ትዳር ሙሉ ሰው ያደርጋል..! ይሉናል... ዘውድአለም ታደሰ

ግጥሞች፣ታሪኮች፣ፎቶዎች፣ሙዚቃዎች
Poems,Short stories, graphics,pictures,musics,Technology
User avatar
zeru
Leader
Leader
Posts: 952
Joined: 19 Aug 2009 17:01
Contact:

ትዳር ሙሉ ሰው ያደርጋል..! ይሉናል... ዘውድአለም ታደሰ

Unread post by zeru » 26 Aug 2014 22:36


ትዳር ሙሉ ሰው ያደርጋል..! ይሉናል...
(ዘውድአለም ታደሰ)


እራሳችን መክረን (አግባ አግባ ብለን) ራሳችን ደግሰን(እቺንኳ ውሸት ነች) ራሳችን ሚዜ ሆነን...እኛኑ ምክር? ሂሂ ዘለቅናታ...!!

ሮቤል ይባላል (ስሙን የሙሽራ መኪና ሾፌር ይጥራውና) አብሯደግ ጓደኛችን ነበር (ነበር ያልኩት ዛሬ ጓደኝነቱን ትቶ አባታችን ስለሆነ ነው) ... ለ26 አመት በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በስተመጨረሻ ከስድስት ወር በፊት.......... አገባ።

ማግባቱን ተከትሎ ጓደኛችን ሮቤል ላይ አንዳንድ የአባወራነት ምልክቶች ይታዩበት ጀመር....
1ኛ- ራሱ ገባ ገባ ማለት ጀመረ...
2ኛ - ሆዱ እንደማበጥ አለ (እኛ ሀሳብ ነው ብንልም እ
ሱ ግን ምቾት የወለደው ቦርጭ ነው ብሎ ተከራከረ)
3ኛ - ስለጤፍ ዋጋ ጣራ መንካትና ስለቤትኪራይ መወደድ ደጋግሞ ያወራ ጀመር ..ወዘተ..

ከሁሉም ከሁሉም ግን አብዛኞቹ የሀገራችን አዲስ ተጋቢዎች እንደሚያደርጉት ምክር ያበዛ ጀመር...

ምክር 1- ያለፈውን ኑሮውን ማጣጣል, መናኛ ማድረግ, በከንቱ እንደባከነ መቁጠር, ያለፈ ህይወቱን በመኮነንም የኛን ያላለፈ የላጤነት ኑሮ መተቸት

ምክር 2 - በትዳሩና በኑሮው..እጅግ ሲበዛ ደስተኛ እንደሆነና ካገባ በኋላ ሙሉ እንደሆነ, ገንዘብ መቆጠብ እንደጀመረ (ድሮምኮ ቋጣሪ ነበር) ኑሮውም እንደተሻሻለ መስበክ

ምክር 3 - ምክር 4 - ምክር 5 - እያለ ይቀጥላል!!

የአመካከሩ ሁኔታ...
በስሜት በመሞላትና በመንቀጥቀጥ...

ባገባ በወሩ... ሚስቱን በፈገግታ እየተመለከታት... <<እግዜር ሀኒዬን ባይሰጠኝ ኖሮ ምን እንደምሆን እንኳ አላውቅም ነበር... ይኸው እንደምታዩኝ ገና በወሬ ሰውነቴ ፋፍቶ የልጅነት ወዜ ተመልሶ (ልጅ ሆኖ እንደምናውቀው ዘነጋው እንዴ? ቅጥል ስሙ ራሱ አመዶ አልነበር እንዴ?) ኪሎዬ ራሱ በአንድ ወር ግዜ ውስጥ ሃምሳ አምስት ገባ... ድሮኮ ሱሪንኳ ስገዛ የመጨረሻውን ጠባብ ቁጥር እንኳ ሰፊ ቤት አስጠብቤ ነበር ምለብሰው.. ድሮኮ ደሞዝ ተቀብዬ በነጋታው እጄ ላይ የለም ነበር..ድሮኮ....(ድሮ ሚለው ከአንድ ወር በፊት የነበረውን ኑሮውን ነው) ድሮኮ...

የድ.........ሮ ሰዎች ሲጃጃሉ የፈጠሩት ትዳር ውስጥ እየኖረ ድሮውን መናቅ አሁን ምን ይሉታል?

ባገኘኝ ቁጥር... <<ዜድዬ እውነቴን ነው ምልህ አግባ!.. የወንደላጤነት ኑሮ እስከመቼ? ዝም ብለህ ከምትንዘላዘል አንዷን አግብተህ ለምን አታርፈውም?(የታባቱ ስንዘላዘል እንዳየኝ እንጃለት)>> እሪሪሪሪሪ... ይልብኛል! በቃ እኔን ሲያይ የመምከር አምሮቱ በሶስት እጥፍ ስለሚጨምር ምሳ እየጋበዘ...ማኪያቶ እየጋበዘ... ፊልም እየጋበዘ ሁሉ ይመክረኛል። ደሞ የታባቱ ስንዘላዘል እንዳየኝ እንጃ አስር ግዜ አትንዘላዘል...ተሰብሰብ... ምናምን...ቡፍፍፍፍፍ...

<<መቼ ተበተንኩና እሰበሰባለሁ? >> እለዋለሁ እየሳቅኩ.. እሱ ግን አይስቅም...
<<ዜድ ተበትነሀል! እውነቴን ነው ምልህ ብትንትንህ ወጥቷል! ግን አሁን መበተንህ አይታወቅህም... መበታተንህን ምታውቀው እንደኔ በትዳር ስትሰበሰብ ነው። ግራ ጎንህን ፈልገህ በአንድ ጎጆ እስካልተሰበሰብክ ድረስ በቃ አንተ ለሁለት ተበትነሀል...ግራጎንህ...እዛ አንተ እዚህ... >> ይለኛል...

መጽሀፎች ያውሰኛል!
የመጽሀፎቹ ርእስ ግን ከማግባት ይልቅ አለማግባትን የሚያበረታቱ ናቸው...
"በትዳር ውስጥ የሚነሱትን ግጭቶች እንዴት ማስወገድ ይቻላል?"
"በትዳር ውስጥ መሰለቻቸትን ለማስወገድ መደረግ ያለባቸው ሶስት ነገሮች" ምናምን የሚሉ..

በርግጥ በዚህ ዘመን መጋባት ፋሽን ሆኗል! ሁሉም እየተነሳ ያገባል.. ሁሉም እየተነሳ ይወልዳል... በዚያው መጠን ደግሞ ፍርድ ቤቶቻችን በፍቺና በንብረት ክፍፍል ጥያቄዎች ተሞልተዋል...ድነገት ዘው ብለው እንደሚገቡት ዘው ብሎ መውጣትም ቀሏል... ሙሽሪቷ ቤት ሽምግልና የሄዱ ሽማግሌዎች ካሁን አሁን ክርስትና ተጠራን እያሉ ሲጠብቁ ለምስክርነት ፖሊስ ጣቢያ ይጠራሉ...

ተማሪዎቹ (አብሶ ሴቶቹ) ከዲግሪ በፊት ውልጃና ውርጃን ያስቀድማሉ... ሚጡ የሰፈራችን ልጅ ነች! ቤተሰቦቿ ሀብታምም ደሀም አይደሉም:: የሰባተኛ ክፍል ተማሪ ስትሆን በትምህርቷም ጎበዝ ነበረች ካየኋት ግን ሁለት አመት ሆኖኝ ነበር... ባለፈው ከሰፈር ስወጣ ሆዷ ክፉኛ አብጦ ቀስ እያለች ወደቤተሰቦቿ ቤት ስትጓዝ አገኘኋት! በዚህ እድሜዋ ማርገዟ ቢያስደነግጠኝም እንዳልደነገጠ ሆኜ ሰላም ካልኳት በኋላ... <<ቆየሁ ካየሁሽ ሰፈር ቀየራችሁ እንዴ?>> ብላት <<አገባሁኮ አልሰማህም እንዴ?>> ብላኝ አረፈቺው... ያረገዘቺው ሁለተኛውን ልጇን እንደሆነ ስትነግረኝማ የደነገጥኩት ድ..ን..ጋ..ጤ...!

ሮቤል ምክሩን ተያይዞታል... <<ሰብሰብ በሉንጂ.. ትዳርኮ ሚገርም ነገር ነው... ደሞ ሚስት በረከት ነች... ሚስት ዘውድ ነች... ትዳር ሙሉ ሰው ያደርጋል... ትዳር ይለውጣል... ትዳር ያረጋጋል...

ትዳር...ትዳር...ትዳር...ትዳር...

ምንጭ: ፌስቡክPost Reply

Return to “Ethio Art and Culture..ኢትዮ ጥበብ ፤ስነ ጽሁፍ ፤”