ማይክል ጃክሰን ለሞት የሚያደርስ መጠን ያለው መድሃኒት ወስዶ ነበር

ግጥሞች፣ታሪኮች፣ፎቶዎች፣ሙዚቃዎች
Poems,Short stories, graphics,pictures,musics,Technology
Post Reply
User avatar
girreda
Runner
Runner
Posts: 55
Joined: 01 Oct 2009 12:45
Location: Adama University
Contact:

ማይክል ጃክሰን ለሞት የሚያደርስ መጠን ያለው መድሃኒት ወስዶ ነበር

Unread post by girreda » 19 Dec 2009 11:03

ባለፈው ሰኔ ወር ላይ የሞተው የፖፕ ሙዚቃ ንጉስ ማይክል ጃክሰን ለሞት የሚያደርስ መጠን ያለው ከባድ አደንዛዥ መድሃኒት ወስዶ እንደነበር ቢቢሲ ዘገበ፡፡ ዘፋኙ ወስዶታል የተባለው ፕሮፖፎል የተሰኘ ከባድ ማደንዘዣ መድሃኒት መሆኑ ታውቋል፡፡

የሎሳንጀለስ ፖሊስ ለማይክል ጃክሰን ዶክተር፤ ዶ/ር ሙሬይ ቃለ መጠይቅ ያደረገ ሲሆን ተጠርጣሪ ተብለው ግን እንዳልተፈረጁ ዘገባው ያመለክታል፡፡

የማይክል ሞት የተፈጥሮ ሞት እንዳልሆነ የሚገልፁ ሪፖርቶች አሉ፡፡ ይህ በትክክል ያልተረጋገጠ ቢሆንም ኦስሽየትድ ፕሬስ ስሙን ያልጠቀሰውን ፖሊስ እንደ ምንጭ ጠቅሶ ሪፖርቱን ፅፎታል፡፡

ፕሮፖፎል የተሰኘው ከባድ ማደንዘዣ መድሃኒት በቀዶ ህክምና ወቅት የሚሰጥ ሲሆን ጭንቀትንና መረበሽን ለመቀነስም ባነሰ መጠን ሊሰጥ ይችላል፡፡

የማይክል ዶክተር የሆኑት ሙሬይ ምንም የተሳሳተ ነገር እንዳልሰሩ የገለፁ ቢሆንም ባለፈው ወር የዘፋኙን ሞት ተከትሎ የፖሊስ መርማሪዎች ቡድን የዶክተሩን ቢሮዎች ፈትሸዋል፡፡

የጃክሰንን እንቅልፍ ማጣት ችግር ለማከም ፕሮፖፎል የተሰኘውን ማደንዘዣ ሰጥተውት እንደነበር ዶክተሩ ለፖሊስ በሰጡት ቃል አረጋግጠዋል፡፡ ይሁንና ማይክል ጃክሰን በመድሃኒቶች ሱስ ከመጠመድ እንዲወጣ አማራጭ መድሃኒቶችን በመስጠት ሊረዱት ይችሉ እንደነበር መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡

ማይክል በሞተ ማግስት ዶ/ር ሙሬይ ሪፖርት እንዳደረጉት እንደ አማራጭ የተሰጡት ሌሎች መድሃኒቶች አልሰራ ካሉ በኋላ ፕሮፖፎል የተሰኘውን ማደንዘዣ መድሃኒት በትንሹ ሰጥተውት እንደነበር ገልፀዋል፡፡ ሆኖም በተደረገው ምርመራ በዘፋኙ ሰውነት ውስጥ የተገኘው የመድሃኒቱ መጠን ለሞት የሚያደርስ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

ሎስአንጀለስ ታይምስ ከስፍራው እንደዘገበው ዶክተሩ ማደንዘዣውን ከሰጡት በኋላ ስልክ ሊያናግሩ ወጥተው ነበር፡፡ ዶክተሩ ወደ ቤት ሲመለሱም ማይክል መተንፈስ አቁሞ ነበር፡፡[/color][/color]

User avatar
girreda
Runner
Runner
Posts: 55
Joined: 01 Oct 2009 12:45
Location: Adama University
Contact:

ማይክል ጃክሰን ሌላ የቀብር ሥነ ሥርዓት

Unread post by girreda » 19 Dec 2009 11:06

ከአይቮሪኮስት ክሪንጃቦ ከተማ እየተሰማ ያለው የሙዚቃ አቀንቃኙ ማይክል ጃክሰን ከሞተበት ሰኔ 18 ቀን 2009 ጀምሮ ማህበረሰቡ በሐዘን ላይ መሆኑን ነው፡፡
ቢቢሲ ከስፍራው እንደዘገበው የአካባቢው ነዋሪዎች ማይክል ከሞተ አንስቶ እስካለፈው እሑድ ድረስ በሐዘን ቆይተዋል፡፡

"አብዛኛው ዓለም ማይክል ጃክሰንን የሚያውቀው ማይክል ጃክሰን በሚለው ስሙ ነው፡፡ ሆኖም በክሪንጃቦ ማይክል የሚታወቀው ልዑል ማይክል አማላ ማን አያዛህ በሚለው ስም ነው" ሲል ዘገባው አሳውቆ፣ ማይክል ይህን የልዑልነት ስም የተሰጠው በክሪንጃቦ አካባቢ የአንጊ ማህበረሰብ አባላትን በ1984 ዓ.ም. በጐበኘበት ወቅት ነው ብሏል፡፡

ማይክል ጃክሰን (ማይክል አማላማን) ለአንጊ ማህበረሰብ ከ1984 ወዲህ ልዑላቸው ሆኖ የቆየ ሲሆን፣ በምትኩ ሌላ ልዑል ከሠየሙ በኋላ ለርሱ የተቀመጡት ሐዘን ያበቃል፡፡

ኢማኑኤል ካሴ ኮፊን በመጥቀስ ቢቢሲ እንደዘገበው ሚ/ር ኮፊ የአካባቢውን ማህበረሰብ በመወከል የማይክል ጃክሰን አስከሬን እንዲሰጣቸውና በአካባቢው ማህበረሰብ ባህል መሠረት በአገራቸው በወንዝ ውስጥ እንዲቀበር በአቢጃን ለሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ጠይቀው ነበር፡፡

አስከሬኑን ለማግኘት ያልታደሉት አይቮሪኮስታውያኑ "የማይክል መንፈስ ከኛ ጋር ነው፡፡ በሰላምም ማረፍ አለበት" ብለዋል፡፡

User avatar
girreda
Runner
Runner
Posts: 55
Joined: 01 Oct 2009 12:45
Location: Adama University
Contact:

Today's Love Poem

Unread post by girreda » 21 Dec 2009 08:07

Today's Love Poem

There's a woman like a dewdrop, she's so purer than the purest;
And her noble heart's the noblest, yes, and her sure faith's the surest:
And her eyes are dark and humid, like the depth on depth of lustre
Hid i' the harebell, while her tresses, sunnier than the wild-grape cluster,
Gush in golden-tinted plenty down her neck's rose-misted marble:
Then her voice's music . . . call it the well's bubbling, the bird's warble!

And this woman says, 'My days were sunless and my nights were moonless,
Parch'd the pleasant April herbage, and the lark's heart's out-break tuneless,
If you loved me not!' And I who (ah, for words of flame!) adore her,
Who am mad to lay my spirit prostrate palpably before her--
I may enter at her portal soon, as now her lattice takes me,
And by noontide as by midnight make her mine, as hers she makes me!

.....Earl Mertoun's Song by Robert Browning [center][/center]

Daily Love Poems

Post Reply

Return to “Ethio Art and Culture..ኢትዮ ጥበብ ፤ስነ ጽሁፍ ፤”