የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Forum rules
No cursing, bad language and offend other users !
No pornographic images or links!
This forum monitored regularly. We will BAN users without warning for not obeying rules.
እባክዎ የፎረሙን ህጎች ያክብሩ::
ቦንካ
Posts: 2
Joined: 06 Jan 2012 22:52
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by ቦንካ »

ሰላም እንዴት ሰነበታችሁ

አደቆርሳ ሰለአባ እስጢፋኖስ ቄስ ትምሕርት ቤት ስታነሳ ለኔም ድንገት ትዝታ ቀስቅሰህብኛል::
በእርግጥ እኔ ከአንተ በፊት የሳቸው ተማሪ ነበርኩ::

ዶሮ ድሮ የራስብሩን ት/ቤት ራስ ብሩ ብሎ የሚጠራው አልነበረም:: እንዲያው በደፈናው የመንግሥት ት/ቤት ነበር የሚባለው::
በተለምዶ ማለቴ ነው:: ታድያ የመንግሥት ት/ቤት አንደኛ ክፍል ለመግባት ፊደል መቁጠርህ ከተረጋገጠ ብቻ ነበር መመዘገብ የሚቻለው::
በዚህም ምክንያት የቄስ ት/ቤት ተፈላጊነቱ በጣም ከፍ ያለ ነበር:: በጊዜው ብዙ ተማሪዎች የነበሯቸው በሚካዔል ብኩል አባ እስጢፋኖስ
በማርያም በኩል አባ ሳሙዔል በመድሓኔዓለም በኩል መምህሬ ተካ ነበሩ:: እነዚህ ዋነኞቹ ሲሆኑ ሌሎችም እኔ የማላውቃቸውና ከጊዜ በኋላ
የመጡም ነበሩ::

አደቆርሳ አንተ የጠቀስካት የግራር ዛፍ ስር እኔም ተምሬአለሁ:: ከመሬት ምንም ያህል ከፍታ ባልነበራቸው አግዳሚ መቀመጫዎች ተደርድረን
በተዘበራረቀ ድምጽ ፊደሎችን ስንጠራ ከፈረንጅ ውሃ ባሻገር ለቆመ ሰው እንኳን መስማት አያዳግትም ነበር:: ሀ ሁ ሂ እያልን በመጠንቆያ
እያንዳንዷን ፊደል እየጠነቆልን እስክ ፐ የምንወርደው በቀን ስንት ጊዜ እንደሆነ እግዚአብሔር ይወቅ:: ከጥቂት ጊዜ በኋላ ድምጻችን ፊደሎቹን
በትክክል ይጥራ እንጂ መጠንቆያው ዬት እንዳረፈ እንኳን ልብ የሚል የለም:: አባም ከቤታቸው በራፍ ላይ በወንበር ተቀምጠው ልባቸውን ጣል
የሚያደርጉት ባማረ ድምጽ ዳዊትን ለሚያነቡት ነው:: ይህ ሁኔታ አባ ለጉዳያቸው ወደሌላ ቦታ ብቅ ካላሉ በቀር ያለማቋረጥ ይቀጥላል:: ሌላ
የሚያስቆመን ፈስ የተፈሳ እንደሆነ ነው:: ሁሉም እፍ እፍ በማለት እርስ በርስ መወነጃጀል ይጀምራል::

ከቄስ ት/ቤት በጣም ትዝ የሚሉኝ ሁለት ነገሮች ናቸው::
አንደኛው አንዳንዶቻችን ከቤታችን በጠርሙስ ውኃና በኪሳችን ቆሎ ይዘን እንሄድ ነበር:: ከጠርሙሱ ውኃ ትንሽ ካጎደልንለት በኋላ ቆሎውን
ጠርሙሱ ውስጥ እንጨምራለን:: ጓደኛችን ውኃ እንድናጠጣው ሲጠይቀን ውኃውን አይከለከልም ከቆሎው ግን አንዷን ፍሬ እንኳን አፉ ውስጥ
እንዲያስገባ አይፈቀድለትም:: በጠጪውና ባስጠጪው ያለው ትንቅንቅ የሚረሳ አይደለም::
ሁለተኛው ደግሞ ከመካከላችን አንዱ ፈስ በመፍሳት ከተጠረጠረና እሱ ደግሞ ከካደ እውነቱን ይሁን ውሸትቱን ለማረጋገጥ የሚደረገው ማረጋገጫ ዘዴ ነው::
ትንሽ ደረቅ ሳር በተጠርጣሪው ግንባር ላይ እንደመርፌ እንወጋና ሳሯን እንለቃታለን ሳሯ ግንባሩ ላይ ተንጠልጥላ ከቀረች ፈስቷል ከወደቀች ግን አልፈሳም
የባላል::

ከአባ እስጢፋኖስ ነገሮችም ትዝ የሚለኝ አባን በከተማው ውስጥ በማናቸውም ቦታ ስናገኛቸው ጫማቸውን መሳም የተለመደ ነበር:: ታድያ ያችን ቀይ ሸራ
ጫማ ለመሳም ጎንበስ ስንል ኧረ ተው ብለው እንኳን ቀና አያደርጉንም ይልቁንም ቀጥ ብለው ቆመው ሁለቱንም እግራቸውን እንስማለን እንጂ:: ቀና ስንል
መስቀላቸውን ወይም እጃቸውን ከተሳለምን በኋላ ጉንጫችንን ስመው ስለቤተሰብ መጠየቅ ይጀምራሉ:: እግራቸው ምንም ሽታ የሌለው ንጹሕ ሲሆን እጃቸውም
በጣም ደስ የሚል ሽታ ነበረው::
አደቆርሳ
Jogger
Jogger
Posts: 45
Joined: 13 Jan 2012 04:13
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አደቆርሳ »

ወንድሜ ቦንካ ሰላም ላንተ ይሁን
እንደው የልጅነት ነገር ቀሰቀስክና አላስችል አለኝ ይገርምሃል እንደልጅነት እና የተማሪነት ታሪክ የሚያስደስተኝ ምንም ነገር የለም:: አልፎ አልፎ ከጓደኞቼ ጋር ተገናኝቼ የድሮ ነገር ከተነሳ ምግብ እንኳ አይርበኝም ::
ሆኖም ይህ የኔ ብቻ ስሜት አይመስለኝም ማንም ሰው የልጅነት ወዳጁን አድጎ ጎልምሶና በተለይም አርጅቶ ሲያገኘው እንደተወለደ ያህል ይሰማዋል ::
አባ እስጢፋኖስ ጋ ተምሬያለሁ ያለኝ የክብረመንግስት ልጅ ካሳለፍነው አራትና አምስት አመታት ውስጥ አንተ የመጀመሪያው በመሆንህ ደስታዬ ወሰን አልፎአል:: ምክንያቱም ብዙ መነጋገር እንችላለን ማለት ነው :. በርግጥ የተናገርከው በሙሉ ትክክልና በአይነ ኅሊና እንደ ስዕል የሚታይ ነበር::
ከጠቀስካቸው የቄስ አስተማሪዎች ውስጥ እኔም እንደማስታውሰውና እንደማውቀው ሁሉም ትክክል ሲሆን ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን አባ ፈለገብርሃን አክሊሉ ያስተምሩ ነበር::
ከሁሉ ይልቅ ያቺን ግራር ዛፍ ስላስታወስካት ምን ያህል ደስ እንዳለኝ ልነግርህ አልችልም::
ለረዥም ዘመን እዚያች ቦታ በሄድኩ ቁጥር ሳላያት አልመለስም ነበር::
ከአንድ ድንጋይ ወደ አንድ ድንጋይ የተጋደመ ጥርብ እንጨት ላይ ተቀምጠን ነበር የምንማረው ይገርምሃል እኔ ብዙ ጊዜ የምቀመጠው ድንጋይ ላይ ነበር ምክንያቱም አንድም ቀን በሰዓቱ ተገኝቼ ስለማላውቅ የነበሩት ጥቂት ቦታዎች ተይዘው ይቆዩኛል ከዚህ የተነሳ የራሴና ማንም የማይፈልጋት መቀመጫ ነበረቺኝ : እንዳልከው አባ አንዳንዴ የጓሯቸውን በቆሎ ሲቆርጡም ሆነ ስራ ሲሰሩ እኛ ፊደል ላይ ስንችጮህ የሚገላግለን የቀትር ጸሃይ መስመር ላይ መድረስ ብቻ ነበር::
አንዳንዴ ቀልባቸውን ጣል ካደረጉ ደሞ ከመሃላችን ፊደል የሳተ ልጅ ሰምተው አንተ እከሌ ደግመህ ውረድ ይሉ ነበር ልክ እንዳሁኖቹ የሙዚቃን ቁልፍ እንደሚለዩ የባንድ ኮምፖዘሮች ዓይነት እሳቸውም ማሳቸው ውስጥ ሆነው ከተማሪዎች መሃል መልክተ ዮሃንስን የሚስት ልጅ ከብዙዎች መሃል ለይተው ያስቆሙ ነበር::
ሰዓት የምንቆጥረው ጸሃይ የአባን ቤት ጣራ አልፋ በምታጠላው ጥላ ሲሆን ምልክቱ ላይ ጥላዋ ሲያርፍ ልክ ከቀኑ ስድስት ሰዓት ይሆናል ::በምንማርባት ግራርም እንዲሁ እንቆጥር ነበር ::
ካስታወስከው ውስጥ ያሳቀኝ የፈስ ጉዳይ ነው የደረቅ ሳር ቀጭን ነዶ ነገር ግንባር ላይ መሰካት እኛም እናደርግ ነበር ይህን የምናደርገው ግን አንድ ሰው ውሸት ተናግረሃ አልተናገርክም በሚል ሲሆን
ፈስን በተመለከተ እኛ እንዲህ በማለት ነበር የምናውጣጣው :-
ፈስ ፈሶ
ፈሳራራ
ቆርጦ ቆርጦ
ደም ያሳራ
ደሙ ሲረጋ
በለው ባለንጋ
አለንጋው ሲበጠስ
ሚኒቄህ /ሽ/ ይበጠስ ! ..... ይህ የመጨረሻው ስንኝ ያረፈበት ሰው እሱ እንደፈሳ ይቆጠርና ሲሰደብ ይውላል ማለት ነው:: /በነገራችን ላይ አንፈራራችን ስለ እርዳታህ ከልብ አመሰግናለሁ /
ከፊደል ቆጠራ ስንመለስ ሹሌ በሚባል ጨዋታ ስንራገጥ እንውላለን ሹሌና እጅ በኪስ በልጅነት ከምንጫወታቸው በጣም የሚታወቁት ናቸው ::
ዳዊትን በማንበብ ጥሩ ጥሩ ልጆች የነበሩ ሲሆን እንዳልከው የዳዊት ንባብ የራሱ የሆነ /ያሬዳዊ ይመስለኛል/ ዜማ ነበረው :
ግነዩ ለእግዚአብሄር እስምኸ
እስመለዓለም ምህረቱ ..........ሲነበብ አባ ከማንም ይበልጥ የሚጠሉት ሰው ቢኖር እኔን ነበር በደንብ አነባለሁ ግን ለሳቸው አላምራቸውም ....አንተ ? አንተማ ዝፈን ፈንጥዝ እንጂ ይሄንን የታባህ ታቃለህ ? ነበር የሚሉኝ ዜማውን ሳጠና ውዬ ባድር እሳቸው ጋ ስደርስ አይሆንልኝም ነበር::
አንዳንዴ አንተም እንዳልከው ከበራፋቸው ላይ ያቺን ቀይ ጨርቅ የሚነጠፍባትን መቀመጫቸውን ያወጡና ቁጭ ብለው ንባብ መስማት ሲፈልጉ እኔ ቶሎ ብዬ ሽንቴ መጣ ብዬ ወጣና ጫካ እቆይ ነበር ::
ጫማ በማሳም ረገድ የነበረው ሥርዓት አሁን ሳስበው ግርም ይለኛል እንኳንስ ቀና በል ሊሉን ይቅርና እዛው ቆየት ካልን ነው ጎሽ የኔ ልጅ እደግ ብለው የሚመርቁን ::
አባ ጠዋት ትምህርት ከመጀመራችን በፊት ጫማቸውን እንድንስም ያስገድዱን ነበር : ተቀጥተንም ተገርፈንም ስናበቃ ጫማ ሳንስም መቀመጥ አይቻልም ነበር::
ጉንጫችንን እንሳም ነበር ስትል አባ እየመረጡ እንደሚስሙ ትዝ ይለኛል እኔ እንኳን ጉንጬን ልሳም ራሴን ዳበስ ዳበስ ካደረጉኝም ትልቅ ነገር ነበር ::
በምሳ ወደቤት ስንለቀቅ ወደ ራስብሩ ጊቢ እየተመለከትን ትልልቆችን እና ቆንጆ ቆንጆ ሴቶችን ስናይ የሚሰማን ቅናት አያድርስ ነበር እኔ ወደፊት እንደዚህ ነው የምሆነው እንባባላለን ሴቶቹንም እኔ ወደፊት ማገባው እንደዚች ያለች ነች አይ እኔ ደሞ እንደዚች እየተባባልን የየራሳችን ሞዴሎች ነበሩን::
ቦንካ ስለ ሚካኤል ጓሮ ምታስታውሰው ነገር አለ ይሆን ? ዶቅማ ለቀማ እንዲሁም በአዲስ አመትና በቡሄ ወቅት ችቦ ለቀማ ትሄድ ነበር ?
ችቦና አውጥ አንድ ወቅት ናቸው መሰለኝ ሁሌ ችቦ ለቀማ ስንወጣ አውጥ ሆዳችንን እስኪያመን ነበር በልተን የምንመለሰው :
ከደበላ ሰፈር ማዶ እየሄድን በትረሎሚ አውጥና መንደሪን እንዴት አድርገን እንደምንሰርቅና እንደምንበላ ሳስታውሰው ምን አይነት ልጆች ንበርን ያሰኘኛል::
ሽልንጋ ቁፋሮ የጀመርኩት የቄስ ተማሪ ሳለሁ ነው ::
ነገሯ አለቀች ሌላ ግዜ ብቅ እላለሁ ወንድሜ ቦንካ ይገርምሃል ከትናንት ወዲያ ቅዳሜ መሄድ ከነበረብኝ ቦታ ቀርቼ ነው የተገናኘነው ጥሩ ስንቅ ነው ያቀበልከኝ ብቅ ስትል ስለስምህ ጥቂት እንደምትለን ተስፋ አለኝ አሁንም ካልሄድኩ እንገናኛለን ቸር ያቆየን
ወዳጃችሁ አደቆርሳ ዘሃገረ አዶላ
አደቆርሳ
Jogger
Jogger
Posts: 45
Joined: 13 Jan 2012 04:13
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አደቆርሳ »

ውድ ኢትዮ ፎረም ... ያለ አንዳች ችግር ስሜ ተመልሶልኝ በቀጥታና በቀላሉ ሎግ ኢን ማድረግ በመቻሌ
ያላችሁን ቅልጥፍና እና መልካም መስተንግዶ ከልብ beማድነቅ ......... ለምስጋና ጎንበስ ብያለሁ ! ! !



ሞፊቲኮ ምነው ጠፋህሳ የነካካ እጅህን አንጋጥጬ እየጠበቅኩ ነውኮ ?
ጎሳንም ይዘኸው የጠፋህ ነው የሚመስለው ::
ለመሆኑ እነዚያ ደጋግ ልጆች አይፋና የቦሪቲ ለምን ተቀየሙን ? እኔ በበኩሌ ገና ከድሮው ሰው እንደማስቀይም ወይንም ሰው ሊቀየመኝ የሚችል አይነት

ባህርይ እንዳለኝና ወዲያው ይቅርታ እንዳይነፈገኝ በአዋጅ ለፍልፌያለሁ ስለዚህ ብዙም አያሰጋኝም::
አንተ ከሆንክ ጥፋተኛው ይቅርታ ብለህ አምጣቸው ::
ራስብሩ ብቅ ብለህ ውረድብኝ እንጂ እኔ ስለተናገርኩ ..... ከሆነ እንጣላለን ዋ !
ባለሱቅም እንደማያስታርቀን እወቅ
በተረፈ ስሜን ቼክ ለማድረግና ኢትዮን ለማመስገን ነው ብቅ ያልኩት
ቸር ያቆየን
Dole
Starter
Starter
Posts: 19
Joined: 04 Jan 2012 20:47
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Dole »

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ
What is this
Dole
Starter
Starter
Posts: 19
Joined: 04 Jan 2012 20:47
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Dole »

I can read and write in this Forum


What is going on freinds?



Wadera please help



I don't want to do this FireFox things.... I have no time as such



SITANADIDU

Bishkoch
አንፈራራ
Runner
Runner
Posts: 50
Joined: 03 Jan 2012 12:51
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አንፈራራ »

ሰላም ለዚህ ቤት

Dole እንክዋን ደህና መጣህ:: ባለሱቅ ወንድምህ ነው? አነጋገራችሁ ይመሳሰላል:: :) ኦኬ Firefox መሄድ ካልፈለክ በለመድከው browser login ማድረግ ትችላለህ:: ለምሳሌ እኔ አሁን የገባሁት በ Internet Explorer ነገር ግን የመጠቀሚያ ስሜን መስኮት ስከፍተው "አንፈራራ" የሚለው ከመጀመሪያውኑ ተመዝግቦ ስለነበር ያንን መጫን ብቻ ነው የሚስፈልገው ለመግባት:: ቀደም ብየ ባለፈ ገጽ ላይ እንደጠቀስኩት መልስ ለመስጠት በመጀመሪያ የምትጫነው "በአማርኛ ለመጻፍ" የሚለውን ሰማያዊውን መስኮት ነው:: ከዚያም የጻፍከውን highlight እና ኮፒ አርገህ "post a reply" የሚለውን መስኮት ከፍተህ ኮፒ ያደረከውን እዚያ መለጠፍ ነው::
እኔ ይኸንን ከዋርካ ይልቅ በጣም ቀላል ሆኖ ነው ያገኘሁት:: አንዴ እስኪለመድ ብቻ ነው::
ሞፊቲ
Jogger
Jogger
Posts: 33
Joined: 03 Jan 2012 14:19
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by ሞፊቲ »

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን::

ከታች አንድ የviዲዮ ሊንክ አስቀምጣለሁ::አቶ ሃይሌ በ ኢሳት የሰጡት ኢንተርቭው ነው::በጣም ኤክሳይተድ የሆንኩበት ነገርን ከ 26ኛው ደቂቃ ጀምሮ አድምጡት::
አደቆርሳና አንፈራራ በዚህ ዙርያ አንድ ነገር እንደምትሉን ተስፋ አደርጋለሁ::አቶ ሃይሌ ለ እድገት በህብረት ክብረመንግስት ዘምተው የመሰንጠቅያ ፋብሪካዎችን እንዴት ለ ወዛደሩ
እንዳወረሱ በጥቂቱ ይናገራሉ::
እርግጠኛ ነኝ ልታውቋቸው ወይም ታሪኩን ልታስታውሱት ትችላላችሁ የሚል ግምት አለኝ:

[youtube]http://www.youtube.com/watch?v=CknoUPUT ... ature=plcp[/youtube]
ወንድሜ ቦንካ ስለቄስ ትምህርትቤት ያካፈልከን ትዝታ ስሜቴን ተቆጣጥሮት ሰንብቶአል::እንዲሁ ይልመድብህ::

አደቆርሳ ያንተ መንገድ (ጉዞ) የሚበቃው መቼ ነው::አዲስ ቤት ውስጥ ብዙም ሳታለማምደን መጥፋት የለብህም::

ቸር እንሰንብት!!
አንፈራራ
Runner
Runner
Posts: 50
Joined: 03 Jan 2012 12:51
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አንፈራራ »

ለኢትዮፎረም አስተዳዳሪ ኦሸንoc

በጀምጀም ልጆች መገናኛ ስም እስካሁን ላደረከው ሁሉ በጣም አመሰግናለሁ:: ይህንን መገናኛ ቤታችንን በቀላሉ ማግኘት እንድንችል ስላደረክልን ከሁሉ በላይ ደግሞ በዋርካ "የክብረ መንግስትና አካባቢ ልጆች" ያከማቹትን ፋይሎች ወደዚህ እንዲመጡ ስላደረክልን ምስጋናየ የላቀ ነው::

ውድ የጀምጀም ልጆች አሁን ቀደም ሲል ሲያሳስበን የነበረ ችግር ስለተወገደ እንደልባችን እዚህ እየመጣን የተቋረጠውን ውይይታችንን መቀጠል እንችላለን::

ራስብሩ አደቆርሳ ባለሱቅ ሞፊቲ የግል ቁሩንፉድ ቦሪቲ አይፋ ውቤጃሎ ቺኮኩባኖ ክ/መ መናኽሪያ ሽልንጌ ቦንካ ጎሌ ምሥራቅ ሌሎችም እየመጣችሁ ሀሳብ የምትሰጡ ኮለኔል ተድላ ብሩክ ወረኢሉ የጃማጦስኝ ብቅ በሉ::
እዚህ በአጠቃላይ ፎረሙ ከነውርና ከብልግና ቋንቋ የራቀ ነው::

እንደገና ለፎረሙ አስተዳዳሪ ለኦሸንoc ምስጋናየ ይድረስህ::
Post Reply

Return to “የጀምጀም ልጆች መገናኛ”