ተረትና ምሳሌ አንደኛመፅሃፍ

ግጥሞች፣ታሪኮች፣ፎቶዎች፣ሙዚቃዎች
Poems,Short stories, graphics,pictures,musics,Technology
mary
Starter
Starter
Posts: 16
Joined: 21 Sep 2009 02:44
Contact:

ተረትና ምሳሌ አንደኛመፅሃፍ

Unread post by mary » 21 Dec 2009 02:28

ሞት ሁሉን እኩል ያደርጋል

ሀብታምና ድሃ ሞተው ሲቀበሩ
መቃብራቸውን ሰዎች ሲቆፍሩ
እጅግ አርጎ በጣም ስለተቃረበ
ሀብታም ተቆጥቶ እንዲህ ተሳደበ።
ምነው አንተ ድሃ እንደዚህ ደፈርከኝ
ምንስ አንተን ዛሬ ለማጥቃት ቢያውከኝ።
ራቅ እንደማለት እኔን ተመልክተህ
አጠገቤ እንደዚህ በጣም ተጠግተህ
እንዴት ይገባሃል ደፍረህ መተኛት
ተነስ ሂድ አሁንም ከምትሄደበት።
ድሃም መለሰና እንዲህ ተናገረ
አልጋና መከዳ ሲያማርጥ የኖረ።
ያንተ ገላ ነበር ያለቦታህ ገብተህ
የተኛህ አንተነህ አሁንም ተነስተህ
ያን የለመድከውን የምቾቱን ስፍራ
ፈልግ እሌላ ዘንድ እዚህ ከኔ ጋራ
ምን አምጥቶ ጣለህ እኔ ግን ከጥንት
ወትሮም ልማዴ ነው መሬት መተኛት።
ጎበዝ አይል ፈሪ ድሃ ባለጠጋ
ሁሉን አስተካካይ ሞት የሚሉት አደጋ።

ታሪክና ምሳሌ
ክቡር ዶክተር ከበደ ሚካኤል።

Post Reply

Return to “Ethio Art and Culture..ኢትዮ ጥበብ ፤ስነ ጽሁፍ ፤”