ተረትና ምሳሌ አንደኛ መፅሀፍ

ግጥሞች፣ታሪኮች፣ፎቶዎች፣ሙዚቃዎች
Poems,Short stories, graphics,pictures,musics,Technology
mary
Starter
Starter
Posts: 16
Joined: 21 Sep 2009 02:44
Contact:

ተረትና ምሳሌ አንደኛ መፅሀፍ

Unread post by mary » 15 Oct 2009 05:32

 • ጽጌ ረዳና ደመና

  የፀሃዩ ንዳድ ያጠቃት በብዙ፡
  ጠውልጎ የሚታይ የቅጠልዋ ወዙ።
  አንዲት ጽጌረዳ ቃልዋን አስተዛዝና፡
  እንዲህ ተናገረች ለሰማይ ደመና።
  ድርቀት በጣም ጎድቶኝ እየኝ ስንገላታ፡
  እባክህ ጣልልኝ የዝናም ጠብታ።
  ቶሎ ካላራስከኝ ጉልበቴ እንዲጥናና፡
  ምንም ተስፋ የለኝ መሞቴ ነውና።
  አሁን መሄዴ ነው ለትልቅ ጉዳይ፡
  ስመለስ መጥቼ ሳልፍ ባንቺ ላይ።
  አዘንብልሻለሁ ጠብቂኝ እያለ፡
  ምንም ሳይጥልላት መንገዱን ቀጠለ።
  ጉዳዩን ጨርሶ ቆይቶ ሲመጣ፡
  ያቺ ጽጌረዳ ስርዋ ውሃ ያጣ።
  እንደዚያ ዘስተዛዝና ጭንቋን ያዋየችው፡
  የፀሃዩ ንዳድ አድርቋት ቆየችው።
  እስኪጎርፍ ድረስ የውንዝ ውሃ ሙላት፡
  ወድያው እንደ መጧ ዝናሙን ጣለላት፡
  ግን ደርቃለችና አልቻለም ሊያድናት።
  ሳልደርስላት ቀረሁ አዬ ጉድ እያለ፡
  ደመናም ጉዞውን ወደ ፊት ቀጠለ።
  ሰውም እንደዚሁ ጭንቁን እያዋየ፡
  በችግሩ ብዛት እየተሰቃየ።
  ብዙ ግዜ ኖሮ ቆይቶ ሲጉላላ፡
  የሚረዳው አጥቶ ከሞተ በሗላ።
  ዘመድ ወዳጆቹ እንባ እያፈሰሱ፡
  ተዝካር ቢያወጡለት አርባ ቢደግሱ፡
  ይህ ሁሉ ከንቱ ነው አይጠቅመውም ለሱ።
  እውነት ከወደደ ሲቸገር ሲጎዳ፡
  በህይወቱ ሳለ ሰው ወዳጁን ይርዳ።

ኦሽንoc
Leader
Leader
Posts: 1129
Joined: 07 Aug 2009 14:20
Contact:

Re: ተረትና ምሳሌ አንደኛ መፅሀፍ

Unread post by ኦሽንoc » 15 Oct 2009 18:25

ደስ የሚል ግጥም ሜሪ...ልጅ ሆኜ ያነበብኩት ሁሉ መሰለኝ :)

ይህ ግጥም በከበደ ሚካኤል ይሆን?

mary
Starter
Starter
Posts: 16
Joined: 21 Sep 2009 02:44
Contact:

Re: ተረትና ምሳሌ አንደኛ መፅሀፍ

Unread post by mary » 16 Oct 2009 03:34

እጅግ በጣም የምወደውና በልጅነቴ ሳነበው ያደኩት ቁም ነገር አዘል መፅሃፍ ነው ደራሲው አንተ እንዳልከው ክቡር ዶክተር ከበደ ሚካኤል ናቸው

ኦሽንoc
Leader
Leader
Posts: 1129
Joined: 07 Aug 2009 14:20
Contact:

Re: ተረትና ምሳሌ አንደኛ መፅሀፍ

Unread post by ኦሽንoc » 16 Oct 2009 15:18

በይ ከንዲህ አይነቱስ በደንብ ጨመርመር አርጊልን: በጣም ጥሩ ጥሩ ምክሮች ያዘሉ ግጥሞች እንዳሉዋቸው አውቃለሁ::
በጣም ደስ የሚል ነው ምስጋናየ ይድረስሽ ሜሪ::

yewondwossen
Posts: 4
Joined: 17 Sep 2009 07:35
Contact:

Re: ተረትና ምሳሌ አንደኛ መፅሀፍ

Unread post by yewondwossen » 18 Oct 2009 12:28

ቆንጆ ግጥም ነው። መለክቱም አስፈላጊ ነው።

User avatar
morefun
Leader
Leader
Posts: 152
Joined: 06 Sep 2009 01:52
Contact:

Re: ተረትና ምሳሌ አንደኛ መፅሀፍ

Unread post by morefun » 19 Oct 2009 02:07

ይሄ ግጥም የሚያተምረን ተልቁ ነገር
እርዳታን ከሰው መጠበቅ እንደሌለብን ነው፡፡

ወይም ለራሳችን ቸግር መፍትሄው ያለው እራሳችን ጋር ነው፡፡

ፅጌረዳዋ ቁጭ ባላ ደመናን ከምትተብቅ ለራሷ ችግር መፍትሄው ያለው እራሷ ጋር መሆኑን ማወቅ ነበረባት፡፡

አዳሜ ሞኝ ሰው ይረዳኛል ብለ አትጠብቅ...ተስፈኛ ሁላ፡፡

Image


mary
Starter
Starter
Posts: 16
Joined: 21 Sep 2009 02:44
Contact:

Re: ተረትና ምሳሌ አንደኛ መፅሀፍ

Unread post by mary » 19 Oct 2009 03:10

በርግጥ ልክ ነህ ሞርፈን ነገር ግን ለሰው መድሃኒቱ ሰው ነው እንደሚባል ሁላ አንዳንዴም ለችግራችን መፍትሄ ሰው ጋር ልናገኝ እንችላለን የሚል እንድምታም አለው...

ኦሽንoc
Leader
Leader
Posts: 1129
Joined: 07 Aug 2009 14:20
Contact:

Re: ተረትና ምሳሌ አንደኛ መፅሀፍ

Unread post by ኦሽንoc » 20 Oct 2009 00:15

ስለ ግጥሙ ያለኝ.....Hi

Post Reply

Return to “Ethio Art and Culture..ኢትዮ ጥበብ ፤ስነ ጽሁፍ ፤”