አቤት እንጀራቸው ሲጣፍጥ ..Abet Enjerachew Sitafit ( Short story)

ግጥሞች፣ታሪኮች፣ፎቶዎች፣ሙዚቃዎች
Poems,Short stories, graphics,pictures,musics,Technology
Martha
ጀማሪ Starter
ጀማሪ Starter
Posts: 7
Joined: 24 Sep 2009 18:12
Contact:

Re: አቤት እንጀራቸው ሲጣፍጥ ..Abet Enjerachew Sitafit ( Short story)

Unread post by Martha » 01 Oct 2009 03:03

ደስ የሚል ነገር። ምስኪን ወይዘሮ አቻም የለሽ ምነው በክፍል አንድ እየጮሁ እንደተውናቸው ቀሩ???? I love the story i think as i understand writer try to tell us about obama that we have to be happy too. because of he is african as well???/ kine kine kine what will happen to him??? i love to know part 3.

helen
Starter
Starter
Posts: 19
Joined: 10 Aug 2009 17:36
Contact:

Re: አቤት እንጀራቸው ሲጣፍጥ ..Abet Enjerachew Sitafit ( Short story)

Unread post by helen » 01 Oct 2009 10:27

:roll: ኡፍ...ያ እንጀራ እንዴት ያስጎመጃል!! አስደሳች ታሪክ ነው,,ለመሆኑ የኪነስ ነገር ምነው የውሃ ሽታ ሆኖ ቀረ??
Click Next.... for more Injera Story >>>>>

ኦሽንoc
Leader
Leader
Posts: 1129
Joined: 07 Aug 2009 14:20
Contact:

Re: አቤት እንጀራቸው ሲጣፍጥ ..Abet Enjerachew Sitafit ( Short story)

Unread post by ኦሽንoc » 02 Oct 2009 20:18

ቅድመ ታሪክ፡
አቶ ቸኮል ግርማ ፣ አቶ ኪነ ጥበቡና፣ ወ/ሮ አቻምየለሽ በሲያትል ከተማ ሬኔር-ቢች በተሰኘው መንደር የሚኖሩ ጎረቤቶች ናቸው።አቶ ቸኮል እድሜው 33 ሲሆን በታክሲ ነጅነት ይተዳደራል። አቶ ኪነ እድሜው 23 ሲሆን በቅርቡ ዲቪ (የአሜሪካ ነዋሪነት እጣ ) አግኝቶ የመጣ ተማሪ ነው። ወ/ሮ አቻምየለሽ እደሜአቸው 63 ሲሆን በሲያትል ሸረተን ሆቴል ማእድ ቤት ውስጥ በረዳትነት ይሰራሉ በተጨማሪም እቤታቸው ውስጥ እንጀራ እየጋገሩ ይቸረችራሉ ። ወ/ት ሱዛን ዞርን እድሜዋ 25 አምት ሲሆን በአዲስ አበባ ተወልዳ ያደገች በዩኒቨርስቲ ኦፍ ዋሽንግተን የህክምና ተማሪ ነች ፣ በተጨማሪም አርብ እና ቅዳሜ ዱከም-አዳራሽ በተሰኘው የኢትዮጵያ ምግብ ቤት ባስተናጋጅነት ትሰራለች ። ወ/ሮ ልሳነ-ማርያም እድሜያቸው 43 ሲሆን የ ‘ዱከም-አዳራሽ’ ባለቤት ናቸው።
ሌሎች በአጭር የተጠቀሱ ስሞች ፣ ቦታዎችና ሁኔታዎች፡
1. ስኖው-ቦርዲንግ፡ በበረዶ ከተሸፈነ ተራራ ላይ ሆኖ ፣ እግር ላይ ጣውላ አስሮ ፣ቁልቁል ፣ እየተንሸራተቱ መጫወት
2. ፉት-ፌቲሽ፡ ካልጠፋ አካል እግር የሚያስወድድ የአእምሮ በሽታ
3. ካርቦ-ሀይድሬት ፡ ዳቦ ፣ እንጀራና ፣ ጥራ-ጥሬ ውስጥ የሚገኝ ፣ ለጤንነት አስፈላጊ ቢሆንም ፣ ሲበዛ ደግሞ ፤ ሆድ አዘርጥጦ ፣ የስኩኳር በሽታ የሚያስከትል ሞሎኪዩል
4. ቶቶ ፡ የአቶ የወንድወሰን አደፍርስ ቅፅል ስም። አቶ የወንድወሰን እድሜው 48 ሲሆን ፣ በዋስትና-ድርጅት-አገልግሎት ተቀጥሮ ይሰራል ፤ በትርፍ ግዜው ደግሞ “ፀፀት” ተብሎ የተሰየመ ፣ የህሊና ወቀሳ ላይ የተመሰረተ ፣ ልብ-ወለድ መፅሐፉን ይጽፋል


[center]አቤት እንጀራቸው ሲጣፍጥ (ክፍል 3)[/center]
[center]ደራሲ የወንድወሰን አደፍርስ[/center]


“የቸኮል የእጅ ስልኩ አቃጨለ”
“ኤይት -ሀንድረድ-ዳለር?” ብሎ በእንግሊዝኛ የገንዘቡን ልክ ተናገረ
“ራይት ናው?” ብሎ አሁኑኑ አገልግሎቱ እንደሚፈለግ አረጋገጠ
“ኦኬ” ብሎ ስልኩን በደስታ ዘጋ
“ሱዚዬ በናትሽ ላስቸግርሽ ፤ ቤሊንገሀም ደርሶ-መልስ የሚሄዱ ተሳፋሪዋች አግኝቻለሁ፣ $800 ብር ለመክፈል ፍቃደኛ ናቸው፤ ኪነን ቤት ትወስጅልኛለሽ? አላት ከሲያትል 130 ኪሎ-ሜትር የሚርቅ ከተማ እየጠራ
ኪነን ፈቅዳዋለች። ሆኖም ይሄንን ሰበብ ማግኘቷ ደስ እንዳላት እንዳያውቅባት ብላ “እኔን ደግሞ ሰኞ ስኖኩዎልሚ ፣ ወጭውን ሁሉ ችለህ ስኖው-ቦርዲንግ ከወሰድከኝ?” አለች ፣ ከሲያትል 50 ኪሎ-ሜትር የሚርቅ ተራራማ የበረዶ መንሸራተቻ እና መዝናኛ መንደር መሄድ እንደፈለገች አስመስላ።
“ደስ እያለኝ! የኔ እመቤት” አላት ፤ ቀጠል አድርጎ ፣ “እኔ እንደሆነ እዛ በረዶ ተራራ ላይ አልወጣልሽም ፣ ከታች ሆኜ አይሻለሁ”
“አንተ እኮ ድሮም ከሴት-ልጅ ታች መሆን ትወዳለህ አለችው ” በጨዋታ መልክ ጀርባዋን አዙራ እየታከከችው
“ሂጂ-ወደዛ ! ባለጌ !” ብሎ ትንሽ ገፍተር አደረጋትና ፣ መቀመጫዋን እንደሚመታ አስመስሎ እጁን በጨዋታ ሰንዘር አድርጎ ሲያበቃ፣ እየሳቀ ቢጫ ታክሲውን አስነስቶ ከነፈ።
“አንተስ ለሞሆኑ ከሴት-ልጅ ታች ሆነህ ታውቃለህ ፣ ወይስ አካኪ ዘራፍ እያለ ከላይ ብቻ እንደሚጋልብ ነፍጠኛ ነህ?” ድምጽዋን ስምምን ፣ አካሏን ቅልስልስ እያደረገችና ወደ መኪናዋ እያመሩ።
ከኪነ መልሱን ሳትጠብቅ በድንገት “እንደውም አንተ ንዳ ፣ እኔ ደክሞኛል” አለች በራሷ መኪና ጋቢና ተሳፋሪ ሆና እየተቀመጠች
“ቀኑን ሙሉ የቆምኩበት እግሬ ሊገለኝ ነው” በአግድመት ተቀምጣ ፣ ሁለት እግሮቿን አነባብራ ፣ መሪው እና የፊት መስታወቱ አጠገብ ደነቀረችው። ጫማዋን አውልቃ ስለነበር ፣ “የላቧ ሽታ ያጠነባኝ ይሆን? ብሎ አሰበና ፣ “ይሁና ! ጨጓራና-እግር ሳይሸት ፣ ሽማግሌና-አሮጊት ሳይሸብት ፣ እንዴት ይሆናል” ብሎ አፍንጫውን ቀስሮ ቢጠብቅ ፣ ሽኔል-ቁጥር-አምስት ከተሰኘው የሽቶዋ መአዛ በስተቀር ሌላ አላገኘም። ከስር ቀላ ብሎ ፣ እንደ አራስ ልጅ ቆዳ ልስልስ ያለ የሚመስለው እግሮችዋ ላይ ያሉት ጣቶችዋ ፣ ረጃጅምና ቀጭን ናቸው ። ጥፍሮችዋ ባጭሩ ተቆርጠዋል ፣ ከሁሉ የገረመው ግን ጥቁር ቀለም መቀባታቸው ነው። ከጉርምስነቱ ጀምሮ በሺ የሚቆጠሩ የሴት እግሮችን አስተውሏል። ጥቁር የጥፍር ቀለም ግን ሴት ላይ ሲያይ የመጀመሪያው ግዜው ነው።
ከመጀመሪያዋ እጮኛው ከወ/ት ወይዘሪት ጋር ያጣላቸውም ፣ ይኸው መከረኛ አይኑና ጥቃቅን ነገር ማስተዋሉ ነበር።
“እንዴ ? አንተ ከጥፍሬ ምን አለህ ? ጥፍራም!” ብላ ትሰድበዋለች ፣ ያለ ቅጥ ተወለጋግደው ያደጉትን የእግሯን ጥፍር ካልቆረጥሽ ብሎ ሲጨቀጭቃት
ወይዘሪት ፣ ቆንጅዬ ልጅ ነበረች ፣ ሆኖም እንከን በቀላሉ ይወጣላታል። ኪነም ጥቃቅን ጉድለቶቿን በየቀኑ እያስተዋለ ፣ በትልቁም በትንሹም ጸብ መጫር ሆነ። በእጁ እንደሚቆፍር ፣ ሰው ከጥፍሯ ስር ቁሻሻ አያጣባትም ። ስታወራ ፣ ምራቋ ከከንፈሮቿ ዳር ይከማቻሉ ። አንዳንዴ የአይን-አርሽን ጥረጊ ይላታል ፤ በልታ ስትጨርስ ፣ ጥቃቅን ፍርፋሪ ፣ ወይም የወጥ ምልክት ጥርሷ-ፊቷና -ልብሷ ላይ ትተዋለች። ሳትታረዝ ፣ የተቀደደ ፣ የተጨማደደ ፣ የተጣፈ ልብስ ብትለብስ ቅር አይላትም፤ ሳትቸገር የተንጋደደ ፣ የተጋጋጠ ብትጫማ ፣ ደንታዋ አይደለም።
ከጥቂት ወራት ኩርፊያ ፣ ንትርክና ፣ ጥል በኅዋላ ፣ ደፍጠጥ ያለ አፍንጫ ፣ ደስ የሚል ፈገግታ ካላት ፤ ከአውራው በስተቀር ፣ አራቱን የግራ እጅ ጣቶችዋን እግዜር ከትውልድ ጀምሮ የነሳት ፣ የእግር ጥፍሮቿን ግን በደንብ ከምትቆርጥና አሳምራ ከምትቀባ ኮረዳ ጋር ፍቅር እንደያዘው ስትሰማ ነበር ፤ “ልክስክስ ውሻ! ከኔ ይልቅ ፣ ፉንጋ እና አካለ-ጎዶሎ አማረህ ? ክብር የት ይወድልሀል?” ብላ ወይዘሪት ፣ ወይዘሮ ሳያደርጋት ጥላው ሄደች።
ድቅድቅ ጨለማ ነው ፤ ቀዝቃዛው የሲያትል ዝናብ ማካፋት ጀምሯል። ካረጀው ቮልቮ መኪናዋ ውስጥ የተከማቸው ቅራቅንቦ ያስደነግጣል ። የት ጋ መብራት ማብሪያውና የዝናብ መጥረጊያው እንዳለ አጥንቶ ሲያበቃ ፣ መኪናውን አስነስቶ እያሽከረከረ እያለ ፤ እግሮቿን አሁንም አጣምራ ከሆዱ በታች ቁጭ ስታደርገው ፣ ሰውነቱ በወንድነት ስሜት ሞቅ አለ።
ኮቴዋ ከታቸ የተሰማውን ግፊት ፣ መጠኑንንና አይነቱን ለክቶ ለአእምሮዋ ስለላከው ፣ የቀሰቀሰችበትን ስሜት ያለ ጥርጥር ተገንዝባለች ። ሆኖም ፣ በአንድ በኩል አይኑን ማየት ስላሳፈራት ፣ በሌል በኩል ደግሞ ምንም ብትፈቅደውም ፣ የማይሆን ተስፋ ላለመስጠት ፤ መጠንቀቅ ነበረባት ። “ አጅሬ ካገር ቤት ስንት አይነት ጠንቅ በሻንጣው አጭቆ እንደመጣ እኮ አላውቅም” አለች በልቧ። እግሯን ቶሎ ሰብሰብ አድርጋ ፣ ቦርሳዋን እቃ እንደጠፋበት ሰው ከውስጥ እያመሰቃቀለች ፣ ሳቅም እየተናነቃት “የወር አበባዬ ላይ ነው ያለሁት” አለችው።
ቦርሳዋ ውስጥ ያለውን የታሸገ ኮንዶም ስታይ ፣ በሀሳብ ተመስጣ እየሰማት “ኤጭ ይሄ ላስቲክ ደግሞ አንዳንዴ ይበጠሳል ወይ ሳያስቡት ውልቅ ይላል አለች”
ምኑ? አላት ዞር ብሎ በመገረም፤ ፊቱን ሲያዞር አጠገቡ ካለ የቆመ መኪና ጋር ሊጋጭ ሲል እግዚአብሔር ለጥቂት አወጣው።
“እረ ቀስ ብለህ ንዳ ! አሮጌ መኪና ነው! ከተጋጨን ፣ ፍሬኑ ተበጥሶ ጎማው ውልቅ ቢል ፣እዚሁ መኪና ውስጥ ማደራችን አይደል?” አለች ይሄ ቀልዷ አላስችል ብሏት
“ውይ !መድሐኔአለም ባደረገዋ”
“መጋጨቱን ? ወይስ አብሮ ማደሩን ?”
“ስንተዋወቅ አንተናነቅ ! ሁሉም ነፍሱን ይወዳል ማ አደጋ የሚመርጥ አለ?”
“ከፀደቁ አይቀር ይንጋለሉበት እንዲሉ ፣ ማደሩስ ይታደር ፤ ግን የኔንስ ጥያቄ እኮ አልመለስክልኝም” አለች
“ምን ነበር የጠየቅሽኝ?” አላት
የቅድሙ ጥያቄ ለቀልድ ፣ ለጨዋታ ነበር ፤ አሁን ግን የቀልድ ፣ የጨዋታ ሰአት አልፏል። በቆንጆ እግሮቿ ተጭና ፣ ደህና የተኛውን ስሜቱን ቀስቅሳ ስላቆመችበት ፣ “ መልሼ እንደዛ አይነት ጨዋታ ማብዛት ፣ በእሳት መጫወት ነው” ብላ እያሰበች “አይ ተወው” ስትል
“እኔ ከሴቶች ፣ በላይም በታችም መሆን አያሰኘኝም፣ በእኩልነት ነው የማምነው” አለ ቅድም የጠየቀችውን አስታውሶ ፤ ቀጠል አድርጎ፣ “እንዳትስቂብኝ እንጂ እኔ የተለከፍኩት እኮ በእግር ነው፤ ችግሬን በቅኔ ልንገርሽ አላትና ማንጎራጎር ጀመረ ።
“እራሴን አሞኝ እያየሽ ፤ ለምን ሰከረ ትያለሽ?
አሁን ማ ሰጠኝ ለኔ ጠጅ? ፤ የግር-ፍቅር አዞረኝ እንጅ”
“ቆንጆ ድምጽ አለህ ፣ ጎሽ መንዜው ተፎካካሪ አገኘ” ፣ የሲያትልን ዝነኛ አዝማሪ እየጠራች “ምን ያስቃል ታድያ ? ኢትዮጵያ እኮ የምትወደድ አገር ነች”
ሳቅ ብሎ “አልገባሽም ! ያገር ፍቅር አላልኩም እኮ ። የግር ፍቅር ነው የሚያሰቃየኝ” አላት አይኖቹ እንባ እያቀረሩ ። ውብ እግሮችዋ ላይ ያጠለቀችው አንባር ላይ አይኑን ትክል አድርጎ ፣ “ከሴቶች ሰውነት ሁሉ፣ የሚማርከኝ የእግራቸው ውበት ነው” አላት
“ውይ የሚገርም ነው ! ፉት-ፌቲሽ ነው እኮ የሚባለው ፤ ያለፈው ሴሜስተር ሳይኮሎጂ ትምህርቴ ላይ ፕሮፌሰሩ ስለሱ አስረድቶን ነበር። “ምን ነበር ብሎ የጠራው? የበሽታውን የሳይንስ መጠሪያው ስም ?” ብላ ስታስብ ቆየችና “ፖዶፊሊያ” አለች። “ግን በሽታ እኮ አይደለም ፣ ጸባይና ዝንባሌ ነው ፣ የሚታፈርበት አይደለም” አለች እራሷን አርማ
“አንተ ግን በጣም ግልጽ ነህ። ብዙ ወንድ እንኳን ፖዶፊሊያ ፣ ጉንፋን ይዞኛል ማለት ያፍራል። አበሾች ስንባል በበሽታ ና በችግር ማላገጥ እንጂ ፣ ማዘን አንወድም”
“ቆዳውን የሚያክ ጭርታም ፣ እከካም ወይ ጫጭባም ፣ ራሱን የሚፈትግ ቆሮቆራም ነው፣ ቅማል የበላውን ቅማላም ፤ በፍርሀት ሳይሆን ፣ ሆዱ ተጣልቶት መታጠቢያ-ቤት የሚሯሯጠውን ተቅማጣም ፤ ሆዱ የተገለባበጠውን ትውከታም እንላለን። አካለ ጎዶሎውን ስንፈልግ ቆራጣ ፣ ካላሰኘን ደግሞ ቆማጣ ነው”
በዚህ ምድር ያሉትን ደዌዎች በሙሉ በዝርዝር ጠቅሳ ፣ በነሱም የሚሰቃዩትን የእግዜር ፍጥሮች ሰድባ ስትጨርስ ለማሳረጊያው “ቂጥኝ ያለበትን ደግሞ” ብላ ሳትጨርስ ፣ የበሽታ አይነት መስማት አንገፍግፎት ፣ ዝም ሊያሰኛት ፣
ፊቱን አጨማዶ አንገቱን እያነቃነቀ “እሺ እሺ ….. እሺ በቃ ገብቶኛል” ሲላት
“እረ የማነህ? ፖዶፊሊያም !” ብላ በቀልድ ሰድባው ፣ እየተሳሳቁ እቤቱ ደረሰ
ከመኪናው ገና ሳይወርዱ ወ/ሮ አቻሜ በመስኮት አይተዋቸው መኪናዋ አጠገብ እየሮጡ መጥተው
“ውይ ሱዚዬ እንኳን አገኘሁሽ” ኑ እስቲ ግቡ ቆንጆ ቡና ላፍላላችሁ” አሏቸው
“ያንን መንግስት “ለጤንነታችሁ ካርቦ-ሀይድሬት ቀንሱ” ብሎ ያወጣውን ንባብ ባማርኛ ተርጉሜ አሰራጫለሁ ብለሽኝ አልነበርም እንዴ? ምነው…….ምነው …..ምነው አባክሽ”
“ትምህርት በዝቶብኝ ለአቶ የወንድወሰን እንዲተረጉሙ ሰጠኋቸው እኮ ፤ ደራሲ ናቸው ፣ እዚህ ሬንተን ነው የሚኖሩት ” ወደ ደቡብ በጣቷ እያመለከተች
ፊታቸውን አጥቁረው “ኤድያ ! ድንቄም ደራሲ? የሚጽፈውን ነገር አንብቤዋለሁ፣ ምንም አይጥመኝም፣ ቁም ነገር የሌለው ፣ ፍሬ ፈርስኪ ነው የሚቦጫጭረው” ደግሞም አንቺ አማርኛውንም እንግሊዝኛውንም ከሱ የበለጠ እያወቅሽ ? ለምን እሱ ያጨማልቀው?”
“ማን ነበር እቴ ስሙን የሚሉት?” አሉ ቀጠል አድርገው “ቲቶ ይሁን? ቱቱ ይሁን?” አሉ የአቶ የወንድወሰን ቅፅል ስም ጠፍቷቸው ፤ “ደግሞ ፣ ወንድ ልጅ ካረጀ በኋላ ፣ እናትና አባት እንደሌለው ፣ የምን ቱቱ ቡቱቱ ነው?”
መጨረሻ የተናገሩትን ለማስረዳት ብለው “ቱቱ ቡቱቱ እናት የለሽ አባት የለሽ” ብለው የልጅነት የጨዋታ ዜማ ሲያዜሙላት ፣ “አይ ወ/ሮ አቻሜ ? እርስዎም ቀልደኛ ነዎት” ታድያ አለቃ ገብረሀናም ብዙ ቁም ነገር በቀልድ አስመስለው አስተምረዋል” አለች በታሪክ የሚታወቁትን ቀልደኛ የቤተ ክህነት ሊቅ እየጠራች
“እረ የምን አለቃ ፣ ማሞ ቂሎ በይው እንጂ ! ይልቅስ ቁም ነገር ካልሽ አይቀር ፣ ያገራችን ሰው በሙሉ ይህንን ካርቦ-ሀይድሬት እየወጠቀ ፣ ሆዱ እየገፋ ፣ ስኳር በሽታ እያተረፈ ነው። ቸኮልዬ እራሱ ፣ የስዊዲሽ ሆስፒታል ሀኪሞች ስኳርህ 200 ደርሷል ብለውት ተደናግጠን !” “እንዴ? ልትገለው እኮ ነበር ፣ እቺ ልሳነ-ዲያብሎስ”
ቀጣሪዋን ፣ ወ/ሮ ልሳነ-ማርያምን በስድብና በሀሜት እንዳነሱ ገብቷታል ፤ ሆኖም የቸኮል ስኳር 200 መግባቱ ሳይሆን ፣ ስሙ ተቆላምጦ ፣ ቸኮልዬ መባሉ ከንክኗት ፣ “ይሄ ጎረቤትዎ ቸኮል ?” አለች በመገረምና ፣ የቀረበ ፣ ሞቅ ያለ፣ ግንኙነት ሳይኖራቸው አይቀርም ብላ በመጠርጠር
“አይ ቸኮለ ዘገየ ይባላል ፣ የእህቴ ልጅ ነው ፣ እዛው ኮሌጅ ካንቺ ጋር ነው እኮ የሚማረው” የሌለ ሰው በቶሎ ፍጥር አድርገው
ፈገግ ብላ ፣ በተራዋ በሰው ስም ልታሾፍ፣ “አይ አንደኛውኑ ተቃራኒ አይሉትም ?” አለቻቸውና ተያይዘው ፣ ኪነም በእንሶስላ ፣ አምሮ ባጌጠው እግራቸው ላይ አይኑን ትክል እንዳደረገ ፣ቡና ሊጠጡ ወደ ወ/ሮ አቻሜ ቤት ገቡ።
“ቀና በል እንጂ! ምንድነው መሬት መሬት እያዩ መፍዘዝ? አቀርቅረህ ስትተክዝ የሬኔር ወሮ በላ ማጅራትህን አንዳይልህ!” የሰፈራቸውን ስም እየጠሩ። በእግራቸው ውበት ተማርኮ ወደ ታች እንደሚያይ ግን አልጠረጠሩም።

[center]ይቀጥላል[/center]

User avatar
selam
Leader
Leader
Posts: 175
Joined: 25 Aug 2009 01:59
Contact:

Re: አቤት እንጀራቸው ሲጣፍጥ ..Abet Enjerachew Sitafit ( Short story)

Unread post by selam » 02 Oct 2009 22:24

እረ እነም የጨነቀኝ የሱ ጉዳይ ነበር...ሚስኪን ምን ገጥሞት ይሆን.....?

መደኒ
Posts: 2
Joined: 18 Aug 2009 03:23
Contact:

Re: አቤት እንጀራቸው ሲጣፍጥ ..Abet Enjerachew Sitafit ( Short story)

Unread post by መደኒ » 02 Oct 2009 23:38

ሴቶች ግን ለምንድነው የወንዶችን ስሜት ካነሳሱ ቡሃላ መፈለጋቸውን ሲያውቁ የሚያፈገፍጉት ?የብዙ ሴቶች ባህሪ ስለሆነ ነው።
በተረፈ ታሪኩ እና ስነጽሁፉ አሪፍ ነው።ሰለ ስቴቱ የኢትዮጵያውያን የኑሮ ሁኔታ መረጃ ይሰልጣል።

helen
Starter
Starter
Posts: 19
Joined: 10 Aug 2009 17:36
Contact:

Re: አቤት እንጀራቸው ሲጣፍጥ ..Abet Enjerachew Sitafit ( Short story)

Unread post by helen » 04 Oct 2009 09:20

እሺ መደኒ...እንዴት ነው? እንደው ስታዬን እንደዚህ ማሾፊያ እንመስላለን እንዴ??? "የብዙ ሴቶች ባህሪ ነው" ከምትል "ብዙ ሴቶች ስላጋጠሙኝ ነው"ማለቱ አይቀልም ነበር??የብዙ ወንዶችን ባህሪስ ልትነግረኝ ትችላለህ?
ለማንኛውም በጣም ተወዳጅ ታሪክ ነው...

Martha
ጀማሪ Starter
ጀማሪ Starter
Posts: 7
Joined: 24 Sep 2009 18:12
Contact:

Re: አቤት እንጀራቸው ሲጣፍጥ ..Abet Enjerachew Sitafit ( Short story)

Unread post by Martha » 05 Oct 2009 10:09

አስደሳች ታሪክ። yekine tarik wedet wedet eyamera new??? endet new negeru konjo egir baye kutir ........................ i like all story.waiting for part 4

tsigehana
Jogger
Jogger
Posts: 31
Joined: 09 Aug 2009 19:44
Contact:

Re: አቤት እንጀራቸው ሲጣፍጥ ..Abet Enjerachew Sitafit ( Short story)

Unread post by tsigehana » 07 Oct 2009 10:33

ወይ የእግር ነገር ጉድ አፈላ እቤት ውስጥስ ምን ይገጥመው ይሆን?????

Post Reply

Return to “Ethio Art and Culture..ኢትዮ ጥበብ ፤ስነ ጽሁፍ ፤”