ፈጣን ድረ ገፅ ለምሥራቅ አፍሪካ

New Tech, Q&A , Softwares, Help ... ቴክኖሎጂ እና ተያያዥ ርዕሶች
User avatar
girreda
Runner
Runner
Posts: 55
Joined: 01 Oct 2009 12:45
Location: Adama University
Contact:

ፈጣን ድረ ገፅ ለምሥራቅ አፍሪካ

Unread postby girreda » 20 Dec 2009 10:02

[center]ፈጣን ድረ ገፅ ለምሥራቅ አፍሪካ[/center]

በምሥራቅ አፍሪካ ድረ ገፆችን ፈጣን የሚያደርግ አዲስ ኬብል ሊዘረጋ ነው፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአፍሪካ በባህር ስር የሚቀበረው አዲሱ ኬብል የምሥራቅ አፍሪካ ነዋሪዎች ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላቸዋል፡፡

የፋይበር ኦፕቲክ ኬብሉ የሚሰራው የአፍሪካ ካምፓኒ በሆነው ሲኮም ሲሆን ደቡብ አፍሪካን፣ ታንዛኒያን፣ ኬንያን፣ ኡጋንዳን፣ ሞዛምቢክን፣ አውሮፓንና እስያን እንደሚያገናኝ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

እንደ ሲኮም አባባል የኬብሉ መዘርጋት የምሥራቅ አፍሪካን ኢንዱስትሪና የንግድ ግንኙነት እንደሚያስፋፋ ይረዳል፡፡

ኬብሉ 17 ሺህ ኪ.ሜ የሚሸፍን ሲሆን የዝርጋታ ሥራውን ለመጨረስ ሁለት ዓመት ይፈጃል፡፡ 650 ሚሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚያስወጣም ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የኬብሉ መዘርጋት ይፋ በሆነበት ወቅት "በአፍሪካና በሌላው ዓለም መካከል አዲስ የተግባቦት ክፍለ ዘመን ሊፈጠር ነው" ሲል ሲኮም ገል"ል፡፡

ድሆች ለስኳር በሽታ የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው

በእንግሊዝ በድህነት የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለስኳር የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ እንደሆነ አንድ ጥናትን ጠቅሶ ኤም ኤስ ኤን ቢሲ ድረ ገፅ ዘግቧል፡፡ እንደ ጥናቱ ከሆነ በድህነት የሚኖሩት በሚመገቧቸው የምግብ ዓይነቶች የተነሳ አብዛኞቹ ከልክ በላይ የመወፈር እድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡ ከልክ በላይ መወፈር ደግሞ ለሁለተኛው ዓይነት የስኳር በሽታ ያጋልጣል፡፡

ለስኳር ከሚያጋልጡ ዋና ዋና ምክንያቶች መካከል ከልክ በላይ መወፈር፣ የሰውነት እንቅስቃሴ አለማድረግ፣ የተመጣጠነ ምግብ እጥረትና ሲጋራ ማጨስ ይጠቀሳሉ፡፡

ጥናቱ እንደሚያሳየው ባለፈው የፈረንጆች ዓመት በእንግሊዝ የስኳር በሽተኞች ቁጥር 2.5 ሚሊዮን ይደርስ ነበር፡፡ ከመካከላቸው ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙትም የገቢ መጠናቸው ዝቅተኛ የሆኑት ነበሩ፡፡ በሽታውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑት ላይ መስራት እንደሚያስፈልግ ድረ ገፁ ዘግቦ አሁን ባለው ሁኔታ ግን በእንግሊዝ የስኳር በሽተኞች ቁጥር እየቀነሰ መሆኑን አብራርቷል፡፡

ሁለተኛው ዓይነት የስኳር በሽታ ከአኗኗር ዘይቤ ጋር ቀጥታ ግንኙነት አለው፡፡ "የመነሻ ምንጩ ቆሽት በቂ ኢንሱሊን ማመንጨት አለመቻሉ ወይንም የመነጨው ኢንሱሊን ተገቢውን ተግባር መፈፀም አለመቻሉ አይደለም፡፡ ይልቁንም በሰውነት የክብደት ሁኔታና በአመጋገብ የሚመጣ ነው"

ጥናቱ እንደሚጠቁመው በእንግሊዝ እቤታቸው የሚውሉና ገቢያቸው ዝቅተኛ የሆኑ ሴቶች ከሌሎቹ ይልቅ በስኳር በሽታ የመያዝ እድላቸው በአራት እጥፍ ከፍ ያለ ነው፡፡

በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ሰዎች ለስኳር በሽታ ከመጋለጣቸው በተጨማሪ በበሽታው ምክንያት ለሚከሰቱ ተጓዳኝ በሽታዎችም በብዛት የተጋለጡ እንደሆኑ ድረ ገፁ ጥናቱን በመጥቀስ አብራርቷል፡፡ ጥናቱ እንደሚጠቁመው የስኳር በሽታ ያለባቸው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ሰዎች የጤና ክትትል የማድረግ እድላቸው አናሳ ነው፡፡ በመሆኑም ለልብ ህመም፣ ለምት (ስትሮክ"፣ ለኩላሊት ህመም፣ ለአይነ ስውርነትና ለሌሎም በሽታዎች እንዲጋለጡ ያደርጋቸዋል፡፡

የተጎዳ ልብን ለመጠገን አዲስ ዘዴ

የተጎዳ ልብ ለመጠገን አዲስ ዘዴ እንዳገኙ ሳይንቲስቶች አስታወቁ፡፡ ሳይንቲስቶቹ እንደሚሉት አንድ የልብ ሴል በበሽታ ምክንያት ከተጎዳ ራሱን መተካት ያቆማል፡፡ ይሁንና የአሜሪካ የሳይንቲስቶች ቡድን የተጎዳውን ሴል ለመተካት የሚያስችል አዳዲስና ጤነኛ ሴሎች የሚፈጠሩበትን ዘዴ እንዳገኙ ገልፀዋል፡፡

ሳይንቲስቶቹ እንደሚሉት በአይጦችና በድመቶች ላይ የተደረገው ጥናት በበሽታ የተጎዳ ልባቸውን ለመጠገን ኤን አር ጂ1 የተሰኘ ንጥረ ነገር በመስጠት የልብ ሴሎቻቸው አዳዲስ ሴሎችን እንዲተኩ ማድረግ መቻሉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

እንደ ዘገባው ከሆነ ዘዴው ከዚሁ በፊት ልብን ለመጠገን የተሻለ ዘዴ ነው የሚባልለትንና በሰፊው ሙከራ ያልተደረገበትን የስቲም ሴል ህክምና (ስቲም ሴል ቴራፒ) የሚያስንቅ ነው፡፡ ተጓዳኝ ችግርም እንደማያስከትል ሳይንቲስቶች ገልፀዋል፡፡

ኤን አር ጂ1 የተሰኘው ንጥረ ነገር አዳዲስ ሴሎች እንዲፈጠሩ በማድረግ የተጎዳው የልብ ጡንቻ እንዲጠገንና አጠቃላዩ የልብ ክፍል ወደተፈጥሯዊ ሥራው እንዲመለስ ያደርጋል ያሉት ሳይንቲስቶች ንጥረ ነገሩን በመርፌ መልክ በወሰዱ አይጦችና ድመቶች መረጋገጡን አብራርተዋል፡፡

User avatar
girreda
Runner
Runner
Posts: 55
Joined: 01 Oct 2009 12:45
Location: Adama University
Contact:

በገዳዩ ሮቦት ዙሪያ ክርክር ያስፈልጋል

Unread postby girreda » 20 Dec 2009 10:04

ራሱን ችሎ በጦርነት መሳተፍ የሚችለውን ገዳይ ሮቦት በተመለከተ ዓለም አቀፍ ክርክር እንደሚያስፈልግ ሺፊልድ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡ዩኒቨርሲቲውን ጠቅሶ ቢቢሲ እንደዘገበው የሮቦት ቴክኖሎጂን በጦርነት ውስጥ መጠቀም ሰላማዊውን ሕብረተሰብ አደጋ ውስጥ ሊጥል ይችላል፡፡

እንግሊዝ ላይ በተደረገው ስብሰባ የአሜሪካ ኃይሎች ለመጀመሪያ ጊዜ የስነምግባር ጥያቄዎችን የሚፈታ እቅድ እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡ "ሮቦቶች የት መግደል እንዳለባቸውና ማንን እንደሚገድሉ መቼ እንደሚገድሉ መወሰን ይችላሉ፡፡" ብለዋል፡፡

ከሺፊልድ ዩኒቨርሲቲ የተሳተፉት ፕሮፌሰር ሻርኬይ በበኩላቸው የሮቦቶች ውሳኔ በሰው ሰራሽ ኢንተለጀንስ ላይ የተመሰረተ መሆኑ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡

ፕሮፌሰር ሻርኬይ ሮቦቶችን በጦርነት መጠቀም ያልተለመደ እንደሆነ ጠቅሰው የጦርነትን ባህሪም እንደሚቀይር ተናግረዋል፡፡ "አንድ ወታደር ቢሮው ውስጥ ቁጭ ብሎ በሪሞት ኮንትሮል በመቆጣጠር ሰው አልባ የሆኑ በአየር የሚበሩ ተሸከርካሪዎችን በ100 ሺህ በሚቆጠሩ ማይሎች ርቀት ይቆጣጠራል፡፡ ይህም በአካል ተገኝቶ ከሚደረግ ውጊያ አንፃር የስነ ልቦና ጫና የለውም ቀን በጦርነት የተሳተፈው ወታደር ማታ ወደ ቤቱ ተመልሶ ራቱን ይመገባል፣ ከልጆቹና ከሚስቱ ጋር የተለመደውን ሕይወት ይቀጥላል፡፡ ይህ ያተለመደ ነገር አይደለም" ብለዋል፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበው ሮቦቶችን ለጦርነት መጠቀም ፅንሰ ሃሳቡ ሰው አልባ ተሽከርካሪዎች በመላክ መዋጋት ብቻ አይደለም፡፡ በምድርም ከሰው እርዳታ ውጭ በራሳቸው የሚወስኑ ሮቦቶችንም በእግረኝነት መጠቀምን ይጨምራል፡፡

እንደ ዘገባው ከሆነ የእንግሊዝ ወታደሮች ባለፈው ወር አፍጋኒስታን ላይ ሰው አልባ የአየር ላይ ተሸከርካሪዎችን ለማሰማራት፣ የአሜሪካ አየር ኃይል በበኩሉ "አንማንድ አርቲክራፍት ፍላይት ፕላን 2009-2047" በሚል በያዝነው ወር ሰው አልባ የሆኑ የጦርነት የአየር ላይ በረራዎችን በተመለከተ እቅዳቸውን አሳትመዋል፡፡ ራሳቸውን ችለው የሚዋጉ አውሮፕላኖችን የማሰማራት ተስፋ እንዳላቸውም ገልፀዋል፡፡ የታመው ዶክመንት እንደሚለው ለውጊያው የሚደረጉ ውሳኔዎችን ዋና ዋና ሚናዎች ሰዎች ይቆጣጠራሉ፡፡

ፕሮፌሰር ሻርኬይ ገዳይ ማሽኖችን በተመለከተ የሚከሰቱ አሉታዊ ገፅታዎችን ጠቅሰው፣ ስራ ላይ ከመዋላቸው በፊት ዓለም አቀፍ ክርክር እንደሚያስፈልገው አሳስበዋል፡፡ በተለይ ውሳኔ ሰጭነቱ ለሮቦቶቹ ቢተው ይሻላል ወይስ ሰዎች መቆጣጠር አለባቸው የሚለው ሃሳብ ላይ ክርክር እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡[center][/center]

User avatar
girreda
Runner
Runner
Posts: 55
Joined: 01 Oct 2009 12:45
Location: Adama University
Contact:

የአሳማ ጉንፋን በ160 ሃገራት ተሰራጭቷል

Unread postby girreda » 20 Dec 2009 10:05

የአሳማ ጉንፋን ቫይረስ በ160 ሃገራት እንደተሰራጨና በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ሁለት ቢሊዮን ያህል ሰዎች በበሽታው ሊያዙ እንደሚችሉ የዓለም ጤና ድርጅት ሰሞኑን አስታወቀ፡፡ ይህም የዓለምን የሕዝብ ቁጥር አንድ ሦስተኛ ማለት ነው፡፡
ከይጄ ፍኩዳ የተባሉ የድርጅቱ አንድ ባለሥልጣን እንዳሉት ቫይረሱ ከአሳማ ወደ ሰው፣ እንዲሁም ከሰው ወደ ሰው መተላለፍ ከጀመረ በኋላ 800 ያህል ሰዎችን ገድሏል፡፡ ይህም በላብራቶሪ የተረጋገጠው ቁጥር ብቻ ስለሆነ የሟቾቹ ቁጥር ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችል ኩፍዳ ገልፀዋል፡፡

የመድሃነት አምራቾች የሃ1ሐ1 በመባል የሚታወቀውን የአሳማ ጉንፋን ለመከላከል የሚረዳ ክትባት እየሰሩ ሲሆን ሂደቱን እንዴት ማፍጠን እንደሚችሉ ጥናት እያደረጉ መሆናቸውን አሰታውቀዋል፡፡ ክትባቱ የሚደርስበት ጊዜ ቢዘገይም ውጤታማነቱ ግን የማያጠራጥር እንደሆነም ገልፀዋል፡፡[center][/center]


Return to “Technology, Softwares & IT Related ...ቴክኖሎጂ ነክ አምዶች”