ፖሊሱና መፅሀፍ ቅዱሱ

User avatar
zeru
Leader
Leader
Posts: 952
Joined: 19 Aug 2009 17:01
Contact:

ፖሊሱና መፅሀፍ ቅዱሱ

Unread post by zeru » 11 Apr 2013 09:12

መቼ ለት ከታክሲ ስወርድ የኪስ ቦርሳዬን ጥዬ ስለወረድኩ
መታወቅያዬ እና መንጃ ፍቃዴ ተሰውረውብኝ ተቸግሬ ነው
የከረምኩት፡፡ አዲስ ለማውጣትም ስሄድ ከፖሊስ ጣብያ ማፃፍ
እንዳለብኝ ስለተነገረኝ ባቅራብያዬ ወደሚገኘው ፖሊስ ጣብያ

አመራሁ፡፡ ጣብያ ውስጥ ተፈትሼ ከገባሁ በኋላ መጀመርያ
ያገኘሁት የፖሊስ አባል ወንበሩን አውጥቶ ፀሀይ እየሞቀ
መፅሀፍ ቅዱስ ሲያነብ በማግኘቴ በጣም ነበር የገረመኝ፤ ደስም
አለኝ… በየጊዜው በክፉ ሲታሙ የምንሰማቸው የሀገራችን
ፖሊሶች አምላክን ቢጠጉልንማ መልካም ነው ብዬ ለራሴ
አሰብኩና ፤ የፖሊሱን የመፅሀፍ ቅዱስ እውቀት እግረመንገዴን
ልፈትን ፈለኩ፡፡ አቀርቅሮ ቅዱሱን መፅሀፍ ከሚያነበው ፖሊስ
ጠጋ አልኩና “ወንድሜ ለመሆኑ የአዳምን ልጅ፤ አቤልን ፤ ማን
እንደገደለው ታውቃለህ?” ብዬ የመጀመርያ ጥያቄዬን
አቀረብኩለት፡፡ ፖሊሱም ለአፍታም ቀና ሳይል በእጁ ዞር
እንድልለት ምልክት እየሰጠኝ “እኔ የት አውቅልሀለሁ፤ ሂድና
ሳጅን እያሱን ጠይቀው እሱ ነው የነብስግድያ መዝገቦችን
የሚከታተለው ብሎኝ እርፍ፡፡Source: Facebook

Post Reply

Return to “Jokes and Funny stuff ...ቀልዶች እና አዝናኝ ርዕሶች”