ጤዛ ፣ ሁሉም ሰው ማየ ት የሚገባው ድንቅ ፊልም!

ግጥሞች፣ታሪኮች፣ፎቶዎች፣ሙዚቃዎች
Poems,Short stories, graphics,pictures,musics,Technology
User avatar
selam
Leader
Leader
Posts: 175
Joined: 25 Aug 2009 01:59
Contact:

ጤዛ ፣ ሁሉም ሰው ማየ ት የሚገባው ድንቅ ፊልም!

Unread post by selam » 12 Oct 2009 19:17

ጤዛ ፣ ሁሉም ሰው ማየ ት የሚገባው ድንቅ ፊልም!
ዳይሬክተር፣ ሃ ይሌ ገ ሪማ
ርዝመት፣ 140 ደቂቃ Image
ቋንቋ፣ አማርኛ - ሰብታይትል፣ እንግሊዝኛ/ፈረን ሳይኛ/ዳች
(በክንፉ አሰፋ - አምስተርዳም)
እ.ኤ.አ. በ1980ዎቹ ከሃ ገ ሩ በተሰደደው ኢትዮጵያዊ ምሁር በዶ/ር አን በርብር
(አሮን አረፈ-ዓይኔ ) ህይወት (narratives) ላ ይ የ ተመሰረተ ታርክ ቀመስ
- እውነ ት ቀመስ - ፊልም ነ ው ጤዛ ።
በዚህ ፊልም ዶ/ር አንበርብር በስደት ይኖር ከነ በረበት ከምስራቅ ጀርመን ወደ
አዛውንት እናቱ ተመልሶ ይመጣል። ከጀርመን ናዚ ርዝራዦች በደረሰበት ክፉኛ
ድብደባ አን በርብር አንድ እግሩን አጥቷል። ከብዙ አመታት የ ምዕ ራቡ አለም ቆይታ
በኋላ ፣ የ ገ ጠር ህይወት ህይወትን መግፋቱ ለአንበርብር እንደሰመመን
ይሆንበታል። አማራጭ ግን አልነ በረውም። ወደ ኋላ ም እየ ተመለሰ የ ጥንቱን
በትውስታ (flashback) ይቃኛል።
በምስልና ድምጽ ጥራት፣ በሙዚቃ አመራረጥና አገ ባብ፣ በሲኒ ማቶግራፊና ስክሪን-
ፕሌይ እስካሁን ካየ ናቸው የ አፍሪካ ፊልሞች ሁሉ ጤዛ አቻ የ ሌለው ፊልም ነ ው
ከማለት ውጪ ምንም የ ምጨምረው የ ለም።
እንደ ፊልሙ ዳይሬክተር አቶ ሃ ይሌ ገ ሪማ አባባል ፊልሙን ለመስራት 14 አመታት
ፈጅቷል።
ፍቅርን፣ ፖለቲካን፣ ሃ ይማኖትን፣ ባህልን....ሁሉንም በየ ፈርጁ ይዳሥሳል። ተመልካቹን፤ ከምስራቅ ጀርመን አዲስ
አበባ... ከአዲስ አበባ ደግሞ ጎ ንደር አያለ የ ገ ጠሩን ና የ ከተሜውን የ ሕይወት ስንክሳር እያነ ጻጸረ ያስቃኘናል።
አንበርብር በምስራቅ ጀርመን ህክምና ተምሮ እንደተመለሰ
ከአንባገ ነ ኑ ስርዓት ጋር ሲጋፈጥ ይታያል። ሰቆቃ
በነ ገ ሰበት በዚያ ዘ መን የ ስርዓቱ ካድሬዎች ሁለቱን
ጓ ደኞቹን ይገ ድሉበታል - እሱንም ስቃዩ ን ያሳዩ ታል።
ዶ/ር አንበ ርብር ከፖለቲካው ራሱን አርቋል፣ ከአንዳቸው
ቡድን ውስጥም የ ለበትም። ከፖለቲካ ነ ጻ መሆኑ ግን
ከአደጋው አላ ዳነ ውም፣ - “መሃ ል ሰፋሪ በሁለት አቅጣጫ
ይመታል” - የ ሚለው የ ሟች ጓ ደኛው ምክርም የ ገ ባው
አይመስልም።
ጓ ደኞቹ በደርግ ካድሬዎች በአሰቃቂ ሁኔ ታ ተደብደበው
ከተገ ደሉ በኋላ ፣ ደርግ ዶ/ር አንበርብርን እንደገ ና
ወደ ምስራቅ ጀርመን ይልከዋል። ጀርመን እን ደገ ባም ሰላም አላ ገ ኘም፤ እዚያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘ ንድ በሰላ ይነ ት
ይጠረጠራል። ከሁሉም ደግሞ የ ቸገ ረው የ ጓደኛውን መርዶ ለቤተሰቦቹ ማርዳት ነ በር። ከነ ጭ ወልዶ አዲስ አበባ
የ ተመለሰው ጓ ደኛው ለዳግም ስደት ሲዘ ጋጅ በጥይት ተደብደቦ ተገ ድሏል።
ጤዛ ፤ ከነ ጭና ከጥቁር የ ሚወለዱ ልጆች፣ ነ ብስ ሲዘ ሩ የ ሚደርስባቸውን የ ስነ -ልቦና ቀውስ ለመዳሰስ ይሞክራል።
ከካሜሩንና ከጀርመን የ ምትወለደውን የ ካሳንድራን አስቸጋሪና የ ሰቆቃ ህይወት በተምሳሌትነ ት ያሳያል። ራሳቸውን
ተራማጆች (progressieve) ነ ን የ ሚሉ እነ ዚህ ሰዎች የ ልጆቻቸውን ህይወት ምን ያህል ለመከራ እንደሚድርጉ
የ ሟች ልጅ ምስክር ነ ው።
አንበርብር ይህን መርዶ ለሟች ልጅና ለጀርመናዊት እናቱ ለመንገ ር በመቸገ ር እያመነ ታ ሳለ ነ ው በዘ ረኞች ተደብደቦ ና
አንድ እግሩን አጥቶ ውደ ኢትዮጵያ የ ተመለሰው።
2
ወደሃ ገ ሩ ሲመለስ ከመጽሃ ፍቶች በቀር ምን ም የ ያዘው ነ ገ ር የ ለም። የ ተወለደባት መንደር ሲገ ባ ያገ ኘው የ ሙሶሎኒ ን
ሃ ውልት በቻ ነ ው። ለማስታወሻ የ ቀረ ሌላ አንዳችም አልነ በ ረም። ከረጅም አመት የ ውጭ ቆይታ በኋላ የ ገ ጠሩን ህይወት
ለመልመድ ባይቸግረውም፤ ሰው ሰራሹ ችግር አዲስ ይሆንበ ታል፣ የ ማያልቀው ጦርነ ትና የ ጦርነ ት ወሬ፣ ካድረዎቹ ወጣቱን
ሲያሳደዱና ሲገ ድሉ... በ ራሱም ተስፋ ይቆጥርጣል።
ፊልሙ ባሕላችን ፣ እምነ ታችንና ማህበራዊ ህይወታችን - በተለይ በገ ጠሩ አካባቢ -በእያን ዳንዳችን ኑሮና ህይወት
ላ ይ፣ ምን ያህል ተጽእኖ እን ዳለውም ያሳየ ናል። ዶ/ር አን በርብር በሁኔ ታዎች ተደናግሮ፣ ገ ራ ገ ብቶትና ፈዞ ፣
የ ተመለከቱት የ አካባቢው ነ ዋሪዎች ችግሩን ሊረዱለት አልቻሉም። መረበሹንና መፍዘ ዙን ያዩ ሁሉ ይልቁንም በላ ዩ ላ ይ
አንዳች ነ ገ ር ሰፍሯል ይሉ ጀመር። ወደ ጸበ ልም ሄ ዶ እንዲጠመቅ ተገ ደደ። ቀሳውስቱም ጸበል እየ ረጩ በዶ/ር
አንበርብር ላ ይ ያለውን ርኩስ መንፈስ ገ ሰጹት።
አንበርብር የ ደህና ቤተሰብ የ ሆነ ችን ኮረዳ እንዲያገ ባ ቢጠየ ቅም ቀልቡ ግን ያረፈው በቤት ስራተኛቸው - በአዛ ሉ
ላ ይ ነ በር። አዛ ሉና አንበ ርብር ተዋደዱ.. ለዚህም ከፈሉበ ት።
አዛ ሉ በዶ/ር አንበርብር እናጥ ቤት ተጠልላ አዛውንትዋን እያገ ዘ ች የ ምትኖር ውብ እመበ ለት ናት። ዶ/ር
አንበርብርን በ ጀልባ እየ ቀዘ ፈች የ ግሌ ወዳለችው ደሴት ትወስደውና - ከደሴቱ ያለችን አንዲት ግማሽ ጎ ንዋ የ ሞተ
- ግማሽ ጎ ንዋ ደግሞ ህይወት ያላ ት ዛ ፍ ጋር ህይወትዋን እያመሳሰለች ትነ ግረዋለች። አዛ ሉ ከዶ/ር አንበርብር ጋር
ፍቅር መጀመርዋን የ ሰማ ወግ አጥባቂው የ አካባቢው ህዝብ ዝም አላ ለም። በመንደሩ ነ ውር እንደሰራችም ፈረዱባት።
በመጨረሻ አዛ ሉም ትሰደዳለች - ወጣቶች ከአፈሳ ሸሽተው ወደሚደበቁበት ዋሻ። እዚያው ከዶ/ር አንበ ርብር
የ ጸነ ሰችውን ወንድ ልጅ ትወልዳለች። ስሙንም ተስፋዬ ብለውታል።
የ ተስፋዬ ተስፋ ግን አሁንም የ ጨለመ ነ ው
የ ሚመስለው። የ ደርግን ኮምኒ ዝም በአልባን ያው
ኮምኒ ዝም ለመተካት በየ ጫካው ህዝቡን እየ ሰበኩ ሎሎች
ብቅ እያሉ እን ደሆነ ም ፊልሙ ጠቆም ያደርጋል።
እዚህ ላ ይ ያሁኖቹን ኮሚኒ ስቶች ነ ካ የ ሚያደርጋቸው።
አንበርብር በስደት ላ ይ ተሰቃይቷል፣ ተቀጥቅጧል፣
እግሩንም አጥቷል። ይህ በ ኔ ላ ይ ለምን ሆነ ብሎ
አይጨነ ቅም። ከዚህ በላ ይ የ ሚያስጨንቀው፣ በ ሃ ገ ሩ
ወገ ን - ወገ ኑን ሲያሳደድ - እያሳደደም ሲገ ድለው
ማየ ቱ ነ ው።
3
ፊልሙን የ ሚመለከቱ ብዙዎች ያለቅሱ ነ በር። አንዳንዶች በትዝታ ባህር ውስጥ ተዘ ፍቀው በ ህሊናቸው ለአመታት ወደ ኋላ
ሲጓ ዙና ያለፉበ ትን ህይወት በ ህሊናቸው ሲቃኙ አስተዋልኩ። በተለይ በስደት ላ ይ ያለነ ው ኢትዮጵያውያን፣
እያንዳንዳችንን በፊልሙ ወስጥ እናገ ኛለን ።
የ ፊልሙ ዲያሬክተር በፊልም ኢንዱስትሪ ስሙ የ ገ ነ ነ ይሁን እንጂ በገ ጠር አካባቢ የ ተቀረጹት የ ፊልሙ ተዋንያን -
እንኳን የ ፊልም ሞያ ሊማሩ - ፊልም አይተው የ ሚያውቁ አይመስለኝም። ደራሲ የ ፈጠራቸው የ ጥበብ ሰዎችም አይደሉም።
ቀሳወስቱ፣ አባወራው፣ ባልቴቷና፣ ወጣቶቹ ያሳለፉትን እውነ ታና የ ለት-ተዕ ለት ኑሯቸውን ሲኖሩ ነ ው ካሜራው
ይቀርጻቸው የ ነ በረው። የ ገ ጠሬው ወግ፣ የ አን ጋገ ር ለዛ ና ትወና (አክቲንግ) .. እን ደወረደ መሆኑ ታሪኩም ምንም
ያልተቀየ ጠ እውነ ታ... ለፊልሙ ውበትን ችሮታል። የ አዛ ሉ ዜማዎችም መንፈስን የ ሚያስደስቱ፣ ትዝታን የ ሚቀሰቅሱ
ትርጉም ያላ ቸው የ ሙዚቃ ቃናዎች ናቸው።
የ ቀይ ሽብርን ይልቁንም የ ኢትዮጵያን የ አስርት-አመታት ሰቆቃ በደንብ ላላጤነ ው፣ ጤዛ ፊልም ሲጀምር በእንካ-
ሰላምቲያ ነ ው ሲጨርም ግን በእንቆቅልሽ። በ ዛ ውስጥ ላ ለፉት ግን በትዝታ ለአመታት ወደ ኋላ ይዞ ይጨልጣል።
ፊልሙን ቀድሞ ላ ልተመለከተው በፊልሙና በ ፊልሙ ዳይሬክተር ይወርድ የ ነ በረው የ ወያኔ ቴለቭዥን ውርጅብኝ ግራ ሊያጋባ
ይችላ ል። እነ ዚህ ጋዜጠኞች ሃ ይሌ ገ ሪማን ከፊልሙ ዋና ተዋናይ ከዶ/ር አንበርብር ጋርም ሳይቀር እያመሳሰሉ ነ በር
በጤዛ ና በሃ ይሌ ላ ይ የ ዘመቱት።
ይህ በሆነ ባሳምንቱ ግን ከወደ ቡርኪና-ፋሶ የ ወያኔ ን ጋዜጠኞች የ ሚያሸማቅቅ አንድ ዜና ተሰማ፣ ጤዛ የ ፌስፓኮ
21ኛው የ ፓን አፍሪካ ፊልም ፌስቲቫል ኦስካር ተሸላሚ ነ ው ተባለ። የ አውሮፓው የ ልማት ሚኒ ስትር ሉዊ ሚሼል ሳይቀሩ
ጤዛ የ ኦስካር ተሸላሚ በመሆኑ የ ደስታ መግለጫቸውን አሰሙ።...ይገ ባዋል።
በርግጥ ጤዛ ሁሉም ሰው ማየ ት የ ሚገ ባው ድን ቅ ፊልም ነ ው።Image

Post Reply

Return to “Ethio Art and Culture..ኢትዮ ጥበብ ፤ስነ ጽሁፍ ፤”