የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Forum rules
No cursing, bad language and offend other users !
No pornographic images or links!
This forum monitored regularly. We will BAN users without warning for not obeying rules.
እባክዎ የፎረሙን ህጎች ያክብሩ::
ራስብሩ
Starter
Starter
Posts: 23
Joined: 03 Jan 2012 09:45
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by ራስብሩ »

ጤና ይስጥልኝ
አንፈራራችን እንኳን በደህና ተመለስክ
ባለፈው እንደተነጋገርነው አንተ ወደኢትዮጵያ እንደሄድክ እኔም በተመሳሳይ ሰዓት አንተ ወደምትኖርበት ብቅ ብዬ ነበር ጥሩ የረፍት ጊዜ አሳልፌ ተመለስኩ::
እንዲሁም ላያቸው የፈለኳቸው ሌሎች የወዩ ቤተሰቦቼም በዚያው ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ሄደው ስለነበር አትላንታን ሳላይ መመለስ ግድ ሆኖብኛል::
የግልዬን ያለችበት (መኖሪያዋ አካባቢ ) ሄጄ አግኝቻታለሁ ሽልንግዬ የሚኖረው ራቅ ያለ ስቴት በመሆኑ መተያየት ባንችልም በቴሌፎን በደንብ ተገናኝተናል::
እንደውም ሌሎች ብዙ የተራራቅን ጓደኞቻችን መሃል አንዳንዶችን በቴሌፎን አገናኝቶኛል በጣም ነው የተደሰትኩት::
ከሞፊቲኮ ጋ ደሞ ልክ እኔ የዕረፍት ጊዜዬ አልቆ የተመለስኩ ቀን እሱ ኳስ ጨዋታውን ለመታደም ወደ ሜሪላንድ ሲመጣ ተለያየን እሱንም እንዳንፈራራ በሚገርም አጋጣሚ ማግኘት አልቻልኩም::
ሌላ የሚገርመኝ አጋጣሚ ደሞ አንድ ቀን አንድ ዘመዴ ቤት በድንገት ጎራ ስል ሌሎች እንግዶችም ቤቱ ውስጥ ነበሩ ዘመዴም እንግዶቹን ሲያስተዋውቀኝ ከመሃል አንዷ የቦሬ ነበረች::
ቶሎ ተመልሼ መውጣት ቢኖርብኝም የቦሪቲን ከእናቷ ጋር ለአጭር ጊዜም ማግኘቴ በጣም አስደስቶኛል ከእናቷ ጋር በቅርብ የምንተዋወቅ ቤተሰብም ነበርን ::
ሌሎች የወዩ ልጆችን ለማግኘት ብዙ ጉጉትና እቅድ ቢኖረኝም ከተወሰኑት በስተቀር ሁሉንም እንደፈለኩት ማግኘት አልተሳካልኝም::
በጣም ከምፈልጋቸው ውስጥ ግን የተወሰኑትን አግኝቻቸዋለሁ::
በተለይ የኳስ ጨዋታውን ፕሮግራም መከታተል ብችል ብዙ የወዩ ልጆችን ማግኘት እቻል ነበር ግን የእረፍት ጊዜዬ በመጠናቀቁ በቁጭት ለመመለስ ተገድጃለሁ::
ባጠቃላይ የአሜሪካ ቆይታዬ አስደሳች ነበር አንዳንድ የተለያዩ አጋጣሚዎቼን ጊዜ እንዳገኘሁ መጠን አጫውታችኋለሁ እስከዛው ሰላም ሁኑ
ራስብሩ
አንፈራራ
Runner
Runner
Posts: 50
Joined: 03 Jan 2012 12:51
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አንፈራራ »

ሰላም ወገኖች
ውድ ራስብሩ .... አንተ ወደ አሜሪካ ስትመጣ እኔ ወደ ኢትዮጵያ ስሄድ እኔ ደግሞ ስመለስ አንተ ወደ "አገርህ" ተመልሰሃል:: ሳንገናኝ በመቅረታችን አዝናለሁ:: ሆኖም በአሜሪካ ቆይታህ በመደሰትህ እኔንም ደስ ብሎኛል።

የኢትዮጵያ ጉዞየ፣ ከዚህ ቀደም እንደጠቀስኩት፣ ፍሬያማ ነበር:: ብዙ የድሮ የክብረ መንግሥት ሰዎችንም ለመገናኘት እድል አግኝቻለሁ። የክብረ መንግሥት መንገድም እያለቀ መሆኑን ተነግሮኛል::


ወደ ሌላ ርእስ ስንሄድ፣


ሁለት መጽሐፎች በመዘጋጀት ላይ ናቸው::


1....የመጀመሪያው "አስቴር!" ይባላል:: እሱም ሊያልቅ ወደ ግማሽ ደርሷል:

2....ሁለተኛው "ልዕልት ሜሮን!" ይባላል:: ወደ 3ኛ ምዕራፍ ደርሷል:: ግን ትንሽ ሪሰርች ያስፈልገዋል።

እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ሁለቱም መጻህፍት በሚቀጥሉት 6 እና 7 ወራት ይደርሳሉ::

በተረፈ አደቆርሳ፣ ሞፊቲ፣ ባለሱቅ፣ ጎሳ፣ የግል፣ የቦሬ፣ ጂግሳ፣ ኦዶሻኪሶ፣ ሌሎችም የማክበር ሰላምታየ ይድረሳችሁ::
Jigsa
Starter
Starter
Posts: 21
Joined: 13 Feb 2013 01:27
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Jigsa »

አንድ ሰው ቢቀየመኝ ወዮለት ምክንያቱም ስለምመርቀው! የወዩ ልጅ አፈጣጠሩ ለእርግማን አይደለማ፡፡
የሆድ ነገር ሆድ ይቆርጣል አሉ፡፡ አዳዲስ እንጀራ ፍለጋ ወዲያ ወዲህ በማለት ቆየሁኝ የሰሞኑ የኢትዮጵያ ኔትወርክም አንጀት ያሳርራል፡፡
እውነቴን ነው በወዩ አድባር ምያለሁ፡፡
ደሞ አኮ የኔ ስራ እናንተ አሜሪካ ባላችሁት ሰዎች ተጽእኖ ስር ያለ ነው፡፡ Funding problem ከገጠመን ያው ችግር ነው፡፡ ስለዚህ ታክስ በደንብ ክፈሉልንስለዚህ ታክስ በደንብ ክፈሉልን፡!መያድ የሚባል ነገር ታውቃላችሁ?አዎ የያ ሆኖብኝ ጥፍት እብስ፡፡
ደሞኮ አሉ ከታች አባባ ወደ አምስተኛ ክፍል ስታልፍ ሳይክል ገዛልሃለው ብለህ አልነበር .. vacation ደሞ እነ እንትና ጋር ነው ምናሳልፈው ይሉሃላ የበታች አካላት… እናም ያው ፈንድ ጠፍቶ ምናምን ብትላቸው አይገባቸውማ፡፡
አሁን ፈንዱ ተገኘ ልጆቹም ተሸኙ እኔም ብቅ አልኩኝ፡፡

ግን ሁላችሁም ሰላም ናችሁ አይደል? አንድዬ ፈጣሪ ከቁጥር አያጉለን ኑሩልኝ! ይሄ ሶሮ የሚባል weather ነገር ደሞ አይስማማኝም ያስለኛል፡፡ በቃ ሲሻለኝ ብቅ እላለሁኝ፡፡ ኡህ ኡህ ኡህ….!
አደቆርሳ
Jogger
Jogger
Posts: 45
Joined: 13 Jan 2012 04:13
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አደቆርሳ »

በአማርኛ ለመጻፍ በጣም ተችግሬ ነው ከብዙ ድካም በኋላ ይቺን የጥሳፍኩት
ቀጥሎስ ምን ማድረግ ይኖርብኛል ፕሊስ ሃሳባችሁን አካፍሉን
ኮምፒውተሩ የአማርኛ ቃል አይጽፍም ለምንድርነው ?
የሸከፍኩትን ይዤው ለመመለስ ተገደድኩ ታዲያ ይሄንን እንዴት ጻፍከው ሳትሉ እርዱኝ
ለርዳታችሁ ከልብ አመሰግናለሁ
ወዳጃችሁ አደቆርሳ ዘሃገረ አዶላ
አንፈራራ
Runner
Runner
Posts: 50
Joined: 03 Jan 2012 12:51
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አንፈራራ »

የአማርኛ ፊደል በኮምፒዩተርህ ላይ ካለህ በሌጣ ወረቀት ላይ ጽፈህ እሱን ኮፒ አርገህ ወደዚህ ገጽ ማምጣት የምትችል ይመስለኛል::
ግን ለምን እንደ ወትሮው ለመጻፍ እንዳልቻልክ የኢትዮፎረም ሃላፊዎች በይበልጥ ሊገልጹልን ይችላሉ ብየ ገምታለሁ::
ራስብሩ
Starter
Starter
Posts: 23
Joined: 03 Jan 2012 09:45
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by ራስብሩ »

እኔ እንደሚመስለኝ የምትጠቀመው ብሮውዘር ዊንዶውስ ኢንተርነት ኤክስፕሎረር ከሆነ በ ፋየር ፎክስ ሞክር ::
ኢትዮፎረም አማርኛ ከምንጽፍበት ቦክስ በታች ኤኒይ ኪይ እና በፋየር ፎክስ አማርኛ እንዴት ለመጻፍ እንደምንችል አሳይተዋል ያንን ተመልከት ::
ችግሩ የ ኤክስፕሎረር ይመስለኛል መቼም እርጅና ሲጫጫን የሚመጡ ችግሮች ብዙ እንዳሉ ስለምናውቅ ...................
አደቆርሳ
Jogger
Jogger
Posts: 45
Joined: 13 Jan 2012 04:13
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አደቆርሳ »

ትልቁ የአዶላ አባት አረፈ ! ባላምባራስ ዓለማየሁ በንቲ ይህቺን ዓለም በሞት ተለይተዋል ለብዙዎቻችንም አሳዛኝ ዜና ሆኖ ሰንብቷል::
እግዚአብሄር የነፍስ ምህረትን ያደርግላቸውና ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን እመኛለሁ::
የሳቸውን ዜና እረፍት እንደሰማሁ ከአንድ ቀን በኋላ (በማግሥቱ) እማማ አለችበት ሄጄ ልነግራት ከቤት ስገባ .....አንተ የድሆቹ አባት አረፈ አይደል ? ብላ ጉንጮቿን በሰላላ እጆቿ ጭምቅ አድርጋ ይዛ ተከዘች:
እንዴት ቶሎ እንደሰማች እየተደነቅኩ ራሴ አጽናንቻት ተመለስኩ::
ባላምባራስ ዓለማየሁ በንቲ በክብረመንግሥት ታሪክ ውስጥ እጅግ ብዙና የመልካም ምግባሮች ባለቤት ናቸው :
ከሰው አክባሪነታቸውና ከተግባቢነታቸው ጋር የከተማው የልማት ደጋፊና የቤተክርስቲያናት በተለይም የደብራችን የቅዱስ ሚካኤል አዲሱ ህንጻ ንዋየ ለጋስ ከሆኑት ውስጥ እሳቸው ቀዳሚው በመሆን ይታወቃሉ::
ክብረመንግሥትን ገናና ካደረጓት ታላላቅ አባቶቻችን ብዙዎቹ ምድሪቱን ተሰናብተዋል ቀሪዎቹን እግዚአብሄር ይጠብቃቸው::
ባላምባራስ ዓለማየሁ እድሜ ጠገብ እንደመሆናቸው ከልጅነት እስከ ሽምግልና እድሜያቸው ብዙ መልካም ስራዎችን የሰሩና ደግ ሰው በመሆናቸው ሁሌም ስናስባቸው እንኖራለን::

ስለ ሞት ሲነሳ ያለንበትን ዘመን ሞት ተናግረን የማንጨርሰው ሆኗል ይሄም ከጉርምስና እስከ ጎልማሳ እድሜ ድረስ እከሌ ሲባል ደህና ነው ከማለት ይልቅ ሞቷል ሲባል የምንሰማበት በመሆኑ አስደናቂው የንጥቂያ ዘመን ላይ መድረሳችንን ልናጤን ይገባናል::
ከዛሬ30 ዓመታት በፊት በ እኛና በትውልዳችን ላይ ይደርስ የነበረውን አሰቃቂ ፈተና ማስታወስ በቻልን አቅም ቀድመን የምናየው የጓደኞቻችንን ሞት ነው ያንንም ዘመን ሁሌ ስንኮንነው እንኖራለን:
ማንም ሰው ያለበትን ዘመን በደስታ አልያም በምስጋና ሊቀበለው እንደሚገባ ወቅቱ ራሱ ያስተምረናል እና ወገኖቼ ንቁና ጸልዩ ኑሯችሁም በትጋት ይሁን !


ከወራት በፊት የወንድማችንን የታምሩ መርጊያን ሞት እዚሁ አዲስ አበባ እንደሰማሁ በጣም ነበር ያዘንኩት::
ታምሩ ረዥም ጊዜ ህመሙን እያስታመመ ይኖር እንደነበር የምናውቅ ሲሆን ለሞት ያበቃዋል የሚል ግምት ግን በማንም ዘንድ አልነበረም::
ታምሩ በጣም ተጫዋችና በወዳጆቹ ዘንድ ቀልደኛነቱ የሚጎላ ፍጹም ቅን ሰው ነበር
የሰማይ አምላክ ነፍሱን የገነት ያደርጋት ዘንድ ልባዊ ምኞቴ ነው ለቤተሰቦቹም ከፍ ያለም መጽናናትን ይስጣቸው::
ታምሩን በቅጽል ስሙ ቡጁጋ እያሉ የሚጠሩት ጓደኞቹ እነ ተስፋዬ (ቃጩር) እነ ጸጋዬ (ቂርቄ)
እነ አየለ (ዴባ) ጥላሁን (ገመድ) ወዘተ ማንም የማያስታውስ አይኖርም ሁሉም መምህራን እንደመሆናቸውም ማለቴ ነው::
ታምሩ ግጥምና ስነጽሁፍ መጻፍ በጣም ነው የሚወደው ከዚህ ጋር በተያያዘ መቼም ብዙ ካደረጋቸው ነበሮች የሚታወሱ ቢኖሩም አንድ የማልረሳውን ላስታውሳችሁ::
ዘመኑ ደርግ ዓለም የኔ ነች የሚልበት የተራማጅ ሶሺያሊስት ወቅት ነበር በዚህም ምክንያት ወጣቱን እንዴት የሶሺያሊዝም ፍልስፍና ተከታይ ማድረግ ይቻላል ለሚለው በቂው መልስ ኪነት ነበርና ችሎታ ያላቸው መምህራን ተጨማሪ ስልጠና ሳያስፈልጋቸው ባላቸው ክህሎት ወጣቱን ያንቁት የኢትዮጵያን የትምህርት ስርዓት ሶሺያሊስታዊ እንዲሆን ያግዛል በሚል መርህ ጸጋዬ መርጊያ አንድ ትልቅ የኪነት ቡድን እንዲያደራጅና በመላው ኢትዮጵያ መምህራን ውስጥ ትልቅ ፖለቲካዊ ሚና እንዲጫወት በሊቀመንበሩ በመንግሥቱ ኃይለማሪያም ትዕዛዝ በጀቱ ይፈቀድለታል ቢሮም ይሰጠዋል::
ይሄኔ ታምሩ ለጸጋዬም ሳይነግረው በቀጥታ ደርግ ጽህፈት ቤት ይሄድና ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማሪያምን ማናገር እፈልጋለሁ ይላል ኖ እሳቸውንማ ማናገር አትችልም ተብሎ ካሳ ከበደን እንዲያናግር ይደረጋል እሳቸው ደሞ ወደ ባህል ሚኒስቴር ይልኩታል ሚኒስትሩም መልሰው ወደ ትምህርት ሚኒስትር ይልኩታል በመጨረሻም ዞሮ ዞሮ ጸጋዬ መርጊያ ጋ ይደርሳል::
<< አንተጋ ለመድረስኮ ሶስት ወር ፈጀብኝ >> ብሎ ታሪኩን ሲያጫውተው ጸጋዬ መቼም ማሳመር ያውቅባታል አሳምሮ ለጓደኞቹ እየነገረ በሳቅ ያፈርሳቸው ነበር::


ወደ ቀሪው ጉዳዬ ልመለስና የሆድ ነገር ሆድ ይቆርጣል እንደሚባለው ራስ የዕድሜ ነገር ዝም አላሰኝ ያላችሁ እናንተን ነው እንጂ እኔንማ ማን ይነካኛል ብለህ ነው::
ፊሊፕስ የጥሩ እቃ ስም .... አለ ንጉሴ አክሊሉ ::
ይልቅ አሜሪካ ስለነበረህ ቆይታ ታጫውተናለህ ብዬ ባፈጥ ባፈጥ ምንም አልተነፍስ አልክሳ ?
እነማንን አየህ አገኘህ ?
የግልዬን እና የቦሪቲን ማግኘትህ መልካም ነው እስቲ ስለ ሌሎቹ አጫውተን ግንድሬን መቼም ሳታገኘው እንደማትቀር እርግጠኛ ነኝ :
ስላየህባቸው ለውጥና አንዳንድ ነገሮች ፕሊስ ...................::
አንፈራራችን መቼም ጥሩና አዳዲስ ነገሮችን መስማት ለተሳናቸው ጆሯችን እንዲህ ያለውን ዜና ማሰማትህ ምን ያህል እንደሚያስመሰግንህ ሆህ ይንገርህ እኔ አልነግርህም::
የጸሃፌ ትዕዛዝን ብልህነት የንጉሰ ነገስቱን ልባምነት ባጠቃላይ የቤተ መንግሥቱን ድባብ ሰሞኑን መልሼ በአይምሮዬ እያሰላሰልኩ ነው ያለሁት ታዲያ ወደመጨረሻው ሰገነት ለመውጣት አልያም ወደ መጨረሻው ወለል ወርዶ ለመቀመጥ ልቤ በጥድፊያ ላይ በምትገኝበት በዚህ ሰዓት
እንደገና ሌላ ዜና መስማት እንዴት ደስ ይላል መሰለህ::
ሜሮን ስለምትባል ልዕልት እስካሁን ትዝ የሚለኝ ነገር ባይኖርም አዲስ ነገር እንደምናነብ ገና ከመግቢያው እረዳለሁ::
አስቴር ስለሚለው መጽሃፍህ ከዚህ ቀደም ካልተሳሳትኩ ከሁለት ዓመት በፊት ከመሃል አንድ ወፈር ያለውን ድርሳነ ፍቅር ወ አስቴር አንብበናል ::
ይሄ ምናልባት የነብሩን ጭራ....... እንደሚባለው ስለሆነ አንተ ዝም ብትልም ዝም ስለማናሰኝህ አስቀድመህ እንደምትሰድልን ተስፋ አለኝ::


ኦቦሌሳኮ ጂግሳ እንደምን አለህ :
መልክትህ እንዲገባኝ ደግሜ ማንበብ ተገድጃለሁ ከባድ አጻጻፍ ነው የተጠቀምከው የሆነው ሆኖ ከጠፋህበት እንኳን ደህና መጣህ::
ሶሮ እኔ የምወደው የአየር ጸባይ ነበር ይገርምሃል ሶሮ ሲሆን ደስስስ ነበር የሚለኝ::
አንዴ ዓመተ ምህረቱንም አስታውሳለሁ በሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ ስድስት ክብረመንግስት በአስፈሪ ሁኔታ ጸሃይ በዝቶ ነበር በበጋው ወቅት ከአዋሳ ተመልሼ ስሄድ ሰፈር መውረዴን ትቼ አራዳ ወረድኩ እንደሰዉ ሻንጣ ቀርቶ አንድም ተለዋጭ ልብስ ስለማይኖረኝ አራዳ ወርጄ አገሩን እያየሁ መመለስ ደስ ይለኝ ነበር::
ልክ እንደደረስኩ አባገዳ ከተማውን እየዞሩ እግዚአብሄርን ሲለምኑ አየሁ አካሄዳቸው እኔ ወደምሄድበት ነበርና ተከተልኳቸው : ገበያ መሃል አረፍ ብለው ከተመራረቁ በኋላ እነሱ ቀጠሉ እኔም ወደቤት ሄድኩ ::
በዚያ የጸሃይ ቃጠሎ ሰሞን ልክ በሰልስቱ ቀኑን ሙሉ ሶሮ ዋለ አቤትትት የነበረኝ ደስታ እስካሁን ድረስ አይረሳኝም::
በፊት ጥቂትም ቢሆን በጻፍካቸው ነገሮች በተለይ ስለ ሃገራችን ተጨባጭ ሁኔታ አንዳንዴ ስሜቶችህን ስረዳቸው ደስ ይለኛል ::ምክንያቱም ማን ይናገር የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ የሚለው ብሂል ምስክር መሆን ስለምንችል ይመስለኛል::
እርግጥ ነው አብረን እያለን በመሃላችን ስላለው ልዩነቶች ስፋት መግለጽ የሚከብድበት ሁኔታ አለ ሆኖም የሰው ልጆች በሙሉ በልዩነት ማነንን መቀበል ብንችል ቅራኔ ይጠፋ ነበር ብዬም አምናለሁ አልያም የተሻለ ይሆናል የሚል እምነት አለኝ::
ከበደ ሶሺያሊዝምን ያምናል አበበ ካፒታሊዝምን ቢቀበል ከቤ ስለምን ሊያጠፋው አልያም ሊጠላው ይችላል ? አበበን ማን ትክክል አደረገው ከበደንስ ?
ስለዚህ ሁሉም እኔ ነኝ ትክክል ይላል ! እንግዲያውስ ማንም ወንድሙን ማሳመን መቻል አለበት ::
እዲህ ያሉ የአመለካከት ልዩነቶችን በመቀበል መወያየትን አምናለሁ እንጂ ከዚህ የተነሳ ሰዎችን መጥላት መቀየም የኛ ባህርይ መሆን የለበትም እላለሁ::
ከበፊት ጀምሮ በእውነታውች ላይ ስንነጋገር ያለህን አስተያየት በጥሞና ነው የማነበው በዚህም ያለህን አመለካከት ከልብ አደንቃለሁ::
በተረፈ ፖለቲካ እንድናወራ ፈልጌ ሳይሆን የቅሬታ ሰው አለመሆንህ ደስ ስላለኝ ይበልጥ እንደምወድህ ለመግለጽ ፈልጌ ነው::
ሁላችሁንም እወዳችኋለሁ !
ቸር ያቆየን ወዳጃችሁ አደቆርሳ ዘሃገረ አዶላ
Bale-Suk
ጀማሪ Starter
ጀማሪ Starter
Posts: 11
Joined: 28 Mar 2013 12:27
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Bale-Suk »

ሰላም ሰላም
እንደመን አላቹልን
የአባባ አለማየሁ እና የጋሽ ታምራትን እረፍት በሃዘን ነው ያነበብኩት... እዚህም ቤት እዚያኛውም ቤት
አምላክ ለቤተሰቦቻችው ጥሰናቱን ይስጥልን
አንፈራራ... አስቴርን ቶሎ አስነብበኝ ባክህ
ሳላቃት አልቀርም... ልቤ ጠርጥሮዋል
ሌሎቹንም መጥሳፎችህን ቶሎ ጨራርሳቸውና አስነብበን
ራስብሩ... ብለህ ብለህ ሳታስፈቅድ... አትላንቲክን መሻገር ጀመርክ?
ህምምምምምምምምምምምምምምም
ለመሆኑ ነበረች ወይ የቀበሌአችን ልጅ?
ከሶአ ጋር ከሆነ... እሰይ እሰይ
የግልን አገኘሃት ወይ?
ምነው አውራን እንጂ የምን ዝም ዝም ነው
አደቆርሳዬ... እንደምን አለህ ወዳጄ
ጥሰጋዬ መርጊያ ከደርጉ ጋር ቢሮ ሰርቶአል ነው ምትለን
ጋሽ ታምራት ከምር ግን እዛ ድረስ የመድረስ አቅም ነበረው እንዴ?
እንዴት ነው ነገሩ
እኔ እኮ ማስታውሰው... 7ኛ ክፍል አማርኛ ሲያስተምረኝ ብቻ ነው
ወይ ጉድድድድድ
ለካስ በኢሰፓኮ እና በኢሰፓ ነው የተማርኩት
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ነፍስ ይማር
አምላክ ለቤተሰቡ መጥስናናትን ይስጥልን
አሚን
Post Reply

Return to “የጀምጀም ልጆች መገናኛ”