የምርጫ ታዛቢ የነበሩ ግለሰብ ባለቤት በታጣቂዎች ተገደሉ: ታዛቢው ምርጫውን በተመለከት ባቀረብኩት ትችት ምክንያት ነው ይላሉ።

by ocean

ምርጫው ተጠናቅቆ የኢህአዴግ አሸናፊነት ይፋ ከተደረገ ሁለት ሳምንታት በኋላ አንዲት የምርጫ ታዛቢ መገደላቸውን መኢአድ

VOA

VOA

ሲያስታውቅ፤ በአባሎቹ ላይ የደረሰ ያለው ወከባና እንግልት የኦሮሞ ህዝብ ኮንግሬስ አመለከተ።

Listen the VOA report ዘገባውን ያዳምጡ

[cincopa 10627120]

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ከተጠናቀቀና የቅድሚያ ውጤቶቹ ከተሰሙ ሁለት ሳምንታት ቢገባደዱም ከምርጫው ጋር ተያይዘው የሚነሱት ውዝግቦች ግን ዛሬም አላበቁም።

«የምርጫ ታዛቢ ሆነው ባቀረቡት ትችት የአንድ አባሌ ባለቤት ተገደሉ፤» ሲል፥ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ መኢአድ አስታውቋል።

በደቡብ ክልል የደራሼ ልዩ ዞን ሰብሳቢው የአቶ ገልገሎ ኮይታ ባለቤት፥ ወ/ሮ አማረች ገላኔ ባለፈው ዕሁድ በአንድ የመንግስት ታጣቂ መገደላቸውንና በጊዜው አብረዋቸው የነበሩ ሁለት ህፃናት ልጆቻቸውም ቆስለው በህክምና በመረዳት ላይ መሆናቸውን የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አቶ ማሙሸት አማረ ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ገልጠዋል።

በሌሎች አካባቢዎችም ደጋፊዎቻችንና አባሎቻችን በመንግስት የሚቀርቡ አገልግሎቶችን እየተነፈጉ ነው፥ ከማኅበራዊ ህይወትም እየተገለሉ ነው፤ ያሉት አቶ ማሙሸት አክለውም፤ «ይህ እየተፈፀመ ያለው ምርጫው ከተጠናቀቀ በኋላ መሆኑ በሠላማዊ መንገድ የሚደረገውን ትግል ይበልጥ አዳጋች አድርጎታል፤» ብለዋል።

የኦሮሞ ኅዝብ ኮንግሬስም በበኩሉ «በደጋፊዎቼ ላይ የሚደርሰው ወከባ አሁንም ቀጥሏል፤» ብሏል።

ከምርጫው በፊትና በምርጫው ዕለት የታሰሩ አብዛኞቹ አባላቱና ደጋፊዎቹ ቢለቀቁም «እየደረሰ ነው፤» ያለው ወከባ ግን፥ አሁንም አለማቆሙን ሊቀ መንበሩ ዶ/ር መረራ ጉዲና ተናግረዋል።

መኢአድም ሆነ የኦሮሞ ኅዝብ ኮንግሬስ ላቀረቧቸው ክሶች ለጊዜው ማስተባበያ የሰጠ ወገን የለም።

ምንጭ: አሜሪካን ድምጽ

Related Posts

Leave a Comment