የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Forum rules
No cursing, bad language and offend other users !
No pornographic images or links!
This forum monitored regularly. We will BAN users without warning for not obeying rules.
እባክዎ የፎረሙን ህጎች ያክብሩ::
ምስራቅ
Posts: 1
Joined: 09 Jan 2012 19:05
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by ምስራቅ »

በጣም ጥሩ ቤት ሰርታችሁዋል ደስ ይላል:: ይሄ በትም እንደ ዋርካ እንዳይበላሽ ባልገዎችን የሚቆጣጠሩ ከሆነ እኔም አዲሱ በታችሁ እየመጣሁ አነባችሁዋለሁ::
ቤት እምቦሳ ብያለሁ:: እኔም ከማንበብ ብቻ ወጣው :)
እህታችሁ
አንፈራራ
Runner
Runner
Posts: 50
Joined: 03 Jan 2012 12:51
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አንፈራራ »

ቦንካና ምሥራቅ ወደ "ጀምጀም ልጆች መገናኛ" ቤት ጎራ ማለታችሁ በጣም አስደስቶናል እንግዲህ እናንተም ቤቱን ሞቅ ሞቅ ለማድረግ ተሳተፉ:: ይልመድባችሁ እናመሰግናለን:: ሰላም ሰው ስለ ገና በዓል ስለ አስቀመጥከው ቭድዮ እንዲሁ እናመሰግናለን::
ለስድስት ዓመት ልሳኑ ተዘግቶ የአልጋ ቁራኛ ሆኖ የኖረው ማቲማቲሻኑ የጀምጀም/አዶላ ልጅ ፕሮፌሰር ሃይለ ሚካኤል ካለፈው ወር ጀምሮ በየቦታው በሚደረግለት ጸሎት ምክንያት አሁን አንዳንድ የመሻሻል ምልክት ማሳየት መጀመሩን ባለቤቱ ትላንትና በጻፈችልኝ ኢሜል ገልጻልኛለች:: እኔም በምሄድበት ቤተ ክርስቲያን ባለፈው ዓርብ ማታ የቤተ ክርስቲያኑ አባላት ሁሉ ተነስተው ፕሮፌሰሩ ከህመሙ እንዲፈወስ አምላክን በጸሎታቸው ተማጥነዋል::የእግዚአብሔር ስም ይባረክ::
ከስድስት ወራት በፊት እዚህ አሜሪካ የሚኖሩት የክ/መንግስቱ የሰሎሞን ጨንቤ ሁለት ልጆች ሕይወትና ራሄል ሰሎሞን በአዲስ አበባ ሰርጋቸውን አንድ ላይ አከናውነው ነበር:: አሁን ሕይወት ከአንድ ከአራት ወራት በኋላ ልጅ እንደምትወልድ ይጠበቃል::
n687914036_1138042_5389.jpg
n687914036_1138042_5389.jpg (43.61 KiB) Viewed 4648 times
ራሄልና ሕይወት

ሌላዋ የክብረ መንግስት ልጅ ሰብለ በለጠም ሰሞኑን እንደምትወልድ ተነግሮኛል:: ሁሉንም እንኳን ደስ ያላችሁ እንላለን::
ሌሎች የጀምጀም ዜናዎች ያላችሁ እንዲሁ ብታካፍሉን መልካም ነው:: ፎቶዎችም ካሏችሁ እዚህ ማስገባት ይቻላል::
አንፈራራ
Runner
Runner
Posts: 50
Joined: 03 Jan 2012 12:51
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አንፈራራ »

አደቆርሳ..ገልገሎ...እንክዋን ደህና መጣህ:: ድሮ በዝናብ ጊዜ ትሬንታ ኳትሮዎች ከወንዶ ወደ ክብረ መንግስት ሲመጡ በየመንገዱ ጭቃ ስለሚይዛቸው አንዳንዴ ሳምንት ድረስ ይፈጅባቸው ነበር:: እንዲያውም የመጀመሪያው የራስ ብሩ ትምህርት ቤት ዳይረክተር ሚስተር ዘካሪያስ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ክ/መ ሲመጣ ከአዲስ አበባ እስከ ክ/መ የፈጀበት ጊዜ 17 ቀን እንደነበር የነገረን ትዝ ይለኛል:: አንተም ዛሬ እዚህ ለመምጣት እንደ ትሬንታዎቹ ችግር ሳይገጥምህ አልቀረም ብየ አስባለሁ። :) እስኪለመድ ድረስ ነው።
በዚህ ፎረም ላይ ለመጻፍም ፎቶም ለማስቀመጥ በጣም ቀላል ሆኖ ነው ያገኘሁት:: አደቆርሳ የሚለውንም ስምህን እንደገና ማስገባት ትችላለህ:: ከዚያ አንዴ የጻፍከውን ስምህን ኮፒ አድርገህ ማስገባት ነው:: ሌላው በጣም ቆንጆ ነገር ሆኖ ያገኘሁት ከዚህ በፊትም ገልጬዋለሁ መልክት ለማስተላለፍ ስትፈልግ በመጀመሪያ ስትከፍት መልስ ከመጻፍህ በፊት "መልስ ለመጻፍ" የሚለውን ሰማያዊ ቀለም ያለውን ትንሽ ሳጥን ስትከፍት ባዶ ገጽ ይከፍትልሃል:: ከጎኑ እንዲሁ ለመመልከት ያህል የአማርኛ ፊደል ሰንጠረዥ አለ:: እርሱ ግን አያስፈልግህም፣ ገጹን እንደከፈትክ በቆንጆ ፊደል መጻፍ መጀመር ነው:: ስትጨርስ የጻፍከውን መልክት "ሃይላይት" ታደርግና ኮፒ አድርገህ ወደ ዋናው መልስ የሚሰጥበት ገጽ ትሄዳለህ:: እዚያ ኮፒ ያደረከውን መልክት ፔስት ታደርጋለህ። ፊደሎቹ ጥቃቅን ስለሚሆኑ እዚያው "ፎንት" በሚለው ስር "ትልቅ" ወይም "በጣም ትልቅ" ለማድረግ ምርጫ ይሰጥሃል:: ያንንም ማድረግ ትችላለህ:: በድንገት እንኳን የጻፍከው ቢጠፋ መጀመሪያ የጻፍከው መልክት አሁንም በጀርባው በኩል ስላለ እርሱን እንደገና ኮፒ ማድረግ ብቻ ነው። አንዳንዴ ዋርካ ላይ ጽፈን ጽፈን መልክታችን እልም የሚልበት ጊዜ ነበር: እዚህ ግን በጭራሽ እንደሱ አይሆንም ራስህ አውቀህ ካላጠፋኸው በስተቀር::
ፎቶ ለማስገባትም ቀላል ነው:: ኮምፕዩተርህ ውስጥ ፎቶ ካለህ መልክት ከመላክህ በፊት "ሳብሚት" ከሚለው ዝቅ ስትል "ብራውስ" የሚልና ፎቶውን ከመረጥክ በኋላ ደግሞ "አድ ፋይል" የሚል አለ። ከዚያም "አድ ፋይል" የሚለውን ስትጫን ያ የመረጥከው ፎቶ መልክትህ ጋር ይቀላልቀላል::
እስቲ እንደዚያ አድርገህ ሞክረው። እርግጥ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ትንሽ ግር ይላል እንጂ ይኸኛው በጣም የሚመች ሆኖ ነው ያገኘሁት:: የዋርካን ፋይሎች ወደዚህ ለማምጣት እየሞከርኩ ነኝና ጊዜ ሳገኝ አመጣቸዋለሁ:: ቻዎ!
ሞፊቲ
Jogger
Jogger
Posts: 33
Joined: 03 Jan 2012 14:19
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by ሞፊቲ »

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን::

ገልገሎ.....በሃገራችን (በ አካባቢያችን) ባህል በማታ የተወለድክ ሳይሆን አይቀርም? ለዚህም ይሆናል ገልገሎ (ገልገላ) ልትባል የተሞከርከው::ውድ አደቆርሳ= እኔም እንዳንተው ይህንኑ
ስምህን ነው የምወድልህ::ለምን እንደቀየርከው ግልጥ አይደለም:: ጹህፍህ በጣም ጥቃቅን ከመሆኑ የተነሳም የነ አንፈራራንና የነ ራስብሩን አይን በጣም ተፈታትነሀዋል::


ጹህፍን ወደዋናው ፔጅ ፔስት ካረክ በኌላ ሃይላይት አድርገውና በምትፈልገው መጠን (ፎንት ሳይዝ) ጠቁመህ ማሳደግ ትችላለህ::እንዳልከው ለመጻፍ እንደዋርካ ምቾት አይሰጥም::
እየቆየን ስንሄድ እንቆጣጠረው ይሆናል::


ባለፈው ስለመንጌ መጽሃፍ ለማውራት ስሞክር ራስ ብሩ አፍ አፌን ብሎኝ ነበር::መጽሃፉ ለኔ ተመችቶኛል::ወደድንም ጠላንም ሰውየው የዚች ሃገር የጥሩም ይሁን የመጥፎ ታሪክ ባለቤት
ነው::ሌሎች ነገሮችን እንኳ ትተን በሱማልያና በኢትዮጵያ መካከል የነበረውን ጦርነት ስናነብ አስገራሚና ልናውቀው የሚገቡ ታሪኮች ተጠርዘው እናገኛለን::
የሲያድባሬ መንግስት በዛ ቀውጢ ሰአት ሃገራችንን ወሮ መላው ሲዳሞን ባሌንና ምስራቅ ኢትዮጵያን ገንጥሎ ሊወስድ የቋመጠበትን ምክንያትና የተደርጉት የሰላም ጥረቶችና
የዲፕሎማሲ ሁጤቶች : የሲያድባሬ ድንፋታና ንቀት : የእናት ሃገር ጥሪ; የሚሊሻ ሰራዊት;
የወገን ጦር አቅምና የጠላት ጦር አቅም ልዩነት; የሶቬቶች ወደ ኢትዮጵያ መገልበጥ ምክንያቶቹና
በጣም በጣም ብዙ ታሪኮች ከባለቤቱ ማግኘት ስሜትን ይቆጣጠራል::ከዚህ ውጪም በሃገራችን ታሪክ ትልቅ ጠባሳ ጥሎ ያለፈው የ60ዎቹ ባለስልጣኖች .የንጉሱ ከስልጣን
መውረድና መሞት ስለኢሃፓ የተነሱትና ሌሎችም አነጋጋሪነታቸው የማይታበል ነው::
የዚህ የመጀመርያው ቅጽ መጽሃፍ መነሻና መጨረሻ ከ1966-1970 ዓም ድረስ ያለውን
ታሪክ የዳሰሰ ሲሆን በቅጽ 2 እና 3 የሚታተመውን ታሪክ ደግሞ በጉጉት እንጠብቃለን!!!


ቸር እንሰንብት!!!!!!!!
አደቆርሳ
Jogger
Jogger
Posts: 45
Joined: 13 Jan 2012 04:13
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አደቆርሳ »

አንፈራራችን ከልብ አመሰግናለሁ ከዛ ተመልጬ በአጋጣሚ ሌላ እድል ተፈጠረልኝና ከአንድ ወዳጄ ዘንድ ይሄንን ቤት ከፍቼ ላሳየው ስሞክር የናንተን ትስሁፍ አየሁና ደስ አለኝ: እንደገናም ለመትሳፍ ጉጉቴን የተረዳ ወዳጄ እነሆ ፈቃዱ ሆነና መጣሁ::
እንዳልከኝ ቅድምም የትሳፍኩት በተከፈተችው ሰማያዊ ምልክት አማካኝነት (አማርኛ ለመትፋፍ) በምትለዋ መስኮት በኩል ነው : እስካሁን ድረስ የሆኑ ቃላቶችን ማግኘት አልቻልኩም እንዳልከው አንድ ቀን ይመጣሉ::
ሚስተር ዘካሪያስን መጀመሪያ ስሙን ያወኩት ካንተ ነው ከዛ በኋላ ግን ብዙ ስለሱ መስማት ችያለሁ በተለይ ኮጪን (ልጁን) ከነስሙና ከነባህሪው ማስታወስ በመቻልህ በጣም የተደነቀብህ ሰው
((ይሄ ሰው ትምህርት ሚኒስቴር ውስጥ የሰራተኛ አስተዳደር መሆን አለበት )) .......... ብሎ መናገሩ ቢያስቀኝም ከምን የተነሳ እንደነበረ ግልጽ ነበር:: በነገራችን ላይ ኤስ እና ኤች አንድ ላይ ሲነበቡ የምትገኘው ፊደል ወይም የስኳር አገዳ ተክል የመጀመሪያ ፊደል የት እንደምትገኝ ልትነግሩኝ ትችላላችሁ ? ምን አይነት ባለጌ ናት በናታችሁ እሷን ፍለጋ ቄስ ትምህርት ቤት ልሄድ ምንም አልቀረኝም ? ከጎን ያለውንም ሞከርኩ እሷ እቴ !
እና ከአዲስ አበባ ክብረመንግስት ለመድረስ 17 ቀን በጣም አስገራሚ ነው : ሆኖም ግን እንኳንስ ከ40 አመት በፊት ቀርቶ ከ40 ቀን በፊትም በጭቃ ጊዜ በአንድ ቀን መግባት ምጥ ነበር::
አውቶቡስ ሳይገባ በትሬንታ ኩዋትሮ ዘመን በክረምት አንድ ሳምንት ይፈጅ ነበር ሲሉም ሰምተናል::
የመንገድ ችግር ምን ያህል እንደሆነ ከእኔ በላይ ምስክር አይገኝም የችማግሌው ዘመዶች ሳላቃቸው ያደኩት ስለማንተያይ ነው : የማንተያየውም ያገራቸው ርቀትና መንገድ አለመኖሩ ነው ::
አንዴ ትዝ ይለኛል ልጅ ሆኜ ሃገራቸው ሄድንና ከመኪና ከወረድን በኋላ ሁለት ቀን መንገድ እሰው ዘንድ የመጨበት እንግዳ ነን እያልን እያሳደሩን ሶስት ቀን በግራችን ሄደን ነው ያየናቸው :: እዚያም ባዶ ቁርበት ላይ አድሬ አልሞቅ ብሎኝ የተቸገርኩት አይረሳኝም የልጅነት ነገር ግን ቆይቼ ሲሞቀኝ የት እንደወደኩ ሳላውቅ ነው የነጋው :: ሞኝነቴ ልብሴን ማውለቄ ነው ከነልብሴ ለምን እንዳልተኛሁ ሳስበው ይገርመኛል : ምናልባት ጭማግሌው ቢያየኝ ይቆጣኛል ብዬ አልያም እንደ ስርአተ ህግ ተመልክቼው ነው የሚሆነው:: ቁም ነገሩ መንገድ ምን ያህል ሰውን እንደሚያቆራርጥ ለመግለጽ መሞከሬ ነው ::
ሌላው ሞፊቲኮም እንደነገርከኝ ስመዘገብ አማርኛ መጻፍ አይቻልም ታዲያ እንዴት አድርጌ ልጽፍ ነበር ብዙ ጊዜ ፈጅቻለሁ አሁን ግን ገብቶኛል ልክ እንደዚህ ኮፒ እና ፔስት ማድረግ ነው ስመለስ አደቆርሳም ይመለሳል ቸር ይመልሰን !
ስለ መንጌ መጽሃፍ ያለህን አመለካከት እጅግ አድርጌ አደንቃለሁ እንኳንስ እሱ ይቅርና ለድንበር ያልታገሉ ጦር ሜዳ ያልዋሉ በጠራራ ጸሃይ ሲረጭኑና ሲገድሉ የነበሩ እነ ጃርሶ ጎዳና እና ታደለ ደገፋም ባለታሪክ ናቸው ::
ማንኛውም መጥፎም ጥሩም ታሪክ ታሪክነቱን ሊጫር የሚቻልበት ሁኔታ የለም ታሪክ ታሪክ ነው ::
እኔም እስካሁን አላነበብኩትም በጣም በጉጉት ነው የምጠብቀው ::
እርግጥ ነው መንስቱ ኃይለማሪያምን የምወደው የኢትዮጵያ መሪ አይደለም ጥሩ የወታደር አቋም አለው ጥሩ የፖለቲካ እውቀት ግን የለውም እንደውም ሃገሪቱንም ህዝቡንም ለወያኔ ያስረከበ ስለሆነ ተጠያቂ ነው::
ዋናው ቁም ነገር ግን በወቅቱ የነበረውን ሚስጥራዊ የፖለቲካ ቁማር ከሱ የተጫለ የሚያቅ ሊኖር አይችልም ::
ራስብሩ ከምን የተነሳ አዲስ ነገር ሊጽፍ አይችልም እንዳለ በውነት ግራ ገብቶኛል
ታዲያ ማን ሊጽፍ ነው ? የደርግን ታሪክ ከደርግ ካልሰማን የአመራሩን ችግር ከመሪዎቹ ካልሰማን ከማን እንሰማለን ? እንደዚህ ያሉ ባለ ትልልቅ ታሪክ ሰዎች ራሳቸው ታሪካቸውን የመጻፋቸውን ባህል እጅግ ከሚያደንቁት አንዱ ነኝ ;:
የምኒሊክን እና የኅይለስላሴን ታሪክ እንደሚጽፍ ወይንም እንደፓንክረስት እና እንደ ኃይለስላሴ ደስታ ወይንም በአሉ ግርማ ወዘተ ካልጻፉት ታሪክ የማይመቸን መሆን የለበትም ::
ውነት ለመናገር ይህንን ዘይቤ ታሪክ በባለታሪኩ መጻፍ መቻሉን ማድነቅ ነው ያለብን : ምክንያቱም ባለታሪኮቹ ካለፉ በኋላ ታሪክ የገቢ ምንችህ እንጂ እውነትነቱ አጠያያቂ ሆኖ ሲገኝ በአይናችን ተመልክተናል: እኔ በበኩሌ ከዚህ የተጫለ ተነባቢ መጽሃፍ ይኖራል ብዬ አላስብም ::
ቸር ያቆየን ወዳጃችሁ አደቆርሳ ዘሃገረ አዶላ
አንፈራራ
Runner
Runner
Posts: 50
Joined: 03 Jan 2012 12:51
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አንፈራራ »

ሰላም አደቆርሳ
ኮምፒዩተርህ ላይ ስትመታ "ሸ" ን ለማግኘት "X" ን መምታት አለብህ:: "ሸ " ይሆናል:: በተጨማሪም Ethioforum ላይ ስትጽፍ የምትፈልገውን ማንኛውንም ፊደል "በአማርኛ ለመጻፍ" የሚለውን ሰማያዊ መስኮት ተጭነህ መጻፍ ስትጀምር በጎኑ ያለውን የፊደል ሰንጠረዥ ብትመለከት ሁሉም ፊደሎች እዚያ ላይ ይገኛሉ:: የፈለከውን ፊደል ስትጭን የመልእክቱ ገጽ ላይ ብቅ ይላል:: በነገርህ ላይ መልስ ለመስጠት በመጀመሪያ መጫን ያለብህ "በአማርኛ ለመጻፍ" የሚለውን እንጂ "Post Reply" የሚለውን አይደለም። ጽፈህ ጨርሰህ ኮፒ አድርገህ ወደ ዋናው ገጽ ስትመጣ ነው እርሱን የምትጫነውና ኮፒ ያደረከውን ፔስት የምታደርገው። ስትለምደው በጣም ቀላል ሆኖ ነው የምታገኘው::

ሞፊቲ... ተው አንተ...እንዳጋጣሚ ትላንት አይን ሀኪሜ ዘንድ ሄጄ "እንዲያውም መነጽር አያስፈልግህም" ብሎኛል:: የአደቆርሳ ጽሁፍ ይታየኛል:: እንግዲህ ችግር ያለባቸው ይናገሩ:::) ቻዎ ሁላችሁም። መልካም ሰንበት።
አንፈራራ
Runner
Runner
Posts: 50
Joined: 03 Jan 2012 12:51
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አንፈራራ »

ሰላም ለዚህ ቤት
Log in ለማድረግ ከመጻፊያው ፔጅ በታች ያለውን ዝርዝር መምሪያ ከተከተላችሁና Firefox browser ለኢንተርኔታችሁ ካስገባችሁ በመመሪያው መሰረት add on የሚለው ላይ any key የሚለውን ካስገባችሁ በቀላሉ የፈለጋችሁትን መጠሪያ ስም ምን ጊዜም ማስገባት ትችላላችሁ::

የማስተማሪያውን ቭዲዮ ተመልከቱ:: በጣም አሪፍ ነው:: አስተዳዳሪዎቹን ለማመስገን እፈልጋለሁ::
Post Reply

Return to “የጀምጀም ልጆች መገናኛ”