ከባራክ ኦባማ....

ግጥሞች፣ታሪኮች፣ፎቶዎች፣ሙዚቃዎች
Poems,Short stories, graphics,pictures,musics,Technology
User avatar
morefun
Leader
Leader
Posts: 152
Joined: 06 Sep 2009 01:52
Contact:

ከባራክ ኦባማ....

Unread post by morefun » 25 Oct 2009 09:56

ሞቱን በሰማሁ ጊዜ አባቴ ለእኔ ተረት ሆነብኝ፡፡ ከሰው ያነሰም የበለጠም ተረት፡፡ በ1963 ከሃዋይ ስወጣ ገና የሁለት ዓመት ህፃን ነበርኩ፤ ስለዚህም እሱን የማውቀው እናቴና አያቶቼ በሚነግሩኝ ታሪኮች ውስጥ ነው፡፡


የራሴን ትዝታዎች መሰብሰብ በጀመርኩበት ዕድሜዬ ላይ እናቴ ከሌላ ሰው ጋር ግንኙነት ጀምራለች፡፡ ነጭና ጥቁር ፎቶዎቹ ለምን ርቀው እንደተቀመጡም ገብቶኛል፡፡ አንዳንዴ ፎቶዎቹ ላይ የሚያስቀውን ፊቱን፣ ግንባሩንና ከዕድሜው በላይ ሽማግሌ የሚያስመስለውን ወፍራም መነፅሩን እመለከታለሁ፤ የህይወት ጉዞው በአንድ ትረካ ተቋጥሮ ሲቀርብልኝም በፅሞና አዳምጣለሁ፡፡

አፍሪካዊ ነበር - አሌጐ በተባለ መንደር ከሉዎ ጐሳ የተገኘ ኬንያዊ፡፡ መንደሩ የደሃ መንደር ነበር፡፡ አባቱንና የእኔ አያት የሆኑት ሁሴን ኦንያንጐ ኦባማ ታዋቂ ገበሬ፣ የጐሳው ሽማግሌ እንዲሁም የመፈወስ ስልጣን የተሰጣቸው ባለመድሃኒት (ሐኪም) ነበሩ፡፡ አባቴ ያደገው የአባቱን ፍየሎች እየጠበቀ፣ ኋላም የእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ባቋቋመው ትምህርት ቤት እየተማረ ነው፡፡ የአባቴ እምቅ ብቃት የተስፋ ጭላንጭል ያሳየው እዚህ ትምህርት ቤት ነው፡፡ በኋላ ናይሮቢ መማር የሚያስችል የትምህርት ዕድል አግኝቷል፤ ቀጥሎ በኬንያ የነፃነት ዋዜማ በኬንያ መሪዎችና በአሜሪካውያን ስፖንሰሮች ተመርጦ፤ የምዕራባውያንን ቴክኖሎጂ ቀስመው አዲሲቱን አፍሪካ ለመመስረት ይረዳሉ ከተባሉ የአፍሪካ ልጆች አንዱ በመሆን ለትምህርት ወደ አሜሪካ ተላከ፡፡

በ1959፣ በሃያ ሦስት ዓመቱ የተቋሙ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ተማሪ ሆኖ ሃዋይ ዩኒቨርሲቲ ደረሰ፡፡ ኢኮኖሚትሪክስ አጥንቶ በሦስተኛው ዓመት ከክፍል ጓደኞቹ አንደኛ ሆኖ ትምህርቱን አጠናቀቀ፡፡ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ጓደኞች ነበሩት፤ ዓለም አቀፍ የተማሪዎች ማህበር እንዲመሰረት ከመርዳቱ በላይ የማህበሩ የመጀመያው ፕሬዚዳንትም ሆኗል፡፡ የሩሲያኛ ቋንቋ የሚማርበት ክፍል ውስጥ ከአንዲት የአሥራ ስምንት ዓመት ዓይናፋር አሜሪካዊት ልጃገረድ ጋር ተዋወቀ፤ ተፋቀሩ፡፡ የልጃገረዷ ቤተሰቦች መጀመሪያ ባይደሰቱም የኋላ ኋላ በጨዋታ አዋቂነቱና በምሁርነቱ ተረቱ፤ እናም ወጣቶቹ ጥንዶች ተጋቡ፤ እሷም ለስሙ መጠሪያ የሚሆን ወንድ ልጅ ወለደችለት፡፡ ይሄኔ ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ዶክትሬት ዲግሪውን የሚቀጥልበትን ዕድል አሸነፈ፤ ቤተሰቡን ወደዚያ የሚያዛውርበት ገንዘብ ስላልነበረው ግን መለያየት መጣ፤ እሱም ለአፍሪካ የገባውን ቃል ለመፈፀም ወደ አፍሪካ ተመለሰ፡፡ እናትና ልጅ ባሉበት ቀሩ፤ የፍቅር ትስስሩ ግን በርቀት ሳይገደብ ከረመ፡፡

(አደብቴ፣ የለውጥና የታላቅነት ምስጢር (ትርጉም"፣ 2001)

Image


Post Reply

Return to “Ethio Art and Culture..ኢትዮ ጥበብ ፤ስነ ጽሁፍ ፤”