"አራቱ ሻማዎች" እና "እንቆቅልሽ"...

ግጥሞች፣ታሪኮች፣ፎቶዎች፣ሙዚቃዎች
Poems,Short stories, graphics,pictures,musics,Technology
User avatar
morefun
Leader
Leader
Posts: 152
Joined: 06 Sep 2009 01:52
Contact:

"አራቱ ሻማዎች" እና "እንቆቅልሽ"...

Unread post by morefun » 25 Oct 2009 10:02

Image

"አራቱ ሻማዎች" እና "እንቆቅልሽ" ለእይታ በቁ

Imageባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ፣ ሁለት የአማርኛ ፊልሞች "አራቱ ሻማዎች" እና "እንቆቅልሽ" በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት አዳራሽና በዓለም ሲኒማ ለእይታ በቅተዋል፡፡


ቅዳሜ መስከረም 30 ቀን 2002 ዓ.ም.፣ በአዲስ አበባ የቴአትርና ባህል አዳራሽ የተመረቀው "አራቱ ሻማዎች" የቀረፃው ሂደት ሁለት ዓመት ከአራት ወር ፈጅቷል፡፡

በአንዲት ልጃገረድ ሕይወት ዙሪያ ባጠነጠነው ፊልም 19 ተዋናይ ሲሳተፉበት ስምንቱ መሪ ሚናውን ይዘው ተገኝተውበታል፡፡ የሚራክል ፊልም ፕሮዳክሽን ውጤት የሆነውን አራቱ ሻማዎች በጌታቸው አደራ ተጽፎ በሰላም ይሁን አሥራት የተዘጋጀ ነው፡፡

ፊልሙ አዲስ አበባና ሐዋሳ ከተሞችን ማዕከል ያደረገና እስከ 200 ሺሕ ብር ድረስ ወጪ የጠየቀ ነው፡፡ በተለያዩ የአዲስ አበባ ሲኒማ ቤቶች ለእይታ እንደሚበቃም አዘጋጆቹ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩልም፣ ምሳሌ ፊልም ፕሮዳክሽን በቤዛ ኃይሉ የተደረሰውንና የተዘጋጀውን "እንቆቅልሽ" የአማርኛ ፊልም፣ በመስከረም 27 ቀን 2002 ዓ.ም. በዓለም ሲኒማ አስመርቋል፡፡ በኢትዮጵያና በዴንቨር ኮሎራዶ በተሠራው ፊልም 50 ተዋናዮች የተሳተፉበት ሲሆን የ1 ሰዓት 37 ደቂቃ ፍጆታ ያለው መሆኑ ታውቋል::

Image


Post Reply

Return to “Ethio Art and Culture..ኢትዮ ጥበብ ፤ስነ ጽሁፍ ፤”