የምስጋና ቀን ምስጋና ለናፈቀው መንግስታችን

User avatar
zeru
Leader
Leader
Posts: 952
Joined: 19 Aug 2009 17:01
Contact:

የምስጋና ቀን ምስጋና ለናፈቀው መንግስታችን

Unread post by zeru » 07 Aug 2014 16:43


ፈረንጆች በየአመቱ Thanks Giving day(የምስጋና ቀን) በሚል በዓል አሳበው ምስጋና ያቀርባሉ፣ እኛም መልካም ነገርን መኮረጅ ተገቢ ነውና ምስጋና የናፈቀው መንግስታችንን ለማሞካሸት ይሄንን ለጠፍን
<¤¤¤>
ሰፈራችን መብራት መጥፋት ቀና ብዬ የጨረቃን ውበት እንዳስተውል እና እንዳደንቅ መልካም አጋጣሚ የፈጠረበት ሁኔታ ነው ያለው::
ኤልፓ በዚህ ረገድ ከተማችን የቲሪ
ስት መናሀርያ እንድትሆን እያደረክ ስላለኸው ያለሰለሰ ጥረት ታላቅ ምስጋና ይገባሀል:: Bravo !
<¤¤¤>
ውሀና ፍሳሽ አገልግሎትም በ10 ቀን አንዴ በምትለቅልኝ ውሀ የተነሳ ለውሀ-ወለድ በሽታዎች የተጋለጥኩ ቢሆንም ለመታከም በሄድኩባቸው ሆስፒታሎች ያጋጠመኝ መስተንግዶ እና አቀባበል የጤና ሴክተሩ ያስመዘገበውን እመርታ እንድገነዘብ አስችሎኛልና ለአንተም ምስጋናዬ ይድረስህ
<¤¤¤>
ቴሌአችን ምንም እንኩአን አንዳንዶች ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ጋር ሲነፃፀር ለምትሰጠው አገልግሎት የምትጠይቀው ክፍያ ከፍተኛ ነው እያሉ ቢያሙህም እኔ በበኩሌ ካርድ ለመግዛት ከቤቴ- ሱቅ ከሱቅ ወደ ቤቴ በየቀኑ የማደርጋቸው እንቅስቃሴዎች የአካል ብቃቴን በመገንባት ጤናማ ዜጋ እንድሆን መንገድ ከፍተውልኛልና አመሰግናለሁ::Source: FacebookPost Reply

Return to “Jokes and Funny stuff ...ቀልዶች እና አዝናኝ ርዕሶች”