የወለላዬ ግጥሞች

ግጥሞች፣ታሪኮች፣ፎቶዎች፣ሙዚቃዎች
Poems,Short stories, graphics,pictures,musics,Technology
Post Reply
ኦሽንoc
Leader
Leader
Posts: 1129
Joined: 07 Aug 2009 14:20
Contact:

የወለላዬ ግጥሞች

Unread post by ኦሽንoc » 23 Feb 2010 10:38

እሳቱን እናጥፋ


ተዛምቶ በሃገር እያደረ ሰፋ
ጠብሶ ሳይጨርሰን እሳቱን እናጥፋ
ጠንክሯል እሳቱ በርትቷል ቃጠሎ
ማጥፋት ይገባዋል ስው ሁለ ሆ ብሎ
ከጨማመርንበት እሳቱ ላይ ቅጠል
ነደን እናልቃሇን አንበቃም ሇትግል
በወገን ተካፍሇን እኛው ስንዋጋ
ወያኔ ተረሳ ህዝቡ ተዘነጋ
ባለቅኔው በፊት ቀድመው ሲናገሩ
ብለውን ነበረ ባንድነት አብሩ
ካልሆነም ጨርሶ ወይ ተሰባበሩ
ስለዚህ ይሄንን ወሬ ቀመስ እሳት
እንዳንበታተን ይገባናል ማጥፋት
አይጎዳም ይጠቅማል ቀርቦ መነጋገር
መለወጥ አለብን ጥላቻን በፍቅር
እሷ/እኮ እሱ እኮ አሁን መባባሉ
ከጉዳት በስተቀር አይጠቅመንም ቃሉ
እንግዲህ ለሃገር ለወገን በማሰብ
ባንድነት ጥላ ስር አስብን መሰብሰብ
ካንዱ ቤት አንዱ ቤት ዘለን እንዶ ጦጣ
ጸቡን አባብሰን ለኳኩሰን አንውጣ
በዚሁ ጉዳይ ላይ ሁለም ይረባረብ
በመጥፎ ጥላቻ አገር አይለብለብ
ጸቡ ከዚህ በላይ እንዳሄድም ገፍቶ
አንተም ተው አንተም ተው ብሎ ሽምጋይ ገብቶ
በእምነት ደረጃም ወይ ቄሱ ገዝቶ
ከዚህ ከከበደም ታቦት ይዞ ወጥቶ
ሰላም እንዲሰፍን ጸብ ጥላቻ እንዲርቅ
ከጥፋት ያድነን ይገላግለን በእርቅ
አለዛ ወያኔ አርማችንን ገፎ
መውሰዱ ሳያንሰው ከዚህ በላይ አልፎ
መጠቀሚያ አድርጎ የኛን መሇያየት
አይቀርም ማምጣቱ መሪዎች ላይ ጥቃት
በነደብሪቱና በጓንጉል በአሽኔ
ባሽብር በግዛው አሳበን በአንቶኔ
ነገር ስናራግብ እኛ ስንፋተግ
ለወያኔ መንግስት ሆኗል የሞቀ ሰርግ
እንዳልፈው እንኳን አብሮ ሇመቃወም
ይሄው ተለያይተን እያጣን ነው አቅም
የነአስካለ ወገን የዱባለ ሆኗል
ጥርጥር የለውም ከገሌ ጋር ቆሟል
ብለን ስንፋተግ እኛው ስንናከስ
ላጭቶ ይጎርሰናል አይምረንም መሇስ
ያንግዜ በለቅሶ ባዘን ከመታረቅ
አፍጦ እያየነው ሞትን ከመጠበቅ
ያቀጣጠልነውን ይሄን የጸብ እሳት
ለራሳችን ስንል በቶሎ በማጥፋት
ባንድነት እናቁም ነገር በማቀዝቀዝ
ጸቡን እንፍታና እንደፊቱ እንጓዝ
መቼም ውሎ አያድር በኛ ጓዳ ፍቅር
ደግሞ ካስካለ ጋር ዱባለ ሲቃቃር
ወልደየስ ከገብሬ ሲለይ በመናናቅ
እምን ቦታ ይሆን እኛ ምንወሸቅ
ያንግዜ የማነን የጓንጉል የጥዱ
አቅጣጫ ሲቀይር ሲበተን ሴት ወንዱ
ማንን ይሆን ያኔ ከበን ምናዋልድ
መቼም የኛ ነገር የምንሆነው አይገድ
ስለዚህ ከመጪው አስችጋሪ ጉዳይ
መዳን እንድንችል በመሆን አንድ ላይ
ይሄንን ነበልባል ወሬ ጨመር እሳት
ከመካከላችን ይገባናል ማጥፋት


እሳቱን እናጥፋ
ከወለላዬ

ኦሽንoc
Leader
Leader
Posts: 1129
Joined: 07 Aug 2009 14:20
Contact:

Re: የወለላዬ ግጥሞች

Unread post by ኦሽንoc » 23 Feb 2010 10:56

የኛ ሰው ሊቁ

የኛ ሰው ሊቁ ...
አባ እረቂቁ ...
አጣሞ ማየት ነገር መጠርጠር
ትልቅ ዕውቀት ነው ብሎ በመቁጠር
የነገርከውን ያፍህን ትቶ
ያጣምመዋል ሌላ ደርቶ
ያላወቀውን ከሰው መረዳት
እንብየው ብሏል ሆኖበት ውርደት
ቢአጠፋም እንኳን የይቅርታ ቃል
ካፉ ሊይወጣ በልቡ ምሏል
እንደው በከንቱ ሰው በመጠርጠር
መላ የሌለው ይፈጥራል ሽብር
ይችልበታል የጠላ መምሰሌ
የምትለውን ካንተ ሊሰልል
ነገሩን ወዶ እሱ ሲፈራ
አንተን ይልካል እንደሙከራ
የኛ ሰው ሉቁ ...
አባ እረቂቁ ...
ገራገር መስል ጨዋ ሳቂታ
የልቡን ሰርቶ ይገባል ማታ
አጥፊ እንዳይባል ሰው እንዳይጠላው
ሰበብ አሳቦ ሁላ ጋባዥ ነው
ባማረ ልባስ አካለን ከቶ
ጨዋ በመምሰል ያድራል ቀምቶ
የዋህ ነህ ብሎ ግምት ከሰጠህ
ያመሻል ቀኑን ወሬ ሲአቅምህ
የሚሰራውን ውስጡ ሸጉጦ
ላለማስቀየም ቃላት አጣፍጦ
ፊት ለፊት ባፉ ቂቤ እየቀባ
ይሰካብሃል ጩቤ በጀርባ
ሊገር ለህዝቡ ሳይኖረው ደንታ
በደሉ ብሎ ይሆናል ዱታ
በአቋራጭ ገብቶ ስልጣን ሊጨብጥ
ሲጋብዝ ያድራል ያለውን ሲሰጥ
ይሄ ሞሽላቃ ብሎ እያማልህ
እጁን ይሰዳል አንተን ሊሰርቅህ
የኛ ሰው ሊቁ ...
አባ እረቂቁ ...
ሚስት ሊአገባ ሲአስብ ወደፊት
ቀድሞ ይይዛሌ የነገር አባት
ቀኑ ሲከፋ ሞቱ ሲቃረብ
ጠላቱ እሚለው መኖሩን ሲያስብ
መቼ ሊተወው እንዲህ በቀሊል
ለልጁ አውርሶ ቂሙን ይተዋል
ይወዳሌ ተረት ምሳሌ መጥቀስ
አልክ እንዳይባሌ እንዳይወቀስ
ትሰማዋለህ በሁሉ ሲያዝን
ጎዳኝ እያለ ይሄ ሰው ማመን
አርቆ አሳቢ ስለሆነ ሊቅ
ያስገርምሃል ላገር ሲጨነቅ
በዛሬ ጊዜ እግርን መሰብሰብ
ይጠቅማል ይላል ለመራቅ ሲያስብ
እንዴት ይቻላል እሱን ለመምከር
ሁለን አዋቂ ለራሱ ምሁር
ማየት አይሻም የደሃን እንባ
እያስለቀሰ እሱ በጀርባ
ጎርጊስን ካልኩኝ ባባቴ ከማልኩ
ፍንክች የለችም አለቀ ጨረስኩ
ብሎ ይልሃል አንዳንዴ ደግሞ
ሲያጠፋፋብህ ነገሩን ቀድሞ
የኛ ሰው ሉቁ ...
አባ እረቂቁ ...
በፌዝ ፈገግታ በውሸት ሳቁ
ሸፋፍኖ ይዞ እራሱን ሳይገልጥ
እመሃል ሆኖ ይኖራል ሲያለምጥ
ወሬ ከሰማ ጆሮውን ጥሎ
የራሱን ከቶ ትንሽ አክሎ
ላቀደው ነገር አርጎ እንዲስማማ
ያዘጋጃታል ፈጥሮ ቅመማ
መስሎ እየታየው ሁለ ሰው ደደብ
ይታዘበኛል ብሎ ሳያስብ
እሱው ያለውን እራሱ ፈጥሮ
በወሬ ብዛት በሌላ ሽሮ
አንዱን ካንዱ ጋር አደበላልቆ
አወታትቦብህ ይሄዳል ስቆ
የኛ ሰው ሊቁ ...
አባ እረቂቁ ...
ነገር አዋቂው ሊቀ ጠበብቱ
ባገሩ ጉዳይ ባለው በወቅቱ
የረቀቀ ነው በፖለቲካ
የትም አይገኝ እሱን ሚተካ
አስር በማውራት በመዘላበድ
የተቃውሞውን ይዘጋል መንገድ
ሌላው አዋቂ ሥልጣን ጨብጦ
እላይ ከወጣ ደረጃ እረግጦ
ዘላለም ገዢ ሆኖ ሊጣበቅ
መሃላ አለበት ሊይነቃነቅ
በሥልጣኑ ላይ ሥልጣን ደራርቦ
የሀገር ሀብትን በእጁ ሰብስቦ
እየገደለ አስሮ ጠፍሮ
እንደሚታየው ይኖራል ከብሮ
የገንዘብ ፍቅሩ የሥልጣኑ ጥም
ይዘልቃል ይዞት እስከራሱ ደም
ይሄን ይመስላል የኛ ሰው ሊቁ
ዘመን ያፈራው አባ እረቂቁ

ጥር 21 ቀን 2000 ዓ.ም. - ስዊድን
(January 30, 2008 – Sweden)
የኛ ሰው ሉቁ ...
ከወለላዬ

ኦሽንoc
Leader
Leader
Posts: 1129
Joined: 07 Aug 2009 14:20
Contact:

Re: የወለላዬ ግጥሞች

Unread post by ኦሽንoc » 23 Feb 2010 17:53

ለጥበብ ሰው እዘኑለት
(ለድምፃዊ ታምራት ሞላ እና ለጥበብ ሰዎች)

ዝነኛ ነው ድምፀ መልካም
አቤት ደግሞ ሲጽፍ ግጥም
ሰዓሊ ነው የረቀቀ
ባገር ዙሪያ የታወቀ
ዯራሲ ነው ስመጥሩ
የገነነ በብዕሩ
ታዋቂ ነው ባለቅኔ
አትበለኝ ይቅር ለኔ
ከዛ ጥበብ በስተጀርባ
ተደብቆ እያደባ
ህዝብ ሳያውቅ ሰው ሳይሰማ
የሚጠብሰው እንደሳማ
አለው እጅግ ክፉ ጠሊት
ለጥበብ ሰው እዘኑለት
ካለው ዝና ተነስታችሁ
ደስተኛ ነው እያላችሁ
አትመኑት እባካችሁ
ችግር ቤቱ ዓይን አፍጦ
ተቀምጧል ተዘርፍጦ
አቤት ለዛው ጨዋታ ሲያውቅ
አቤት ድምጹ ሠርግ ሲያሞቅ
አቤት ቃላት አወጣጡ
አይ ሠላምታ አሰጣጡ
አቤት መድረክ ሲቆጣጠር
ደግሞ መልኩ ገጹ ሲያምር
ሽቅርቅር ነው ባለባበስ
ማንም የለ ከሱ እሚደርስ
ከገጠመ ከጻፈማ
ለሁሉ ነው የሚስማማ
የሚል ዝና በማላበስ
ለችግሩ ቀድመን ሳንደርስ
ያንን ስሙን ተሸክሞ
ስንቱ ቀረ ሳይድን ታሞ
ሃቅ ሲያምጥ ጥበብ ሲጭር
ማጣት ገብቶ እጎጆው ስር
እላዩ ላይ አድሮ ውል
ጠርቦ ጥሎት አጥመልምሎ
ተሰቃይቶ ያ ወንድሜ
ሀብት ነፍጎት ተርፎት ዕድሜ
በእጁ ሳይተርፍ ትንሽ ቅሪት
ፍግም ሲል በባድ ቤት
ተመልክቷል ሁለት ዓይኔ
አትንገሩኝ የሱን ለኔ
ለኛ ደስታ ጮማ እንዲቆርጥ
አለልኩ ግተን መጠጥ
አስጨፍረን አስደንሰን
ለለት ውሎ ሆዱን ሞልተን
ሸኝተነው በጭብጨባ
ባድ ኪሱን እየገባ
ቀን ሲጨምር ወር ሲገፋ
ችግር ውጦት አጥቶ ተስፋ
እዛ እሮጦ እዛ በሮ
ቀን ተጠብሶ ሲመሽ አሮ
ይቆይና ሲይዝ አልጋ
ሳንሰጠው ምንም ዋጋ
ጥልን ያልፋል ማቆ ማቆ
ጠያቂ አጥቶ ሁሉን ናፍቆ
ይሄ ጉዳይ ይሄ ድርጊት
እንደመጣ ባሁን ሰዓት
አድርጋችሁ አትንገሩኝ
ድሮም አለ አውቃለሁኝ
አይቻለሁ ፊትም ከጥንት
ደራሲውን ችግር ውጦት
አይቻለሁ የጥበብ ሰው
በባድ ቤት ሞት ሲልሰው
አይቻለሁ ፊቱ ቆሜ
ተቆራምዶ ያ ወንድሜ
እኔን ተዉኝ አትንገሩኝ
በዚህ ጉዳይ ቤተኛ ነኝ
ያቺ ቆንጆ ሙዚቀኛ
ያ ሸበቶ ጋዜጠኛ
ብዙዎቹ ጥበበኞች
የተባለ ሕይወት ኮትኳች
በዛን ጊዜ በሰዓቱ
እንዴት ሆነው እንደሞቱ
አይቻለሁ ምስክር ነኝ
እባካችሁ አታንሱብኝ
ያሳለፉት ውጣ ውረድ
እንደሆነ እጅግ ከባድ
ተመሌክቷል ሁለት ዓይኔ
አትንገሩኝ ያንን ለኔ
እናንተ ግን አደራችሁ
የጻፈውን አንብባችሁ
ድምጹን ከሩቅ አዳምጣችሁ
እንደደላው እንዳትቆጥሩት
ለጥበብ ሰው እዘኑሉት
ያሁኑ እንኳን ያውቅበታል
ጊዜው ጥሩ ሆኖለታል
በአስዮ በቤላማ
በቀን እና በጭለማ
በእቴሜቴ በአቦጊዲ
ቀሎለታል የኑሮ ዕዲ
የድሮው ግን ተንከራቶ
ለአርባ ዓመታት ለፍቶ ለፍቶ
ይሄው ቀረ ሁለን አጥቶ
እሱ ለሰው ሲያጨበጭብ
ሰዉ ለሱ ሲያጨበጭብ
በኡኡታ በቸብቸብ
በብርቱካን በአልማዜ
በትዝታ ውዝዋዜ
በእሹሩሩ በኔ ፍቅር
ሽቅብ ቁልቁል ሲውተረተር
ለፋሲካ ለእንቁጣጣሽ
እዛው ውሎ እዛው ሲያመሽ
ለልደት ቀን ለድል በዓል
ወይ ሲያቅራራ ወይ ሲሸልል
ይውልና ዋቶ ዋቶ
ድፍት ይላል ጎጆው ገብቶ
ደራሲውም ገንዘብ አጥቶ
ማሣተሚያ ዕዳ ገብቶ
ካንዱ ወስዶ ላንዱ ሰጥቶ
በአንድ ክፍል በጠባብ ቤት
ተጨናንቆ በመጻሕፍት
በሷው ውሎ በሷው አድሮ
ይገኛታል እዛው ከሮ
ይሄንን ሰው አስጊጣችሁ
እሰማይ ላይ አውጥታችሁ
ታዋቂ ነው ድምፀ መልካም
አይ ችሎታው ሲጽፍ ግጥም
ሰዓሊ ነው የረቀቀ
ባገር ዙሪያ የታወቀ
ደራሲ ነው ስመጥሩ
የገነነ በብዕሩ
ዝነኛ ነው ባለቅኔ
አትበለኝ ይቅር ለኔ
ከጥበቡ በስተጀርባ
ተደብቆ እያደባ
ህዝብ ሳያውቅ ሰው ሳይሰማ
የሚጠብሰው እንደሳማ
አለው እጅግ ክፉ ጠላት
ለጥበብ ሰው እዘኑለት


ሚያዝያ 7 ቀን 2000 ዓ.ም. - ስዊዴን
15 April 2008 - Sweden

ኦሽንoc
Leader
Leader
Posts: 1129
Joined: 07 Aug 2009 14:20
Contact:

Re: የወለላዬ ግጥሞች

Unread post by ኦሽንoc » 23 Feb 2010 23:11


ለአርቲስት አለባቸው ተካ ሙት አመት መታሰቢያ

------------- የቀረበ -------------


አቤት መገስገሱ ቀንና ወራቱ
ይሄው ከተለየን አለቤም አመቱ
ጅምሩን ሳይጨርስ ጥበቡን ሳይቋጨው
ይሄ ደፋሩ ሞት ከርስ አይሞሌ ቀጨው
ቤቷ ቦዶ ሆነ በራፍዋ ተዘጋ
አጋጥሟት ከረመ ጥበብም አደጋ
ጎዳት እጅግ አርጎ አያ ከሞት አትርፍ
አጣች በሱ ምትክ ቦታው የሚሰለፍ
ደካማን ፈልጎ አስታውሶ እሚአመጣ
እሱ ብቻ ነበር ጭራሽ መተኪያ አጣ
በፈጣሪ ስራ በገዛ ፍጥረቱ
ባይመስልብኝ ድፍረት እጣልቃ መግባቱ
ለሚንዛዛው እድሜ ተርፎ ለሚቀረው
በምን ጥፋት በደል አለቤን ነሳኸው
ብዬ ባልኩት ነበር በግላጭ ባገኘው
ብቻ ምን ያደርጋል ከንቱ ነው ቢወራ
ማን ይከራከራል ደፍሮ ከሱ ጋራ
ሆኖም ከደጋጎች ከጻድቃኖች ተርታ
ነብሱን እንዲያኖራት ሰጥቶ ከበሬታ
እንለምናለን በአንድነት ለጌታ ::

እለተ ሞቱ እንደተሰማ


------- አያ ከሞት አትርፍ -------

አለቤ ሞተ አሉኝ አለባቸው ተካ
የጥሩ ፍሬ ዛፍ የቁም ነገር ዋርካ
ሀዘን ስልጣን ያዘ ደስታን አሽቀንጥሮ
ቀልድም ተቀበረ ካለቤ ጋር አብሮ
ቁም ነገር ቤት አጣ እሜዳ ላይ ቀረ
ደግነትም በቃው ጎኑ ተሰበረ
ሰብስቦ አቃፊያቸው አለቤ ነበረ
አለቤ ደራሹ አያ ከሞት አትርፍ
ጅማ ስትጠበቅ ምን አገኘህ ዮሴፍ

ወለላዬ

ኦሽንoc
Leader
Leader
Posts: 1129
Joined: 07 Aug 2009 14:20
Contact:

Re: የወለላዬ ግጥሞች

Unread post by ኦሽንoc » 02 Mar 2010 14:00

ጀግና አይደለንም ወይ?መቼም የሚያቃጥል የሚያጨስ አይጠፋ

አንዱ ትናንትና እሰው ፊት በይፋ

በጀግንነታችን እንደሚጠራጠር

ቃላት አሳምሮ ሰማሁኝ ሲናገር”ለሦሰት ሺህ ዘመን ድንቁርና ማርኮን

ከክፉ አስተዳደር መላቀቅ አቅቶን

ኋላ ቀርነትን ረሃብ ሳንዋጋ

ጀግና ነን ብትሉኝ አልሰጠውም ዋጋ

መሬቱን ጠብቀን ብንይዝም ከጠላት

እንደልብ በልተን ካላጋሳንበት

እላዩ ገንብተን ካላስተማርንበት

ወንዞቹን ለልማት እንዲውሉ አድረገን

ገቢ ካላመጣን በብዛት አምርተን

ምኑን ጨብጠን ነው የምንባል ጀግና

አልሸትህ ብሎኛል የወኔያችን ቃና

ነጭን ብናስወጣም አባረን ከሀገር

ሥልጣን የጨበጠ እኛን መሳይ ጥቁር

በዘር ተደራጅቶ ተነስቶ በእብሪት

አሳጥቶ ነፍጎን መብትና ነፃነት

በቁም እየሞትን ምንድነው ጀግንነት

ማፍረጥረጥ አለብን ይሄንን ገበና

አገር ወዳድ እንጂ አይደለንም ጀግና

የትም አያደርስም በከንቱ መጎረር

ጀግንነታችንን እናሳይ በተግባር

እሱ እራሱ መሪው በፍርሃት ታምቆ

ሲወጣ ሲገባ ተጠቦ ተጨንቆ

ህዝቡን እያዞረ እሱ ባለፈበት

እምኑ ላይ ይሆን የኛ ሰው ጀግንነት

ዘመኑ ሠልጥኖ ባይኖር ቴሌቭዥን

ባላወቅነው ነበር ገጽታውን የሱን

የቀድሞ ሠራዊት የመንግሥት አመራር

እንደዛ ሲጠፋ በአንድ ቀን አዳር

ጀግና ነን ማለቱ አይገባኝም ጭራሽ

ፍራቻም እንዳለች ጠፍቶ ነው አስታዋሽ”

በማለት አንስቶ ፈጥሮብን ጭቅጭቅ

አመሸ ሲያጨሰን ልባችንን ሲያደርቅ

አያትና አባቴ ከጠላት ተናንቀው

ላገራቸው ክብር እጦር ሜዳ ወድቀው

እኔ በሶማሌ የቀድሞ ወረራ

በሰሜኑ ክፍል በኋላም ኤርትራ

በፈጸምኩት ጀብዱ ስሜ የተጠራ

መሆኔን ዘንግቶ ሲናገር እኔ ፊት

ንቀት አይደለም ወይ ዓይን ያወጣ ድፍረት

ግድ የለም ይቅርብን እኛስ እንረሳ

ላገሩ የሞተው የቋራው አንበሣ

እነ ዘርዓይድረስ እነዛ እነ አብዲሳ

እነ አሞራው ውብ ነህ እነ አበበ አረጋይ

ጠላትን ያሰኙት እጦር ሜዳ ዋይ ዋይ

ኃይለማርያም ማሞ የጦሩ ገበሬ

ፈረሱን እንደሰው ያስታጠቁት ሱሬ

አሉላ አባ ነጋ እነ እራስ ጎበና

ምን እንበላቸው ካልተባሉ ጀግና

ቆራጡስ አርበኛ ያ በላይ ዘለቀ

ምን ታሪክ ሊኖር ነው ሥራው ከተናቀ

ያሁኑ የቅርቡ ለገሠ ተፈራ

በጀት ያነደደው የጠላትን ጎራ

የፈጸመው ጀብዱ ምን ይባል ሲወራ

ወራሪን ተናንቀው በየጦሩ ሜዳ

ተቀብረው የቀሩት የቆጠሩት ፍዳ

ለዲሞክራሲና ለህዝብ እኩልነት

ተሰልፈው ወጥተው ሕይወት የገበሩት

ጀግና አይደሉም ካልን ጭራሽ ከተረሱ

ምን አይነት ሰው ይሆን ታሪክ ሠሪ ለሱ

እንደ ወሬውማ እንደሱ አነጋገር

ኖረች ማለቱ ነው በታምር ይቺ ሀገር

ያውም ተምሬአለሁ ነኝ የተመራመርኩ

የሚል በመሆኑ ተናደድኩም አፈረኩ

በሌላው ግድ የለም ጨዋታ ቢያመጣ

ይሄ ግን አጉል ነው ያስከትላል ቁጣ

በዚህ ተናድጄ ስጨስ በማደሬ

ደሜ ሰማይ ወጣ ከፍ አለ ስኳሬ

በሉ ተናገሩ ቁርጡን በዚህ ጉዳይ

ዓለም ያደነቀን ጀግና አይደለንም ወይ?


ከወለላዬ
welelaye2@yahoo.com

Post Reply

Return to “Ethio Art and Culture..ኢትዮ ጥበብ ፤ስነ ጽሁፍ ፤”