ሽንፈትን አለመቀበል አሸናፊ አያደርግም!

ግጥሞች፣ታሪኮች፣ፎቶዎች፣ሙዚቃዎች
Poems,Short stories, graphics,pictures,musics,Technology
User avatar
zeru
Leader
Leader
Posts: 952
Joined: 19 Aug 2009 17:01
Contact:

ሽንፈትን አለመቀበል አሸናፊ አያደርግም!

Unread post by zeru » 19 Nov 2014 22:35

ሽንፈትን አለመቀበል አሸናፊ አያደርግም!
(መላኩ የእናት ልጅ)

ይሄ ግን እውነት ነው…?
“ሀበሻ በአገሩ ሽንፈት ይመረዋል
ድል ተደርጎ መግባት ይጎመዝዘዋል
ያንገሸግሸዋል፣ ይቆረቁረዋል፣ ይሰቀጥጠዋል

እንኳንስ በውኑ ተኝቶም በህልሙ
ሰላም ይነሳዋል ኢትዮጵያ ናት ደሙ
ይሄው ነው ሐበሻ ጥቃትን አይወድም
ድል ሆኖ መተኛት ሰውነቱ አይለምድም
ምግብና ውኃ ወደ ሆዱ አይርድም….”
እሺ……….
“እኛ ሀበሾቹ- በጥበበ-አምላክ ጥንት ስንፈጠር
ጀግንነት ተሰጦን ባንዳች ልዩ ምሥጢር
ከኖርን ጀምሮ- ታሪካችን ሁሉ የማሸነፍ ነበር”
እሺ ነበር… በነበር ማን ኖረ?
ያው ማንም አልኖረ ይህ ከራቀን ቆየን
ብቻ አሁን አሁን… ምን ሰይጣን እንዳየን
ከጀግንነት ጣሪያ…ይሄው ወርደን…ወርደን
በብዙ ሜዳዎች- ያልለመደብንን ስንሸነፍ ታየን
እና ምን ይጠበስ….?
ምን ነካው ሀበሻ… ሽንፈቱን ሲነግሩት “ምን ይጠበስ?” ይላል
መሸንፍን ለምዶ አሜን ብሎ ኖረ…? ከሆነ ይገርማል
ያ ጀግና ሀበሻ ለሽንፈት እጅ ሰጠ…? ይሄስ በእውነት ያማል
ቆይ በምን ተሸነፍን…?
“ቆይ ምን ተሸነፍን?” አሁን ይሄ ጠፋን… ታሪክ እንኳን ባናውቅ
ተፈጥሮን የሙጥኝ… ለውጥን አለመሻት… ድህነትና ድርቅ
በታሪክ፣ በክብር፣ በኩሮነት ካባ……. በማይምነት ጨርቅ
ተቀፍድዶ መኖር ውጭውጩን መከበር ውስጥወወስጡን ማማረር
የአደባባይ ምሥጢር የደበቅን መስሎን ተደብቀን ማረር
ይህ ሽንፈት ካልሆነ ቆይ “ሽንፈት ምን ነበር???”
................................
እንንቃበት ጎበዝ!... ይሄ ሽንፈት ማለት
ገዝግዞ… ገዝግዞ… አንዴ የጣለን ‘ለት
መነሳት ያቅተናል ከተዘፈቅንበት!
.............................
Image
Source: Facebook የመልአኩ ገጽ


Post Reply

Return to “Ethio Art and Culture..ኢትዮ ጥበብ ፤ስነ ጽሁፍ ፤”