ሁለቱ ባለ-ቁምጣዎች አአ ሲገቡ

ግጥሞች፣ታሪኮች፣ፎቶዎች፣ሙዚቃዎች
Poems,Short stories, graphics,pictures,musics,Technology
User avatar
zeru
Leader
Leader
Posts: 952
Joined: 19 Aug 2009 17:01
Contact:

ሁለቱ ባለ-ቁምጣዎች አአ ሲገቡ

Unread post by zeru » 29 Aug 2014 11:40


ሁለቱ ባለ-ቁምጣዎች አአ ሲገቡ
======================

“ክላ እዚ ነዉ ምሆን!” አለ አበረ በተጎተተ አማርኛ
“እረ ይቁረጥህ አያ!... እሱ ሶስት ነዉ” ደመቀ ቀጠለ
“ቢሆንሳ!” ግንባሩን ቋጠር አርጎ አቤዉ ተሳፈጠ
“ያእ ብሽቅ!…” ደምሻ ደሙ ፈላ… ከዛም አኮረፈ…
.
.
አቤዉና ደሜዉ የቆሎ ተማሪነትና “ተሜ! የፈስ መዳኒት ስራልኝ?” የሚላቸዉ ሰዉና በየጎዳናዉ የቁራሽ መቀበያ አኮፋዳቸዉን ባየ ቁጥር በሚያንባርቅባቸዉ ዉሻ ስልችተዉ ጥበብ ለምኔ ብለዉ ቀጥታ ወደ አዲሳባ ተሳፈሩ… እንደዉም በገደምዳሜ ስሰማ አቤ አንድ ዉሻ በቆመጡ «ምናባክ ለኔ ያለዉ ላንተ አይሆን!» ብሎ ወገቡን ቢለዉ ዉሻ ሆዬ ባለበት
ቀረ ተብሎ ይወራል…
.
.
አቤ ከልጅነቱ ጀምሮ ያዉራ ጎዳና መኪና እያባረረ ሲንጠላጠል እንጅ ወንበር ይዞ ተሳፍሮ አያዉቅም ነበርና ዛሬ ዛፎቹ ሲሸሹ ወደኋላ እየዞረ እስኪሰወሩት ድረስ ለማየት እንዲመቸዉ ነበር ጥግ መቀመጥ የመረጠዉ… ምን ዋጋ አለዉ ደሜ ቀድሞ አዉቶቢሱ ዉስጥ ድንጉር ብሎ ጥግ ያዘና አልለቅም አላ…
.
.
ሲያስበዉ ግን ዘገነነዉ… መምሬ ይገዙ ስላዲሳባ ሲወሩ የሰማዉ ባህር ነዉ ብለዉ ነዉ… እሱና አቤዉ ደግሞ ካሁን ጀምረዉ ተለያይቶ መቀመጥ አልጣመዉምና
የምንተፍረቱን ዉዳሴ ማሪያሙን ከብብቻዉ እያወጣ “ና በቃ!” ብሎ ሸሸት አለ…
አቤዉ ፊቱ ወገገ…
.
.
«የከበረዉ ያክብርልኝ!» ብሎ በተሜኛ መረቀዉና የፅሐይ መከለያ ጨርቁን ጠቅልሎ አንድ ዛፍ ሲመለከት ወደኋላ እየሸሸ ሲሄድ “ደሜ!... ደሜ!...” አለዉ…
እረ ስለግዚሐር ተወኝ አንተ ሰዉ… ደሜዉ ተቆጣ
ዋዕ! እኔኮ ዛፉ ወደ ኋላ ሲሄድ አይቼ ላሳይህ ነበር… እረ በበዛይት…
.
.
እንዲህ እነዲህ እያሉ እያለ ትኬተሩ ፊታቸዉ መታና ተገተረ…

“ትኬት?” አለና ጠየቀ

“ምንድነዉ እሱ?” ሻል የሚለዉ ደምሻ ቀጠለ… የልጅ ነገር መስኮት ላይ
እንደተንጠለጠለ ነዉ…

“ትኬት ነዋ!”

አቤዉ “እረ ወዲያ ክላ!” አይን ፈጠጠ

ቁንኑ አቤዉ ዘወር ሲል ችግር ተፈጥሯል… ዱላዉን ከእግሩ ስር መዠረጠ

“ምንድነዉ?” አገጩን ወደፊት እያሾለ አቤ ተንጠራራ…

“ትቸት ይላል!” ወስደሀልንዴ አንተ? አንስተህ እንደሆን ስጠዉ…

እረ በእግዝትነ… እመብርሀንን አልነካሁም…ዱላዉ ዝቅ እያለ ነበር…

ትኬተሩም ነገሩ እንዳልገባቸዉ ስለገባዉ ማስረዳት ጀመረ…

“እየዉላችሁ በእንደዚህ አይነት መኪና ስትሳፈሩ ብር ትከፍላላችሁ! እና ያንን ዋጋ ነዉ የጠየቅኩ” አለ

ምን? በጦቢያ መኪና ምናገባህና አንተ… ምን ቤት ነህና? ደሜዉ ደሙ ገነፈለ…
.
.
ይህን ሁሉ ነገር ሲመለከቱ የነበሩ አንድ ጎምቱ ሰዉ ነገሩን ለማብረድ ብለዉ ችግር የለም እኔ እስጥሀለሁ ተዋቸዉ አሉ… ትኬተር ተንዘረዘረ…

“ምናባታቸዉ…” ሲል
“ትንኩሽቱ ደሜ! እንኩዋን ሲነኩኝ እንዲሁም ቅርብ ነዉ ደሜ!” አለና ቆሞ ዱላዉን አቀባበለ…

አቤዉ ነገር አለሟን እረስታ መስኮቷን እያለመች ነዉ…
.
.

ዛጎል የበዛበት ኮትና ቁምጣ ሱሪ እንደለበሱ አዉቶቢስ ተራ ሲወርዱ Gemechu ገሜዉ እንዳገኙት ይወራል… እናጣራታለን ይላል ዝግጅት ክፍሉ… ወራት አለፉ ወራት ተተኩ… ባህሩ አዲስ ከገቡ ይኸዉ ድፍን 2007 ዓ.ም 23ኛ አመታቸዉን ይይዛሉ… ያገኛቸዉ ሰላም ይበልልኝ አደራ!!!

Source:


ሱለይ አደም on Facebook

Post Reply

Return to “Ethio Art and Culture..ኢትዮ ጥበብ ፤ስነ ጽሁፍ ፤”