የግጥም ቤት...

ግጥሞች፣ታሪኮች፣ፎቶዎች፣ሙዚቃዎች
Poems,Short stories, graphics,pictures,musics,Technology
Post Reply
User avatar
selam
Leader
Leader
Posts: 175
Joined: 25 Aug 2009 01:59
Contact:

የግጥም ቤት...

Unread post by selam » 03 Oct 2009 16:36

Image :roll:
Last edited by selam on 03 Oct 2009 17:02, edited 1 time in total.

User avatar
selam
Leader
Leader
Posts: 175
Joined: 25 Aug 2009 01:59
Contact:

Re: እንባየ...

Unread post by selam » 03 Oct 2009 16:43

ይብላኝ ለወይኒቱ! :roll:
Aይሆንም Eያለች ልሳምሽ ቢሏት፣
Aይሆንም Eያለች Eናግባሽ ቢሏት፣
ስንቱን ሽማግሌ Aማጭ ላኩባት፣
መምህሩም በመስቀል ቢያወርዱ ግዝት፣
ቀልድ መሰሎ ታያት Eንደ ልጅ ተረት…
ወይ ገዳም ግቢና መንኩሺ በወግ፣
ወይም Eንዳርሽ፣ Eንድንበላ ሰርግ
ጊዜው ሳያልፍብሽ የትዳር መዓርግ
ወልደሽና ከብደሽ በትዳር፣ በሕግ!
ካልሆነ’ማ Aፈር ነሽ፣ ነገ ወደ ፍግ…
ጥፍሯንም በቀለም Aሽቀረቀረችው፣
ከንፈሯን በቀለም Aሽቀረቀረችው፣
በEሾኽ፣ በሽቦ ራሷን ያጠረችው፣
መልኳና ውበቷን Eንዳፈቀረችው፣
ይብላኝ ለወይኒቱ፣ ቆማ ለቀረችው…
ገ/I. ጐርፉ።

User avatar
selam
Leader
Leader
Posts: 175
Joined: 25 Aug 2009 01:59
Contact:

Re: የግጥም ቢት...

Unread post by selam » 03 Oct 2009 17:03

Image

bekalu
ጀማሪ Starter
ጀማሪ Starter
Posts: 8
Joined: 08 Sep 2009 09:51
Contact:

Re: የግጥም ቤት...

Unread post by bekalu » 04 Oct 2009 08:26

ከንቱነት

ስንናገር በትህትና ". አንዴ ለማውራት ያሰብነውን
ማን ይሆን ፌዙን ትቶ ". የሚሰማ ድምጻችንን".
እንደ ነዳያን የስቃይ ዜማ"" ድምጻችን በሀዘን ተሞልቶ
ማን ይሆን አዳማጩ". ፌዝና ቧልቱን ትቶ
ለስቃይ ለችግራችን እንደነገሩ ካዘንንማ
ከአንገት በላይ ካለቀስን
ከነገሮች ጅማሬ ጋር ስሩን ሰዶ ከመጣብን
ምንስ አይኖች ከቶ ሊያዩት ይህን ቁስል አፋችንን
እንደ ኪንታሮት እንደ ዕጢ እንደ ዕባጭ ሆኖ በቅሎ
በአሳዛኙ ጉሮሮአችን ውስጡ ጠልቆ አጎንቁሎ
ምንስ ጆሮ፣ ከየት ሊገኝ የሚያዳምጥ ሆነ ብሎ
የማንስ ልብ ሊያስታውሰው". የኛን ሀዘን እንጉርጉሮ
ማነው ስሚው ለቁጣችን ". ለኛ ብሶት ለእኛ ሮሮ""

(ካሣሁን ከበደ፣ ከጃርት ወደ ዳርት፣ 2000)

User avatar
selam
Leader
Leader
Posts: 175
Joined: 25 Aug 2009 01:59
Contact:

Re: የግጥም ቤት...

Unread post by selam » 13 Oct 2009 20:29

Image

User avatar
ሰላም
ጀማሪ Starter
ጀማሪ Starter
Posts: 9
Joined: 27 Oct 2009 17:07
Contact:

Re: የግጥም ቤት...

Unread post by ሰላም » 02 Nov 2009 14:17

እማምዬ

ብትናፍቀኝ እሙዬ
ቢጎርፍ ትዝታው -
ያ ! ሀሪቲ ምድሯ
ዝንተ አለም ማልረሳው -
አረንጓዴ ቢጫ
ቀዩን ምልክቴ -
ታጥቄ ብቅ አልኩኝ
ቢደበቅ ብሶቴ ::
ሰውንቴ ደልቶት
ጉንጮቼ ቢሞሉም -
ሞልቶ የተረፈኝ
ቱጃር ሰው ብመስልም -
እኔ መች አጥቼው
መክሳት መጥቆሬን -
ውስጤን ናፍቆት ሰብሮት
ሽባ መሆኔን -
ግን ወጣሁ ከመንገድ
ካደባብዩ ላይ -
ሀ ሁ ዬን ለብሼ አርማዬን ታጥቄ -
ማንነቴ ላሳይ ::
ቢበላ ቢጠጣ
በች ተበላ ያሰኛል -
ቢተረት ቢቀለድ
መች እንዳገር ያምራል -
ወልደው ቢያሳድጉ
አይሆን እንደሐገር -
ስለውነት በእውነተ
ካልን እንነጋገር -
የአንቱታን ማዕረግ
አያስታጥቅ ክብር ::
ናፈኩኝ ናፈኩኝ
የኔን ኢትዮጵያዬ -
ወደውስጥ አነባሁ
እስኪነድ ገላዬ -
ምን አካል አለኝ
የተቀባ ሸካላ -
ፍቅር ያልዳሰሰው
ሳቅ ያልነካው ገላ -
በናፍቆት ሰቀቀን
በቁም የተበላ ;
መንፈሴ ድሪቶን ደርቶ
እግሩ ተፈንክቶ -
አመድ ነዝቶና
በአጥንቱ ቀርቶ -
ምን ገላየ አምሮበት
ቢለጠጥ ቢሰፋ -
ከእማምዬ ጠረን
ሚዛንን አይደፋ :[img][img][/img][/img]

Post Reply

Return to “Ethio Art and Culture..ኢትዮ ጥበብ ፤ስነ ጽሁፍ ፤”