
ቦታው የተገበረበት ካርኒዎች ተሰባስበው ቀሪው እንዲፈል ከተማ አስተዳደር ጉዳዩን በማሳወቅ ቀጠሮ ተሰጠ::
በቀጠሮው ቀን የቆዩና የተከፈለባቸው ካርኒዎች ከፋይሉ ውስጥ ጠፉ እነዚህ ካርኒዎች ግን በመጀመሪያው ቀን ነበሩ ::
የት ሄዱ ማን ወሰዳቸው አይታወቅም : ከዚያም ዋናውን በከፋይ እጅ ያለው ካርኒ ቢቀርብ አንቀበልም እኛ ጋ ያለው ኮፒ ወይንም ቀሪ ካርኒ እስኪገኝ ጠብቁ አሉ :: ቢጠበቅ ቢጠበቅ ምንም የለም በኋላ እኛኮ ዋናው በጃችን አለ ማህተሙም ሰፍሮበታል ተብሎ ሲጠየቁ አይ የናንተ ኦሪጅናል መሆኑን ስለማናውቅ ከዋናው ኦሮሚያ ፖሊስ ሄዳችሁ ኦሪጅናል መሆኑን አረጋግጣችሁ አምጡ የሚል መልስ ሰጡ::እግዚአብሄር ያሳይህ የትሄደህ የ40 እና የ50 ዓመት ካርኒ አረጋግጡልኝ ብለህ መረጃ ልታመጣ እንደምትችል ? በኋላ ነገሩ ሲገለጽ የከጀሉት ሲሰጣቸው ፋይሎቹ ከየተደበቁበት ብቅ ብቅ አሉ እልሃለሁ:: እነዚህ ሰዎች እንደዚህ እያደረጉ ህዝቡን አላነቃንቅ እንደሚሉት ማዕከላዊው መንግሥት በሚገባ ያውቃል : ወፋፍራም መረጃዎችም አሉት እንደገናም አንተ ከላይ እንደተናገርከው
ፍጹም ተመሳሳይ ሰዎች አካባቢያቸውን ቢያስተዳድሩ ፖለቲካው ወዴት እንደሚዞር ማወቅ ከባድ አይደለም እኔና አንተኮ ከተማችንን ብናስተዳድራት እንግባባለን በትክክልም ልናራምዳት እንችላለን ህዝባችንን ልንጠቅመውም እንችላለን ሌላም ሌላም ....”
“ ጉቦ መስጠትም ሆነ መቀበል እንኳን በምድራዊ ህግ ወንጌሉም የሚፈቅድ አይመስለኝም:: ቁርአንም ላይፈቅድ ይችላል :: እዚህ ላይ ባለሱቅ የሚለን ካለ ቅቅቅቅ ያም ሆኖ መጠኑና አወሳሰዱ ይለያይ እንጂ በየትኛውም ሀገር እና ደረጃ ሙስና ያለ ነው:: ዛሬ የአዶላ ወረዳ ባለስልጣናት የጀመሩት ነገር አይመስለኝም:: ከኢህአዴግ በፊት ጉቦ አልነበረም ይሆን? ስለ ክብረመንግስት ብዙ ስለማላውቅ በደንብ የማውቀውን የቦሬን ከተማ ብንወስድ ሞፊቲ የሚያውቃቸው እነ አየለ ተሰማ፣ አበራ ደርሶልኝ፣ ቦጋለ አለሙ እና ሌሎችም ቁጥር ስፍር የሌላቸው ባለስልጣናት ህዝብን ያራቆቱ እና ያስለቀሱ ጉበኞች እንደነበሩ ስንሰማ ነው ያደግነው:: ዛሬ የአከባቢው ተወላጆች የጉጂ ልጆች ስልጣን ላይ ስለተቀመጡ ያመጡት አዲስ በሽታ አይደለም::”
ከኮንተክስቴ ውጪ ሙስናን ደጋፊ አድርገኽኝ ልታቀርበኝ ስለሞከርክ ብቻ ነው የጥቅስ ጋጋታ ያበዛሁት::
ሌላው...እስከ ዛሬ ድረስ ሁለት የተለያዩ አስተሳሰቦች ያላቸው ኦሮሞዎች ብቻ ናቸው የገጠሙኝ:: ጭራሽ ከሌላ የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ምንም ሳንነካካ ሉአላዊት ኦሮሚያን መስርተን ተገንጥለን እንኑር የሚሉት የኦነግ አይነት አስተሳሰብ ያላቸው እና በፌደራሊዝም ሲስተም የራሳችንን ስቴት እራሳችን እያስተዳደርን በራሳችን ቋንቋ ተምረን ሰርተን ከሌሎቹ ጋር በሰላም እንኑር የሚሉት ናቸው እንጂ ለቋንቋዬ እና ለባህሌ ምንም ግድ ስለሌለኝ የራሴን ቋንቋ አሽቀንጥሬ ትቼ የተጫነብኝን አሜን ብዬ ተሸክሜ እዘልቃለሁ የሚል አንድም የኦሮሞ ልጅ አላጋጠመኝም:: እውነትም “ከቋንቋ እና ከነገድ ዋጅቶናል” ብለህ የመጽሀፍ ቅዱሱን ቃል አንግበህ ተነስተህም ከሆነ ያ መብትህ ነው:: ነገር ግን የብዙሀኑ የኦሮሞ ህዝብ ፍላጎት በጥቂት ሰዎች ፍላጎት ብቻ የሚገታ አይደለም: ዴሞክራሲ...የብዙሃን ድምጽ::
“አንተ የምትኖርበትን ጨምሮ በአለም ያሉ ትልልቅና እጅግ የበለጸጉ ሃገሮች አሁን ያሉበት ደረጃ ሲደርሱ በታላቅ የብሄሮች መቻቻል ውስጥ አልፈው አሁን ምንም አይነት የዘር የብሄር የቋንቋ ወዘተ ችግር እንደሌለባቸው ሁሉ አደቆርሳ እንዲህ ያለች ኢትዮጵያን ይናፍቃል ! ከዚህ ውጭ የሆነ አስተያየትም ሆነ ምኞት የለኝም ::”
እኔ ያለሁበት አገርማ ከአዶላም ከኢትዮጵያም ጋር ስለሚመሳሰል ትንሽ ላጫውትህ:: አዶላን ይመስላል ያልኩት በሌላ መልኩ አይደለም... የእንግሊዝ ወንጀለኞች ከየቦታው ተሰብሰበው የተጣሉበት ስለሆነ ነው...ልክ እንደ አዶላው "ግፋ ቢል አዶላ: አንሳ ቢል አካፋ " አይነቱ ነገር:: ሌላው እንግሊዞችም ሲገቡ ልክ እንደነምሊንክ ያገሪቷን ህዝቦች (አቦርጅኖቹን) ከምድረ ገጽ ጠራርገው ሊያጠፏቸው ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም:: እውነቱን ለመናገር አጥፍቶኧቸዋል ለማለት ይቻላል :: እንደው ምህረቱ በዝቶላቸው ነው ዛሬ ያሉት አቦርጅኖች በነብስ ተርፈው የሚኖሩት:: እንግሊዘኛው በግድ ተጭኖባቸውም ባህላቸውን አጥተው እኔ ከኢትዮጵያ መጥቼ ባገራቸው የምኖረውን ህይወት እነሱ ባገራቸው አይኖሩትም:: ባህላቸውን ቋንቋቸውን ማጣታቸው ሳያንስ የሚኖሩት የዲስክርምኔሽን ኑሮ እጅግ በጣም ያሳዝናል:: መንፈሱ ሞቶ ቆሞ ከሚሄድ ሰው ሞቶ የተገላገለው ሳይሻል አይቀርም:: እኔ ብነግርህ ላታምነኝ ስለምትችል ይህንን ሊንክ አንብበው::
UN says discrimination embedded in Australia
http://www.abc.net.au/news/2010-08-28/u ... lia/961306
እንግዲህ ABC ትልቁ የአውስትራሊያ ሚዲያ ነው:: ሌላም ልጨምርልህ
UN says Aboriginal health conditions worse than Third World
http://www.smh.com.au/national/un-says- ... z2P7XOo7Hi
እና የኦሮሞም ህዝብ ጉዳይ ይኽው ነው:: እድገት ስልጣኔው ቀርቶበት ባህል እና ቋንቋው ተጠብቆለት አይደል የሶስተኛ.... የአራተኛ አለም የድህነት ኑሮ መኖሩን ይመርጣል:: ቋንቋው እና ባህሉ ተረግጦ እናውቅልሀለን ባዮች በሚመሩት አቅጣጫ እንደፈረስ እየተጎተተ ዘመኑን ለመጨረስ የሚስማማ ሰው ከእንግዲህ አይኖርም አልልም:: ግን አብላጫው እጅግ አብላጫው እራሱን ሽጦ ማንነቱን ቀብሮ የሌላ ሰው ባንዲራ እያውለበለበ ለመኖር እንደማይፈልግ የትም የሚታይ ጉዳይ ነው:: ባጭሩ ለኦሮሞ ህዝብ ከፌደራሊዝም እና ከመገንጠል ሌላ ሶስተኛ አማራጭ አለ ብዬ አላምንም::
በመጨረሻም ለማለት የምፈልገው...አንድ ጎጃም አካባቢ ከአማርኛ ውጪ ሌላ ቋንቋ ሳይሰማና ሳይናገር ያደገ ሰው አፋን ኦሮሞን ቢቃወም ምንም አይገርመኝም:: ክብረመንግስት አካባቢ ተወልዶ ያደገ ሰው ግን ልጆች በኦሮምኛ እንዳይማሩ እና ምስኪን ገበሬዎች በሚገባቸው ቋንቋ በየሄዱበት ጉዳያቸውን እንዳያስፈጽሙ እና ባህሉን እና ቋንቋውን በሚናገሩት ባከባቢው ልጆች እንዳይገለገሉ የሚቃወሙ ሰዎች መኖራቸውን ሳይ...ምን እላለሁ "...ምን ከሩቅ አይመጣም " የሚባለው ለካ ያለ ነገር ነው ከማለት በስተቀር:: ይህ ሀሳብ ደግሞ "ኦሮሞ ነኝ " ከሚል ሰው በይፋ መንጸባረቁ....:: ስለሆነም ይህንን እያየሁ እና እየሰማሁ የዚህ ቤት አባል ሆኜ መቀጠል ስለማልፈልግ በራሴ ፍላጎት ከዚህም ሆነ ከዚያኛው ቤት እራሴን አስወግጃአለሁ:: ለክፉም ሆነ ለደግ የምትታገሉት ሁሉ መልካም የትግል ዘመን ይሁንላችሁ::

አንፈራራ
Runner
Runner
Posts: 50
Joined: 03 Jan 2012 12:51
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አንፈራራ » 01 Apr 2013 07:55

ሰላምውድወገኖች

ሰሞኑን ሲካሄድ የነበረውን ውይይት በጥሞና ስከታተለው ነበር::ጂግሳ አደቆርሳና ጎሳ ስታካሄዱት የነበረው ርእስ ተገቢና ሁሌም በኢትዮጵያውያን መካከል የሚነሳ ርእስ ነው::ይህ ደግሞ የሚያንጸባርቀው ሁላችንም ለአገራችን ካለን ፍቅር የተነሳ ነው::

ሁላችሁምበጨዋነትመንፈስውይይታችሁንማካሄዳችሁየሚያስመሰግናችሁነው::ቤታችንምየታወቀውአባላቱበሚያሳዩትየጨዋነት ባህሪይነው::ተከባብረንናተፈቃቅረንያቆየነውቤትነው::ኦዶሻኪሶምየጠቆመውይህንኑነው::የሰጠኸውምክርምበጣምየሚያስመሰግንነው::

ግንይህንቤትከሌሎችለየትየሚያደርገውበአባላቱመካከልመከባበርናየጨዋነትመንፈስከመታየቱባሻገርእንደፖለቲካዓይነትከሚያናቁርር
እስበአብዛኛውየጸዳመሆኑነው::ባልሳሳትላለፉትሰባትወይምስምንትዓመታትበዋርካምሆነበዚህቤትሆንብለንየውይይትትኩረታችንን
ያደረግነውስላደግንባትአካባቢየነበረንንየሕይወትተሞክሮአለበለዚያምእዚያምባይሆንባለንበትየደረሰብንንገጠመኝከቤቱአባላትጋር
መካፈልሲሆን:ባጭሩበያለንበትእንድንዝናናየሚያደርገንቤትሆኖቆይቷል::አሁንምበዚሁመንፈስእንደሚቀጥልአልጠራጠርም::
የአደቆርሳትምህርታዊናአስቂኝትዝታዎች:የማይጠገበውየባለሱቅከልጅነትእስከእውቀትየደረሱበትአዝናኝገጠሞችናቀልዶች:
የራስብሩየሞፊቲየአይፋየወቤጃሎየቺኮኩባኖየአይፋየግልነሽየቁሩንፉድየክ/መመናኸሪያየሽሊንግየየቦሬዋእንዲሁምየአንፈራራደስደስ
የሚሉታሪኮችይዘውንተጉዘዋል::ከዚያምወዲህየተቀላቀሉንየነኦዶሻኪሶየጎሳየጂግሳእንዲሁምየሌሎችጽሁፎችቤቱንሲያደምቁትቆይተዋል::
ለዚህምነውበዋርካምሆነበኢትዮፎረምየዚህገጽተወዳጅነትበቀላሉሌሎችንበልጦየሚገኘው::

ሆኖምቀደምብየእንደጠቆምኩትከጅምሩይህቤትሲያተኩርየቆየውባብዛኛውከፖለቲካናከሃይማኖትየጸዳውይይትላይነው::
አሁንምበዚሁእንደሚቀጥልተስፋአለኝ::

ወንድሜጎሳወደዚህቤትላለመመለስያደረከውውሳኔሁላችንንምቅርእንደሚያሰኘንጥርጥርየለውም::ምናልባትያደረከውውሳኔበግዜያዊ
ስሜትሊሆንስለሚችልበበኩሌይህንውሳኔህንእንደምትቀለብስተስፋአለኝእንድትቀለብሰውምበጽናትእማጸንሃለሁ::ሁላችንምወንድሞችህና
እህቶችህነን::ጽሁፎችህናአተራረኮችህበጣምየሚናፈቁናቸው::እባክህእንደገናስለውሳኔህአስብበት::

አደቆርሳስለምንግዜምጨዋነትህአመሰግንሃለሁ::ጂግሳናኦዶሻኪሶሁኔታውንለማብረድያደረጋችሁትጥረትየሚያስመሰግንነው::

እርግጠኛነኝሌሎቻችንበመሐልያልገባነውበአንድበኩልሁኔታውያልተለመደበመሆኑግራስላጋባንእንዲሁምደግሞብንገባሁኔታው
ሊባባስይችላልበሚልፍርሃትነው::ስለዚህአሁንየመብረድመልክስለሚታይቤቱንእንደተለመደውሞቅሞቅእናርገው::


ለሁላችሁምመልካሙንእመኛለሁ::
አክባሪያችሁአንፈራራ

Post Reply

Return to “የጀምጀም ልጆች መገናኛ”