Page 1 of 1

VERY FUNNY AMHARIC JOKE.

Posted: 11 Mar 2010 16:52
by selam
ከአቶ ገላጋይ ዳኘው
አሜሪካን ለምትገኚው ከይሲዋ ባለቤቴ ለወ/ ፈለቀች በልሁ
ይድረስ ለጉደኛዋ ከይሲ የሰይጣን ቁራጭ ለሆንሺው ለፈለቀች፡- እዛ
ቁልቢ ገብርኤል አንቺን ያገኘሁበትን ቀን እየረገምኩ እሱ መልአኩ ግን
የስራሺን እንዲሰጥሽ ጠዋት ማታ ከመማፀኔም ሌላ ሳልሞት ያንቺን ጉድ
እንዲያሳየኝ ከድሬዳዋ ቁልቢ የእግር ጉዞ ለማድረግ ተስያለሁ፡፡
የአሜሪካንን አገር ግሪን ካርድ እንዳንቺ አገኛለሁ ብዬ በሌለኝ ደሜ
ሦስት ብልቃጥ ሙሉ ደም ለምርመራ ሰጥቼ እዚህ ግቢዬ ውስጥ
የተተከለውን የሣተላይት ዲሽ የሚያክል ጆሮ ያለው ዶክተሩ ልጅሽ የእኔ
ልጅ እንዳልሆነ ያው የአሜሪካን አምባሲ .ኤን.. በተባለው የደም
ምርመራ አረጋግጦ ጉድሽን አፈላው፡፡
ጭንቅላታም ልጅሽ መቼ በጤናው ከልጆቼ ሁሉ ተለይቶ ተፈጠረ፡፡
አሁንማ ልብ ብዬ ሳስበው የዛ የዘበኛዬን የውቃው ልጅ እንደሆነ
ገብቶኛል፡፡ መቼ ማእረግ ይወድልሻል፤ አንቺ ማእረገ ቢስ፤ በየሜዳው
ስትባልጊ ይኼው በአርባ ዓመቱ ጉድሽ እንደ / አልማዝ ያልተወቀጠ
ቡና ተንተከተከልሽ፡፡
ይኽን ጉድሽን አሜሪካን አምባሲ ከሰጠኝ ደብዳቤ ጋር ፎቶግራፍሽን
አያይዤ ጋዜጣ ላይ አወጣዋለሁ፡፡ ደግሞ አገር አለኝ፤ ቤት ንብረት አለኝ
ብለሽ እዚህ አገር እንኳን እስከነፍስሽ ሬሳሽ ዝር እንዳይል፡፡ ይኽን
ጉድሽን ለሀገር ለሠፈሩ፤ ለእድርሽ ሳይቀር ተናግሬ ቀባሪ አሳጣሻለሁ፡፡
እዛው ፈረንጅ አገር ሬሳሽን ያቃጥሉት፤ እንዲህ አንጀቴን
እንዳቃጠልሽኝ፡፡
ደግሞ ያንቺ ጉድ ማለቂያ ስለሌለው እነዚህን የቀሩትን ዘጠኙ
ልጆችሽን አሰልፌ ነገ በጠዋት አስመረምርልሻለሁ፡፡ አርባ ዓመት ሙሉ
ልጄ ነው ብዬ አሳድጌ፤ አስተምሬ፤ ፈረንጅ አገር ልኬ ለካስ የዘበኛዬ
የውቃው ልጅ ኖሯል? አንቺ ጉደኛ ብቻ እዚች አገር እግርሽን አንስተሸ
እንዳትመጪ! ብሞት እንኳን ቀብሬ ላይ እንዳትቆሚ ለንስሃ አባቴ
ኑዛዜዬን እናገራለሁ፡፡
የአባት የእናቴ አምላክ አንጀትሽን የእኔ አንጀት እንዳረረ ያሳርርሽ፡፡
አብረን እንቀበርበታለን ብዬ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን ያሰራሁትን መቃብር
ቤት መነኩሴ አስቀብርበታለሁ፡፡
ገላጋይ ዳኘው
አዲስ አበባ አሮጌው አውሮፕላን ማረፊያ
ነፍስሽን ያሳርፈውና! ከይሲ!
23 ጥር 22 .. ናፍቆት Iትዮጵያ
ጉድ ፈላ!”
በአልሣቤት ገበየሁ
2 ዓመት ቁጥር
በአልሣቤት ገበየሁ

የወ/ሮ ፈለቀች በልሁ የመልስ ደብዳቤ

Posted: 11 Mar 2010 16:54
by selam
የወ/ ፈለቀች በልሁ የመልስ ደብዳቤ
ይድረስ ለአቶ ገላጋይ፡-
እንደምታውቀው ወይም እንደሰማኽው የፈረንጁ አገር ኑሮ በጣም ቢዚ
ስላደረገኝ ጊዜ አጥቼ የደብዳቤህን መልስ በሁለት ቀን ከፋፍዬ ነው
የምፅፍልህ፡፡
የእኔ ወንድም ‹‹በሠፈሩት ቁና መሠፈር አይቀርም›› ወይም
በእንግሊዝኛው ‹‹ዋት ጎዝ አራውንድ ካምስ አራውንድ›› ሲባል
አልሰማኽም ወይ? ለነገሩ መች እንግሊዝኛ ታውቃለህ! ለመሆኑ
ያንተን ጉድ የማላውቅልህ መሰለህ ወይ? የገዛ ሠራተኛዬን ከሙሽራ
ቤት ሳልወጣ አስረግዘህ እድሜዬን ሙሉ አሣድጌ አረብ ሀገር የላኳት
ትርንጎ የማን ልጅ መሠለችህ? የኛ ጨዋ! ኡ!ኡ!!
ታዲያ እኔ ከውቃውዬ ዶክተሩን ልጄን ብወልደው ምን ይጠበስልህ?
ዘበኛ ቢሆን ታዲያ ሠርቶ መብላት ያስነውራል ወይ? አዚህ ሀገር ቢሆን
ኖሮ ሴኩሪቲ ነበር የሚባለው፡፡ እንግዲህ እርፍ በለው...አዎ ዶክተሩ!
ዶክተሩ ! ልጄ የውቃውዬ ነው፡፡ ለምን መስሎሃል ከልጆቹ ሁሉ ተለይቶ
በትምህርቱ ጂንየስ (ጎበዝ ማለት ነው) የሆነው?... አሜሪካን ኤምባሲ
መርምረው የደረሱበት ያንተ .ኤን.. ስለሌለበት ነው፡፡ እረፈው!!
ስለ .ኤን.. ደግሞ እኔ ፈሊ...ኦፕራ የምትባለዋ ሴትዮ በቴሌቭዥን
በደንብ አስረድታኛለች፡፡ እንግሊዝኛውን እንደሆን ለነወ/ ምንትዋብ
በየሆስፒታሉ አስተርጓሚ ነኝ፡፡ የቁልቢው ገብርኤል ለተበደለ
የሚፈርድ መልአክ ነውና ይኼው ለግሪን ካርድ ብለህ ሄደህ የአሜሪካን
መንግሥት ቀይ ካርድ ሰጠልኝ፡፡ እሱ ምን ይሳነዋል?
ከሁሉም ግን ስለ ልጄ ጆሮ ትልቅነት ያወራኽው አናዶኛል፡፡
የሳተላይት ዲሽ ቀርቶ ብረት ምጣድ ቢያክል ጆሮው በሱ ሰምቶ አይደል
እንዴ ይኼው ዛሬ ዶክተር ሆኖ እነ / ምንትዋብ እስኪቀኑ ድረስ
በጥቁር ማርቼዲስ እያንፈላሰሰ ቤተክርስቲያን የሚወስደኝ? ብቻ
ውቃውዬ ይህንን ሳያይ ያንተን ፔጆ 504 በውድቅት ለሊት እየተነሳ
ሲፈገፍግ ብርድ አጠናፍሮት ሞተልህ፡፡
ደግሞ ቤት አለኝ፤ ሀገር አለኝ ብለሽ እንዳትመጪ ላልከው ንጉሡ
ባራክ ኦባማ ንግሥቲቱ ሚሽል ኦባማ ይኑሩልኝ፤ ደልቶኝ እንደልቤ
ፈረንጅ ሀገር እኖራለሁ፡፡ ደስ ካለኝም ከልጄ ጋር ሀገሬ መመለስ
የሚከለክለኝ ማንም የለም! “የስ ካን!..የስ ካን!”
ፈለቀች ወይም ፈረንጆቹ እንደሚጠሩኝ ፈሊ
ከዋሺንግተን . ከኦባማ ቤት ትንሽ ዝቅ ብሎ