አቤት እንጀራቸው ሲጣፍጥ ..Abet Enjerachew Sitafit ( Short story)

ግጥሞች፣ታሪኮች፣ፎቶዎች፣ሙዚቃዎች
Poems,Short stories, graphics,pictures,musics,Technology
ኦሽንoc
Leader
Leader
Posts: 1129
Joined: 07 Aug 2009 14:20
Contact:

አቤት እንጀራቸው ሲጣፍጥ ..Abet Enjerachew Sitafit ( Short story) Par

Unread post by ኦሽንoc » 08 Oct 2009 01:06

ቅድመ ታሪክ፡
አቶ ቸኮል ግርማ ፣ አቶ ኪነ ጥበቡና፣ ወ/ሮ አቻምየለሽ በሲያትል ከተማ ሬኔር-ቢች በተሰኘው መንደር የሚኖሩ ጎረቤቶች ናቸው።አቶ ቸኮል እድሜው 33 ሲሆን በታክሲ ነጅነት ይተዳደራል። አቶ ኪነ እድሜው 23 ሲሆን በቅርቡ ዲቪ (የአሜሪካ ነዋሪነት እጣ) አግኝቶ የመጣ ተማሪ ነው። ወ/ሮ አቻምየለሽ እደሜአቸው 63 ሲሆን በሲያትል ሸረተን ሆቴል ማእድ ቤት ውስጥ በረዳትንት ይሰራሉ በተጨማሪም እቤታቸው ውስጥ እንጀራ እየጋገሩ ይቸረችራሉ ። ወ/ት ሱዛን ዞርን እድሜዋ 25 አምት ሲሆን በአዲስ አበባ ተወልዳ ያደገች በዩኒቨርስቲ ኦፍ ዋሽንግተን የህክምና ተማሪ ነች ፣ በተጨማሪም አርብ እና ቅዳሜ ‘ዱከም-አዳራሽ’ በተሰኘ የኢትዮጵያ ምግብ ቤት ባስተናጋጅነት ትሰራለች ። ወ/ሮ ልሳነ-ማርያም እድሜያቸው 43 ሲሆን የ ዱከም-አዳራሽ ባለቤት ናቸው።
ሌሎች በአጭር የተጠቀሱ ስሞች ሁኔታዋችና አነጋገሮችዋች

1. ዋች ዩ ሉክን አት ኒገር!፡ የእንግሊዝኛ አነጋገር ነው፤ ትርጉሙ ፣ አንተ ባርያ ምን ታፈጣለህ ! ማለት ነው
2. መንዜው ፡ የአቶ ማርቆስ ሉቃስ ቅፅል ስም። አቶ ማርቆስ እድሜው 53 ሲሆን መኪና በመጠበቅ ይተዳደራል፤ በተጨማሪም አልፎ አልፎ በአዝማሪነት ፣ በሬንተኑ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን በዜማ ያገለግላል። በመጨረሻም የመመማ (መንዝ-መረዳጃ ማህበር) ሊቀ-መንበር ተብሎ በሚኒያፖሊስ ከተማ በመጋቢት 11 በተደረገው የማእከላዊ ጉባዬ ላይ ተመርጧል።
3. የስ ዩ ማዘር ፋከር!፡ የእንግሊዝኛ አፀያፊ ስድብ ነው ፤ ትርጉሙ ፣ እናትን ል**! አንተን ነው እኮ የምናገረው እንደማለት ነው
4. ዘ ማን እዝ ሲክ፡ የእንግሊዝኛ አነጋገር ነው፤ ትርጉሙ ፣ ሰውየው ታሟል ማለት ነው
5. አልካይዳ ፡ እስራኤልንና አሜሪካንን በማጥቃት ሰበብ ፣ ሰላማዊ ህዝብም ሳይለይ ፣ በመላው አለም ላይ የሽብር ድርጊቶችን የሚያካሂድ ስውር ድርጅት ነው[center]አቤት እንጀራቸው ሲጣፍጥ
(ክፍል 4)
አቤት ሱሺያቸው ሲጣፍጥ[/center]

መንዜው የተኛበት የሐርበርቪው ሆስፒታል 3ኛው ፎቅ በመ.መ.ማ (መንዝ መረዳጃ ማህበር) አባል ጠያቂዎች ሞልቶ መራመጃ ቦታ የለም ። ዶክተሮቹና ነርሶቹ በዚህ ሁሉ ጠያቂ የሚታጀብ በሽተኛ ፣ ወይ በጣም ትልቅ ባለስልጣን ፣ አለበለዚያም የረጅም ርቀት ሯጭ መሆን አለበት እያሉ ይከራከራሉ። “እረ እሱ ምስኪን መኪና ጠባቂና ተራ አዝማሪ ነው” አለቻት ለነርሷ ፣ አንዷ የመ.መ.ማ አባል ፣ እንዲታዘንለት ብላ ። እንግሊዝኛዋ ፣ ግንባሯ ላይ እንደተነቀሰችው መስቀል ትንሽ ወልገድ ቢልም ፣ ነርሷ ተረድታታለች ።
“የሚታመን ነገር አይደለም የዛሬ ስንት አመት ነበር ?” አለችና ትንሽ ስታስብ ቆይታ “አዎን 11 አመት አካባቢ ጥላሁን ገሰሰ ሲታከም እኮ እዚህ ተረኛ ነበርኩ ፤ ብዙም ጠያቂ አላየሁኝም”
ቀጠል አድርጋ “ጥላሁን እንግዲህ ፤ ሱዚ እንዳጫወተችኝ ፣ መዝፈን ብቻ ሳይሆን ፣ የተዘፈነለትም ባለሞያ ነው” አለችና ወደ ሱዚ ዞር ብላ “እንዴት ነበር እስቲ ያልሽው ያንን ዘፈን? ንገሪያት በቋንቋችሁ” አለቻት
ሱዚም “ኩሪ ኩሪ ብትኮሪም ያምርብሻል ፤ አበበ ቢቂላ ይድርሻል ፣ ጥላሁን ገሰሰ ያገባሻል” ብላ ስትጀምር ባለንቅሳቷ በንዴት አቋረጠቻትና
“እግሩን እናንተ ናችሁ እንዴ የቆረጣችሁት” አለች ወደ ነርሷ ዞር ብላ ግንባሯን እያኮሳተረች
“አይ እሱን አላውቅም ፣ ለሌላ ጉዳይ ነበር የመጣው”
“የምን ጉዳይ?” አሁንም በቁጣ
“ይቅርታ አድርጊልኝና ስለ በሽተኛ የግል ታሪክ ማውራት በህግ ያስቀጣኛል” ስትላት ወደ ተሰበሰቡት መ.መ.ማ አባሎች አንዱ ሐኪም ተጠግቶ “አቶ ሉቃስ ደህና ነው ፣ አሁኑኑ መውጣት ይችላል” አለ ፣ መንዜውን ባባቱ ስም እየጠራው
በንዴት ባለ ንቅሳቷ “ዘ ማን እዝ ሲክ” ስትል ሐኪሙ ስለ አቶ ሉቃስ ነው የምታወራው ? ወይስ እኔን መሳደቧ ነው ብሎ ግራ እንደተጋባ ያስታውቃል። ጠበብ ያሉት አይኖቹ የእስያ ዘር እንዳለው ይናገራሉ
ባለንቅሳቷ እንደማይሰማት ብታውቅም አይኑን ለማየት ፈርታ ወደ መሬት እያየች “እኔ እኮ እነዚህን ጭፍኔዋች በጣም ነው የምጠላቸው ፤ አረመኔዎች! ጥቁርማ ሲጠሉ”
መንዜው የሆስፒታል አልጋውን ለጠናበት ህመምተኛ ለቆ ፣ እቤቱ ማገገም አለበት መባሉ አናዷታል
“እግዚአብሔር ደግሞ ኦባማን አመጣባቸዋ! የታባታቸው!” አለች በጥላቻ መልክ የእስያውን ሐኪም እየተመለከተች
በመጨረሻ “እረ እንኳን እግዜር አተረፈው ልጄ ፣ እቺ ቀውጢ ቀን አለፈች” አለች የሲያትል ጀንበር መጥለቋን በመስኮት እያስተዋለች

[center]*************[/center]

ቀውጢው ቀን የተጀመረው ፣ ኪነና መንዜው ወደ ሲያትል መሀል ከተማ ለመሄድ ሬኔር የሚባለው መንገድ ላይ ሰባት ቁጥር አውቶቡስን እየጠበቁ ፣ የባጥ የቆጡን እያወሩ ነበር “መቸም እስካሁን የሲያትልን ሴተኛ አዳሪዎች ቀማምሰሀል አይደል?” ብሎ መንዜው ኪነን ጠየቀው
“በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ! በእጁ እያማተበ “እረ እኔ በህይወቴ አድርጌውም አላውቅ! እንደዚህ አይነት ነገር አልወድም”
“ያልቀመስከውን ምግብ እንዴት እንደማትወደው ታውቃለህ? ለምሳሌ ጃፓኖቹን እንውሰድ ፤አቤት ሱሺያቸው ሲጣፍጥ? የባህር ቁርጥ ማለት ነው ፤ ሚጥሚጣ እንደበዛበት ክትፎ ፣ ሲገባም ሲወጣም ነፍስ ግቢ ፣ ነፍስ ውጪ አይምሰልህ ። እንደ ቶዮታ ገብቶ ፣ እንደ ኒሳን ውልቅ ነው የሚለው
“አይዞህ ፣ ሹሼዎቹ ገበያተኛ ዘና ማድረግ ያውቁበታል! ልእልት የመሳሰሉ ናቸው እኮ! ደግሞ ትህትናቸውስ? የእንጎቻቸውን ነገርማ አታንሳ ፣ አቤት ሲጣፍጥ!”
“ብቻ አንዳንዴ ያሳዝኑኛል ፣ ብዙዎቹ የደህና ሰው ልጆች የነበሩ እኮ ናቸው፣ ይገርምሀል አዲስ አበባ የአሜሪካን አንባሳደር ሚስት የነበረችውን ስትሸረሙጥ በአካል እዚህ አላገኛት መሰለህ”
“የማይታመን ወሬ አይነት አለው ። ይሀኛው ግን ከውሸትም አልፎ የእብድ ቋንቋ ነው” ብሎ ኪነ በልቡ እያሰበ እያለ
መንዜው ቀጠል አድርጎ “ግን አውሮራ ላይ የሚሰጡትን ሸርሙጦች እንዳትነካ እነሱ ጤነኛም የለባቸው” ሲያትልን ሰሜኑንና ደቡቡን የሚያገናኘውን ሰፊ ጎዳና እየጠራለት
“የኔ ደንበኛ አለች ጅል (Jill) ይሏታል ፣ ግን አቤት ብልጠቷ ፣ ምላጭ ናት ፣ የሱዋን ቁጥር ልስጥህ” ብሎ ብላክቤሪ የተባለ ስልኩን መፈተሽ ጀመረ
“ጅንጅን ማጨስ ያስተማረችኝ እሷ ነች ፤ እኔ ደግሞ ውለታ ለመመለስ ብዬ ጫት መቃም አስተማርኳት”
“ግድ የለም ሌላ ግዜ ትሰጠኛል ፣ ይልቅ ስለ አሜሪካን አንባሳደር ሚስት ጉዳይ አውራልኝ አለው ፤ የመንዜው አእምሮ በማሪዋና ተመርዟል ብሎ በመጠርጠር”
“አዲስ አበባ እንደራሴ ሆቴል አጠገብ የዛሬ 3 አመት ኣካባቢ ፣ የአሜሪካን አንባሳደር ጥቁር መኪና ባንዲራውን እያውለበለበ መጥቶ በድንገት ፊት ለፊቴ ቀጥ አይልልህም ፣ ሞተሩ አካባቢ መጨስ ጀመረ
እኔ ያኔ ቦዘኔ ነኝ ፣ ከሌሎች ስራ ፈቶች ጋር ዝም ብለን እየተጫወትን ነበር ፣ ከዛ አንዱ ከህዋላ “እረ ጎበዝ እግሬ አውጭኝ በል! አልካይዳ መኪናውን ፈንጂ ጠምዶበታል!” ብሎ ሳይጨርስ ተያይዘን ጭቃ የሞላበት ገደል ውስጥ ገባን
ከፊት ከሾፌሩ አጠገብ አንድ ነጭ ዩ ኤስ መሪን የሚል መለዮ የለበሰ ወታደር ኤም ስክስቲን መትረየሱን ይዞ ወጣ ። አንድ ፍሬ ልጅ ነው ፣ ሆኖም ፊቱ ላይ ምንም የመሸበር ምልክት አይታይበትም ነበር
ለካ ራዲያተሩ ተቀዶ ሞተሩ ግሎ ነበር መኪናው የሚጨሰው ፤ ልብሴ በጭቃ ተጨማልቋል፤ ሆኖም ከእንደራሴ ሆቴል በባሊ ዉሀ ወስጄ መኪናውን እያበረድኩላቸው እያለ ፣ የኋለኛው መስኮት ተከፈተና ቆንጅቷ የአንባሳደሩ ሚስት አንገቷን ብቅ አደረገች ፣ ከዚህ በፊት በቴሌቪዥን ከፕሬዘዳንት ግርማ አጠገብ ተቀምጣ አይቻታለሁ፤ $20 ዶላር አወጣችና አንቦ ዉሀ እንዳመጣላት ፣ ፈገግ እያለች ጠየቀችኝ ፤ ትህትናዋ አሁንም አይረሳኝም። ፕሊስ ፣ ቴንኪው ማለት የማይታክታቸው ፍጡሮች! ከዛ መልሱን የኢትዮጵያ $180 ብር ስሰጣት “ዚስ ኢዝ ፎር ዩ” ብላ መለሰችልኝ ፣ አሁንም ቆንጆ ጥርሷቿን እያሳየችኝ
ታድያ ይኸውልህ እዚህ ዩኒቨርሲቲው ኦፍ ዋሽንግተን አካባቢ ስትሸረሙጥ አገኘኋታ። እንዴት ደነገጥኩ? እንዴት አዘንኩ መሰለህ? ከዛ አልቤርጎ ተከራየን ፣ ልብሳችንን አወለቅን ፣ እንደራሴ ሆቴል በሰማሁት ድምጽ ፤ እግሮቹዋን ብልቅጥ አድርጋ ፈገግ እያለች “ዚስ ኢዝ ፎር ዩ” ስትለኝ ፣ ወላዲትን እኔ ወንድምህ ውሀ ሆንኩልህ
ያወራለትን ነገር አንዱንም ቃል እንዳላመነው ገብቶታል
“ስማ የመንዝ ልጅ የለውም ኣባይ ሲባል አልሰማህም? አሁን እሱ ዜማ የውሸታም ዘፈን ሆኗል
የሲያትል ልጅ የለውም አባይ…የሬንተን ልጅ…የፖርትላንድ ልጅ…የዲሲ ልጅ … የሳንፍራንሲስኮ ልጅ……የምንትሴ ልጅ……የለውም አባይ ፤ በቃ እንደዛ ሆኑዋል ፤ ውሸታም ፣ ሌባ ሁሉ በላቸው ።
እኔ ግን መማል ብቻ ሳይሆን እገዘትልሀለሁ ፤ የማንአልሞሽ ዲቦን ዘፈን አልሰማህም
“ሳር ሲነቅሉ ውለው አዝመራው አይነጥፍም ፣
መንዝ የተናገርው ቃሉ አይታጠፍም”
ኪነ በጸጥታ የሰማውን የማይታመን ወሬ እያሰላስለ እያለ ፤ “ለመሆኑ ምንድነው ትምህርትህ?”አለው
“አግሮ ኢኮኖሚክስ ነው ያጠናሁት ፣ አለማያ ኮሌጅ ”
“ስለ እርሻ ካጠናህማ እኔ ደግሞ ፈተና ልፈትንህ”
ስለ ሰሜን ሸዋ ግብርና፣ በተለይም ስለ መሬት መለኪያና መስፈሪያ እቃዎች አይነት ይጠይቀው ጀመር።
“ጋሻ ስንት ነው?” መልሱን ስላላወቀ አይኑን ዝም ብሎ አቁለጨለጨለት
“ጋሻ ፤ አርባ ሄክታር ነው”
“ጥማድስ?” አሁንም ዝም አለ
“ጥማድ ደግሞ የሄክታር ሩብ ነው”
“ድኩማንስ?” ብሎ ጠየቀው
“እረ አትሳደብ አካለ ሰንካላ ትለኛለህ እንዴ”
ኤድያ! ስለ እርሻ እያወራሁልህ?
“ድኩማን ማለት ደግሞ ፣ ትንሽ መሬት ናት፣ የጥማድ አንድ አራተኛ ብትሆን ነው” ብሎ ሲጨርስ ደግሞ ወደ እህልና ውሀ መለኪያ ዞረ።
ጋን መቶ ሊትር ነው ፣ ቅል ቢበዛ ከስምንት ሊትር አይበልጥም ፣ ጣሳ አንድ ሊትር ነች ፣ ስልቻ 64 ኪሎ አካባቢ ነው አለና ፣ ዳውላ ደግሞ 160 ኪሎ ነው ብሎ ሳይጨርስ አቋረጠና “ስብሀት ለአብ” አለ ቀጠል አድርጎ “እቺማ አራት ዳውላ አይደለች እንዴ?”
እንዳጋጣሜ ዞር ሲል ነበር ወፍራምዋን ጥቁር አሜሪካዊ ያያት ። ውፍረት ብቻ ሳይሆን ጎልያድን የሚያክል ቁመና እግዚአብሄር አድሏታል።
ልክ አማርኛ እንደ ሰማ ሰው በንዴት “ዋች ዩ ሉክን አት ኒገር!” አለችው
ከመደንገጡ የተነሳ ባማርኛ “ ማ? እኔ? ” አላት በአጁ ወደ ደረቱ እያመለከተ
ጎልያድ ለካ እንደ ዲዳዋች በእጅ መናገርና በአይን መስማት ትችላለች ፣ በንዴት እሳት ጎርሳ እሳት ለብሳ “የስ ዩ ማዘር ፋከር” አለችና በቃርያ ጥፊ ጆሮ ግንዱን ስታደባየው ፤ ከብረት የተሰራው የዝናብ መጠለያ ጭንቅላቱን መትቶት ከመሬት ላይ ተዘረጋ ። መንዜው 53 አመቱ ነው ፣ ሽማግሌ ባይባልም ፣ ከጎረምሳ ወሮበላ ሴት ጋር የሚያፋልም አቅም የለውም
ከጆሮው ውስጥ ትንሽ ደም ኩል ብሎ ፈሶ የተዘጋው ከንፈሩ ላይ ተከማቿል። ለጥቂት ደቂቃዋች ነፍሱን አያውቅም
ኪነ እሱም በጎልያድ ቃርያ ጥፊ እንደተመታ ሰው ፈዞ ቀረ።
ጎልያድ ከዚህ በፊት ከአበሾች ጎረቤቶች ጋር አንድ አንድ ተባብላ ታውቃለች
የሚያሰለች ዘፈናቸውን እያስጮሁ የሚያሰሙ ፣ 24 ሰአት የሚገማ ወጥ እየወጠወጡ የሚያጠነቧት ፣ ዘወትር ሰርግና ምላሽ ይመስል ቤታቸው ውስጥ እንግዳ ፣ ድምጽና ውካታ የማያጡ ነበሩ።
የጎልያድ ዘመዶች አንዳንዴ ሊጠይቋት ሲመጡ ፣ የመኪና ማቆሚያውን በሙሉ አበሾች ጥቅጥቅ አድርገው ይዘውት ፣ ዘመዶቹዋ ሲንከራተቱ ስታይ በጣም ትናደድና ጮክ ብላ ጎረቤት ሁሉ እንዲሰማ “ዚስ ማዘር ፋከር ኢትዮፒያንስ” ትላለች ።
ለነገሩ የቁም እሳር ያሳይዋት ጎረቤቶቿ ኤርትራውያን ነበሩ ፤ ጎልያድ ግን የምስራቅ አፍሪካን ጆግራፊና ፓለቲካ አታውቅም። ለሷ ቀጠን ያለ አፍሪካዊ በሙሉ ፣ ማዘር ፋከር ኢትዮፒያን ነው

[center]*********[/center]

ከሆስፒታል እየወጡ ወደ ወ/ሮ አቻሜ ቤት ለቡና እያመሩ “ይገርማል ጥዋት ያወራህልኝ ወሬ ፣ የአንባሰደር ሚስት የነበረች እንዴት ሴተኛ አዳሪ ትሆናለች?”

ለትንሽ ግዜ ትክ ብሎ ተመለከተውና
“ያምሀል እንዴ? ጨዋታም አታውቅ? እዚህ ያገኘኋት ሸሌ ፣ የአንባሳደሩን ሚስት ትመስላለች ለማለት ነው እኮ እንደዛ ያልኩት ፤ የምን ገገማው ነህ እባክህ፣ ኮሌጅ ተምሬያለሁ እያልክ?”


[center]ይቀጥላል....[/center]

ኦሽንoc
Leader
Leader
Posts: 1129
Joined: 07 Aug 2009 14:20
Contact:

Re: አቤት እንጀራቸው ሲጣፍጥ ..Abet Enjerachew Sitafit ( Short story)

Unread post by ኦሽንoc » 16 Oct 2009 17:43

ቅድመ ታሪክ፡ አቶ ቸኮል ግርማ ፣ አቶ ኪነ ጥበቡና፣ ወ/ሮ አቻምየለሽ በሲያትል ከተማ ሬኔር-ቢች በተሰኘው መንደር የሚኖሩ ጎረቤቶች ናቸው።አቶ ቸኮል እድሜው 33 ሲሆን በታክሲ ነጅነት ይተዳደራል። አቶ ኪነ እድሜው 23 ሲሆን በቅርቡ ዲቪ (የአሜሪካ ነዋሪነት እጣ ) አግኝቶ የመጣ ተማሪ ነው። ወ/ሮ አቻምየለሽ እደሜአቸው 63 ሲሆን በሲያትል ሸረተን ሆቴል ማእድ ቤት ውስጥ በረዳትንት ይሰራሉ በተጨማሪም እቤታቸው ውስጥ እንጀራ እየጋገሩ ይቸረችራሉ ። ወ/ት ሱዛን ዞርን እድሜዋ 25 አምት ሲሆን በአዲስ አበባ ተወልዳ ያደገች በዩኒቨርስቲ ኦፍ ዋሽንግተን የህክምና ተማሪ ነች ፣ በተጨማሪም አርብ እና ቅዳሜ ዱከም-አዳራሽ በተሰኘው የኢትዮጵያ ምግብ ቤት ባስተናጋጅነት ትሰራለች ። ወ/ሮ ልሳነ-ማርያም እድሜያቸው 43 ሲሆን የ ‘ዱከም-አዳራሽ’ ባለቤት ናቸው።
ሌሎች በአጭር የተጠቀሱ ስሞች ፣ ቦታዎች ፣ ሁኔታዎችና ትርጉሞች
1. ኤፍ-ዲ-ኤ፡ ፉድ ኤንድ ድራግ አድሚኒስትሬሽን ፤ ምግብና መድሀኒትን በተመለከት ጉዳይ ሁሉ ስልጣን ያለው የፌዴራሉ መንግስት ድርጅት
2. መይሳው ካሳ፡ የአፄ ቲዮድሮስ ሌላ የቁልምጫ ስም
3. ኑረዲን ሁሴን፡ እድሜውን ከ 30 እስከ 40 ባሉ ቁጥሮች ውስጥ የሚላክክ ፣ ዜግነቱን እንዳሰኘው ኢትዮጵያዊ ፣ ኤርትራዊ ፣ ሶማሌ አለበለዚይም የጅቡቲ ሰው ነው ነኝ የሚል ፣ ስራውም የማይታወቅ
4. “ወላሂ ሀበሽ መጅኑን” አረብኛ አነጋገር ሲሆን ትርጉሙ ፣ እግዚአብሔርን! አበሻ ሲባል ሁሉ እብድ ነው! ማለት ነው[center]አቤት እንጀራቸው ሲጣፍጥ (ክፍል 5)[/center]

(ክፍል 5 ፡ ለልጄ ለወ/ት አንኮበር የወንድወሰን በስጦታ መልክ ቀርቧል)
ደራሲ የወንድወሰን አደፍርስ


ወ/ ሮ አቻምየለሽ ስኒዋቹን ረከቦቱ ላይ ደርድርው የተፈላው ቡና እስኪሰክን ድረስ በትግስት ይጠብቃሉ። ከሰልና ጊርጊራ ስለሌላቸው ፣ በኮረንቲ የሚሰራውን ምድጃ አብርተው ፣ ትልቁ ክብ ፍም ላይ ትንሽ እጣን አስቀምጠው ምድጃውን አጠፉት። የእጣኑ መአዛም ከእንጀራው ሽታ በላይ አይሎ ቤቱን ሞላው።
ቡናው እስኪሰክን ድረስ የቡና ቁርስ ብለው እንጀራ በ ነጭ ገንፎ የሚመስል ነገር አቀረቡ “ምንድነው ይሄ አለ” ኪነ አይቶት የማያውቅው ምግብ ስላየ
ሱዚ ቶሎ ብላ “ስልጆ ነዋ” አለች
ወይዘሮ አቻሜ “አይ ህልበት ነው” ብለው አረሟት
“ለነገሩ ስልጆውንም ማወቀሽ ጉደኛ ነሽ ! ስልጆ እንዴት እንደሚሰራ ታውቂያለሽ?” አሏት
“እንዴታ!” አለችና ሞያዋን መናገር ጀመረች
“የአቱሩን ዱቄት በሱፍ ውሀ ልቡ እስኪጠፋ ድረስ በብሌንደር እመታውና ከዛ አገነፋዋለሁ ። ሲቀዘቅዝ ጨውና ሰናፍጭ በልኩ ጨምሬ ፣ ነጭ ሽንኩርቶች በስንጥር አያይዤ ፣ ውስጡ መሰካትና በረዶ ቤት ውስጥ ማሳደር ነው” አለች
“ወይ ጉድ የምትደነቂ ነሽ ! ታድያ ህልበትም እኮ አሰራሩ ተመሳሳይ ነው። የምስርና የነጭ አብሽ ዱቄቱን በጠራ ዉሃ መትቶ ማገንፋትና ፣ ሲቀዘቅዝ ነጭ ሽንኩርት እና ጨው በልኩ ጨምሮ ማቀዝቀዝ ነው” አሉ
ቴሌቪዥናቸው ተከፍቶ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ በቅርቡ በኑው ዮርክ የአውሮፕላን አደጋ ሟች ዘመዶችን ሲያጽናና ያሳያል። ፣ፕሬዘዳንቱ አንዲቷን ቆንጆ ለቀስተኛ ለረጅም ግዜ እቅፍ አድርጎ ሲያጽናና ታየ።
“እረ በቃህ ! ” አሉት፤ ኦባማ ከቴሌቪዥኑ ውስጥ ሆኖ ይሰማቸው ይመስል
ቀጠል አድርገው ፣ “ወንድና ውሻ አንድ ነው” አሉ
“ቀሚስ ከለበሰ ጋር ሁሉ መልከስከስ ነው ፤ አሁን ደግሞ ወደ ምሼል ኦባማ ላይ ዞሩ “ የኔ እናት አይ ቁመት? መለሎ የሆነች ነገር ! ምን ዋጋ አለው ታድያ? ማ ያውቃል ? አጅሬ አጭር አማረኝ ቢልስ? ክሊንተን እንኩዋን ያቺን እመቤት የመሰለችውን ሚስቱን ትቶ ፣ አንዴ ጀነፈር ፣ አንዴ ሞኒካ ፣ አንዴ ምንትስዬ ሲል! ኤድያ” የቀድሞውን ፕሬዘዳንት ዝሙተኛነትን አስታውሰው
ከእጣኑ ጢስ ጋር ተኖ ወደ ኑውዮርክ የሄደውን ሀሳባቸውን ሰብሰብ አድርገው ፣ “ሌባ በያት ! እቺ መተተኛ ! ሊጡ ውስጥ የምትጨምርበት አንድ ነገር አለ” አሉ ቀጠል አድርገው “እኔ ደግሞ ኤፍ…ዲ….ኤን ባልጠራባት አቻሜ አይደለሁም
ወደ ሱዚ ዞር ብለው ስለ አለቃዋ ፣ ስለ ወ/ሮ ልሳነ-ማርያም የጥላቻ ሀሜታቸውን ቀጠሉ
ወ/ሮ ልሳነ-ማርያም የተወለደችው አንኮበር ወረዳ ፣ ሙቅ ምድር በተሰኘው አካባቢ ነው። ባለ ፀጋ ያደረጋትን ሙያ ሁሉ የተማረችው ከናቷ ከወ/ሮ ለማወንዝ አዱኛ ቢሆንም ፣ ብዙ የምትመካውና የምትኮራው ፣ በአፄ ምኒሊክ ትውልድ አገር በተሰየሙት በአባቷ በፊት-አውራሪ አንጎለላ ነው። ፊት-አውራሪ አንጎለላ ማንደፍሮ የተከበሩ አርበኛ ናቸው። አሁንም ፣ ኑሮ ካሉት መቃብር ይሞቃል እንዲሉ ፣ በርበሬ-ውሀ የሚባል መንደር ውስጥ ደህይተው ፣ አይናቸው ጠፍቶ፣ ጥርሳቸው ረግፎ ፣ ጆሯቸው ተደፍኖ ፣ ሰውነታቸው መንምኖ ፣ እንደ አረጀ አንበሳ ፣ ዝንብ እየተጫወተባቸው በጥገኝነት ይኖራሉ። አንደበታቸው ከመዘጋቱ በፊት “ወይኔ አጎለላ ! ምነው እግዚ አብሔር በቃህ ብሎ ቢጠራኝ?” እያሉ ዘወትር ሞታቸውን ይመኙ ነበር።
“ምን የማትለው ነገር አለ?” የሴት አያቴ ናቸው የዶሮ ዳቦ የፈለሰፉት እያለች ቱልቱላዋን ካለ ምንም ሀፍረት የምትነፋ። ሆዷ እንደ ስልቻ ይነፋና ! እግዚአብሄር ያሳይሽ ፤ የዶሮ-ዳቦ በቀልቃላዋ ቀለመወርቅ ባጋጣሚ ምክንያት እንደተፈለሰፈ በታሪክ ባይፃፍም ፣ በአፈ-ታሪክ ማህደሮች ውስጥ እንደተመዘገበ ፣ የማይካድ ነው”
“ቀልቃላዋ ቀለመወርቅ የአፄ ቲዮድሮስ ወጥ ቤት ነበረች ፣ እንደው ከፈሷ የተጣላች ሴት ናት ፣ ስራዋ ሁሉ ፣ መደነባበር ፣ ያንንም መድፋት ፣ ያንንም መከለስ ነው። ሆኖም ባለ ሙያ ነች ፣ አፄ ቲዮድሮስም እሷ ያልሰራችውን ካልሆነ ፣ እንድች ብለው ሌላ ያበሰለውን አይነኩም፤ አንድ ምሽት እንደልማዷ ስትደነባበር ቀኑን ሙሉ የለፋችበትን ቆንጆ የዶሮ ወጥ ፣ ድፎ ዳቦ እጋግራለሁ ብላ ያቦካችው ሊጥ ውስጥ ትጨምረዋለች። መይሳው ካሳ ደግሞ በአገሩ እና በእራቱ የሚመጣበት ሰው እንደማይወድ ስለምታውቅ ፣ እራት ዘግይቷል ከምል ይልቅ ፣ ይህንን የተደበላለቀ የወጥ እና የሊጥ ጉድ ልጋግርና ፣ የመጣው ይምጣ ብላ ዶሮ-ዳቦውን ጋገረችው” ይሀው ነው ታሪኩ አሏት
“ቆንጆ ታሪክ ነው” አለችና ማለቴ “አፈ-ታሪክ” አለች እራሷን አርማ
ወ/ሮ አቻሜ አሁንም የጥላቻ ወሬአቸውን ቀጠሉ
“የውሸቷ ብዛት ማለቂያ የለውም ።ያኔ ለሷ ዱከም አዳራሽ ተቀጥሬ እንጀራ ስጋግርላት እያለሁ፣ አንድ ቀን ሊጥ የሚቦካበትን ክፍል “ በሩን ዝጊው እባክሽ አታስበርጅኝ ፤ የሙቅ ምድር ሰው ብርድ አይወድም” ስትለኝ ፣ “ሙቅ ምድርን እኮ አውቀዋለሁኝ ቆላ ሳይሆን ፣ ደጋና ወይና-ደጋ ነው” ስል ፣
“ጉድ ነው አንቺ የአንኮበር ሴት፣
በየሄድሽበት ምቀኛ ማፍራት”
ብላ በግጥም ሰደበችኝ። ከቤቴ ውስጥ እንጀራ መሸጥ መጀመሬን ስትሰማ እኮ ነው ምቀኛ ብላ የሰደበችኝ ፤ እንኳን እንጀራ ቀርቶ ካቲካላ ብሸጥ ምን አባቷ አገባት? እቺ ሸራፋ ጋለሞታ !”
“ከሁሉ የሚያናድደኝ ግን ፣ አንኮበር አንኮበር የምትለው ጉራ? አንኮበርን የማናቃት መስሏት ነው ? ደሳሳ ከተማ ! ኮረንቲ እንኳን አሁን ነው የገባላት። እምዬ ምኒሊክ እራሱ ንቋት አይደል እንዴ እንጦጦን የመረጠው? የቸኮልዬን ሰፈር” አሉ ታሪክ ሊያስተምሯት
አሁንም ፍቅረኛቸውን አቆላምጠው መጥራታቸውን ብቻ ሳይሆን የድሮ ሰፈሩንም መግለጻቸውን ዘንግተውታል
በዚህ ግዜ ሱዚ ስለ ቸኮል እንደዋሿት ተገንዝባ ፣ በአንኮበርም ስም መጥፋት ቅር ተሰኝታ
“አንኮበር እኮ የምትናቅ አይደለችም ። ብዙ ታሪክ አላት ፣ ከይኩኖ አምላክ ጀምሮ እስከ ምኒልክ ድረስ ብዙ ትልልቅ ሰዎች ያፈራች መሬት ናት” አለቻቸው። መልስ ሊሰጥዋት አፋቸውን አሞጥሙጠው “ታድያ….” ብለው ሳይጨርሱ አቋረጠቻቸውና “ እንዴ? ዝነኛው ሰአሊ አፈወርቅ ተክሌ እንኳን እዛ ነው እኮ የተወለደው” አለች
“ኤድያ ! ታድያ አፈወርቅ ተክሌ እዛ ቢወለድ አንቺን ነጫጭባ ፣ እመቤትሽን ወላቃ አድርጎ ነው እኮ የሚስላችሁ” ሲሏት፣
ልትጎርሰው የጠቀለለችውን ፣ የቡና ቁርስ ተብሎ የቀረበውን እንጀራ፣ መልሳ ቁጭ አደረገችው።
ወ/ሮ አቻሜ ሀይለኛ ሴት እንደሆኑ ታውቃለች ። ምላሳቸው ግን ፣ እንደሰንጢ ወግቶ ፣ አንጀት ይዘከዝካል ብላ አልጠረጠረችም።
የፊቷን በሀዘን መለዋወጥ ወዲያውኑ ተገንዝበው ፣ “ምነው ገብርኤልዬ በዛ በሰይፉ ምላሴን በቆረጠው ?” ብለው ይቅርታ ለመጠየቅ እግሩዋ ላይ ወደቁ ። አርባ አራቱን ታቡት እየጠሩ ይማጸንዋት ጀመር
“የምሬን አይደለም የኔ እመቤት ፣ አንቺን እኮ እንደ ልጄ ነው የማይሽ ፤ ጸቤ ካንቺ አይደለም” አሁንም እንደተንበረከኩ “የሬንተኑ ኡራኤል ምስክሬ ነው ፣ እንደበደልኩሽ እክስሻለሁ ። ልሳነ-ማርይምን ግን እፋረዳታለሁ” አሉ ለመጀመሪያ ግዜ የቀድሞ ቀጣሪያቸውን በስደብ ሳይሆን በስምዋ ጠርተው
ሱዚ፣ በድንገት ብድግ ብላ “እንደውም መሄድ አለብኝ” አለች። ቡናውንም ሳትቀምስ ፣ደህና ዋሉም ሳትል ፣ መሬት ላይ እንደተንበረከኩ ጥላቸው ፣ መኪናዋን አስነስታ ከነፈች
በ ወ/ሮ አቻሜ መንበርከክ የተደሰተ ኪነ ብቻ ነበር ፤ በእንሶስላ ተሽሞንሙነው በገሀድ የሚታዩት የውስጥ እግሮቻቸው ላይ አይኑን እንደ ፎቶግራፍ -ማንሻ ትክል አድርጎ ምስሉን በአእምሮው እየቀረፀ እያለ፤ ወ/ሮ አቻሜ የቀኝ እግራቸውን አሳከካቸውና እዛው ሱዚ የተቀመጠችበት ወንበር ላይ ተደግፈው እንደተንበረከኩ በእግራ እግራቸው የቀኙን ማከክ ጀመሩ። ይህም ስላላረካቸው በቀኝ እጅ ጥፍሮቻቸው ቡዋጨር ቡዋጨር አድርገው ሲያበቁ እግራቸውን ማሸት ጀመሩ። አይናቸውን ጨፍነው በጸሎት መንፈስ ክፉ ተናገረው ወዳጅ ማስቀየማቸውን እያሰላሰሉ ቆዩ።
በዚህን ግዜ ነበር ኪነ በድንገት እግሮቻቸውን ይዞ መሳም የጀመረው ፤ ከንፈሮቹ ብቻ ሳይሆን ምላሱም ከውስጥ እግራቸው ጋር ተነካካ ። እግሮቻቸው የተሰማቸውን ርጥበት ለአእምሩዋቸው ቢናገሩም ፤ በድንጋጤ ደንዝዘው “እረ የመድሀኔ አለም ያለህ ምን ጉድ መጣ?” ከማለት ሌላ ሰውነታቸው በፍርሀት ተውጦ ቀረ ።አእምሮአቸው ግን ከዚህም የባሰ አደጋ ሊከተልባቸው እንደሆነ በስእል ቁልጭ አድርጎ ነገራቸው።
በዚህን ግዜ ነበር “በወላዲተ አምላክ ይዤዎታለሁ ስራ ሸረተን እንዲያስቀጥሩኝ” በማለት ሰበብ እግራቸውን መላስ ቀጠለ።
ልባቸው በጭንቀት ተውጦ በፍጥነት ከመምታቱ የተነሳ ሊፈነዳ የደረሰ ይመስላል። ከወላዲተ አምላክ ስም መጠቀስ በስተቀር ሌላ የተናገረውን ነገር በሙሉ አለሰሙትም ሆኖም፤ የማርያም ስም መጠራቱ ትንሽ ዘና አደረጋቸው።
በድንገት ኑረዲን ሁሴን እንደልማዱ እንጀራ ሊገዛ ገርበብ ያለውን በር ገፋ አድርጎ ሲገባ ሁለቱም አላስተዋሉትም ። የወ/ሮ አቻሜን ወንበር ተደግፎ መንበርከክ ፣ የኪነ ከሁዋላቸው ሆኖ እግራቸው ላይ ተጠምጥሞ መሳም ፣ ትርጉሙ ግራ ገብቶት “ወላሂ ! ሀበሽ መጅኑን” አለ።

[center]ይቀጥላል....[/center]

ኦሽንoc
Leader
Leader
Posts: 1129
Joined: 07 Aug 2009 14:20
Contact:

Re: አቤት እንጀራቸው ሲጣፍጥ ..Abet Enjerachew Sitafit ( Short story)

Unread post by ኦሽንoc » 15 Nov 2009 01:24

[center]አቤት እንጀራቸው ሲጣፍጥ .... ክፍል 6 [/center]

ቅድመ ታሪክ
አቶ ቸኮል ግርማ እና ወ/ሮ አቻምየለሽ በሲያትል ከተማ ሬኔር-ቢች በተሰኘው መንደር የሚኖሩ ጎረቤቶች ናቸው።አቶ ቸኮል እድሜው 33 ሲሆን በታክሲ ነጅነት
ይተዳደራል። ወ/ሮ አቻምየለሽ እደሜአቸው 63 ሲሆን በሲያትል ሸረተን ሆቴል ማእድ ቤት ውስጥ በረዳትንት ይሰራሉ ፤ በተጨማሪም እቤታቸው ውስጥ እንጀራ
እየጋገሩ ይቸረችራሉ።


[center]“ተጣሩ እቴጌ አቤት በል አሽከር ፣ ወደህ ከገባህ አትከራከር
ክብሬ ተነካ ሳትል ማረጌ ፣ አቤት ብቻ ነው ሲጣሩ እቴጌ
ወዶ በገባ በእቴጌ ቤት ፣ አዲስ አይደለም አቤት ማለት”

ቴዲ አፍሮ[/center]


የሲያትል ከተማና አካባቢው በዝናብ ብዛት የታወቀ ነው። በታህሳስ 22 ቀን ግን ፣ ሰው ሁሉ የአውሮፓውያንን አዲስ አመት ለማክበር በጉጉት እየጠበቀ እያለ ፣ ከምእራበ-ደቡብ አቅጣጫ ፣ ውቅያኖስ አቁዋርጦ የቀዘቀዘ እርጥበት ተሸክሞ ፣ የነፈሰው አየር ከተማውንና አካባቢውን 20 ሴንቲ-ሜትር ጥልቀት ባለው በረዶ አለበሰው ። ወ/ሮ አቻም የለሽ ቁሻሻ ሊያወጡ ከቤታቸው ወጥተው ሲመለሱ ፣ ቤታቸው አጠገብ የተከመረው በረዶ ያዳልጣቸውና በመቀመጫቸው ይወድቃሉ ።
ቸኮል አካላቱን ታጥቦ ትልቅ ፎጣ ወገቡ ላይ አገልድሞ ሲወጣ ነበር የሴት ድምጽ ከውጪ የሰማው።
ጫማውን አጥልቆ ፣ ማሰሪያውን ሳያስር ፣ እየሮጠ ደረሰላቸው። በጣም ከሚሞቅ ውሀ ውስጥ ስለወጣ ፣ ሰውነቱ ግሎ የውጭው ብርድ አልተሰማውም። ብዙ አልተጎዱም ፣ በህመም ሳይሆን በድንጋጤ ነበር ዋአ……አይ! ብለው የጮሁት
ከወደቁበት እንዲነሱ ወገባቸውን ይዞ ረዳቸው ። ለመራመደ ቢሞክሩ ግን፣ እግራቸው ደንዝዞ ከዳቸው
በዚህን ግዜ ነበር 40 ኪሎ የማይሞላውን ሰውነታቸውን አንከብከቦ፣ እንቅልፉ እንደመጣ ህፃን ልጅ እቅፍ አድርጎ ፣ ወደ ቤት አስገብቶ ፎቴአቸው ላይ በጀርባቸው ያስተኛቸው።
ትንፋሻቸው የአልኮል ሸታ አለው ፤ መንፈሳቸው ዘና ብሏል ። እንደዚህ ሆነው አይቷቸው አያውቅም።
ቴሌቭዥናቸው በተለያዩ በምስራቅ እና በመካከለኛው አሜሪካ የሚገኙ ከተማ ነዋሪዎች ፣ የአዲሱን አመት በደስታ ሲያከብሩ ያሳያል።
“ቸኮልዬ ፣ እናትህ ስም አወጣሁ ትበል ! የኔ ፈጥኖ ደራሽ” አሉት በሆዳቸው ተገላብጠው
ፊታቸውን ወደ እሱ እያዞሩ “የኔ መልአክ ፤ አንተ ባትኖርልኝ ኖሮ እዚህ ብርድ ላይ ወድቄ ፣ እግሬ ተሳስሮ ፣ ምን ይውጠኝ ነበር?” “እኔ እኮ ሁሉ ነገርህ ሸዋላይን ነው የሚያስታውሰኝ” ደርግ የገደለውን የቀድሞ ባለቤታቸውን ስም እየጠሩ።
የዛሬ አርባ አመት አካባቢ ፣ ከባለቤታቸው ከኮሎኔል ሸዋላይ ዳኛቸው ጋር ፣ በሶደሬ በመዝናናት ያሳለፉት ግዜ ሀሳባቸው ላይ መጣባቸው። ኮሎኔሉ ፣ ኩሊ ይመስል ፣ አይንና ከንፈራቸውን እንደ እየሩሳሌም ፣ እንደ አክሱም ጽዮን ከመሳለሙ ፤ የታረዘውን ሰውነታቸውን እንደ ጣኦት ከማምለኩና የተራበውን የወንድነት ስሜቱን ከማርካቱ በፊት ፣ ልክ እንደ ቸኮል አቅፎ ፣ ተሸክሞ ወደ አልጋ የሚወስዳቸው ትዝ አላቸው ።
“የኔ አለኝታ” የሱሪ ፒጃማቸውን ዝቅ እያደረጉ ፣ ከላይ “ሄይንስ” ተብሎ የተፃፈበት ነጭ ቡታንታም አብሮ ተላጥፎ ዝቅ አለ
“ደምቷል እንዴ” የወደቁብትን መቀመጫቸውን አካባቢ በአይኑ እንዲመረምር እየፈቀዱ
“አ…አይ ትንሽ ነው ያበጠው ። በረዶ ላምጣ እንዴ እንዲይዙበት?”
“ምነው የኔ አለኝታ? ምን አልኩህ? እኔ እኮ ቀዝቃዛ ነገር ሰውነቴ ላይ አልወድም! ፤ በረዶውንስ አምጣው ፤ ግን ፣ ከውስኪ ጋር ፤ ማቀዝቀዣው አጠገብ ያለው መደርደሪያ ውስጥ አለልህ”
“የኔ አካል ፣ አንተም ተጋበዝ”
በሆዳቸው እንደተጋደሙ ፣ ከአንገታቸው ቀና ብለው የሰጣቸውን ውስኪ በአንድ ትንፋሽ ጅው አድርገው ብርጭቆውን መሬት ላይ አስቀመጡት።
“እኔ ከሁሉ የሚያናድዱኝ ‘ውስኪ -በኮክ’ የሚሉ ሴቶች ናቸው” ድምፃቸውን ቀጠን አድርገው እያሾፉ “ከመረቁ ጨልፉልኝ ፣ ከስጋውስ ጾመኛ ነኝ ፤ እንደማለት እኮ ነው”
ፎጣ ብቻ ያገለደመው ሰውነቱ በውስኪው ዘና ብሎ ፣ አይኑ በ ወ/ሮ አቻሜ ውብ-አካል ትርኢት ፈዞ ፣ መንፈሱ በኩምክናቸው ደስ ብሎት እየሳቀ እያለ
በድንገት “ና እስቲ ጀርባዬን እሸኝ” አሉት
ከዝች ቀን በፊት ፣ ይሄንን የመሰለ ጥያቄ ከአንደበታቸው ሊወጣ ይችላል የሚል እምነት ቀርቶ ሃሳብም ኖሮት አለማወቁን አላስተዋለም።
ጠረጴዛ ላይ ‘ኒቪያ-ሎሽን’ ከሚል ብልቃጥ ውስጥ ቅባት በቀኝ እጁ ተጭኖ ፣ ፊጪጭ አድርጎ ግራ እጁ ላይ አወጣና ፣ ሁለት እጆቹን አጣምሮ ለማሞቅ እያፋጨ “እሺ የኔ እመቤት” አለ
“ኦ-ማይ-ጋድ!” አሉ በእንግሊዝኛ ። ወደ አማርኛው ደግሞ ተመለሱና “ሸዋላይም እኮ እንዳንተው እመቤቴ ብሎ ነበር መኝታ ቤት ውስጥ የሚጠራኝ ። ወዳጅ ማለት ፣ አማርኛ አስረስቶ በሌላ ቋንቋ የሚያናግር ነው”
ለአንድ ደቂቃ ያህል በቅባት የተለቀለቁትን እጆቹን በዝምታ ሲያፋጭ ቆየና ታቹን ጀርባቸውን ጫን ሲለው
“አዎ እ……….እሱ ጋ!” አሉ
“አቤት …… አቤት ……. አቤት………አቤት”
“ውይ………….ውይ………..ውይ………….ውይ”
“እረግ………እረግ……….እረግ………..እረግ”
“ትእ………እንሽ ወደ ታች…………..ወደ ጎን”
“አዎ እ……….እሱ ጋ!” ልክ እንደ መዝሙር አዝማች
“እፎይ………እፎይ………እፎይ………እፎይ”
ይሄንን እየደጋገሙ ሲሉ ቸኮልም ሞቅ ፣ ልስልስ ያለውን ሰውነታቸውን እንደ ወጌሻ ሲዳስስና ሲጫን ቆይቶ መጨረሻ ላይ “ተንፈስ ! የአሮጊት ነብስ ! ” አሉ በመዝናናት መልክ
እጆቹን ሊያነሳ ሲል ፣ በፍጥነት እጁን ቀጨም አድርገው ይዘው ፣ ወደ ታች ሰውነታቸው መሩት።
እንደ ሐኪምና እንደ ወጌሻ ሳይሆን ፣ እንደ ፍቅረኛ ሰውነታቸውን እንዲዳስስ ፣ በአካለ ስጋቸው ተደስቶ እንዲያስደስታቸው ጋበዙት።
ግብዣውን በደስታ መቀበሉን ለማብስር ይመስል ፣ ያገለደመው ፎጣ እግሩ ስር ወደቀ።
የጀርባውን ዋና በራቸውን አንኩዋክቶ በረገደው ፤ ቁልፉን አውጥቶ ፣ የተዘጉትን የውስጥ ካዝናቸውን ወለል አድርጎ ከፈተው ። እንደ አናጺ ፣ መዶሻውን መዞ ፣ የላሉ ሚስማሮቻቸውን ቀጠቀጠላቸው። ያልተጠቀመው መሳርያ አልነበረም ፤ ካቻ ቪቴው ሲሰለቻቸው ፤ መሰርሰሪያውን ፣ መላግይዋን ፣ መቦርቦሪያውን አፈራረቀላቸው።
የሳሎን ቤታቸው ግድግዳ ፣ በቀኝና በግራ በኩል ፣ ከኢትዮጵያ በመጡ ቅርሳ-ቅርሶች አጊጧል። ፊት ለፊት ግን ፣ ትልልቅ የእመቤታችን የድንግል ማርይምና የልጇ የመድሐኔ አለም ምስሎች ፣ በሀዘንና በትዝብት ሲመለከቱት ፣ በጭንቀት ትንሽ ፍጥነቱን ቀነስ አለ።
“አታቁም እንጂ የኔ ጌታ ፣ የኔ ወለላ ፣ ደከመህ እንዴ? ምነው ያንን ቫያግራ የምትሉትን ኪኒን እንደ ቆሎ በቃምከው ኖሮ”
“አዎ እ……….እሱ ጋ!” አሉ
“አቤት …… አቤት ……. አቤት………አቤት”
“ውይ………….ውይ………..ውይ………….ውይ”
“እረግ………እረግ……….እረግ………..እረግ”
“ትእ………እንሽ ወደ ታች…………..ወደ ጎን”
“አዎ እ……….እሱ ጋ!” ልክ እንደ መዝሙር አዝማች
በድንገት ፣ መንቀጥቀጥ ለሁለት መንዘፍዘፍ ሆነ ። መላው ሰውነታቸው ዛር እንደያዘው ሰው ሶፋው ላይ ረግፎ ተውረግርጎ ሲያበቃ ፣ ታስሮ እንደተፈታ ወፍ በደስታ ወደ ሰማይ መጠቀ
የደስታ እንባ ተናነቃቸው ፣ ትንፋሻቸውም ፍጥነቱን እየቀነሰ እየቀነሰ እየቀነሰ እየቀነሰ መጥቶ ፣ ልዩ የሆነ የሰላምና የእረፍት አየር ተነፈሰ
ጸጥታ ፤ ፍጹም ጸጥታ ፤ ልዩ ጸጥታ ፤ ልብ ለልብ ተያይዞ ጸጥታ ፤ ልብ ለልብ ተገናኝቶ ጸጥታ ፤
ግሩም ሰላም፤ ……………..
እሳቸውም እሱን የማግኘታቸውን እድል ፣ ደግመው ደጋግመው እያመሰገኑ እጃቸውን ከደረቱ ላይ ሳያነሱ ብዙ ቆዩ።
ቸኮልም በደስታና በእረፍት መካከል ተውጦ ፣ የተሰማውን ስሜት ወደ ቃል ለመተርጎም ቃላት አጥረውት በጸጥታ ፊደላትን በጭንቅላቱ ሲያወጣ ሲያወርድ ቆይቶ በመጨረሻ “አቤት እንጀራቸው ሲጣፍጥ” ብሎ አሰበ።
ቴሌቪዥኑ ላይ በሲያትል ‘ስፔስ -ኒድል’ በተሰኘው ህንጻ ላይ ፣ አዲሱን አመት ለማብሰር በየአመቱ የሚደረገው የርችት ፍንዳታ ትሪት መታየት ጀመረ።
እንደ ሁለት የተጣበቁ ማንኪያዎች ፣ ጀርባና ፊት ተላጥፈው ተቃቅፈው ተኙ ።
“አበበ ቢቂላን አስታወስከኝ እኮ” አሉት
“ወይ ጉኡ…..ኡድ ! ቅድም የመጀመርያ ባለቤትዋን ፣ አሁን ደግሞ አበበ ቢቂላን ላስታውስዎ? ፤ ጎሽ ! እንኳንም ከነኒሳ በቀለ አልሆነ” አላቸው ቅድም ስለ ቫያግራ ያነሱት ትዝ ብሎት። “ ግን ፣ ንገሩኝ እስቲ እንዴት ነው “አበበ ቢቂላን ያስታወስኩዎ ?” አላቸው ቀጠል አድርጎ።
“አ………አይ ስንተዋወቅ-አንተናነቅ ! ከአሁን ወዲያማ አንቺ በለኝ ! ባይሆን እትዬ ማለት ትችላለህ” አሉ ታሪኩን ከመናገራቸው በፊት
ይኸውልህ “አበበ ቢቂላ በሮም ከታማ ማራቶኑን አሸንፎ ሲጨርስ ፣ አንዲት ቆንጅዬ ጣልያን ፣ ቀረብ ብላ በጆሮው ፣ በእንግሊዝኛ አይ-ላቭ-ዩ ትለዋለች። እሱም ፈገግ ብሎ ጥርሱን እያሳያት “የላቡንስ ነገር አታንሺው! ተጠምቄልሻለሁ” ይላታል ግንባሩን እየጠረገ። ወደ ማታ ያረፈበት ሆቴል ትሄድና እንደፈቀደችው በሁኔታዋ ታስረዳዋለች። ለካ አጅሬ የሩጫ ብቻ ሳይሆን የፍቅርም ማራቶን ይወዳል ፤ አልጋ ውስጥ ካሁን ካሁን ይጨርሳል ብላ ብትጠብቅ ፣ ጭራሽ እየበረታባት መጣ። የፈረንጅ ሴቶች ደግሞ እንደኛ ጠንካሮች አይደሉም ፤………ምን ላንተ እነግርሀለሁ? ቀማምሰሀቸው የለ? ፤ ምን ልበልህ? ውልቅልቁዋን አወጣት። ቢጨንቃት በቋንቋዋ እንዲያቆም ብላ ፣ ባስታ-ባስታ-ባስታ ! ብላ ብትጮህ ፣ የራባት መስሎት ፣ ይቀቀልልሻል ! እያለ ስራውን ቀጠለ”


[center]>>>ተፈጸመ<<<[/center]

[center]ስለ ድርሰቱ ያላችሁን አስተያየት ከዚህ በታች ብትጽፉለት ለጸሃፊው የወደፊት ስራዎች ታላቅ እገዛ ያደርግለታል[/center]

User avatar
selam
Leader
Leader
Posts: 175
Joined: 25 Aug 2009 01:59
Contact:

Re: አቤት እንጀራቸው ሲጣፍጥ ..Abet Enjerachew Sitafit ( Short story)

Unread post by selam » 17 Nov 2009 23:04

hahaha..betam funny !!gin,gin? qir yaleleghn neger binor, ye kene gudaye mechershaw alemetaweku naw. eger eger endaye kere beka..?meskin : ;)
batekalye, nice fiction like it!

Tina
Posts: 3
Joined: 17 Sep 2009 04:14
Contact:

Re: አቤት እንጀራቸው ሲጣፍጥ ..Abet Enjerachew Sitafit ( Short story)

Unread post by Tina » 29 Dec 2009 08:49

Amazing!!!! :lol: :lol: what a nice history

ኦሽንoc
Leader
Leader
Posts: 1129
Joined: 07 Aug 2009 14:20
Contact:

አቤት እንጀራቸው ሲጣፍጥ ..Abet Enjerachew Sitafit ( Short story) Par

Unread post by ኦሽንoc » 28 Mar 2010 21:42

በዚህ ታሪክ የተጠቀሱ ስሞችና ሁኔታዎች:

ገበየሁ ሹክሪ፡ የሲያትል ሀብታም ነጋዴ ።
አበባ ጭሩም፡ የገበየሁ ሹክሪ ሚስት ።
አባ አራጌ፡ የሬንተኑ ኡራኤል ዋና ካህን ።
መንዜው ፡ የአቶ ማርቆስ ሉቃስ ቅፅል-ስም ፣ አቶ ማርቆስ በሬንተኑ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን በዜማ ያገለግላል፣ የመመማ (መንዝ-መረዳጃ ማህበር) ሊቀ-መንበርም ነው።

አቤት እንጀራቸው ሲጣፍጥ (ምእራፍ-2 ክፍል-1)

ልቦለድ
ደራሲ የወንድወሰን (ቶቶ) አደፍርስ


አበባ ባሏን ቫንኩቨር የምትባል ከሲያትል በሰሜን አቅጣጫ 200 ኪሎ ሜትር የምትርቅ የካናዳ ከተማ ካልሄድን እያለች እየተለማመጠችው ነው። ዳግማዊ ጥላሁን የተሰኘ ከአዲስአበባ የመጣ ታዋቂ የመንፈሳዊ መዝሙር ዘማሪ ለማየት በጣም ጓጉታለች
“ዳጊዬን ማየት እፈልጋለሁ ብዬህ አልነበረም? ያለፈው ግዜ እንግሊዝ አገር ለእረፍት ሔጄ አመለጠኝ፣ እዚህ ሲያትል መጥቶ ነበር እኮ ”
“ኤዲያ ! የጴንጤ መዝሙር ደግሞ ከዘፈን አይለይም ፤ ዲያቆን ከዘፈነ ፍየል ከቀዘነ የተባለው ነው እኮ”
ድምጽዋን እንደ ቀበጥ ሕጻን ጉትት እያደረገች “እረ በየሱስ እንደሱ አትበል” አለች ።ሰልካካ ረጅምና ቀጭን ነች። ከስራ በህዋላ 4 ኪሎ ሜትር በቀን እየሮጠች ነው እቤት የምትደርሰው ፣ በተጨማሪ ቅዳሜ እና እሑድ ሰውነቷን ለማጠንከር እያለች ከተለያያ ማሽንና ብረት ጋር ስትታገል ትውላለች ። እግርና እጇ ከመደንደንም አልፎ ጡንቻ እያወጣ ነው። የለበሰችው አጭር ቀሚስ ጎንበስ ባለች ቁጥር ነጩን ቡታንታዋን ያሳያል።

“እረ የቀረኝን አይኔን እንዳታጠፊው” አላት ጀርባዋን ሰጥታው አጭር ጠረጴዛ እየወለወለች
“እንዴት?” አለች ስላልገባት
“ምንድነው ዛሬ ደግሞ የለበሰሽው” ታቹን ቤትሽን እኮ ወለል አድርጎ ያሳያል
“ምን አገባህ? የፈለኩትን ብለብስ !”

በናቷ ኤርትራዊ ስለሆነች ሁል ግዜ የዜግነት ታማኝነቷ የት ላይ እንደሆነ እንደቀልድ እያስመሰለ ይጠይቃታል። “አሁን ጦርነት ቢነሳ ለማን ነው የምታግዥው?”
“የምን ጦርነት?”
“ኤርትራና ኢትዮጵያ”
“እረ እባክህ አንተ ሰውዬ! እግዚዮ በል! አሁን ጦርነት ምን አመጣው? አንድ ህዝቦች አይደለን እንዴ? ለምንስ ክፉ ትመኛለህ?” በሀዘን አንገቷን እየነቀነቀች
“ሂጂ! ሌባ! ለጥቅማችሁ ሲሆን አንድ ህዝብ ነን ፤ ጥጋብ ሲይዛችሁ ደግሞ እኛ የተለየን ፣ የተሻልን ነን ትላላችሁ ብሎ ጠንጋራ የፕላስቲክ አይኑን አፈጠጠባት

ግራ አይኑ ሰው ሰራሽ ነው። የኢ. ሐ. ድ. ግ ሰራዊት መጀመሪያ አዲስ አበባ ሲገባ ገበየሁ ሽኩሪም ከህዋላ አይዞህ ፣ ግፋ! እያለ ተከትሎ ገብቶ ፤ የሰልባጅ ንግዱን ጀመረ። ዛሬ ከካይሮ እስከ ጆሐንስበርግ ድረስ የሰልባጅ ንግድን የሚቆጣጠር ሰው ነው። በዚህ ንግድ ብዙ ሀብትና ወዳጅ ቢያገኝም ፣ በዛው መጠንም ጠላት አፍርቷል።
ጨርቃ ጨርቅን በተመለከተ ሞያና ስራ ላይ የተሰማሩ ብዙ ነጋዴዎችን ፣ አገሩን በፈረንጅ ውራጅ ልብስ አጥለቅልቆ አክስሯቸዋል። ወንድወሰን ሰልጢ የተባለው የጣቃ ጨርቅ አከፋፋይ ራሱን ከዛፍ ላይ ሰቅሎ ፣አስከሬኑ በሶስተኛው ቀን ከእግር ጣቱ እስከዳሌው ድረስ በጅብ ተበልቶ ነው የተገኘው ፤ በሶስት ሚልዮን ዶላር ደብረብርሐን ላይ ከኮሪያ አስመጥቶ የተከለው የጨርቅ ፋብሪካ በኪሳራ ተዘግቶ ከማየት ፣ ሞቱን መረጠ።
ገበየሁ ሹክሪ ግን ተቀናቃኞቹም ላይ ሆነ ፣ ገበያተኞቹ ላይ ፣ እኩል ያሾፋል። “ጉራጌ ይሉኛል ግራ የገባቸው ፣ በፈረንጅ ዲሪቶ ሰው አስመስያቸው” እያለ ይሳለቅባቸዋል

የጨርቃ ጨርቅ እንዱስትሪ ፣ ገበየሁ ሽኩሪ ነፍስ ላይ አስር ሚሊዮን ዷላር አስቀምጧል የሚባል ወሬ ስላለ ፤ ሌላው ወሬ ደግሞ አዲስ አበባ ውስጥ ያለ ችግረኛ በሙሉ አንድ ቀን ወይ ሎተሪ ይደርሰኛል ፣ አለበለዚያም የሽኩሪን አንገት ቆርጬ ያልፍልኛል እያለ በተስፋ ሰንጢውን እየሳለ ይጠብቃል የሚል ነው።

የሽኩሪን አንገት ለማረድ በጉጉት የሚጠብቁት ችግረኞች ግን በሙሉ የሚለብሱት የሱኑ የሰልባጅ ዲሪቶ ነው።
ደማስቆ ውስጥ ተኩሰውበት ግራ አይኑን ቢያጠፉበትም ፤ ነፍሱ ተርፎ የእስራኤል የአይን ቀዶ ጥገና ሀኪሞች ከመስታወትና ከፕላስቲክ የተሰራ አይን ከተቱለት። ሆኖም ሰው ሰራሹ አይን ሳይንቀሳቀስ አንድ ቦታ ቦግ ብሎ የጠንጋራ መልክ ሰጥቶታል።
***************
አበባ የዳግማዊን የቪዲዮ ትሪኢት ሸክላ ሶኒ የተሰኘ ማጫወቻ ውስጥ ቀረቀረችና ፕሌይ የሚለውን ቁልፍ ስትጫነው፤ ቴሌቪዢኑ ነፍስ ዘራ
ወደ ላይ በመንፈስ እንጣጥ እንጣጥ እንጣጥ ብሎ ሲያበቃ “ጌታ ይመስገን” አለ ዳግማዊ ጥላሁን ፤ ከጥላሁን ገሰሰ ጋር ዝምድና የለውም ።ሆኖም ጥላሁን እራሱ “ማህደር” በተሰኘው ጋዜጣ ላይ በሰጠው ቃለ መጠይቅ “በአሁን ግዜ ካሉ ወጣት ድምጻውያን ማንን ታደንቃለህ” ቢባል “እናት ስም አወጣሁ ትበል ፤ ዳግማዊ ጥላሁን ፣ ‘እየሱስ’ ከማለቱ በስተቀር እኔኑ የወጣትነቴን ነው የሚያስታውሰኝ” ብሎ መስክሮለታል
ከቴሌቪዥኑ ውስጥ አሁንም ደግሞ “ጌታ ይመስገን” አለ
ምእመናኑ ብዙም አልተንቀሳቀሰም
“እረ ጌታ ይመስገን!” ብሎ ደገመ ፣ ጌታ በደንብ አለመመስገኑ ቅር እንዳለው አስመስሎ
ምእመናኑ በእልልታ ፣ በጭብጨባና በጭፈራ ቅሬታውን አረካለት
*****************
የገበየሁ የኪስ ስልኩ አቃጨለ ፡ ማ እንደደወለለት ሲያይ አባ-አራጌ የሚል ጽሁፍ አየ።
ከሰላምታ በህዋላ “ምነው በደህና?” ብሎ ጠየቃቸው
“በጥብቅ የማናግርህ ነገር አለ” ቀጠል አድርገው “ደግሞ ብለህ ብለህ ባንኮበር የጴንጤዋች ዳንኪራ ልትሄድ ነው ማለትን ነው የምሰማው” ቨ የሚለው ፊደል ካፋቸው ስለማይወጣላቸው ነው ቫንኩቨርን ባንኮበር ያሏት
“ስማ ሰይፈ” አሉት ፣ ሰይፈገብርኤል የተሰኘውን የክርስትና ስሙን ለሁለት ገምሰው
“ለምን ራስህ ላይ መቅሰፍት ታመጣለህ? ስንት ግዜ ነበር እመብርሐን ከሞት ያዳነችህ? እንደ ድመት ሰባት ነፍስ የሰጠህ እኮ ልጇ ነው”
ደማስቆ ላይ አይንህን አጠፉት ፣ ናይሮቢ ላይ በዱላ ጭንቅላትህ ተፈንክቶ ዳንክ ፣ ሞዛንቢክ ውስጥ አንጀትህን በሳንጃ ተረተሩት ፤ ይህ ውል ሲደርስብህ እመብርሐን አልተለየችህም
“ለይስሙላ ነበር እንዴ የበላየሰብንና የመቤታችንን ታሪክ አጫውቱኝ ያልከው?” አሉት
“አባታችን ስለ በላየ-ሰብ ታሪክና ስለእመቤታችን ታሪክ ያስተምሩናል?” ብሎ ያለፈው ግዜ ከቤተክርስቲያን በኋላ የጠየቃቸውን አስታውሰው
“ምን አሳሰበህ ልጄ?” ብለውት ነበር በጥያቄው በመደነቅ
“በፕሮቴስታንት ሐይማኖት የተሳማሩት ወንድሞቻችና እህቶቻችን ያሾፉብናል ይሳለቁብናል”
“ጴንጤና ጂሆቫ ማለትህ ነው?” ብሎ መንዜው ሲስቅ
“እባክህ እስቲ ረጋ በል” አሉት መንዜውን በቁጣ ፤ ረጅም ጢማቸውን ወደ ታች እይጎተቱ “ቀጥል ልጄ”
“በቀጥታ ወደ እግዚአብሔር ቤት መግባት እያለ ለምንድነው አማላጅ የሚያስፈልገው እያሉ ነው የሚያስተምሩት። ወደ እመቤታችን ማልቀስ እንዴት እንደ ጣኦት ማምለክ ይቆጠራል”
“ጥሩ ብለሃል ፤ እግዚአብሔር ይባርክህ” ብለው ፤እመቤታችን ድንግል ማርያም እንዴት አድርጋ አረምኔውን በላየሰብን እንዳማለድችው ተርከውለት ነበር።
*************************
“ስማ እግርህን ታነሳና ገዝቸሀለሁ”
“በድያለሁ አባቴ ይቅር ይበሉኝ”
“ጾም ሲፈታ አስር ቀን ጨምረህ እንድትጾም” ብለው የቅጣት ጾም መረቁለት
አበባም የባሏንና የአባ አራጌን ወሬ እያዳመጠች ተደናግጣለች
ስልኩን እንደያዘ ፣ እንዳይሰሙት የአፍ መነጋገሪያውን በእጁ ሸፍኖ ድምጹን ዝግ አድርጎ “ማን ነው የነገራቸው?” ይላታል
በሹክሹክታ “እኔ እንጃ” በማለት ትከሻዋን ከፍ ስታደርግለት
“ለመሆኑ ለምን ነበር የፈለከኝ? እዚህ ድረስ መጥተህ እንዳጣኸኝ መንዜው ነገረኝ” አሉት
“አንዱም ለራሴ ጉዳይ ነበር” አለና ሚስቱ እንዳትሰማው ስልኩን ይዞ ወደ በረንዳ ሄዶ ሲያበቃ የበረዳውን ተንሸራታች በር ዘግቶ ወሬውን ቀጠለ
“የባለበቴ ሚስት ከባሏ ተጣልታ ፣ አራሱን ልጅ ብቻ ይዛ ፣ ሶስቱን ትልልቆቹን በየቦታው በትና ፣ እዚህ እላዬ ላይ መጥታ ሰፍራብኛለች። ወዳጅ ፣ ዘመድ ፣ ቤተሰብ ለማስታረቅ ያልሞከርነው ነገር የለም። እርስዋ ብቻ ነዎት የቀሩን ፤ እርስዋን ትሰማዎታለች” ብሎ ሳይጨርስ “ኤዲያ! እኔ ደግሞ የሰለቸኝ ፣ የታከተኝ ነገር ቢኖር የትዳር ችሎት መዋል ነው! ቤተክሲያን እኮ ፍርድ ቤት አይደለችም! ተቻችለው መኖር እስካልቻሉ ድረስ ፣ የራሳቸው ጉዳይ!። ስማ እነሱ እንደሆን ማንንም አይፈሩም። ተክሊሉንማ እየደጋገሙ ሲረግጡት ዘወትር የምናየው ነገር ነው። አንተንም እንደ ነፍስ አባት ሳይሆን እንደ ልጄ ልምከርህ ፣ የሽምግልና ሸንጎ ሳይሆን አርፈህ ተቀመጥ” አሉና ደህና ዋልም ሳይሉ ስልኩን ጆሮው ላይ ዘጉበት።

ይቀጥላል...

Post Reply

Return to “Ethio Art and Culture..ኢትዮ ጥበብ ፤ስነ ጽሁፍ ፤”