ዓለም አቀፍ እውነታዎች

ግጥሞች፣ታሪኮች፣ፎቶዎች፣ሙዚቃዎች
Poems,Short stories, graphics,pictures,musics,Technology
User avatar
selam
Leader
Leader
Posts: 175
Joined: 25 Aug 2009 01:59
Contact:

ዓለም አቀፍ እውነታዎች

Unread post by selam » 08 Jan 2010 18:24

ዓለም አቀፍ እውነታዎች

  - በዓለም ላይ በግዙፍነቱ ተወዳዳሪ የሌለው ትልቁ መፅሐፍ 31ሺ ኪሎ ግ ራም 310 ኩንታል ክብደት ያለው ሲሆን መፅሐፉን ለመጠረዝ የ34 ሺ ፍየሎች ቆዳ ፈጅቷል፡፡ ይህንን መፅሐፍ

  አንብቦ ለመጨረስ ብቻ 6 ዓመት ይፈጃል፡፡


  - በዓለም ላይ በግዙፍነቱ ተወዳዳሪ የሌለው ትልቁ መፅሀፍ ቅዱስ የሎስአንጀለስ አናፂ ለሁለት ዓመታት ቀንና ሌሊት ከእንጨት ሰርቶ ያዘጋጀው መፅሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ የዚህ መፅሐፍ ቅዱስ እያንዳንዱ ገፅ ከ3 ጫማ በላይ ርዝመትና 8.048 ጫማ ውፍረት አለው፡፡
  - በዓለም ላይ በትንሽነቱ ተወዳዳሪ የሌለው ትንሹ መፅሐፍ ቅዱስ በእንግሊዝ ሃገር የታተመው ሲሆን መጠኑም የአንድ ክብሪት ሳጥን ያህላል፡፡ በውስጡም 878 ገፆችና በርካታ ስዕሎች አሉት፡፡ ይህ መፅሐፍ ቅዱስ የሚነበበው በአጉሊ መነፅር ብቻ ነው፡፡
  - በዓለም ላይ ከሚገኙት ጎሳዎች ሁሉ በቁመታቸው ረጃጅም የሚባሉ ጎሳዎች በማዕከላዊ አፍሪካ ክልል በሩዋንዳና ቡሩንዲ የሚኖሩት የቱትሲ ጎሳዎች ናቸው፡፡ የቁመታቸው አማካይ ርዝመትም 1 ሜትር ከ83 ሳንቲ ሜትር ነው፡፡
  - በዓለም ላይ ከሚገኙት ጎሳዎች ሁሉ በቁመታቸው አጫጭር የሚባሉት ጎሳዎች በቀድሞዋ ዛየር በአሁኗ ዲሞክ ራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚኖሩት የፒግሚ ጎሳዎች ናቸው፡፡ የቁመታቸው አማካይ ርዝመትም የወንዱ 1 ሜትር ከ37 ሳ.ሜ ሲሆን የሴቷ ደግሞ 1 ሜትር ከ24 ሳ.ሜ ነው፡፡
  - በዓለም ላይ እስከ አሁን ከተሰሩት ፊልሞች ውስጥ በጣም በርካታ እንስሳት የተሳተፉበት ብቸኛው ፊልም#Around the World in 80 days$የተባለው ፊልም ሲሆን በዚህ ፊልም ላይ 4 ሰጎኖች፣ 15 ዝሆኖች፣ 17 በሬዎች፣ 512 ዝንጀሮዎች፣ 800 ፈረሶች፣ 950 አህዮች እና 2448 ጎሾች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
  - በዓለም ላይ ካሉት ሴቶች መካከል በህፃንነቷ አርግዛ በመውለዳ ስሟ ለዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ የተመዘገበችው ሴት የፔሩ ዜጋ የሆነችው ሊና ሜዲና ትባላለች፡፡ ሊና ሜዲና አርግዛ የወለደችው የ5 ዓመት ልጅ ሳለች ነው፡፡ ሊና የ10 ዓመት ልጅ ሳለች ልጇ ደግሞ የ5 ዓመት ልጅ ስለነበረች እናትና ልጅ የተማሩት አብረው በአንድ ክፍል ውስጥ ነው፡፡
  ቴዎድሮስኃይሌKNH)

  Post Reply

  Return to “Ethio Art and Culture..ኢትዮ ጥበብ ፤ስነ ጽሁፍ ፤”