ጠብቄሽ ነበረና ሌሎች ግጥሞች

ግጥሞች፣ታሪኮች፣ፎቶዎች፣ሙዚቃዎች
Poems,Short stories, graphics,pictures,musics,Technology
User avatar
morefun
Leader
Leader
Posts: 152
Joined: 06 Sep 2009 01:52
Contact:

ጠብቄሽ ነበረና ሌሎች ግጥሞች

Unread post by morefun » 25 Oct 2009 10:07

ጠብቄሽ ነበረ

መንፈሴን አንጽቼ
ገላዬን አጥርቼ
አበባ አሳብቤ
አዱኛ ሰብስቤ
ጠብቄሽ ነበረ፤
ብትቀሪ ጊዜ፣
መንፈሴን አሳደፍኩ
ገላዬን አጎደፍኩ
አበባው ደረቀ
አዱኛው አለቀ፤
ብትቀሪ ጊዜ፣
የጣልኩብሽ ተስፋ
እኔን ይዞ ጠፋ፡፡
(ደበበ ሰይፉ፣ ለራስ የተጻፈ ደብዳቤ፣ 1992)

Image


User avatar
morefun
Leader
Leader
Posts: 152
Joined: 06 Sep 2009 01:52
Contact:

Re: ጠብቄሽ ነበረና ሌሎች ግጥሞች

Unread post by morefun » 25 Oct 2009 10:15

አልቅስ አልቅስ አለኝ

ልጓም እንደ በላች
ያልተገራች ባዝራ፤
የዕንባ ቆቤን ረግጣ
ጉንጬን አርመስምሳ
የዕንባ ጫፌን ቋጥራ፤
ስታነኳኩረኝ
ዓይኔ ጭጋግ ለብሶ
ባር - ባር የሚል ስሜት
አልቅስ አልቅስ አለኝ፡፡
በ፣ነ ወይ-ወዩ አገር
ባለ ድርብ ሙሾ፣
እድሜ ሙሉ እዬዬ
ሳቃቸው የቁርሾ፤
ስስቅ ስስቅ ስስቅ . . .
ስቄ ስቄ ስቄ . . .
እንባዬ ፈሰሰ፣ ከሚሉቱ ሠፈር
ሣቅና ልቅሷቸው በተደፋረሰ፤
መች አነሰን አሉ
ቁናው የዕንባ ሥፍር
አልቅሼ ማስለቀስ
ለራሴም ውጦኛል
ሕይወት የ፣ንባ ባህር፡፡

(ወንድዬ አሊ፣ ወበት እና ሕይወት፣ 1998)

Image


User avatar
morefun
Leader
Leader
Posts: 152
Joined: 06 Sep 2009 01:52
Contact:

Re: ጠብቄሽ ነበረና ሌሎች ግጥሞች

Unread post by morefun » 25 Oct 2009 10:19

ያመሻሽ ወርቅ

እምንተዋወቅ መሰለኝ እምንተዋወቅ
አንቺ የጥልቀት ጀምበር
ፍመት ፍልቅቅ
ተቅላለት ድምቅ
ያቴና ተራሮች አድማስ፣ ያመሻሽ ወርቅ፡፡
ርቀት መጦች ጮራዎችሽ
ርችቶችሽ
ርጭቶችሽ
አሸን ምጣትሽ
ተብጫጮት ቅልቅል ተቅላሎትሽ፡፡
በነሱ ተቅለመለመው
ያውሮፕላን ማረፊያ አካባቢው፡፡
ትራንዚት
ጉዞ ለመቀጠል ጉዞ
እያልኩ በካሁን አሁን
ሊንቀሳቀስ፣ በረራውን ሊጀምር ቆመነው፡፡

(ሰይፉ መታፈሪያ፣ ውስጠት፣ 191)

Image


User avatar
morefun
Leader
Leader
Posts: 152
Joined: 06 Sep 2009 01:52
Contact:

Re: ጠብቄሽ ነበረና ሌሎች ግጥሞች

Unread post by morefun » 25 Oct 2009 10:23

መሰላል

መሰላል ለመውጣት
አለው ትልቅ ብልሀት፡፡
የላዩን ጨብጦ፤
የታቹን ረግጦ፣
ወደላይ መመልከት
እጆችን ዘርግቶ በሀይል መንጠራራት፡፡
ጨብጦ መጎተት የላዩን፣
ላይ ታች እንዲሆን፡፡
አንድ በአንድ እየረገጡ
መሰላል የወጡ፣
ብልሆች የማይጣደፉ
ሞልተዋል በያፋፉ፡፡
ዘርግተው የጨበጡትን መርገጥ
የመውጣት ሕግ ነው የማይለወጥ፡፡
ሲወርዱ ግን ያስፈራል
የረገጡትን ያስጨብጣል፡፡

(መስፍን ወልደማርያም፣ እንጉርጉሮ፣ 1967)

Image


User avatar
morefun
Leader
Leader
Posts: 152
Joined: 06 Sep 2009 01:52
Contact:

Re: ጠብቄሽ ነበረና ሌሎች ግጥሞች

Unread post by morefun » 25 Oct 2009 10:25

ያገረሸ ፍቅር

የሰማይ
አሞራ
ላዋይህ
ችግሬን፡፡
ብረር ሒድ ንገራት”.
ከትልቁ
ዛፍ
ሥር፣
ዱሮ በልጅነት
ከተጫወትንበት
ከትልቁ ዛፍ ሥር አታጣትም ፍቅሬን
ብረር
ሒድ ንገራት፣
ንገር መናፈቄን፣

(ገብረ ክርስቶስ ደስታ፣ መንገድ ስጡኝ ሰፊ፣ 1998)

Image


User avatar
morefun
Leader
Leader
Posts: 152
Joined: 06 Sep 2009 01:52
Contact:

Re: ጠብቄሽ ነበረና ሌሎች ግጥሞች

Unread post by morefun » 25 Oct 2009 10:26

በድንቅ አብቃይ ምድር

አገሩ በሙሉ፣ የብስና ባህሩ፣ ውሃ ሰራሽ ሆኖ
ለምን ያስቡታል? ዓባይን ለመስኖ
ለእኛ አልተሰጠንም? ዓለምን መመልከት፣ ከጥቅም ነጥሎ
ውሃ ተሸምኖ፣ ባዬር ሲተጣጠፍ፣ ማዬት ዝም ብሎ
ሃሳብን ማሳረፍ፣ ከማር ከሰም ስሌት
ለእኛ አልተሰጠንም? ማዳመጥ፣ ማጣጣም፣ የንብን ማህሌት
ዶሮን ከዶሮ ወጥ ነጥሎ መመኘት
ለሣታዊ ክንፉ፣ ለንጋት መዝሙሩ፣ ላጫጫር ምስጢሩ፣ ቃል
መርጦ መቀኘት
ፈልጠው ሳይማግዱን፣ ወይም ሳይዳስሱት፣ ከስሩ ሳይሰግዱ
ዋርካ አይደነቅም? በእንግዳ ህላዌው፣ በቅጠል በንግዱ?
መልስ የለም
መልስ የለም፡፡
ከጢስና ውሃ የተሰራ ሸማ፣ ባዬግ ይታጠፋል፣
ንቡም ይዘምራል፣ ዶሮውም ይጭራል፣ ዋርካውም በጆቹ
አየሩን ይቀዝፋል
የማይገርመው ትውልድ፣ በድንቅ አብቃይ ምድር፣ እየኖረ ያልፋል፡፡

(በእውቀቱ ስዩም፣ የሣት ዳር ሐሳቦች)

Image


User avatar
morefun
Leader
Leader
Posts: 152
Joined: 06 Sep 2009 01:52
Contact:

Re: ጠብቄሽ ነበረና ሌሎች ግጥሞች

Unread post by morefun » 25 Oct 2009 10:29

ባንቺ እንደተመሰጥኩ

ባንቺ አንደተመሰጥኩ
ማልዳ የነቃችው
ፀሐይ አሸለበች
ጨረቃዋ ደምቃ
በቅፅበት አረጀች፡፡
ባንቺ እንደተመሰጥኩ
የሌለን ለመፍጠር
አማጡ
ያንቺ በለጠና
በሀፍረት ተዋጡ
ባንቺ እንደተመሰጥኩ
ቀልቤ እንደተነካ
አካሌም ደከመ
ዕድሜም ጣራ ነካ፡፡

/አማኑኤል መሐሪ፣ ጥለት፣ 1996/

Image


User avatar
morefun
Leader
Leader
Posts: 152
Joined: 06 Sep 2009 01:52
Contact:

Re: ጠብቄሽ ነበረና ሌሎች ግጥሞች

Unread post by morefun » 25 Oct 2009 10:30

ያልተማረ ይግደልህ

ትናንትን አፈቀርኩት" ዛሬን ግን ጠላሁት
አፌን ለሆድ ብቻ ሲጮህ አገኘሁት፡፡
ትንሽ መግፋት ቢቻል ጊዜን ወደ ኋላ
እኔስ በተሰየምኩ ካባቴ ፊት ለፊት ከአያቴ በኋላ
ወይ ታሪኬ ሊፃፍ ወይ ግፌ ሊሰላ፡፡
አባባ ገድልህን ለምን ነው የነገርከኝ?
ለትናንት አሻቅለህ ዛሬ አስጠላኸኝ
ብትከፍተው ገለባ
ሕይወት ትግል አልባ፣ ትግሉም ሕይወት አልባ
የተማረ ይግደለኝ ብለህ አጓግተኸኝ
ፊደል ከቆጠረ ቁጥርን ከደመረ ለሆዱ ካደረ
መንጋ መሀል ጣልከኝ
እኔም ተማከርኩልህ" ተመራመርኩልህ
የመብት አቡጊዳ ትግሌን ጀመርኩልህ
መብሌን አትንኳት ብዬ ፎከርኩልህ
ኧረ በሞትኩልህ
ይልቅስ ልንገርህ" ሞትክን በተማረ መመኘትክን እርሳው
ጽድቁን ከፈለግከው
ፊደል ያልቆጠረው ያገሬ ገበሬ ተኩሶ ይጣልህ፣ ይግደልህ ከማሳው፡፡

(ቼበለው መኩሪያ፣ ማለዳ፣ 1993)

Image


Post Reply

Return to “Ethio Art and Culture..ኢትዮ ጥበብ ፤ስነ ጽሁፍ ፤”