Abere Vs Demeke በሰባ ደረጃ- በሱለይ አደም

ግጥሞች፣ታሪኮች፣ፎቶዎች፣ሙዚቃዎች
Poems,Short stories, graphics,pictures,musics,Technology
User avatar
zeru
Leader
Leader
Posts: 952
Joined: 19 Aug 2009 17:01
Contact:

Abere Vs Demeke በሰባ ደረጃ- በሱለይ አደም

Unread post by zeru » 29 Aug 2014 11:33


Abere Vs Demeke በሰባ ደረጃ
=====================

“እገገገገ መሬቱን እየዉስቲ…

እንዴት በድንጋይ እንደተለጠ…

ቲኸዱ ቢዉሉ ምን ቸገሮ እዚህላይማ… እገገገገ ዉነትም አዲሳባ…” አለ ደመቀ

“እሪዉ! እሪዉ! እሪዉ” አቤዉ ዘንዶ ላይ የቆመ ያህል ጮኸ


ደመቀ “ምነ ምናገኘህ?” በድንጋጤ ወደኋላ እየዞረ

“አትታይህም ይቺ ወንዲላ” መለሰ አቤ

“በማምላክ በዚ ዱላ ልዘብጣትማ” ከንፈሮቹን ነክሶ አቤዉ ኮስተርተር አለ

“ዋእ ወንድ እንደሆነሳ?”

“አያንተ!... ተፊት'ኮ አጎጠጎጤ አላት”

“ምን!” አለ ደሜ ራሱን በሁለት እጆቹ ይዞ… “ተሳሊነ ቅድስት! ምን ይሄማ አዲስ አሮጄ ነዉንጅ…

ገመቹ ነገሩ አዲስ እንደሆነባቸዉ ሲረዳ ሲመክራቸዉ «ወንድሞች! አየ ሴትኮ እንዲህ ነዉ አዲስ አበባ የምትለብሰዉ! እናንተጋ እንዲህ አይለብሱምንዴ?” እያለ ሲያራቅቅ

ደመቀ ቸኮል ብሎ አቤዉን ጎሸመዉ…

“ስማ ሊበላህ ነዉ…”

“እረገኝ!” አቤዉ ደነገጠ

“እማምላክን ኪስየ ነዉ ንአ!”

ሁለቱም አንዲት እርምጃ ወደነሱ እስቲራመድ ብቻ ነዉ የሚጠብት… ሁለቱም በተጠንቀቅ ላይ ናቸዉ…
ነገራቸዉ አልጣመዉም… አያያዛቸዉ ለቁርስ ያስተርፉት ስላልመሰለዉ ትቷቸዉ ወደ ሸንኮራ በረንዳ ወረደ…
“ነቃንበታ ነአንበት!...” ደምሻነቄዉ ተኩራራ ከዛም በኋላ አቤ የሚጠጋዉን ሰዉ ሁሉ በመሸሽ ኪሱን ጨምድዶ ይዝ ነበር…
==================

ሃሎ ያይዋ ልጅ አለ አቤ

“እንዴት ነህ ጋሽ አበረ” አለ Yonas…

“አንተ ልይ እንቢ አልክ አደለም?” አቤ ተቆጥቶ... የሱ ነገር ንዴቱ አፍንጫዉ ስር ናት… ትንሽ ይበቃዋል...

“ምነዉ ምናጠፋዉ ጋሽ አቤ?” ዮኒ ደንገጥ ብሎ

“ወንድማለም አትልም፣ ወንድም ጋሼ አትልም… የምን ጋስ አቤ ነዉ? ሰዉን አንጠልጥሎ መጥራት!”

“ዮኒ ድምጹ ተቀየረ… ቀዝቀዝ ብሎ ወንድም ጋሼ እልሀለሁ ከዚ በኋላ”

“እንዲ ነዉ እሰይ እሰይ! እናልህ” አለ እናልህን ረገጥ አርጎ

“ምንልኝ?!”

“እንደዉ አንዲት ቦታ ታደርሰናለህ ብየ ነበር ተባልንጀሬ ጋር ነዉ እምንኀድ”

“ሃሃሃ ደግሞ ባልንጀራ ምንድነዉ?” የከተማዋ አራዳ ዮኒ ጥያቄ ታበዛለች ችግሯ…

“አይ የዛሬ ልጅ… የልብ ጓደኛ… አብሮ አደግ… ማለት ነዋ!”

“አሃ! እሽ የት ላድርሳችሁ? ጋሽ አቤ…” ካፉ ከወጣ በኋላ ባቄላ አከለ ዮኒ

አቤዉ አኮፈኮፈ «ተሰባ ደረጃዉ»

ዮኒ በድንጋጤ ላይ “ሰባ ደረጃ ምን ትሰራላችሁ?” ማለት…

“አቤዉ አንተ ልጅ ጎርብጠሀል… እሽ መሆኑ ነዉ? እከከከ” አለና እንደሚፎክር ሰዉ ሆነ
==================

“ሃሎ…” አቤ ደወለ

“አቤ--- ት”

“እንደምን ሰነበትህ” አቤዉ በመጠይቅ ጀመረ… ይህኔ ደሜ ያዉቃል ታለሱ በድፍን አዲሳባ ስልክ ደዉሉ ጥያቄ የሚጠይቅ “እንደምን ሰነበትህ!?” የሚል

“ስባክን”

“ምነ?”

“ምን አንተ ደግሞ ለቁራሽ” ደሜ ባዘቶ ዲሳባ ኑሮን ሊተርክ ሲል

“ያልጅኮ እሽ አለ!”

“አለ!”

“አዎና”

“ታያ መች እናርገዉ?”

“ሰዉ ሳይበዛ አይሻልም?”

“እዉነትክን ነዉ! ተሰንበት በተስኪን መልስ ይሁና?

“በጀ!” አለ ደሜዉ

“አንተ ሸጋ ሁነህ ልበስ!” አቤ ከወዲሁ መሽቀርቀር ጀምሯል…

“እረጋ! እንዲህም የለ! ሸጋ ሁኔ እመጣለሁ”

“በጀ!”
=====================

በቀጠሮ እንደተገናኙ ዮኒ አፍሮ አንይኑን ሰበረና “ወዴት እንሂድ ወንድምገሼ?”

“አይ አሁንማ ረፈደ ሰዉ ሳይበዛ አይቀርም…”

“አንዲት ደረጃ ስሟን አንሳልኝማ!” አለ አቤዉ

“እእ አያንተ ዘንድሮም አልሰልጥነህ!” ደሜዉ አስከተለ… ተሳሳቁ

“በልማ ማን ነበረች ሳባ ደረጃ ነት መሰል”

“ሰባ ደረጃ…” አለና ዮኒ “ጃ”ን ረገጣት

“አዎ አዎ እንዲህ አምጣልኝንጅ!”

“ወንድም ጋሼ ግን ግን እዛ ምን እንሰራለን?”

“ምን ይላለ ሲላ… እህ ፊልም እንነሳለና” አቤዉ ተቆጥቶ

“ፎቶ ማለትህ ነዉ”

“አዎ!... አዎ!... የኔ ነገር ፎቴን እንነሳለን”

------------------------------

-----------------------

ቀኑንም ሙሉ አቤዉና ደሜዉ በሰባ ደረጃ ፎቶ ሲነሱ ዋሉ… ጋቢም ሲቀያሩ እንደነበር የዜና ምንቻችን አድርሶናል!!!

Image
source:ሱለይ አደም on Facebook

Post Reply

Return to “Ethio Art and Culture..ኢትዮ ጥበብ ፤ስነ ጽሁፍ ፤”