ተረት ናምሳሌ-የፈላሰፎች ንግግር

ግጥሞች፣ታሪኮች፣ፎቶዎች፣ሙዚቃዎች
Poems,Short stories, graphics,pictures,musics,Technology
mary
Starter
Starter
Posts: 16
Joined: 21 Sep 2009 02:44
Contact:

ተረት ናምሳሌ-የፈላሰፎች ንግግር

Unread post by mary » 25 Dec 2009 08:40

የፈላስፎች ንግግር

ሀብታም ይደኸያል ሀኪምም ይሞታል
ጎበዝ ይሸነፋል ብልህ ይሳሳታል
የበራውም ጠፍቶ የሰሩት ይፈርሳል
የቆመውም ወድቆ የሳቀ ያለቅሳል
ጌጥም ሆነ ጥበብ ውበት ሆነ ክብርም
ያማረበት ነገርማስቀየሙ አይቀርም።
*
ፍሬ መሬት ወድቆ ከዋለ ካደረ
ሰው ገንዘብ አግኝቶ መክበር ከጀመረ
የመጣ ነውና ቀድሞውን ከጥንት
ሁለቱም አይድኑ ከመበላሸት።
*
የሰዎችን ጠባይ የተመራመረ
አንድ ፈላስፋ ሊቅ እንዲህ ተናገረ
በጣም በማስተዋል ከላይ እስከ ታች
ስመለከታቸው የሰውን ልጆች
እያጣሁባቸው ግብሩ እሚመሰገን
እንቃቸው ጀመር እጅግ ያለመጠን።
*
የደንቆሮ መንፈስ ምንኛ ታደለ
ብልጥነት አላጣም ጅል እየመሰለ
እንኳን መፅሃፍ ማንበብ ፊደል ሳያጠና
ሁሉንም ያወቀ ይመስለዋልና።
*
የሊቅ ሰው መከራ የብልህ አባዜ
ሲጨነቅ መኖር ነው ባሳብ በትካዜ
አቶ ዐሳበ ቢስ ይተኛ ዝም ብሎ
ከትራሱ ጋራ ዐሳቡን ጠቅልሎ።
*
ኩራትና ትእቢት የሞሉት አናት
ሰይፍና ጎራዴ የመቱት አንገት
አይገላገሉም እንዲህ በቀላሉ
እመሬት ላይ ወድቀው ሳይንከባለሉ።
*
ገንዘብ መፈጠሩ ለሰው አገልጋይ
ሆኖ ሊሰራበት አልነበረም ወይ
አሁን ግን መስገብገብ በጣም ስለበዛ
ሰው ባሪያ እየሆነ ለገንዘብ ተገዛ።

Post Reply

Return to “Ethio Art and Culture..ኢትዮ ጥበብ ፤ስነ ጽሁፍ ፤”