መንግስቱ ለማ-የግጥም ጉባኤ ከሚለው ስብስብየተወሰደ

ግጥሞች፣ታሪኮች፣ፎቶዎች፣ሙዚቃዎች
Poems,Short stories, graphics,pictures,musics,Technology
Post Reply
mary
Starter
Starter
Posts: 16
Joined: 21 Sep 2009 02:44
Contact:

መንግስቱ ለማ-የግጥም ጉባኤ ከሚለው ስብስብየተወሰደ

Unread post by mary » 19 Oct 2009 07:09

ኪስ
የኢትዮጵያ ያገራችን ልብስ
እጀጠባብ ሱሪ ኩታና ቀሚስ
ኪስ የለባቸውም አብዛኛውን ጊዜ
የሚለብሳቸውም ይተክዝ ትካዜ

የፈርንጆችን ልብስ ካየ ካስተዋለ
ያውቀዋል መቶ አይነት ልዩ ኪስ እንዳለ
የደረት ኪስ አለ ከሁሉ አስቀድሞ
የዳሌ ኪስ አለ የወገብ ኪስ ደግሞ
<<የእንደዚያም>> ኪስ አለ ለመደምደሚያው
ከዚህ ከጎደለ አዋቂ ይሙላው።

ለምንድን ይረባል
ለምንስ ይጠቅማል የኪስ ብዛት ማት?
ብሎ የሚጠይቅ ካለ ምናልባት
ያስቸግራል በጣም እሱን ማስረዳት።

ኢትዮጵያዊ የጠራው አበሻ
ጥሬው ያገሬ ልጅ ለመደሰት ቢሻ
ምንጭ ያመሰግናል አባይን ሳያይ
የማይዋጥ ነገር አይመስለው ሲሳይ።

User avatar
morefun
Leader
Leader
Posts: 152
Joined: 06 Sep 2009 01:52
Contact:

Re: መንግስቱ ለማ-የግጥም ጉባኤ ከሚለው ስብስብየተወሰደ

Unread post by morefun » 24 Oct 2009 07:05

በጣም እናመስግናለን አሪፍ ግጥም ናት..... ;) ;) ;) ;)

Image


mary
Starter
Starter
Posts: 16
Joined: 21 Sep 2009 02:44
Contact:

Re: መንግስቱ ለማ-የግጥም ጉባኤ ከሚለው ስብስብየተወሰደ

Unread post by mary » 26 Oct 2009 04:18

አመሰግናለሁ... ሌላም ይጨመራል

Post Reply

Return to “Ethio Art and Culture..ኢትዮ ጥበብ ፤ስነ ጽሁፍ ፤”