አዲስ የቴዲ አፍሮ ቃለ መጠይቅ ...Teddy Afro New Interview.

ግጥሞች፣ታሪኮች፣ፎቶዎች፣ሙዚቃዎች
Poems,Short stories, graphics,pictures,musics,Technology
Post Reply
ኦሽንoc
Leader
Leader
Posts: 1129
Joined: 07 Aug 2009 14:20
Contact:

አዲስ የቴዲ አፍሮ ቃለ መጠይቅ ...Teddy Afro New Interview.

Unread post by ኦሽንoc » 14 Oct 2009 14:05

Teddy Afro New Interview a day early of his biggest Fund raising concert.

ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ )፡ ባለፈው እሑድ ጥቅምት 1 ፣ 2002 ቁጥራቸው ከ 40ሺህ በላይ ለሆኑ፡ የሙዚቃ አፍቃሪዎቹ «ልመና ይብቃ»፤ በሚል መርህ፣ ቅዱስ ተግባር ያለው ልዩ የሙዚቃ ኮንሠርት ማዘጋጀቱ ይታወሳል ::

ይሄን ኮንሠርት ከማድረጉ አንድ ቀን ቀደም ብሎ፤ ማለትም በዕለተ - ቅዳሜ፡ መስከረም ፴፣ ፳፻፪፤ ቃለ - መጠይቅ አድርጎ ነበር።

በዚህ ቃለ መጠይቅ፡ ቴዲ፤ ስለ ስታዲዬሙ ኮንሠርት ዓላማና ዝግጅት፣ ስለ አዲሱ ነጠላ ዜማው፣ ከፊታችን ዓርብ ጀምሮ በተለያየ የዓለም ክፍሎች ስለሚያደርገው የሙዚቃ ዝግጅቱ፣ ስለ አቡጊዳ ባንድ፡ እንዲሁም ስለ እስራቱና እስር ቤት ሲገባ የሻማ አምጣ ስለመባሉ እና ስለሌሎቹም ጉዳዮች በርቱዕ አንደበቱ ያወጋናል ::
Teddy afro.jpg
Teddy afro.jpg (19.27 KiB) Viewed 7722 times
ክፍል 1


ክፍል 2


ምስጋና ለአውሎንፋስ

[center]Leave your comment Click POSTREPLY አስተያየት ለመተውPOSTREPLYን ይጫኑ[/center]

User avatar
selam
Leader
Leader
Posts: 175
Joined: 25 Aug 2009 01:59
Contact:

Re: አዲስ የቴዲ አፍሮ ቃለ መጠይቅ ...Teddy Afro New Interview.

Unread post by selam » 14 Oct 2009 19:36

አለ ገና ….አለ ገና……..በአውሮፓም አለ ገና…..በአሜሪካም አለ ገና….በሚድል ኢስት አለ ገና…..በሲድኒም አለ ገና……ገና ገና……እናም ሀገር ቤት ብቻ ሳይሆን በመላው አለም ቴዲን ናፍቀናል ….እስክናየው ጉዋጉተናል…[youtube]http://www.youtube.com/watch?v=7joaj5KKPkw[/youtube]

eyobaye
Posts: 1
Joined: 11 Aug 2009 13:07
Contact:

Re: አዲስ የቴዲ አፍሮ ቃለ መጠይቅ ...Teddy Afro New Interview.

Unread post by eyobaye » 14 Oct 2009 21:44

በጣም ያምራል ኦሽን የቴዲ አፍሮን ቃለ መልልስ ማየት የምይፈልግ ሰው ያለ አይመስለኝም፤ ኦሽን ቀሪውን ክፍልም እንደምታሰማን አልጠራጠርም፤ ለሁሉም በጣም እናመሰግናለን ፣

User avatar
selam
Leader
Leader
Posts: 175
Joined: 25 Aug 2009 01:59
Contact:

Re: አዲስ የቴዲ አፍሮ ቃለ መጠይቅ ...Teddy Afro New Interview.

Unread post by selam » 15 Oct 2009 14:28

ImageImage 12 October 2009 — When Teddy Afro leaps onto the stage the crowd goes wild, clapping in the air and singing along with the man seen by many as the voice of Ethiopia's conscience.

Fresh from his prison cell, the singer known as Ethiopia's Michael Jackson delighted tens of thousands of fans with his benefit concert for street children on Sunday.

"He was in jail for more than a year because of his songs. He wants democracy and freedom for us the Ethiopian people. We love him," shouted Alorachew, a student attending the show at the capital's sports stadium.

"Last time we saw him it was two years ago. He's a great artist, different from the others. He comes always with new things," enthused Sammy, a computer engineer who came along with a bunch of friends.

"He's talking about topical issues. Most people say there is a political message in his lyrics. I think his message is not always political, but when there is a political message, it is obviously against the government."

Next to him and slightly the worse for wear, Fredo, a young Ethiopian living in the United States, confided: "I missed Teddy a lot. He's the best in Ethiopia".

The singer, whose real name is Tewodros Kassahun and who is seen as close to Ethiopia's opposition, was sentenced to six years in prison and a heavy fine for manslaughter after a 2006 traffic accident left a homeless man dead.

The Supreme court reduced his sentence on appeal in February and he was freed in August. He has always protested his innocence, saying he was not even in the country at the time of the accident.

For his return to the stage Teddy Afro decided to take up the cause of street children and beggars, who throng the streets of Ethiopia's cities in their thousands.

All proceeds from the concert will go to an Ethiopian NGO, El Shady, which looks after several thousand street children.

"There are a lot of people. It is even more successful than we had hoped," Addis Legesse, Teddy Afro's manager and one of the organisers of the concert, said at the event.

Asked about his protege's political dimension, Addis said: "Whenever you do something for the good of the people, people talk ... but we have no political agenda, we just want to help that's all".

Teddy Afro's goal is to ease the hardship of tens of thousands of the country's poor children, he said.

"200.000 people are begging in the street in Ethiopia, people able to work, so we have to organise them and take them out of the street. We don't want to be seen as a begging nation," said Legesse.

User avatar
selam
Leader
Leader
Posts: 175
Joined: 25 Aug 2009 01:59
Contact:

Re: አዲስ የቴዲ አፍሮ ቃለ መጠይቅ ...Teddy Afro New Interview.

Unread post by selam » 17 Oct 2009 17:38

የተቸገሩትን ለመርዳት የተዘጋጀን ዝግጅት ወያኔ/ኢሕአዴግ ለሕዝብ እንዳይተላለፍ አገደ

አስተያየቶን ይተዉልንለ

አቡጊዳ -ጥቅምት 2 ቀን 2002

ቴዴ አፍሮ በታላቁ ስቴዱየም ያደረገዉ ዝግጅት ከተገመተዉ በላይ ህዝብ የተገኘበት እንደሆነ አዲስ አበባ በስቴድየሙ የነበሩ ምንጮቻችን ገለጹ። የተገኘዉ ሕዝብ ገና የድምጻዊዉ ወደ መድረኩ ሲመጣ በጩኸትና በፊጨት ደስታዉን የገለጸ ሲሆን በስታዲየሙ የነበረዉ ስሜት ከፍተኛ እንደነበረ ለማወቅ ችለናል።

«በስታዲየሙ የመጣሁት ሁለት አላማ ይዤ ነዉ። የመጀመሪዉ የምወደዉን ድምጻዊ ለመስማት። ሁለተኛዊ ደግሞ ወያኔዎች በቴዲ ላይ የፈጸሙት ግፍ ትክክል እንዳልነበረ መልእክት ለማስተላለፍ ነዉ» ስትል አንዲት ወጣት ስትናገር፣ አብሯት የነበረዉ አንድ ሌላ ወንድ ወጣት ደግሞ « ያ ብቻ አይደለም። በአገራችን ትልቅ ድህነትና ረሃብ አለ። ጥቂቶች በሚሊዮን ብር የሚቆጠሩ ቤቶች ሲሰሩ፣ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን በመንገድ ላይ ነዉ የሚያድሩት። ቴዲ ይህንን ለመቀየር ቆርጦ ስለተነሳ እኔም የዚህ በጎ ተግባር አጋር መሆን ስለፈለኩኝ ነዉ እዚህ የመጣሁት» ሲል ለተደረገው ዝግጅት ያለዉን አድናቆት ገልጿል።

«ቴዲን ያሰሩት መንፈሱን ለመስበር ነበር። እርሱ ግን አሥር እጥፍ ጠንካራ ሆኖ ወጥቶላቸዉዋል። እኛንም ለአገራችንን ለወገናችን እንድናስብ እያበረታታን ነዉ። እነርሱ ሰዉን መግደልና ማሰር፣ በጉቦና በሙስና ተዘፍቀዉ የሕዝብን ገንዘብ መብላት ነዉ ሥራቸዉ። እኛ ግን ከነርሱ ምንም ከአሁን በኋላ አንጠብቀም። እርስ በርስ እየተረዳዳን አንዳችን ለአንዳናችን እንቆማለን። የደከሙትን እናነሳለን።» ሲል በኮንሰርቱ የነበረ እድሜዉ ወደ አርባ የሚጠጋ አንድ የሕክምና ባለሞያ፣ አሁን በቴዲ አፍሮ የተጀመረዉ እንቅስቃሴ በሰፋ መልኩ በኢትዮጵያዉያን ሁሉ መስፋፋት እንዳለበትና ከፈረንጆችና ከአምባገነኑ አገዛዝ ከመጠበቅ ይልቅ ኢትዮጵያዉያን ለኢትዮጵያ መቆም እንዳለባቸዉ በማስረዳት፣ የቴዲ ኮንሰርት ፈር ቀዳጅ መሆኑን የገለጸዉ።

ወያኔ/ኢሕአዴግ የሚቆጣጠረዉ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን፣ ተራና ርካሽ የግዢዉ ፓርቲን ፕሮፖጋንዳ እየደጋገመ ሲያቀርብ፣ በብዙ ሺህ የሚቆጠር ሕዝባችን የተገኘበትንና የተጎዱ ወገኖቻችንን ለመርዳት ያስቦ የተዘጋጀዉን የቴዲ አፍሮ ዝግጅት ያላቀረበ ሲሆን አፍቃሪ ወያኔ የሆነዉ የኢትዮጵያ ፈርስት አዘጋጅ ሁሉ ሳይቀር፣ በችግር ላይ ወገኖቻችን ለመርዳት ታስቦ የተዘጋጀዉን ዝግጅት የመንግስት መገናኛ ብዙሃን አለማስተላለፈቸዉ ቅር እንዳሰኘዉ ገልጿል።

አቶ መለስ ዜናዊ በአሥር አመት ዉስጥ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በቀን ሶስቴ ይመገባል ብለዉ ቃለ ገብተዉ እንደነበረ ያስታወሱን አንድ ያነጋገርናቸዉ የፖለቲካ ተንታኝ «አሥራ ስምንት አመት ሥልጣን ላይ አሉ። ለሕዝብ ደህንነት መቆም የነበረባቸዉ እነርሱ ነበሩ። በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሕጻናት የሚበሉት ሲያጡ፣ ብዙዎች ቤት አላባ ሆነዉ በጎዳና ላይ ሲያድሩ፣ ድህነት ሲበዛ፣ ትልቅ ቅድሚያና ትኩረት ሰጥተዉት መንቀሳቀስ የነበረባቸዉ የመንግስት ባለሥልጣናት ነበሩ። ነገር ግን ህዝብን ማስተዳደር አልቻሉም።» ሲሉ የተራቡ ወገኖቻችን ለመርዳት ተብሎ የተዘጋጀዉ ይህ የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት፣ አሁን ያለዉን አገዛዝ ህዝቡን ማስተዳደርና አገሪቷን ከድህነት ማወጣት እንዳልቻለ በግልጽ ያጋለጠ ኮንሰርት እንደሆነ አስረድተዋል።

መንግስት ስልጣን ከተቆናጠጠት ጊዜ ጀምሮ ከአርባ ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ እርዳታ ማግኘቱ ይታወሳል። አሁንም አንድ ሶስተኛዉ የመንግስት ባጀት ከፈረንጆች የሚደጎም ሲሆን አቶ መለስ ዜናዊ «ለማኝ ቁጥር አንድ» በመሆን በበለጸጉ አገራት ስብሰባ ላይ ደጋግመዉ መገኘታችቸዉ ያታወሳል።

ኦሽንoc
Leader
Leader
Posts: 1129
Joined: 07 Aug 2009 14:20
Contact:

Re: አዲስ የቴዲ አፍሮ ቃለ መጠይቅ ...Teddy Afro New Interview.

Unread post by ኦሽንoc » 18 Oct 2009 11:04

የተወዳጅና ዝነኛው አርቲስት ልዑል ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ ) ተከታይ ቃለ ምልልስ እነሆ !
teddyafro2.jpg
teddyafro2.jpg (34.03 KiB) Viewed 6816 times
ክፍል 3


ክፍል 4


User avatar
selam
Leader
Leader
Posts: 175
Joined: 25 Aug 2009 01:59
Contact:

Re: አዲስ የቴዲ አፍሮ ቃለ መጠይቅ ...Teddy Afro New Interview.

Unread post by selam » 19 Oct 2009 14:55

' :lol: ያንቺ ትዳር ነው ወይስ የነና ያንቺ ፍቅር
ውደ ንገሪኝ የቱ ነው ትክክል
ተያት ይህቺ አለም ለአቅ የላትም ዳኛ
ልክ ባንሆንም ልክ ነን እኛ.''
ትክክል ቲዲ :!:Image

Post Reply

Return to “Ethio Art and Culture..ኢትዮ ጥበብ ፤ስነ ጽሁፍ ፤”