ጠብቄሽ ነበረና ሌሎች ግጥሞች

ግጥሞች፣ታሪኮች፣ፎቶዎች፣ሙዚቃዎች
Poems,Short stories, graphics,pictures,musics,Technology
User avatar
morefun
Leader
Leader
Posts: 152
Joined: 06 Sep 2009 01:52
Contact:

Re: ጠብቄሽ ነበረና ሌሎች ግጥሞች

Unread post by morefun » 25 Oct 2009 10:32

ነጠብጣብ ሐሳቦች

ሰማይ ከሚመክን ይፀንስ መከራ
ያርግፍ" ያርግፍ" ያርግፍ" መአት እያፈራ
የ፣ሣት ዛፍ ባለበት ሰደድ ላያስፈራ፡፡

ከሐምሌት ጋር ሞቷል፣ የማመንታት ዓለም
ከሆኑ በኋላ፣ አለመሆን የለም፤
ሸክም ፀጋ ሆኗል ፀጋህን አትግፋ
በጠባብ ዓለም ውስጥ ትከሻህን አስፋ፡፡

አንድ ህልም እንደ ጠጅ፣ እየደጋገሙ
ንግር፣ ትንቢት ሳይሆን ታሪክ እያለሙ
ተኝቶ መነሳት
አቤት ሲያቅለሸልሽ
ጌታ ሆይ አትንሳት
ነፍሴን እንቆቅልሽ፡፡

(በእውቀቱ ስዩም፣ የ፣ሣት ዳር ሐሳቦች፣ 2000)

Image


User avatar
morefun
Leader
Leader
Posts: 152
Joined: 06 Sep 2009 01:52
Contact:

Re: ጠብቄሽ ነበረና ሌሎች ግጥሞች

Unread post by morefun » 25 Oct 2009 10:33

የሞት ዓይነት

ያበቡበት
የሳቁበት
የቦረቁበት
ደረት ነፍተው - ተዝናንተው
ጣት ቀስረው - ቆርጠው
የኮሩ የገነኑበት - ባመኑበት
ሳያፍሩ የለፈፉበት
ዘመን
ዘመኑ አልፎ፣
ማደብ - ዝምታው ሲገዛን
ከንቱ - ፈገግታ ሲበዛን
ትዝብት - ምፀቱ ሲጠጋን
እሱ ነው ምልክቱ
መኖር ማለት ለማብቃቱ፡፡

(አቪዬሽን ፣ፈቃደ አዘዘ፣ 1992)

Image


Post Reply

Return to “Ethio Art and Culture..ኢትዮ ጥበብ ፤ስነ ጽሁፍ ፤”