በደመና ውስጥ ባክቴሪያ ተገኘ

New Tech, Q&A , Softwares, Help ... ቴክኖሎጂ እና ተያያዥ ርዕሶች
User avatar
girreda
Runner
Runner
Posts: 55
Joined: 01 Oct 2009 12:45
Location: Adama University
Contact:

በደመና ውስጥ ባክቴሪያ ተገኘ

Unread postby girreda » 19 Dec 2009 04:45

በደመና ውስጥ ባክቴሪያ ተገኘ
ደመና መፈጠር ዋና ሚና ባለው በረዶ ውስጥ ባክቴሪያ መገኘቱን የአሜሪካ ተመራማሪዎች ገልፀዋል፡፡ Very Happy
ሮይተርስ አጥኚዎቹን ጠቅሶ እንደዘገበው ግኝቱ በደመና ውስጥ አየር ወለድ ባክቴሪያ ስለመኖሩ የመጀመሪያው ማረጋገጫ ነው፡፡
በአየር ንብረት ላይ ምርምርና ትንበያ የሚያደርጉ ሳይንቲስቶች እስካሁንም ድረስ ለደመና መፈጠር እንደ ዘር የመሆን ያህል ሚና ባለው በረዶ ላይ ያሉትን ስብጥሮች ማወቅ አልቻሉም ነበር፡፡
በኔቸር ጂኦሳይንስ ላይ እንደሰፈረው አሁን በተደረገው ጥናት በደመና ውስጥ በሚገኙ የበረዶ ቅንጣቶች ላይ ጥልቅ መረጃ አግኝተዋል፡፡
"በእያንዳንዷ የበረዶ ቅንጣት ውስጥ ያለውን የኬሚካል ውህደት በመለየትና በማጥናት ለደመና መፈጠር የስነህይወት ቅንጣቶችም ሆኑ በአቧራ ውስጥ የሚገኙ ማዕድናት ከፍተኛ ሚና አላቸው" ብለዋል፡፡

User avatar
girreda
Runner
Runner
Posts: 55
Joined: 01 Oct 2009 12:45
Location: Adama University
Contact:

ወጣት ከጥፋት የተመለሰ

Unread postby girreda » 23 Dec 2009 02:17

(በምሕረት አስቻለው)

"የወጣትነት ጊዜዬ የጥፋት ነበር፡፡ ወላጆቼ ድሆች ስለነበሩ ውሎዬ ወይም ትምህርት ቤት መሄድ አለመሄዴ ብዙ የሚያስጨንቃቸው አልነበረም፡፡ እኔም ጐርሶ ለማደር በልጅነቴ ሊስትሮ መጥረግ ጀመርኩኝ፡፡

ሱቅ በደረቴም ሠርቻለሁ፡፡ ልጅም ብሆን የወላጆቼ ሁኔታ ሠርቶ መብላትን ገንዘብ መፈለግን አሳወቀኝ" ያለን ወጣት ሲሳይ ደጉ ይባላል፡፡

እድሜው እየጨመረ በአፍላ የወጣትነት ጊዜው ምንም እንኳ ለስርቆት ባይሠማራም ይኖር በነበረበት አካባቢ ሰዎችን በማስፈራራትና በማስጨነቅ ገንዘብ ይቀበል እንደነበር ያስታውሳል፡፡ ከሌሎች የእድሜ አቻዎቹ ጋር በመሆንም በቡድን ይደባደቡ፤ ገንዘብ ላላቸው የግል ጠባቂና ደብዳቢዎች በመሆን ሌሎችን ያጠቁ ነበር፡፡ "ከቤተሠብ ያገኘሁት ምንም ትምህርት ወይም ግብረ ገብነት አልነበረም፡፡ በልጅነቴ የጀመርኳት ሊስትሮ እድሜዬ እየጨመረ ሲሄድ ለውጥ እንዳላመጣች ተሠማኝ፡፡ ያኔ ሌላ ገንዘብ ማግኛ መንገድ ማሰብ ጀመርኩ፡፡ በአካባቢያችን ብዙ ሠዎች በፀበኛና በተደባዳቢነቴ ይፈሩኝ ይሽቆጠቆጡልኝም ነበር፡፡ እኔም ያን አስጨንቆና አስፈራርቶ ገንዘብ ለመቀበል እጠቀምበት ነበር"፡፡

እንኳንስ ጐርሶ ጥያቄ ከሚሆንበት ደሀ ቤተሠብ ሁሉ ከሞላበት ባለፀጋ ቤተሠብ ለወጡ ልጆች እንኳ የወጣትነት ጊዜ አስቸጋሪ እንደሆነ ያምናል፡፡ የሱም አፍላ የወጣትነት ጊዜ የረብሻ፣ የአመፅና የእኩይ ተግባር የሆነው በአመዛኙ ከዚያ አንፃር እንደሆነ ይናገራል ሲሳይ፡፡

እሱ እንዳለው ከሌሎች የሠፈር ጓደኞቹ ጋር በመሆን እለት በእለት አስፈራርተው ገንዘብ ይቀበሉ፣ በቡድን ይደባደቡ ነበር፡፡ በዚህም በተደጋጋሚ ለእስር ተዳርጓል፡፡ አንድ አጋጣሚ ግን ስለ ህይወቱ፣ ስለ ወጣትነት ጊዜው ቆም ብሎ እንዲያስብ አስገደደው፡፡ "ስድስት ጓደኞቼ ተገደሉ፡፡ ምክንያቱም ሁላችንም ወንጀለኞች፣ ጥፋተኞች ስለነበርን እንፈለግ ነበር፡፡ የወጣትነት ጊዜአችን በአመፅ የተሞላ ነበር፡፡" በማለት ከጓደኞቹ መካከል በህይወት መትረፉ እንዳስደነቀው፣ ስለ ህይወቱና ስለማንነቱ ብዙ ጥያቄዎችን እንዲያነሳ እንዳደረገው ይናገራል፡፡ ከዚህ በኋላ ጠፍቶ ወደ የመን ሄደ፡፡ በህገወጥ መንገድ ወደ አገሪቱ በመግባቱ በየመን ለስምንት ወራት በእሥር ከቆየ በኋላ ወደ አገሩ መመለሱን፤ በዚያ ወቅትም ገና የአሥራ ስምንት ዓመት ወጣት እንደነበር አጫውቶናል፡፡

ከስምንት ወር የየመን የእስር ቤት ቆይታ በኋላ ወደ አገሩ ሲመለስ በሥነ ምግባር፣ በአመለካከትና በአስተሳሰብ ሲሳይ ከቀድሞ የተለየ ሠው ሆነ፡፡ ሠዎችን አስፈራርቶና አስጨንቆ ገንዘብ በተቀበለበት አካባቢ ዝቅ ብሎ መኪና ማጠብ ጀመረ፡፡ ከዚያም ባሻገር ገንዘብ ለማግኘት ያስችለኛል ያላቸውን ሥራዎች ይህ ትልቅ ነው ይህ ትንሽ ነው ብሎ ሳይንቅ ያገኘውን መሥራትና በላቡ ደክሞ መብላትን አወቀ፡፡ "በፊት የሚያውቁኝ መኪና ሳጥብ አይተው ያለቀሱ ሁሉ አጋጥመውኛል፡፡ እኔ ግን ለምን? አልኳቸው፡፡ በፊት ሳስፈራራ፣ በጉልበቴ ተጠቅሜ ገንዘብ ስቀበልና በቡድን ስደባደብ ነበር እንጂ ዛሬ ሥሠራ ለምን ታለቅሳላችሁ ብዬአቸዋለሁ፡፡ ምን ሆነህ ነው እንዲህ የተቀየርከው ሁሉ የሚሉኝ ነበሩ"

ለብቻው ጐንበስ ብሎ መኪና ከማጠብ በመነሳት ሌሎች ዘጠኝ የአካባቢውን ወጣቶች በማስተባበር ተደራጅተው መኪና በማጠብ የራሳቸውን የገቢ ምንጭ እንዲፈጥሩ መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡ ተደራጅተው መኪና ለማጠብ እንዲሰጣቸው የጠየቁትን ቦታ ለማግኘት ብዙ ውጣ ውረዶችን አልፏል፡፡ "አባላቱ አሥር እንሁን እንጂ ዘወትር ቀበሌም ክፍለ ከተማም የምመላለሰው ለብቻዬ ነበር" የመኪና እጥበት ማህበራቸው ጥረት የተስፋ ምልክት ዛሬ ላይ 15 አባላት ሲኖሩት ለሌሎች 18 ወጣቶች የሥራ እድል መፍጠሩን ከሲሳይ ንግግር ተረድተናል፡፡

"የወጣትነት እድሜዬ ሳያልቅ ከጥፋት ተመልሻለሁ፡፡ የመመለሴ ምስጢር ደግሞ ቤተክርስቲያን ነች፡፡ ከዚያም ሳይረፍድብኝ በወጣትነቴ መሮጥን አውቄአለሁ፡፡ ትዳር መስርቼ ልጆች አፍርቼአለሁ፡፡ የልጆቼ ትምህርት፣ ባህሪና ስብእና ያስጨንቀኛል፡፡ ኃላፊነትም አለብኝ፡፡ ነገ አገራቸውንና ወገናቸውን የሚጠቅሙ ዜጐች እንዲሆኑ ማድረግ አለብኝ"

በሲሳይ አመለካከት የአብዛኛው ወጣት ሥራ ማጣትን፣ በተለያዩ ሱሶች ስር መውደቅንና ሌሎች አላስፈላጊ ባህሪያትን መከላከል ወይም ማስወገድ የመንግሥት ኃላፊነት ብቻ እንደሆነ መታየት የለበትም፡፡ ይልቁንም እያንዳንዱ ዜጋ የአቅሙን መስዋዕትነት ከፍሎ የበኩሉን ሊያበረክት ይገባል፡፡ ጥፋቶችና ጉድለቶች በወጣቶች ላይ ቢታዩም በተወሰነ መልኩ ከሌላው ወገን ታጋሽነት እንደሚያስፈልግ የሚናገረው ሲሳይ "ተቀጥረው መኪና ከሚያጥቡ ወጣቶቻችን አንዱ ከመኪና ውስጥ የአንድ ደንበኛችንን ሞባይል ስልክ አግኝቶ ይወስዳል፡፡ የተሠረቀው ሞባይል ላይ ስልክ ስንደውል ልጁ ኪስ ውስጥ ስልኩ ጮኸ፡፡ ለባለመኪናው ወጣቱን ወደ መልካም ሥነ ምግባር የመመለስ ኃላፊነት ስላለብን አንተም ደንበኝነትህን እንዳታቋርጥ እኔም ከሥራ ገበታው አላባርረውም አልኩት፡፡ ልጁም መጥፎ ባህሪው ተቀይሮ ከዚያ በኋላ ለሁለት ዓመታት ቆይቶ የተሻለ ሥራ አግኝቶ ለቋል" በማለት አጋጣሚውን አስታውሷል፡፡

ጥረት የተስፋ ምልክት የህብረት ሥራ ማህበር የሥራ እድል የፈጠረላቸው 18 ወጣቶች ከእሑድ በስተቀር ዘወትር ከጥዋቱ አንድ ሠዓት እስከ ምሽቱ አንድ ሠዓት ይሠራሉ፡፡ በቀን እስከ ሀምሳ ብር ድረስ የሚያገኙ ሲሆን በዚህ ቤተሠብ የሚያስተዳድሩ፣ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚማሩና እቁብ እየጣሉ ገጠር ቤት የሠሩና መሬት የገዙ መኖራቸውን ሲሳይ ነግሮናል፡፡

ሲሳይና ጓደኞቹ መኪና የሚያጥቡት በአራት ማሽኖች ሲሆን አሁን እየሠሩበት ካለው በተሻለ ፍጥነትና ጥራት መኪናዎችን ሙሉ በሙሉ አጠቦ የሚያደርቅ ማሽን ከውጭ ለማስገባት በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡ ማሽኑ ስምንት መቶ ሺህ ብር የሚያወጣ ሲሆን ከወጭው አንድ አራተኛ የሚሆነውን ከጥቃቅንና አነስተኛ የብድር ተቋም ተበድረው ለመሸፈን ሲያስቡ ቀሪውን ወጪ ከራሳቸው የማውጣት አቅም አላቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት የቀበሌያቸውን ይሁንታ ካገኙ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ማሽኑን ማስገባት እንደሚችሉ ገልጾልናል፡፡ "ማሽኑ መሬት ላይ መተከል አለበት፡፡ ያለን ቦታ በቂ ቢሆንም ለማሽኑ መተከል የቀበሌ ድጋፍ ያስፈልገናል፡፡ ይህን ድጋፍ ለማግኘትም በመንቀሳቀስ ላይ ነን"


Return to “Technology, Softwares & IT Related ...ቴክኖሎጂ ነክ አምዶች”