የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Forum rules
No cursing, bad language and offend other users !
No pornographic images or links!
This forum monitored regularly. We will BAN users without warning for not obeying rules.
እባክዎ የፎረሙን ህጎች ያክብሩ::
kasa
Posts: 4
Joined: 15 Mar 2012 16:26
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread postby kasa » 12 Apr 2012 15:38

Imageለአንፈራራ ም ሆነ ለጀምጀም ልጆች መገናኛ ማህበራዊ ርዕሶች ተሳታፊዎ ም ሆነ ጎብኚዎች መልካም የትንሳዔ በዓል ይሁንላችሁ !! እኔንም ጨምሮ !
አንፈራራ ባዶ ቤት ብቻ የከረምኩ መሰለህ ? ቁንጫውን ም ችዬ መርፌዬንም አሹዬ እግሬ ስጠብቅ ነው በተስፋ የቆየሁት እናም ይኸው በጌታ ትንሳዔ ባዶ ቤቱ

ተንኳኳ ተጽናናሁ::

የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትርአርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ማረፋቸውን ስሰማ እጅግ በጣም ነው የደነገጥኩትም ያዘንኩትም በአንድ ወር ውስጥ ሀገራችን 3ስት ምርጥ ልጆቿን አጣች ስብሃትን ማሞ ውድነህን ሎሬት አፈወርቅ ተክሌን ለእኔ 3ቱም በህይወቴ ውስጥ የሩቅ መምህሮቼ እና ተፅዕኖ ፈጣሪዎቼ ነበሩ

እግዜር በገነት ያኑራቸው ::

አደቆርሳ
Jogger
Jogger
Posts: 45
Joined: 13 Jan 2012 04:13
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread postby አደቆርሳ » 12 Apr 2012 16:59

ኅማማተ ኃሙስ ጌታችን እንግልቱን እየተቀበለ ያለበት ወቅት ነው የአትክልቱን ስፍራ ጌቴሲማኔን በኅሊናዬ ስቃኝ የሆነ ልዩ ስሜት ይሰማኛል:: የደስታ ስቃይ !
ለጽድቅ የምንራበው ርሃብ
ለፍቅር የምንከፍለው መስዋዕትነት
ለህግ በመገዛት ራሳችንን ስንገታ የሚሰማን የአሸናፊነት ስሜት ...... እኔ በውነት መግለጽ ይቸግረኛል::
እየሱስ ስለ እኛ ጽድቅ ራሱን አሳልፎ ሲሰጥ ምን ያህል ኩራት ሊኖረን ይገባል ???? በጣም ብዙ ማለቂያ የሌለው ኩራት !
ከትናንት ጀምሮ እስከ እሁድ ሌሊት ሶስት ሰአት ድረስ ኅማማት ነውና መከራውን እያሰብን መቆየት ይገባናል::


አንፈራራችን እንዴት አለህ ? እኔኮ የዚህች ቤት ፍቅር እንዳሰከረኝ ነው እንደው ቤተሰቡ ሁሉ እንደ ይሁድ ተበትኖ ለማሰባሰብ ተቸግሬ ነው እንጂ ያለኝ ፍቅር የሚቀዘቅዝ አይደለም ስለዚህ በኔ በኩል ኢንሶዳቲን !
የካሳ አባባል አስቆኝም ገርሞኝም ነው ብቅ ያልኩት <<<< መርፌዬን አሹዬ ቁንጫውን ስጠብቅ ነው የቆየሁት >>> ይለናል ቅቅቅቅ ቁንጫ ድሮ ቀረ ዛሬ ቁንጫ ምን ሊበላ ይመጣል ብለህ ነው ?
ከምር ግን ቁንጫ ክብረመንግሥት እንደድሮው የለም : ድሮ እኮ እጃችን ውስጥ ሁሉ እየገባ ያስቸግረን ነበር ቢያንስ በሳምንት አንድ ሁለት እጄ ውስጥ ትገባብኝ ነበር ዛሬ በሁለት ወር አንድም እጅ ውስጥ አትገባም:: ለምን እንደሆነ በውነት አላውቅም ድሮ ከተማ አካባቢ የሚኖር ሰው ጫማ ከሌለው እግሩ ዋጋ የለውም: ሆዴ የሚባል አንድ ሰው ነበረ ሙየሌ ሲያስቸግረው ከባድ መኪና የቆመበት ሄዶ ከየጥጉ ላይ ግራሶ ይጠራርግና እግሩን በደንብ አድርጎ ይቀባዋል ሌሊቱን ፍንድትድት ብሎ ያድራል ነገር ግን እግሩ ይቆስልበት ነበር ምናልባት ግራሶው ሙየሌውን ይፈነቅለዋል ለእግሩ ግን ጥሩ አልነበረም ማለት ነው::
ካሳ ከዛሬ በኋላ አምበረጭቃ ይዘህ ቁጭ በል ሙየሌ መርፌ አትፈራም::

ስለ ተከበሩ ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ የተሰማግህን ጥልቅ ሃዘን ስትገልጽ ከታች የደራሲ ስብሃት ገብረእዚአብሄርን እና የደራሲ ማሞ ውድነህን ስም አንሰተሃል ::
በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ስራቸው ምትክ ያገኛል ብዬ የማላስባቸው ሶስቱም ድንቅ ኢትዮጵያውያን ናቸው::
ስብሃት ከቅርብ አመታት ወዲህ በር ተዘግቶ የሚነበብ መጽሃፉን ለንባብ ካበቃ በኋላ ጽሁፍ አንብቦ የማያውቀውን ሬሳ ሁሉ ቀስቅሶ እንዲያነብ ማድረጉን ተመልክተን ትውልድ ቀስቃሽ አርቲስት ብለነዋል::
ማሞ ውድነህ ከጻፋቸው መጻህፍት ውስጥ
የበረሃው ተኩላ : የስድስቱ ቀን ጦርነት ...... ታሪካቸውን እንደ ቤተሰብ ታሪክ የማንረሳቸው ሆነው በውስጣችን የተቀረጹ የማሞን ትርጉምና ወጥ ስራዎች አስታውሼም አልጠግባቸውም እነ ፊልድ ማርሻል ሮሜል እነ ፒተር ሚለር እነ ሞሼ ዳያን እና ሌሎችም የደራሲ ማሞ ቤተሰቦች ናቸው::
ሰላይነት እና የመንግሥታት ጦርነትና ጦረኞች ምን እንደሚመስሉ በማሞ ውድነህ መጻህፍት ውስጥ አይናችንን ገልጠን ተመልክተናል::
ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ በግለኑሯቸው በኩል ልጅ ያልነበራቸውና ጀንደረባ መሆናቸውን ሰምተን ያደግን ብንሆንም በይበልጥ ከስማቸው ባሻገር ያለውን እሳቸውን ያወቅነው ስራዎቻቸውን ማየትና ማድነቅ ከቻልን (ከቻልኩ) በኋላ ነው::
አርቲስት አፈወርቅ ግርማዊ ጃንሆይን ግብዣ ይጠራሉ
ጃንሆይም በሰዓቱ ቤት ይደርሳሉ ጉብኝት ይጀመራል
የሥዕል ማዕከሉን ከተመለከቱ በኋላ
ወደ መኖሪያ ቤትና እልፍኝ ያመራሉ ከዛም ይህ መኝታ ቤት ነው ይህ እልፍኝ ነው እያሉ ሲያስጎበኙ ሳለ አንዱን ክፍል ከፈት አድርገው ይህ ደሞ የልጆች መኝታ ቤት ሲሉ ጃንሆይ እያሽሟጠጡ.... ድንቄም የልጆች ክፍል እሱንስ ተወው !! አሉ ይባላል:: ሌሎችም ብዙ ብዙ የምንሰማቸው ነገሮች ነበሩ::
አርቲስቱ በኢትዮጵያ አብያተ ቤተክርስቲያናት በቤተ መንግስትና በተለይም በአፍሪካ አንድነት ድርጅት የሚገኙት ስዕሎቻቸው በሃገሪቱ ውስጥ አሻራዎቻቸውን ካሳረፉባቸው ጥበቦች ቀዳሚዎቹ ናቸው::
አርቲስት አፈወርቅ የኢትዮጵያን ስነጥበብ ከማሳደግ ከመርዳትና ከመደጎምም አንጻር የነበራቸው ዕገዛ አናሳ እንደነበረ ከዚህ በፊት በቤታችን ውስጥ ተጽፎ አንብቤያለሁ ::
እንደኔ እምነት ግን አርቲስት አፈወርቅ በኢትዮጵያ የስነጥበብ ቀንዲል ናቸው::
ቸር ያቆየን ወዳጃችሁ አደቆርሳ ዘሃገረ አዶላ

ሞፊቲ
Jogger
Jogger
Posts: 33
Joined: 03 Jan 2012 14:19
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread postby ሞፊቲ » 13 Apr 2012 16:33


ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን::

ለምወዳችሁና ለማከብራችሁ የዚህ ቤት ታዳሚዎች! መልካም የፋሲካ በዓል እንዲሆንላችሁ ፍጹም በሆነ ፍቅር እመኛለሁ::

ወደዚህ ቤት ለመምጣት መንገድ ስጀምር ያ ጎሳ የሚሉት አብሮ አደግ ወንድሜ በጥንቱ ቤት እያስቀረኝ ትንሽ ጠፋ በማለቴ ይቅርታችሁን ጎንበስ ብዬ እቀበላለሁ::

በ ሎሬት አፈውርቅ ዙርያ ያቀረባችሁትን ምግብ መቋደሴን እየገለጸኩ የ እረፍታቸውን ዜና እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሃዘን መቀበሌን መንገር የሚያስፈልግ አይመስለኝም::

ለኢትዮጵያ ህዝብ ያወረሱትን ስራዎቻቸውን ያሁኑ መንግስት ምን ያህል ጠብቆ ሊያቆይልን እንደሚችል ማሰብና መጨነቄን በአጋጣሚው ሳልናገር ማለፍ አልፈለኩም::

ስጋቴ አሁን ያለው ጸረ ኢትዮጵያዊው መንግስት የሃገራችንን ታሪክ ከማውደምና ከማጥፋት ባሻገር ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር እንዳትኖር ሌት ተቀን የመልፋቱን ያህል እንደ ሎሬት
አይነት የሃገር ሃብት ከ 60 አመት በላይ የለፉበትን ስራዎቻቸውንና ልዩና ውብ የሆነው የሞኖርያ
ቤታቸው( ሙዝየም)ን ለ ህዝባቸው አውርሰው የማለፋቸውን ያህል ይህን የሚጠብቀውና የሚያስፈጽመው
የሃገሪቱ መንግስት ቢሆንም አሁን ያሉት ተኩላዎች በዚህ መልኩ እምነት ስለማይጣልባቸው ስጋቴ እርግጥ መሆኑን እንድትረዱልኝ እፈልጋለሁ::::::

መልካም ፋሲካ!!

ቸር እንሰንብት!!!!!

ራስብሩ
Starter
Starter
Posts: 23
Joined: 03 Jan 2012 09:45
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread postby ራስብሩ » 14 Apr 2012 13:00

እንኳን ለጌታ ትንሳዔ በሰላም አደረሳችሁ ! መልካም ለተመኛችሁም ሁሉ ምስጋናዬ ይድረስልኝ::
ወድንማችን ካሳ እንኳን በደህና መጣህ ቤት ለእምቦሳ ብለናል ::
እጅግ የተከበሩ የአለም ሎሬት አፈወርቅ ተክሌ ዜና እረፍት አሳዛኝ ነው :
ማንም ሰው ከዚህ እረፍት አይቀርምና ከሳቸው ሞት በኋላ እኔንም ያሳስበኝ የነበረው ሞፊቲኮ የተናገርከው ነገር ነው ::
በጣም ደስ የሚለው ነገር ግን ያላቸውን የጥበብ ስራዎች በሙሉ ለሃገር ቅርስ አውርሰው ስለነበር በህይወት እያሉ ከህዝብ ምስጋናን አግኝተዋል::
ምናልባት ወደፊት ሊያሳዝን ይችላል የምለው አርቲስቱ ያላቸው የግል ስቱዲዮ የስነጥበብ ትምህርት ቤት እንኳን ሩቡን አያክልም
በሺዲዮ አይቼዋለሁ በጣም ልዩ ነው ::
ወደፊት እንደሳቸው አድርጎ ሊጠብቀውና ሊይዘው የሚችል ይኖራል ብዬ አላስብም :ምክንያቱም ከዚህ በፊት ብዙ ብዙ አሳዛኝ የታሪክ ማጥፋት ሁኔታ አሳልፈናል:
አርቲስቱ መሞታቸው እንደተሰማ ወዲያው አልፋ ሺላ በጥበቃ ስር መዋሉ አግባብ ያለው ነው ጥያቄው ወደፊትስ ? የሚለው ይሆናል :

እግዚአብሄር ነፍሳቸውን ይማር !
መልካም ፋሲካ


ራስብሩ

kasa
Posts: 4
Joined: 15 Mar 2012 16:26
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread postby kasa » 15 Apr 2012 11:40

Image መቼም የሃገሬ ልጆች እንግዳ መቀበል እና ማልመድ ስትችሉበት ልዩ ናችሁ ለሁላችሁም ላደረጋችሁልኝ ወንድማዊ አቀባበል በድጋሜ ከልብ አመሰግናለሁ መልካም የፋሲካ በአል !
እጅግ የተከበሩ የአለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ዜና እረፍት አስደንጋጭ ነው ከዚህ በሆዋላ
ጥበበኛው ጥበብ ሰርቶ ጥበብ ለብሶ ከነግርማ ሞገሱ ባናየውም የጥበብ ስራው ከነ ባንዲራችን እስከ ጨረቃ ነውእና እንፅናናለን:: በነገራችን ላይ ራስ ብሩ ውስጥ እሰኔ ሰመሮ ጌድዮን እና አበበ አካሉ ወዘተ ጎበዝ
ሰዐሊዎች ነበሩ እኔም ካሳ ስዕል ባልሰራም ክፉኛ የስዕል ዛር አለብኝ የጥበብ አዶከብሬ ሲነሳብኝ አይጣል
ቀለም ቀለም ሸራ ሸራ ብሩሽ ብሩሽ ምን ነበረበት አሁን በርካሹ የሚገኘውን አርቲ ሎሚ ቢያሰኘኝ ቢጠፋ ቢጠፋ ከአዶቆርሳ አይጠፋ አዶቆርሳዬ ድሮ አንተ ሰፈር አስር አለቃ ሰፊሳን ተዋቂ ወጌሻውን ክብረትን
ሲሳይ አየለን አንበሴ ወንድሙ ሃይሉን ስኞር ቫይ እና ሰንቲኖን ጭምር 12ቱን ዶቅማዎችንም አውቃቸዋለሁ በሉ ዛሬ ፋሲካ ሰለሆነ ይኸው በአመት አንደየ ስጋ በልቼ ከየት አመጣኽ ይሁን እንደ ቻይና ሞባይል ሪንግ ቶን እየጮኸብኝ ስለሆነ በስኒ በምትሰፈረዋ ነገር ፀጥ ላደርገው ሄጃለሁ በበአል ቀን ጩኸት
አይፈቀድም !! ቂ ቂ ቂ ቂ ቂ ሰላም ሁኑልኝ

ካሳ ከሻኪሶ

አደቆርሳ
Jogger
Jogger
Posts: 45
Joined: 13 Jan 2012 04:13
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread postby አደቆርሳ » 22 Apr 2012 16:29

10 አለቃ ሰፊሳን ካላወቅኩማ ማንን አውቃለሁ ወዳጄ ካሳ የአካባቢው ሰው እንደነበርክ አልተጠራጠርኩም::
አስር አለቃን ዓመላቸውን ጸባያቸውን አሳምሬ አውቃለሁ ከአስቴር ጋር አንድ ላይ አብረን ተምረናል:: የሚገርመው በእርሳቸው መኖር ብቻ
ያ እሳቸው የሚኖሩበት አካባቢ ከከተማው ተለይቶ የራሱ አስተዳደር የነበረው እስከሚመስል ድረስ ተሰሚነት ነበራቸው:: ክብረት ወጌሻውን
ስትል ደሞ ይሄ ሰውዬ ሊነካኝ ነው እንዴ ? አልኩና በብዙ ትዝታ ሳቅ አልኩ : የ9 ብር በግ ስብራት በ12 ብር ወጌሻ ተጠግና መዳኗን ታውቃለህ ?
ካላወክ አጫውትሃለሁ::የጠራህልኝን አንድ በአንድ ነው የማውቃቸው በተለይ የሃይሉ ድርቅናና ኮሚክነት በልጅነቴ ከማውቃቸው
ኮሚኮች ትልቅ ስፍራ የሚይዝ ነው ድሮማ ሳየው ቀርቶ ሳስበውም እስቅ ነበር ሌሎችም ብዙ የራስብሩ ተማሪዎችም ከአደቆርሳ
የፈለቁና ከፍ ወዳለ ደረጃ የዘለቁ አሉ ::
የገረመኝ ሲኞር ቫይ አልዶን እና ሲኞር ሴንቲኖን ማስታወስህ ነው::
ሲኞር ቫይ የፋብሪካው ባለቤት ነው : ሲሞት ልጅ ብሆንም በደንብ ትዝ ይለኛል አሟሟቱም ድንገተኛና አሳዛኝ ነበረ::
የአካባቢው ሰው ሁሉ በቫይ መሞት እጅግ አዝኖአል
ሲኞር ሴንቲኖ በጣም የታወቀ መካኒክ ነው :ቫይ የሚነዳትን ሬንጅሮቨር መኪና ጨምሮ የራሱንም ፊያት የፋብሪካውን ላንድሮቨሮችም
የጭነት ካሚዮኖቹንም ምናምናቸው ሳይቀር የሚጠግናቸው ሴንቲኖ ነው::
ሴንቲኖ የፋብሪካውም ዋና መካኒክ ነው እንደውም ከተልተሊኖ ይበልጣል የሚባል ነገርም እንሰማ ነበር::
ስለ 12ቱ ዶቅማዎች ስታነሳ ሸረፋን አስታወስከኝ መቼም ሸረፋን የማያውቅ አይኖርም :
በነገራችን ላይ ሸረፋ ትልቅ ታሪክ ያለው ልጅ ነው :ትምህርቱን አቋርጦ ወደ እርሻ እንደገባ የተሳካለት ገበሬ ሆኗል
እዛው ዶሌ ትልቅ ቤት ሰርቶ ጥሩ የጫት ምርት አቅራቢም ነበር : የተማረና ቀለም የገባው ልጅ ስለነበረ የግብርናው ስራ ምንም አላስቸገረውም አሁንማ እርግጠኛ ነኝ አያት ይሆናል::
ታዲያ ተማሪ እያለ ተንኮለኛም ነበር አንድ ቀን ዶቅማ አራግፈን እኔና መዱካ ቁጭ ብለን በዘምቢል ሞልተን ስንበላ ገርሞት ይሄንን ዘምቢል ሙሉ ልትበሉት ነው ? ሲለን አዎን አልነውና ተናደደ
ብትሸጡት እኮ አንድ ብር ታጣሩታላችሁ ከአስር ዛፍ ብትሸጡ ደሞ 10 ብር አላችሁ
ካልፈለጋችሁ ደሞ ልክ እንደዚህ አርጋችሁ ጥሬ የሌለበት ከለቀማችሁ ዘንቢሉን ሽልንግ ሽልንግ ገዛችኋለሁ ሲለን ብድግ አልንና ከዛፍ ዛፍ እየዞርን ማራገፍ ጀመርን ሳር ላይ እየከመርን እንደምንም አምስት ዘምቢል እንደሞላን ስንደምረው ሁለት ብር ከሃምሳ መቼ ልንጨርሰው ነው በቃን ተባባልንና
ሸረፋን ጠርተን በል ሁለት ከሃምሳ ስጠን ስንለው የለቀምነውን አየና ጥሬ አታርጉበት አላኩም አይሆንም ? ደሞ ቅጠልም አለበት ምናምን እያለ እንደውም አልገዛም ብሎን ጥሎን ሲመለስ በጣም ተናደድን ከዛ እንደገና ያዘነልን መስሎ መጣና በሉ እንኩ ብሎ 75 ሳንቲም ሰጥቶን አምስት ዘንቢል ዶቅማ ወሰደ : ትልልቆች ሆነንም ብር ከሰባ አምስታችንን አታመጣም እንለው ነበር::
ወዳጄ ካሳ እንደው የክብረመንግስት ቤት ነገር ሆኖ ነው እንጂ ጨዋታችን ያለሞራል ነው ::
በሳምንት አንዴ እንኳ ብቅ የሚል የሌለበት ቤት ውስጥ ብቻዬን ምች ስለሚመታኝ ፈራለሁ እኔ ደሞ ምች ይወደኛል ትንሽ ግራ የሚገባኝ ምን መሰለህ ? ብቅ ብቅ እያሉ ከጠፉት ልጆች የበለጠ ይሄንን ቤት የሚወድና እና የሚጽፍ እንደሌለ ስለማውቅ ምክንያታቸው ለነሱው ይቀመጥና እኔና አንተ ብቻ በእንደዚህ ያለ ሁኔታ የምንዘልቅ አይመስለኝም:
የምወድህና የማከብርህ አንፈራራችን ፍቅረኛዬ ባለሱቅ ልቤ ሞፊቲኮ አካሌ ራስብሩ ኩላሊቴ ኦዶ እንዲሁም ገላዬ ካሳ ሌሎቻችሁም ሁሉ አምላክ በቸርነቱ ያቆያችሁ : ዛሬ ዳግም ትንሳዔ ነው (ዳግማትንሳዔ)እንኳን አደረሳችሁ !
ቸር ያቆየን ወዳጃችሁ አደቆርሳ ዘሃገረ አዶላ

አንፈራራ
Runner
Runner
Posts: 50
Joined: 03 Jan 2012 12:51
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread postby አንፈራራ » 23 Apr 2012 10:09

ውድ የጀምጀም ልጆች
የክብረ መንግስት ልጆችና አካባቢዋ መሰብሰብያ የነበረው ዋርካ ጄነራል አጸያፊ የሆኑ መልክቶቹን እያስተናገደ ለ ሁለት ዓመት ያህል ከዘለቀ በኋላ ብዙዎቻችን እዚያ ቤት ላለመለስ ቆርጠን ሌላ ቤት ስንፈልግ ይህን አገኘን::

ከብዙ አንጻር ይህን ቤት ከዋርካ ጋር ስናነጻጽረው በጣም የበለጠና የተሻለ ነው:: በቀላሉ በአማርኛ መጻፍ ይቻላል ፊደሎቹን ከፍና ዝቅ ማድረግ ይቻላል፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ ፎቶዎችንና ቪዲዮችን ማስገባት ይቻላል፣ በዚያ ላይ ኢሳትን፣ ኢቲቪን፣ ቪኦኤን፣ የጀርመን ሬዲዮንና ሸገር ሬዲዮን በቀላሉ ለማግኘት እንድንችል አመቻችቷል:: ከነዚህ ሁሉ አንጻር ሲታይ ኢትዮፎረም ከዋርካ በጣም የተሻለ ነው::

ግን ምን ያደርጋል? ሰው ያኛውን ቤት ከነምናምኑም ስለለመደው ወደዚህ መምጣት ተሳናቸው::
በጣም የምንወድህና የምናከብርህ አደቆርሳ ለዋርካም ሆነ ለዚህ ቤት አንተ ነበርክ ሞተሩ አሁንም እስቲ አንድ ቀን እንደገና ከዚህ በፊት ከ 3 ከ 4 ዓመት በፊት እንደነበረን ውይይት እንመለስ ይሆናል:: እስከዚያው ሰላም ሁን:: ውድ ወንድሜ ካሳ አንተም ሊመሽ ሲል መጥተህ ብዙም እራት አልተረፈህም:: ፡) ካንተም ጋር ሌላ ግዜ እንደምንገናኝ ተስፋ አለኝ:: በተረፈ ባለሱቅ ራስብሩ ሞፊቲ ለሁላችሁም መልካም ጊዜ::

ሞፊቲ
Jogger
Jogger
Posts: 33
Joined: 03 Jan 2012 14:19
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread postby ሞፊቲ » 23 Apr 2012 17:18

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን::

አንፈራራና አደቆርሳ ምርር ያላችሁ ይመስላል::
እውነት ለመናገር ያኛውም ቤት ቢሆን የጎሳ መምጣት እንጂ እንደድሮው ሙቀት የሚሰማው አይደለም::
ሁላችንም በስንት ግዜ ነበር ብቅ የምንለው?
ዋርካ ድሮ ቀረ ብሎ ብቻ ዝም ማለቱ ይሻላል::


እዚህ ቤት ያለው ምቾት እንደተጠበቀ ሆኖ ለረዥም ግዜ የለመድከውን ሰፈር ለመቀየር ወይም ከኖርክበት አካባቢ ወደ ሌላ አካባቢ ሄደህ ለመለማመድ የሚኖርህ አይነት ጭንቀት ያለውም ሰው
ሊኖር ይችላል::ዋርካ አሁን ጥሩ ሁኔታ ላይ ናት ብንል እንኳ ወደፊት የዛው አይነት ተመሳሳይ ብልግና ሊፈጸምባት አይችልም ብለን የምናረጋግጠው ነገርም አይኖርም::


በኔ በኩል ዋርካ ውስጥ አዲሱ ልጅ ጎሳ የሚያነሳቸው ነገሮች ከ 70% በላይ እኔንም ስለሚመለከቱ ግዴታ ማድነቅ መንቀፍ ማውራት ስላለብኝ የግድ ቀልቤ ተስቦአል::
በተቻለን መጠን ወደ አንድ መድረክ የምንመጣበትን መንገድ ለማመቻት አንድ ኮንፍረንስ ቢኖረንና ብንነጋር መልካም ይመስለኛል::


ልቤ ከዚህም ከዛም ነው::ሁላችሁም ለኔ ፍቅር ናችሁ::ሁላችሁንም ማጣት አልፈልግም::
ግን ሁላችንም ቅን እንሁን ::
ፕሊስ ቅን እንሁን::


ቸር እንሰንብት::Return to “የጀምጀም ልጆች መገናኛ”