አቤት መልክታቸው ሲጣፍጥ SWEET VOICE MAILS

ግጥሞች፣ታሪኮች፣ፎቶዎች፣ሙዚቃዎች
Poems,Short stories, graphics,pictures,musics,Technology
Post Reply
yewondwossen
Posts: 4
Joined: 17 Sep 2009 07:35
Contact:

አቤት መልክታቸው ሲጣፍጥ SWEET VOICE MAILS

Unread post by yewondwossen » 10 Oct 2009 13:45

አቤት መልክታቸው ሲጣፍጥ SWEET VOICE MAILS

ስለፅሁፉ አስተያየት ፣ በኤሌክትሮኒክ ደብዳቤ enjera.story@gmail.com" onclick="window.open(this.href);return false" ለደራሲው በቀጥታ ማስተላለፍ ይቻላል
የደራሲው መብት በህግ የተጠበቀ ነው
Copyright©2009 by Yewondwossen Adefris. Seattle, WA. USA. All rights reserved.

--------------------------------------****************************-------------------------------------
አቤት መልክታቸው ሲጣፍጥ
ደራሲ የወንድወሰን አደፍርስ


Image

ብዙ ግዜ ቤተሰብ ፣ጉዋደኛ ፣ዘመድና ወዳጅ በስልክ ደውለን ወዲያው ማግኘት እንደማንችል የታወቀ ነው። የተደወለለት ሰው በተለያየ ምክንያት ወዲያውኑ ስልኩን መመለስ አይችልም።
ታድያ የደወልንለት ሰው መልሶ እንዲደውልልን ስንፈልግ ፣ ቆንጆ የአማርኛ ቋንቋ እግዚአብሔር አድሎናል ፤ ለምንድነው በግጥምም ሆነ በቅኔ ያማረ፣ እጥር ምጥን ያለ መልክት የማንተወው?

በምሳሌ ለማስረዳት ያህል የምወዳቸውን የቤተሰቦቼንና የጉዋደኞቼን ስም ጠቅሻለሁ።

ለጓደኞች፡
ዳንኤል አሉላ ጠፋህብኝ የምር
ዘመናዊው ያሬድ የሙዚቃው ምሁር
ቀልድህ ቁም ነገርህ ሁሉም ናፈቀኝ
በሶስቱ ስላሴ ፈጥነህ ደውልልኝ

የኔማ አለምጸሐይ የሐረርዋ እመቤት
ብታሳርስ ነጭ ጤፍ ብታደልብ ሙክት
ስትጠፊብኝ ግዜ ስልኩን ደወልኩት
ስታገኚ ደውይ ደቂቃና ወቅት

*********
ለባለቤት ወይ ለፍቅረኛ፡
ከወንድ፡
የኔ እሌኒ ነጋሽ የአይኔ ወለላ
ፍቅሬ ፣ባለቤቴ ፣የልጆቼ እናት ሁሉም ነሽ ጠቅላላ
ድምጽሽን ከሰማሁ እኩለ ቀን ሞላ
ባክሽ ደውይልኝ ፣ እረ ምን ጉድ ፈላ?
ከሴት ፡
ሔኖክ አለኝታዬ ማር ወተቴ ፍቅሬ
ሳትደውል ቆየህ ቀልድም የለ ወሬ?
ቀልድና ጨዋታ አያሻኝም አሁን
እኔ እምፈልገው መስማት ነው ድምጽህን

***********
ለአባት፡
የኔማ አባብዬ የምወድህ በጣም
እንደምን ሰነበትክ አገኘህ ወይ ሰላም
ደውየለህ ነበር በጣም ናፍቀህኝ
እስክትደውል ድረስ ደህና ቆይልኝ
ለእናት፡
የኔማ ንጋቷ አሳዳጊ እናቴ
ድምፅሽን መስማቱ ነበር ፍላጎቴ
ልጠብቅ እንግዲህ በትግስት ከቤቴ
ቶሎ ደውይልኝ አደራ በሞቴ

**********

ለእህት
የኔማ ወላንሳ እቴሜቴዬ ነሽ
አይኔ ላይ መጣብኝ ፈገግታሽ ውበትሽ
ደውዬ ነበረ መስሎኝ እማገኝሽ
ተራሽን ደውይ ድምጼን እንደሰማሽ
ለወንድም
ተስፋዬ አደፍርስ ወንድም ጌታዬ ነህ
ጸሎት ፣ዜማ ፣ስእል ወይስ ጽሁፉ ነው? እንደዚህ ያጠፋህ?
ቢቸግር ቢጨንቀኝ አሁን ደወልኩልህ
እባክህን ደውል መልሱን እንዳውቅልህ

*************
ለሴት ልጅ፡
የኔማ አንኮበር የኔ ብልጣ ብልጥ
ስልኬን የማትመልሽ ምንድነው በርግጥ?
አንቺን ባልናፍቅሽ እኔን ናፍቀሽኛል
ስልክሽን መጠበቅ አላስችል ብሎኛል

********
ለወንድ ልጅ፡
አዬ ልጅ ምኒሊክ የጎረምሳ ንቀት
ስልኬን የማትመልስ ጥጋብ ነው ኩራት?
አላስገድድህም አልል ደውል በግድ
ማሳደጌ ቀርቶ ፣ደግሞ አንተን ልማለድ?

ተፈጸመ

Yonas G.
Posts: 2
Joined: 19 Aug 2009 07:36
Contact:

Re: አቤት መልክታቸው ሲጣፍጥ SWEET VOICE MAILS

Unread post by Yonas G. » 12 Oct 2009 15:43

ሄሎ ሄሎ ተናፋቂ እህቴ
ስልኩን አታነሺም ስደዉል በሞቴ
በጣሙን በጣሙን ተጨንቁያለሁኝ
ስልክሽን በአስቸኴይ እጠብቃለሁኝ

yewondwossen
Posts: 4
Joined: 17 Sep 2009 07:35
Contact:

Re: አቤት መልክታቸው ሲጣፍጥ SWEET VOICE MAILS

Unread post by yewondwossen » 14 Oct 2009 14:44

ዮናስ በጣም ቆንጆ ነው።

ቶቶ አደፍርስ

selome11
Posts: 2
Joined: 30 Oct 2009 21:06
Contact:

Re: አቤት መልክታቸው ሲጣፍጥ SWEET VOICE MAILS

Unread post by selome11 » 06 Nov 2009 02:44

hahaha nice we should use this.. :lol: i like this.

Post Reply

Return to “Ethio Art and Culture..ኢትዮ ጥበብ ፤ስነ ጽሁፍ ፤”