አምሮኛል is አምሮኛል አይገባህም!?

ግጥሞች፣ታሪኮች፣ፎቶዎች፣ሙዚቃዎች
Poems,Short stories, graphics,pictures,musics,Technology
User avatar
zeru
Leader
Leader
Posts: 952
Joined: 19 Aug 2009 17:01
Contact:

አምሮኛል is አምሮኛል አይገባህም!?

Unread post by zeru » 29 Aug 2014 11:24

አምሮኛል is አምሮኛል አይገባህም!?
=======================

ማስመለስ ከጀመራት ሀሙስ ሁለት ወሯ… የአምሮቷ ብዛትና አይነት ግራ የሚያጋባ… ወይንሸት የሴት ዘለላ፣ የሴት ቁኒ፣ የሴት ቀጠፋ፣ የሴትነት ማዕረግ… የሴት ልክ… የሴት ቁንዱፍቱ… ወይንዋ! አርግዛለች…
.

.
ግቢያቸዉ ከግቢያችን እጅ ለእጅ የተያያዙ ናቸዉ… እረ እንደዉም እዝጌር መሬቱን ሲዘረጋ የኛንና የነወይኗን መሬት ከንፈር ለከንፈር እንዳከናፈራቸዉ የሷ አባትና አጎቴ የየግቢያችንን አጥር ሲገነቡ ደግሞ የባስ አስተቃቀፏቸዉና እርፍ… የኛን አጥር የነወይኗ፣ የነወይኗን ደግሞ የኛ አቅፎት ይኸዉ አለላችሁ…
.
.
ከመሬቱ ነዉ መሰል፣ ከአጥሩ ነዉ መሰል እኔና ወይኗም ወደ ት/ቤት ስንመላለስ ሌላ ጓደኛ አስጠግተን አናዉቅም—ሁሌ፣ ሁሌ እኔና እሷ ብቻ… እጆቼ ያችን ሚጢጢ ትከሻ አንቃ እንደያዘች የሷ ሚጢጢ እጆችም የኔን ተበጣጥሳ ያለቀች ሹራብ በጀርባየ በኩል ተጠምጥማ እንደጨመደደች ተማርን… ሰዉ ደብተሩን ሲያጠና እኔ ወይኗን አጠናሁ ሰዉ መምህሩን ሲያዳምጥ ወይኗ ተናግሬ ያለፈዉን የኔን ድምጽ ከክፍል እስከምንለቀቅ እንደቴፕ ወደ ኋላ እያጠነጠነች ስታዳምጥ…
.
.
ከት/ቤት መልስ በሰበብ አስባቡ አንዳችን ወዳንዳች ቤት እንላካለን… «የወይኗን እናት ወንፊቱን ላኪልኝ አለችሽ እናቴ» ተብዬ ስሄድ ወይኗ ደግሞ ቆያይታ እኒያን እጆች እያሻሸች «ማንከሽከሻ አለቾት ማዘር» ብላ ባይኗ እኔን እኛ ቤት ዉስጥ ትፈልጋለች… ወደ ሶፋዉ፣ ወደ መደቡ፣ በቃ ምናለፋችሁ ሩሕ ለሩሕ ተናበናላ…
.
.
በዚህ የኔ ጥናት፣ በዚህ የሷ ጥናት መቼም መንኩራኩር እናበራለን ብለን አናስበዉም… “ስታድግ ምን መሆን ትፈልጋለህ?” ስባል “የወይኗ ባል!” ብዬ ነበር የምመልሰዉ… እንግዳ በመጣ ቁጥር የምጠየቀዉ ይህንን ነበር የኔም መልስ ራሱኑ… ወይኗን በገሀዱ ዓለም የሚተካት ምኞት የለኝም… መንኩራኩር ላ… ዶክተር ኖ… ኢንጅነር ወላ ፓይለት ኣኣ…
.
.
ቤተሰቤ ከሳቁ በኋላ የሚያስከትሉት ነገር ቢኖር “የልብህን ይስጥህ” ነበር ተሽቀዳድሜና አጎንብሼ መሬት ሳይነካት ምርቃኗን እፍስ… “አሜን” ነበር ምላሼ ምርቃትም ቤት ይመታልና ይኸዉ አደግን ተመነደግን ወይኗና ’ኔ ቤት ሰራን ጎጆ ቀለስን… “እሰይ ስለቴ ሰመረ!” ሙሉ ለሙሉ መዝሙሩ እኔጋ ነዉ… ከኔ ተሰርቆ ነዉ… መጀመሪያ የዘመርኩት እኔ ነበርኩ…
.
.
አንድ ቀን ሶፋ ላይ ጋደም ብላ “ሶል!” አለችኝ ፍጹም ለስላሳ በሆነ ሰባኪ ድምጽ… “ወዬ!” ካላልኩና “አቤት!” ካልኩማ

“ስታዬኝ ፍርድቤት እመስላለሁ… ስታዬኝ ቀበሌ እመስላለሁ… ወይስ…” ብላ አንጠልጥላ ትተወዋለች… ተሳስቼ ካልኩም ራት ማ ሊያባላኝ… በቃ ሌቱም አይነጋልኝ…
“ሶል!”
“ወዬ! የኔ ማር… ወዬ የኔ ዘመናይ… ወዬ የኔ ዘይቱና” አከታተልኩት
“ደጋግሞ እያስታወከኝ ነዉ… ምንድነዉ?”
“የበላሽዉ አልተስማማሽም? ወይስ…”
“ወይስ ምን…” ለመሳቅ የዳዱ ጉንጮች ለሳቅ እየተነሳሱ…
ዝም
“አንተ!? ወይስ ምን?”
“እህ በቃ…” ተግባብተናል ግን ማፋጠጥ ትወዳለች…
“እና መጥተህ አትስመኝም!?” አዋ ተግባብተናል አላልኳችሁም… ነፍስ ለነፍስ ተናበናል…
ተፈናጥሬ ተነሳሁ ወደ ወይኗ ገሰገስኩ… የሚባክኑ ደቂቆች አይኖሩም ለዚህ የምስራች… እንደኛና እንደነሱ ኩታገጠም መሬት «ክርችም!» እዛዉ ዝም… ንፋሱ መንሿሿቱን ቆም… ብርዱ ጥሎን ተሰደደ…
.
.
ሌላ ቀን… ሌላ ወቅት… ሌላ ጊዜ…
“ሶል”
“ወዬ የነፍሴ ሳዱላ፣ የለኝ ካንቺ ሌላ!”
“አማረኝ!”
“ምን አማረሽ ትርንጎ”
“የሆቴል ትራፊ” አለች በቀዘቀዘ ድምጽ… እንደፈራችኝ ይታወቅባት ነበር…

Source:

ሱለይ አደም on Facebook


Post Reply

Return to “Ethio Art and Culture..ኢትዮ ጥበብ ፤ስነ ጽሁፍ ፤”