ለአድዋ መታሰቢያ Remember Adwa Victory

ግጥሞች፣ታሪኮች፣ፎቶዎች፣ሙዚቃዎች
Poems,Short stories, graphics,pictures,musics,Technology
Post Reply
ኦሽንoc
Leader
Leader
Posts: 1129
Joined: 07 Aug 2009 14:20
Contact:

ለአድዋ መታሰቢያ Remember Adwa Victory

Unread post by ኦሽንoc » 26 Feb 2010 18:01

ለአድዋ መታሰቢያ

ሰለፍ ካንተ ነው በለው
ድል የፈጣሪ አድርገውያገሬ ሰው
በበደልኩህ ይቅር ብለህ
ጉልበት ያለህ በጉልበትህ
ጉልበት የሌለህ በፅሎትህ
ሀገርክን አድን በፍቅርህ
በድየህ ከሆነ ይቅር ብለህ
ወስልተህ ሳገኝህ ላልምርህ
ማሪያምን ብያለሁ ላልተውህ

ያዋጁ ሙሉ ቃል ይሄ ነው
የክተት አዋጁ ጥሪው
የቤተሰብ የጋራ ነው
ጀሌው ካለቃው ሳይለያይ
ቀና ብሎ ሳይተያይ
ላዋጁ ቆመ ሳይዘገይ
ንጉሱ አዋጁን አስነግረው
ወረይሉ ላይ ተቃጥረው
ጠላትን ለመግጠም ቸኩለው
ዋስ መከታቸውን አስቀድመው
ሰልፈኛውን ብቻ አስቀድመው

ጦርነቱን በጀግንነት ጀመሩ
አዋጅ ነጋሪት አስነገሩ
ንሴብሆ ብለው ሲጀምሩ
የጠላትን ቅስም ሰበሩ

በውነት ትውነስተው ንጉሱ
ተሳክቶላቸው ድል ነሱ
ጀግኖችን ሁሉ አስነሱ
ዛሬም ቢጠሩ ቢወደሱ
የታሪክ ምራፍ የከፈቱ
ለሀገር ለወገን የሞቱ
መጠሪያ ይቁም ሀውልቱ
የአድዋን ሰላሴ ጠላት አረከሰው
ገበየሁ በሞቴ ግባና ቀድሰው
ገበየሁ ቢሞት ተተካ ባልቻ
መድፍ አገላባጭ ብቻ ለብቻ
የህን ታሪክ ላቆዮህ
ጉልበት ያለህ በጉልበትህ
ጉልበት የሌለህ በጸሎትህ
የጀግናው ቃሉ አደራው
የሔ ነው መልክቱ የዳኘው

ወንድወሰን ሰብስቤ
2009 02

ኦሽንoc
Leader
Leader
Posts: 1129
Joined: 07 Aug 2009 14:20
Contact:

የአጼ ሚኒሊክ የአድዋ ጦርነት አዋጅ

Unread post by ኦሽንoc » 26 Feb 2010 18:07

አፄ ምኒልክ ጣሊያን አገራችንን በወረረ ጊዜ የሚከተለውን አዋጅ አወጁ።
«እግዚአብሔር በቸርነቱ እስካሁን ጠላት አጥፍቶ አገር አስፋፍቶ አኖረኝ። እኔም እስካሁን በእግዚአብሔር ቸርነት ገዛሁ።
እንግዲህ ብሞትም ሞት የሁሉ ነውና ስለእኔ ሞት አላዝንም። ደግሞ እግዚአብሔር አሳፍሮኝ አያውቅም። ከእንግዲህም ያሳፍረኛል ብዬ አልጠራጠርም።
አሁንም አገር የሚያጠፋ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት እግዚአብሔር የወሰነልንን የባሕር በር አልፎ መጥቷልና እኔም ያገሬን ከብት ማለቅ የሰውንም መድከም
አይቼ እስካሁን ዝም ብለው ደግሞ እያለፈ እንደፍልፈል መሬት ይቆፍር ጀመር።
አሁን ግን በእግዚአብሔር ረዳትነት አገሬን አሳልፌ አልሰጠውም። ያገሬ ሰው ካሁን ቀደም የበደልኩህ አይመስለኝም።
አንተም እስካሁን አላስቀየምኸኝም። ጉልበት ያለህ በጉልበትህ እርዳኝ። ጉልበት የሌለህ ለልጅህ ለሚስትህ ለሃይማኖትህ ስትል በሃዘን እርዳኝ።
ወስልተህ የቀረህ ግን ኋላ ትጣላኛለህ። አልተውህም። ማርያምን ለዚህ አማላጅ የለኝም።
ዘመቻዬ በጥቅምት ነውና የሸዋ ሰው እስከ ጥቅምት እኩሌታ ድረስ ወረይሉ ከተህ ላግኝህ»

ኦሽንoc
Leader
Leader
Posts: 1129
Joined: 07 Aug 2009 14:20
Contact:

Re: ለአድዋ መታሰቢያ

Unread post by ኦሽንoc » 27 Feb 2010 21:35


ኦሽንoc
Leader
Leader
Posts: 1129
Joined: 07 Aug 2009 14:20
Contact:

Re: ለአድዋ መታሰቢያ

Unread post by ኦሽንoc » 27 Feb 2010 22:37

Image
ይስማ ንጉስ ሚያዚያ 24 1881 ዓ.ም. በምኒሊክና በ አንቶኔሊ
መካከል የተደረገው የውጫሌ ውል የተፈረመበት
ታሪካዊ ቦታ።
Yisma Nigus Wuchale. A Historical place where the Wuchale treaty took place.

ኦሽንoc
Leader
Leader
Posts: 1129
Joined: 07 Aug 2009 14:20
Contact:

ፈረሱ ዳኘው ሚስቱ ጣይቱ ምጥዋ ወርዳ ቀዳች ወጥቤቱ

Unread post by ኦሽንoc » 01 Mar 2010 03:52

በዓለም ሁለት ታላላቅና አስደናቂ የድል ታሪኮች አሉ። አንደኛው ከ2ሺህ ዓመት በፊት ሃኒባል ሮማውያንን ያሸነፈበት ነው። ሁለተኛው ደግሞ ከ2ሺ ዓመት በኋላ ምንሊክ እኚሁ ሮማውያን በአድዋ የቀጡበት ነው። ይህም ለጥቁር ሕዝባች ሁሉ የነፃነት ጐህ ቀዷል፣ አውሮፓውያንም ለጥቁር ያላቸውን ግምት አስተካክለዋል። የዴቪድ ካርል ጥንቅር እንዲህ ይነበባል።

"ፈረሱ ዳኘው ሚስቱ ጣይቱ ምጥዋ ወርዳ ቀዳች ወጥቤቱ"


(ዴቪድ ካርል)

ዛሬም ሸጋ ሆኖ የተሰናዳ የታሪኩ ቡፌ ለክቡራን የፊያሜታ ደንበኞች አቅርበናል። ታላቁንም የሃበሾች ተጋድሎ ትኮመኩሙ ዘንድ ግብዣችን ነው። አንዳች የሚጣል የለውም! ... እነሆ የታሪክ በረከት!
እንግዲህ የዕርቀ ሰላሙን ስብሰባ ለሳምንት እናቆየውና፣ በፊት ጊዜ በቦታ ጥበት ምክንያት የተውናቸውን ጣፋጭ ታሪኮች እናወጋለን። የዚያን ዘመን ማስታወሾዎችና ደብዳቤዎችም አሉን፣ ሁሉም በትዝታ ያዋዙናል። የጣሊያን ምርኮኞች ታሪክ ይቀጥላል...
የአድዋ ድል በአውሮፓ እንደተሰማ ከባድ ድንጋጤ ሆነ። የኢጣሊያም ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ። የምክር ቤት አባላት እንደዚያን ቀን አዳራሹን አጣበውት አያውቁም። ጠቅላይ ሚንስትሩ፣ ሲኞር ክሪስፒ በታላቅ የፖሊስ አጀብ ወደ ምክር ቤት ሲገባ በሃፍረት አንገቱን ደፍቶ ነበር... ሲኞር ክሪስፒ የሚመራው የቀኝ ክንፍ ፓርቲ አባላትም ልባቸው በሃዘን ተሰብሯል፣ ስብሰባው ተጀመረ።
የሶሻሊስትና የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት "ጠቅላይ ሚኒስትሩንና በኢትዮጵያ የሚገኙት የጣሊያን ጦር አዛዦች ለፍርድ እንዲቀርቡ" በማለት ምክር ቤቱን በጩኸት ሞሉት። የተከበረውም ጠቅላይ ሚንስትር ወደ መድረኩ ወጥቶ...
የተከበራችሁ የምክር ቤት አባላት... የኢጣሊያ ሠራዊት እስከቻለው ድረስ በጀግንነት ተዋግቷል። በአጋጣሚ ድሉ ለምንሊክ መሆኑ እንደማናችሁም ሁሉ አሳዝኖኛል... በአሁኑም ወቅት ለንጉስ ኡምቤርቶ የስንብት ወረቀት ጠይቄ፣ ስራዬን በገዛ ፈቃዴ ለቅቂያለሁ..." ሲኞር ክሪስፒ፣ የጣሊያን ጠቅላይ ሚንስትር ንግግሩን አልጨረሰም። አዳራሹ በጩኸት ተናጠ...
"ውጣ! ይሄን ከሃዲ አስወጡልን! እንግዲህ" ብዙ ተጮኸ፣ ሰደቡትም። ክሪስፒ ግን አለ፣ ካቢኔው "ለተወሰነ ጊዜ በስራ ላይ ይቆያል!" በዚህ ጊዜ ዛቫቴሪ የሚባለው የም/ቤት አባል ተነስቶ ነበልባላዊ የስድብ መዓት አውርዶበት ሲያበቃ... "እንግዲህ አንተን በፍርድ ቤት እንጂ፣ በምክር ቤታችን ውስጥ አንፈልግህም። በቅተኸናል..." አለው።
የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ረብሻውን ለማቆም ጥረት ቢያደርግም ከቶ አለተሳካለትም... የምክር ቤቱም ስብሰባ ለሌላ ጊዜ ተዛወረ። የካቲት 27 ቀን 1888 ዓ.ም።
ከዚህ በኋላ በኢጣሊያ ዋና ከተሞች ከፍተኛ ረብሻ ሆነ። በሮም ከተማ፣ የትሪቶኒ ጐዳና በሰላማዊ ሰልፈኞች ተጨናነቀ። በዚሁ ትሪቶኒ ጐዳና ኦዲስካልኬ የሚባለው የጣሊያን መስፍን በሰረገላ ሲሄድ ሳለ በሞልሜንቲ ፖምፒዮ የሚመሩት ሶሻሊስቶች ሰረገላውን ገለበጡበት። መስፍኑንም ጭቃ እየቀቡ "ምንሊክ ህያው ይሁን!" አሰኙት።
ያን ሰሞን የጣሊያን ቲያትር ቤቶችና ዩኒቨርስቱዎች ላለተወሰነ ጊዜ ተዘጉ። ቀኝ ክንፎቹ የክሪስፒ ተከታዮች ተጨማሪ ጦር ወደ ኢትዮጵያ እንዲላክ ጠየቁ... ሶሻሊስቶቹ ደግሞ በኢትዮጵያ ያለው ጦር ባስቸኳይ ወደ ሮም እንዲመለስ... አሉ። በዚሁ ግርግር በሚላኖ ከተማ አንድ ሰው ሞተ፣ አገር ትናጥ ጀመር። ጋዜጦችም በካርቱን ስዕል ጠቅላይ ሚንስትር ክሪስፒ ላይ ቀለዱበት።
ብዙዎች ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ፣ ሲኞር ክሪስፒ ቤት ሄደው ቤቱን በድንጋይ ናዳ አክለበለቡት። በኔፓል የወጣውም ሕዝብ ከፖሊስ ጋር ከፍተኛ ግጭት አድርጐ ጉዳት ስላደረሰ በጦር ሰራዊቱ ኃይል ተበተነ። በቱሪንና በፓቪያ ያሉ ሰዎች ደግሞ ተጨማሪ ወታደር ወደ ኢትዮጵያ እንዳይሄድ የባቡሩን ሃዲድ ከጥቅም ውጪ አደረጉት... የጣሊያን ቤተ ክርስቲያናትም ለሞቱትም ሆነ ለተማረኩት የኢጣሊያ ወታደሮች ፍታት አደረጉላቸው... መጋቢት 7 በታላቅ ድምቀት ይከበር የነበረውም የንጉስ ኡምቤርቶ የልደት ቀን በሃዘን እንዲከበር ተወሰነ። በለንደን በኒዮርክ፣ በቺካጐና በቦነስ አይረስ የሚገኙ ጣሊያኖች ገንዘብ አዋጡ... ለሟች ወታደሮች ቤተሰብም ሰጡዋቸው።
አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የኢጣሊያን ምክር ቤት ተናወጠ። አዲስ ጠቅላይ ሚንስትርና አዲስ ካቢኔ እንዲቋቋምም ሆነ። ደግሞም ጠቅላይ አዛዥ፣ ጄኔራል ባራቲየሪ ባስቸኳይ ሮም መጥቶ እንዲፈረድበት ተወሰነ፣ እንደ ሃሳባቸውም አደረጉ።
አስደሳቹ ዜና ግን ወደ ኢጣሊያ የደረሰው ዘግይቶ ነበር። እስከ 4, 00 የሚጠጉት የጣሊያን ምርኮኞች በኢትዮጵያ መኖራቸው ሲነገር የወላድ አንጀት ዳግም ተንሰፈሰፈ። "ልጄ ሞቷል" ያለች እናት እንደገና በተስፋ አለቀሰች... ትግሉ ኢትዮጵያን በጦርነት ለማሸነፍ ሳይሆን ምርኮኞችን ለማስለቀቅ ሆነ። ሰላማዊ ሰልፈኞችም፣ "የኢትዮጵያ ሉአላዊነት ታውቆና የጦር ካሳ ተከፍሎ ወንድሞቻችን ከሃበሻ ምድር ይፈቱ" አሉ። ሮም ዳግም ተረበሸች።
እነሆ የሃበሻ ምድር ከትግራይ ግድም፣ በደም መዓት ተጨማልቃለች። የሞተው ሞተ፣ የቆሰሉትም ጣሊያኖች ለትግራይና ለአካባቢዋ ገዢዎች በጦር ምርኮኛ ደንብ ተሰጥተዋል። እዚያ የቀሩ የምንሊክ ወታደሮችም ነበሩ... አብረው ወደ ሸዋ የወረዱም አሉ... ሚያዝያ፣ 1888 ዓ.ም።
አብረው ወደ ሸዋ የወረዱት ብዙ ተረትና ታሪክ አላቸው። ሸንጌ ላይ፣ ዞብል አካባቢ በደረሱ ጊዜ ከአዘቦ ኦሮሞዎች ጋር ተዋግተዋል። ወደ አዲስ አበባ በተደረገው የመልስ ጉዞ የእቴጌ ጣይቱ ገረዶች የተደፈሩበት አጋጣሚም አለ... በጉዞ ላይ ብዙ ገጠመኝ ይኖራል። እሱ ይቆየንና አዲሳባ ስለገባው ድል አድራጊ የምንሊክ ጦር እናውጋ... የጣሊያን ሕዝብና ምክር ቤቱ በጭንቅ ላይ ነው። እናቶች ዘወትር ያለቅሳሉ። የአድዋ ድል ሰሞን ምፅዋ የተራገፈውና በጄ/ል ባልዲሴራ የሚመራው አዲስ ጦር ደግሞ በጣሊያን ሽንፈት ቁጭት ውስጥ ገብቷል። የበቀል ሰናድሩም በደም ቆሌ ተቅበዝብዟል... የምንሊክ ጦር ግን "ሆ!" እያለ አዲስባ ገባ!
ልብስና ጫማቸው ያለቀ፣ ቡቱቶ የለበሱ የጣሊያን ምርኮኞች በዚህ ሁሉ የሃበሾች ደስታ መሃል አንገታቸውን ደፍተው አለፉ። ፉከራውም፣ ቀረርቶውም፣ እልልታውም፣ ሽብሸባውም ሁሉ በምርኮኞች ልብ ውስጥ የሃዘን እሳት ነው የሚፈጥር፣ የሰቆቃ ትንታግ ሁለመናቸውን ይፈጀዋል። እነሆ ናፍቆትና ቁጭት እያንበለበላቸው ከነፃይቱ ከተማ፣ ከኢትዮጵያ መዲና ደረሱ። ግንቦት 15፣ 1888 ዓ.ም።
ሽለላው የእንጦጦን ጋራ ሸበለቀው... ግጥምና ገጣሚው ተስተካክለው ግጥም አሉ።
[blockquote] ጣሊያን ገጠመ ከዳኘው ሙግት
አግቦ አስመሰለው በሰራው ጥይት...
አሁን ማን አለ በዚህ ዓለም
ጣሊያን አስደንጋጭ ቀን ሲጨልም...
ሸዋ ነው ሲሉት አድዋ የታየው
ጣሊያንን መላሽ ወንዱ አባ ዳኘው...
አይኰረተም እጁ የዘናው
ወንዱ ምንሊክ ዘላለም ይቅናው...
[/blockquote]
የግንባር ቀደሙ ጦር እንዲህ በፊታውራሪዎች እየተመራ አገር በደስታ ነወጠች። ከፊታውራሪዎቹ ጦር ቀጥሎ በብር ያጌጠች በወርቅና በኢትዮጵያ ባንዲራ የተንቆጠቆጠች በቅሎ አለች፣ ምንሊክ ከዚህች በቅሎ ላይ ነው ያሉ። ግራና ቀኝ በታላላቅ መኳንንቶች ታጅበዋል። ደንገላሳ የሚጋልቡት የኦሮሞ ፈረሰኞችም የምንሊክ አጀብ ናቸው።
አፄ ምንሊክ የዘወትር የሃር ካባቸውን ነፋስ እያሸለበለበው በታላቅ ግርማ ታዩ። የንጉስ ነገስታትነታቸውን ምልክት ነጭ የሃር ጨርቅ በግንባራቸው ሸብ አድርገዋል፣ በአናታቸውም ላይ ባለወርቅ ክፍካፉን ጥቁር የሞስኮ ባርኔጣ ደፍተዋል፣ እንደ ጃንሆይነት ደንብም ትላልቅ ቀይ ዣንጥላዎች ተይዞላቸዋል... አገር በደስታ ቀለጠች።
ከምንሊክ ቀጥሎ እቴጌ ጣይቱ ሁለመናቸው በሃር ጨርቅ ተሸፋፍኖ በበቅሎ እየሰገሩ፣ አጀቦቻቸውም እየፈከሩ ነው ያሉ...
[blockquote] "ፈረሱ ዳኘው ሚስቱ ጣይቱ
ምጥዋ ወርዳ ቀዳች ወጥ ቤቱ" እየተሰኘ።
[/blockquote]
ከእቴጌ ጣይቱ ቀጥሎ ራሶች አሉ። የበቅሎና የአህያው ቁጥር ይታክታል። ስንቅ ተጭኖባቸው የነበሩት ግመልና ዝሆኖችም በእርጋታ ይሰግራሉ... ወደ ነፃይቱ የምንሊክ ከተማ!
ከጣሊያን ምርኮኞች ቀጥሎ ሴቶችና ሕፃናቶች አሉ። እንግዲህ "ስምን መልዓክ ያወጣዋል" እንዲሉ፣ ከተከታዮቻቸው አንዱ ቶክልት "ዓሊ" ሳይላቸው አልቀረም... የጣሊያን ምርኮኞች ካገር እስኪወጡ ድረስ የቅፅል ስማቸው ዓሊ ነበር። እነሆ በሃዘናቸው ላይ ቅፅል ስም፣ በቅፅል ስማቸው ላይ የካህናት ዝማሬ ተጨመረላቸው። ዜማው ደስ ይላል..
[blockquote] "ሰላም ለዝክር ስምከ መልዕክተ ኩሉ ዘኰነ
ወበግርማሁ ግሩም እንተ አጥፍዓ ጣልያነ
ንጉስ ነገስት ምንሊክ ዘኢትዮጵያ መድኅነ
[/blockquote]
ቀተልኮ ለአላዊ በምድረ ትግሬ መካነ "የእንጦጦ ማርያም፣ የራጉኤል፣ የስላሴና የኡራኤል ደግሞም የጊዮርጊስ ካህናት ልብሰ ተክህኗቸውን ዝቅ አድርገው በያሬድኛ አሸበሸቡ። "...ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐፂባ በደመ ኢጣሊያ" እያሉ አዜሙ። (የድጓን ዜማ ያስታወሱማ!)
በዚህ ሁሉ ሁካታና ደስታ መሃል ቀደም ብሎ አዲሳባ የገባው የሊቀ መኳስ 50 መድፍ ተንቧተጉ፣ በፈረቃ አገር አቀለጡ። የአዲስ አበባ ጋራዎች የመድፉን ድምፅ ደግመው ደጋግመው አስተጋቡ። የድል ምስራችም ሆነ። አሸሼ ገዳሜው ከምርኮኞች በቀር ለሀበሾች ትርጉም ነበረው።
ደግሞም ባሏንና ልጅዋን ከአጅቡ መሃል የምትፈልግ ሴት ባሏን ብታገኝ ደስ ብሏት፣ ልጅዋንም ብታገኝ አገላብጣ ስማ በደስታ ታለቅሳለች። የሞተባትም እንዲሁ ታለቅሳለች...
በአድዋ ዘመቻ ጊዜ የምንሊክ ዙፋን የተረከቡትና ምንሊክ ቤተመንግሥት የነበሩት ራስ ዳርጌም በደስታ ማልቀሳቸው ከቶ አይዘነጋም። የምንሊክ አጐት፣ ራስ ዳርጌ የወንድማቸውን ልጅ በደስታ ዕንባ ነው የባረኩ... የደስታውም መድፍ ሲንፈቀፈቅ ሁላቸውም በደስታ ጭምር አለቀሱ። ምርኮኞቹ ግን በሃዘን...
ሁሉም ያልፋል። ያቺም ቀን አለፈች። አሁን የምርት ዘመን ተጀምሯል። ምርኮኞቹም የጣሊያን ወታደሮች በየባላባቱ ቤት ተመሩ። የዚያ ዘመኑን የታሪክ ማስታወሻ እንናበብ...
"አንድ ግብጣን (ካፒቴን) አዲስ አበባ ላይ ታሞ ሞተ። የቀሩት ወታደሮች በያገሩ ተመሩ። ምግቡን እጠገቡ ድረስ ይብሉ ብለው ምንሊክ አዘዙ። ዛሬ ከባላገር ጋር በጣም ተሰማምቷል። ልብሱንም እንዳገሩ እየሰፋ ሰጡት። ምንሊክም ሰባት ሰባት ብር ደሞዛቸውን ሰጧቸው... ከመንገዱም ላይ የኢጣሊያ ሹማምንት የወደደውን እንዲገዛ አራት አራት ብር ሰጥተዋቸው ነበር። በቀረው ሰራተኛው ስራው እየተጠየቀ በየስራው ለሰራተኛው አከፋፈሉት። ደሞዙንም፣ ምግቡንም እንደስራው ሰጡት። ደግሞ ከወዲያ አገር ፖስታ ሲመጣ ስማቸው እንዳይጠፋ በያሉበት አገርም ለመስደድ ስማቸውን አፅፈነዋል..." የግራዝማች ዮሴፍ ማስተወሻ ብዙ ነው።
ይልቅዬ ሁልጊዜ አንጀቴን የሚበላ ታሪክ አለ፣ እሱ ታወሰኝ። አንድ ቀን በአዲስ አበባ ጡሩምባ ተነፋ። "ከኢጣሊያ ደብዳቤ በፖስታ መጥቷልና የየራሳችሁን ወረቀት ከጊቢ እንድትወስዱ ተብሏል።" ይባላል።
"ጊቢ" ማለት ቤተ መንግሥት ነው።ይሄን ጊዜ ከጄኔራሉ እስከተራ ወታደሩ ድረስ በምንሊክ ቤተመንግሥት ይግተለተላል። ስሙን ከዝርዝር መሃል ካገኘ ታላቅ ደስታ ነው... ደብዳቤውንም ሲቀበል በደስተና በሲቃ ነው።
ያን ቀን ቤተመንግሥቱ ተሸበረ። አንድ ወጣት ምርኮኛ ደብዳቤውን ተቀብሎ ሲያበቃ እዚያው አንብቦ እዚያው ይንፈቀፈቅ ጀመር። በቃ እንደሕፃን ልጅ ሆነ። ህቅ ስቅ እያለ አንጀቱ እንኪንሰፈሰፍ ድረስ አለቀሰ...
ምንሊክ ይሄን ነገር ሰምተው ወጣቱን የጣሊያ ወታደር አስጠሩት። አስጠርተውትም ያለቅሳል። የጣሊያን አፍ የሚያውቁት እነ ግራዝማች ዮሴፍ አስለቃሹን ደብዳቤ እንዲያነቡ ታዘዙ። እንዲህ ይላል..
የምወድህ ትንሹ ልጄ አሁን የት እንዳለህ አላውቅም። ትንሹ የሮማ ወታደር የምወድህ ልጄ... ሞትህን ባውቅ እንደሌሎቹ እናቶች አልቅሼ ይወጣልኝ ነበር። አሁን ግን ቀንም ለሊትም አለቅሳለሁ። አሁን የት እንደወደቅክ አላውቅም ልጄ። ከአፌ እየነጠልኩ ያሳደኩህ ልጄ፣ አሁን ምን እንደምትበላ አላውቅም... እንደምወድህ ታውቃለህ። እናም በሕይወት እስካገኝህ ድረስ ውሎዬ በቅድስተ ማርያም ቤተክርስቲያን ነው። ለእምዬ ማርያምም አንዳንድ ሻማ በየቀኑ እያበራሁ ስለቴን እንድትሞላልኝ እፀልያለሁ። እስኪ አንተም ባለህበት ፀልይ። ደግሞም እንደምንም ብለህ ኑር፣ አይዞህ ፀሎታችን ነፃ ያወጣሃል። የምወድህ ልጄ ፀሎቴም ለቅሶዬም ባክኖ አይቀርም። አንተም ብትሆነ እንደምትናፍቀኝ አውቃለሁ..." አንዳንድ መኳንንቶች ሳያስቡ አለቀሱ... ልጁ እንደሆነ አልቅሶ ጨርሷል።
ምንሊክ ግን አሉ፣ ከዛሬ ጀምሮ በነፃ አሰናብቼአለሁ። የእናትህ እንባ አማለደህ..." አስፈላጊውን በቅሎና ስንቅ ሰጥተውት የይለፍ ጦማር፣ ደግሞም ለእናቱ የሚሰጥ ደብዳቤ ይዞ በሃዘን ወደምትናጠው ሮማ ሄደ። እናቱም ቅድስተ ማርያም ቤተክርስቲያን ሻማ አብርተው እየፀለዩ ነበር...
እናም በምርኮኞች ታሪክ ነፃ የተለቀቀው ይሄ ልጅ ብቻ ነው። የተቀሩት አዲሳባ ነው ያሉ። ወጋችን ሳምንት ይቀጥላል። በነገርዎ ላይ ይህ ወደ እናቱ የተላከ ጣልያን በአዲስ አበባ ሳለ ጥሬ ስጋ መብላትና ጠጅ መጠጣት ለምዶ ነበር። እንደው ነገሩን ካልረሳነው ሳምንት ወይም በሌላ ሳምንት ወጋችን መቀጠሉ እውን ነው።
ምንሊክ ሕያው ይሆን... አዲዮስ ክሪስፒ!!

ምንጭ፡


ከፊያሜታ ነሐሴ 8 ቀን 1990

User avatar
zeru
Leader
Leader
Posts: 952
Joined: 19 Aug 2009 17:01
Contact:

RAS ALULA THE ABYSSINIAN

Unread post by zeru » 01 Mar 2010 16:21

RAS ALULA THE ABYSSINIAN

The New York Times
April 12 1887

From The Paul Mall Gazette

The great Abyssinian chief Ras Alula is at present a person of much interest to the Italians, and the Riforma is publishing a sketch of his life, in the course of which it is stated that he is the son of Abyssinian peasants. He was born about 45 years ago in the village of Pamaka, near Mekalle, and served for many years as groom under the Negus Ras Area. Later on he became Master of the Wardrobe at Court, and married the daughter of Ras Area, who died not long after the marriage. He then rose to the rank of Chamberlain, and was finally made Governor of Tigre, with the title of Ras.

Ras Alula is of middle height, has a chocolate-colored skin and a thin face, but it is otherwise rather stout. He never laughs, talks slowly, polite to strangers, but haughty to inferiors. His orders are given only once. If they are not executed, he horsewhips his servants. As a rule he wears a white cotton shirt and trousers. A red fez covers his close-cut hair. On special occasions, he wears a red silk shirt, the robe of the Governor. He is an excellent horseman, and it will be difficult to find an Abyssinian who bears the hardships of traveling better than he. He accompanies the Negus barefooted on all his tours, and never show a sign of fatigue. Having had no education, he can neither read nor write, but is very intelligent and cunning, but pious and superstitious withal. His avarice is extreme; he takes everywhere and gives nowhere. Wherever he goes he takes everything he can lay hold of. On his marches he is accompanied by his servants, who carry his wine, made of honey. Ras Alula is fond of women, but tries to conceal that fact. One of the many Abyssinian poems in his honor runs thus:

"He is as fair as angel
And strong as a lion,
Swift-footed as a leopard,
Sly as a fox,
Wise as Solomon,
Generous as a King,
Is most valiant of all."

The King has promised him the crown of Kassala, if he can earn it. Eight generals fight under him. His daughter is a good and beautiful woman, who has protected Count Salimbeni and his companion, and it is due to her influence that they have not been killed.

http://query.nytimes.com/gst/abstract.h ... 94669FD7CF

Post Reply

Return to “Ethio Art and Culture..ኢትዮ ጥበብ ፤ስነ ጽሁፍ ፤”