Page 2 of 2

Re: ቀ ልዶች

Posted: 21 May 2011 21:20
by zeru
ልጅ ለመጀመርያ ቀን ወያላነት ሲሰራ ውሎ ሌሊት በእንቅልፍ ልቡ “ፒያሳ..ፒያሳ..ፒያሳ” እያለ ሲጮህ ወላጆቹን ከእንቅልፍ ቀሰቀሳቸው።
እናት ካልጋቸው ተነስተው ፣ ጸጉሩን ሲያሹለት ቅዠቱን ትቶ ዝም ብሎ ተኛ።
ትንሽ ቆይቶ “አምባሳደር..አምባሳደር..አምባሳደር” እያለ ሲጮህ ፤ አሁንም እናት እየተነጫነጩ ተነስተው ትራሱን ሲያስተካክሉለት፣ ዝም ብሎ ተኛ።
ከ 5 ደቂቃ በኋላ አሁንም በቅዠት “ወሎሰፈር..ወሎሰፈር..ወሎሰፈር” ሲል ወደ ባላቸው ዞር ብለው “ምን ላድርግ? ዝም ብሎ ይቃዣል እኮ” ሲሉ ፣
ባልየው “ተይው ባክሽ! ታክሲው ሲሞላ ራሱ ያቆማል”

Re: ቀ ልዶች

Posted: 21 May 2011 21:23
by zeru
የ 36 አመቷ እርጉዝ እናት በወጣትነት ከወለደችው ከ20 አመት ልጇ ጋር በመኪና ወደ ናዝሬት ስትሄድ መኪናው ይገለበጥና ነፍሷን እንደሳተች ሆስፒታል ትገባለች።
ዶክተሩ መንታ ሴቶች በቀዶ ጥገና ያዋልዳታል። በሳምንቱ ነፍሷን እንዳወቀች “ልጆቼስ?” ብላ ስትጠይቅ ፤ ሐኪሙ “እንኳን ደስ አለሽ! መንታ ሴቶች ተገላግለሻል”
ይላታል ። “ጤንነታቸውስ?” ስትል ... “በጣም ጤነኞች ናቸው! ደግሞ ሲያማምሩ! መልአክ ነው የሚመስሉት” አለና ጨመር አድርጎ “ስማቸውን ደግሞ ወንድ ልጅሽ ነው
ያወጣላቸው ፤ የትውልድ መረጃቸው ላይ መዝግበነዋል” ሲላት... “ወይኔ ጉዴ! ለምን ስም እንዲያወጣ ፈቀዳችሁለት? እሱ እኮ ጤነኛ አይደለም! አለችና ቀጠል አድርጋ
“ለመሆኑ ምን ብሎ ነው የሰየማቸው?” ስትል ...ዶ/ሩ፡ “ 1 ኛዋን «እቴነሽ» ነው ያላት አለ... “ውይ የኔ እናአአ..አአት! ቆንጆ ስም ነው! 2ኛዋንስ ማን አላት?”...
«አንቺም-እቴነሽ»

Re: ቀ ልዶች

Posted: 21 May 2011 21:25
by zeru
አንድ ሰካራም ለሚስቱ ይደውልና “መኪናዬን መርካቶ አቁሜ ፣ ሌቦቹ አወላልቀው ወሰዱት” አላት... “ምን ማለትህ ነው?”..
“በቃ ምንም አልተረፋቸውም! መሪው ፣ ሬዲዮኑ ፣ ምን አለፋሽ? ፊት ለፊት ያለው ቦርዱን ጭምር ነው የዘረፉኝ።
እነዚህ ቅማላሞች! ፍሬኑና የቤንዚን መስጫው እንኳን አልቀራቸውም”...
“እሰሰሰሰይ! ደግ አደረጉ! እየሰከሩ ማምሸት ይቅርብህ ብዬህ አልነበረም!” ስትል ፤ ከት ብሎ መሳቅ ጀመረ። “ምን ያስቅሃል?”...
“ይቅርታ! ለካ በኋላ በር ገብቼ ነው”